Sheko Wereda Communication Affairs

  • Home
  • Sheko Wereda Communication Affairs

Sheko Wereda Communication Affairs Sheko Wereda Communication Affairs

የፖሊስ አመራሩና አባላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ !!!በማጥራት ግምገማ ነጥረው የወጡ ችግሮችን ፍጥኖ ማረም እንደሚገባ ተጠቁሟል ።=======================ታህሳስ 1...
22/12/2024

የፖሊስ አመራሩና አባላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ !!!በማጥራት ግምገማ ነጥረው የወጡ ችግሮችን ፍጥኖ ማረም እንደሚገባ ተጠቁሟል ።
=======================
ታህሳስ 13/2017ዓ/ም
ወታደራዊ ስነምግባር የተላበሰ የፖሊስ አመራርና አባላት በመፍጠር የፖሊስ ተቋምን ማጠናከር እና ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ከክልል ጀምሮ በተዋረድ እየተካሄደ የሚገኘው የግምገማ መድረክ በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል ።

የአባላቱ የግምገማ ውጤት በኃይል መድረክ ቀርቦ በተደረገው ግምገማ የ11 ፖሊስ አባላት የግምገማ ውጤት ዳግም እንዲታይ ተደርጓል ።በፖሊስ አባላቱ ላይ ዳግም በኃይል መድረክ በተሰጠው ውጤት የሰባት አባላት ውጤት ከሂስ ወደ ማስጠንቀቂያ ወርዷል እንዲሁም የአራት አባላት ግምገማ ውጤት በአብላጫ ድምጽ በነበረበት ጸንቷል።

በሶስት ቀን ቆይታቸው የፖሊስ አባላቱ ከተቋም አካላዊ ገጽታ እስከ ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር የዳሰሰ ግምገማ መደረጉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ምክትል ኮማንደር አለማየሁ ድረስ ገልጸዋል ።

ከመጠቃቃት የጸዳ አመራሩንና አባላቱን ከችግር በማላቀቀ ቀልጣፋ ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት በተካሄደው መድረክ የአመራሩና አባላቱን መሰረታዊ ችግሮች መለየት ተችሏል ያሉት ኮማንደሩ የተሻለ ህዝባዊ ወገንተኝነት የተላበሰ የፖሊስ መዋቅር መፍጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክስ ንግድ ነክ ወንጀል ምርመራ ዲቭዥን ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አለማየሁ አማረ እንደገለጹት አራቱ መሰረታዊ የፖሊስ ትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ ግምገማ መደረጉን ጠቁመዋል ።በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በአገልግሎት አሰጣጡ የተስተዋሉ ችግሮችን ማረም የሚያስችል ግምገማ መካሄዱን አመላክተው ከግምገማው ማግስት ጀምሮ የተለዩ ችግሮች ታርመው ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል ።ከግምገማ በኃላ የተመዘገቡ መሻሻሎችን ክትትል በማድረግ ግብረመልስ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ በኩል ይሰጣል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ታምራት ምናሴ እንደገለጹት ግምገማው መካሄዱ ወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ እያከናወኑ ለሚገኙት ወንጀል መከላከል እና ህግ ማስከበር ስራዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል ።ፖሊስነት ለህዝቡና ለህገመንግስቱ ወገንተኝነት የሚቆሙበት ታላቅ ሙያ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ ታምራት ምናሴ ህብረተሰቡ በትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም በጫኝ አውራጆች ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

ህብረተሰቡ ለትራንስፖርት ከ500 እክከ 1000 እንዲሁም 20 ኪሎ ለማይሞላ እቃ ለትራንስፖርት እስከ 200 ብር እንዲሁም ለጫኝ አውራጅ ከ100 ብር በላይ የሚከፍሉ በመሆናቸው የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል ።

አሁን በወረዳው እና ከተማ አስተዳደሩ አስተማማኝ ሰላም በመፈጠሩ ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የሚባክን አንድም ጥይት ፍሬ እንደማይኖር ጠቁመው የተጀመሩ የመንገድ ደህንነት እና ሌሎች ስርዓት አልበኞችን ስርዓት የማስያዝ ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አክለዋል ።

ህብረተሰቡን ከብዝበዛ ለመታደግ ፖሊስ በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ ድምበር የለሽ ወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ጠንካራ የፖሊስ አመራር ፣አባላትና ተቋም ለመገንባት እየተደረገ ላለው ጥረት ከግብ እንዲደርስ ከተማ አስተዳደሩም ሆነ ወረዳው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።አያይዘውም ፖሊስነት ሰብዓዊነት እና ሙያው ግልጸኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ከቂም በቀል ራሳቸውን በማላቀቅ አንድነታቸውን ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።

የሸኮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ ገዛኸኝ ኡፕም በበኩላቸው የሂስ ግለ ሂስ ግምገማው በአመለካከት፣ በተግባር አፈጻጸም፣ በወታደራዊ ዲሲፕሊን እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማጥራት በሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ እንዲሁም ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው አባላት ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል ።

ፖሊስነት በስነ ምግባር መታነጽ፣ለአላማ መጽናት፣ተልዕኮን በብቃት መወጣት እና ወንጀልን መከላከል በመሆኑ አባላቱ በስነ ምግባር ፣በአመለካከት እና በተግባር የታዩባቸው ችግሮች ምረምና የተስተካከለ ቁመና መላበስ እንደሚኖርባቸው መክረዋል ።

የፖሊስ አባላቱ በሰጡት አስተያየት ከችግሮቻው በመውጣት ህዝዊነትን የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት ቃል በመግባት ግምገማው ተጠናቋል ።

የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል እና ህብረተሰቡን የትሩፋቱ ተጠቃሚ ለማድረግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ፤ተግባራቱንም በአደረጃጀት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!======================...
21/12/2024

የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል እና ህብረተሰቡን የትሩፋቱ ተጠቃሚ ለማድረግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ፤ተግባራቱንም በአደረጃጀት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!
============================
ታህሳስ 12/2017ዓ/ም
የሸኮና ሼህ ቤንች ወረዳ ክላስተር ባለፉት 21ቀናት በመንግሥት እና ፓርቲ ያከናወኗቸውን ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በሸኮ ወረዳ ተገምግሟል ።

ወረዳዎቹ በስራ እድል ፈጠራ ያስራጩትን ገንዘብ በመሰብሰብ ለስራ አጥ ወጣቶች ስራ እድል መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።ያደሩ እና ውዝፍ የግብዓት እዳዎችን ባለቤት በመፍጠር ተመለሽ ማድረግና የመንግስት በጀት ክፍተቶችን መሸፈን እንደሚገባም ውይይት ተደርጎበታል ።

የወረዳዎችን የ21ቀን ተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የመሩት የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ማርቆስ ጎቢ እንደገለጹት የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል እና ህብረተሰቡን የትሩፋቱ ተጠቃሚ ለማድረግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ፤ተግባራቱንም በአደረጃጀት መምራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ግብርና ላይ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ህብረተሰቡን የጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

ሰላምን ለማጽናት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ጤናማ ፖለቲካ መፍጠር እንደሚገባ የጠቆሙት የመንግስት ተጠሪው በዚሁ ረገድ አመራሩ የፖለቲካ ቅኝት አዝማሚያ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በመድረኩ ጠንካራ አፈጻጸሞች ተለይተው ተሞክሮ የተወሰደበት ሲሆን ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጎበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሞዴል አደረጃጀት ማስፋት ፣የፓርቲ አባላት መዋጮ ፣የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ ቢስት ባር፣የሸኮ ብሄር ዘመን መለወጫ ቲከሻ ቤንጊ ፣በልግ እርሻና ሌሎች መደበኛ ተግባራትን ለማከናወን በተቀመጡ አቅጣጫዎች መግባባት ላይ ተደርበሶበት መድረኩ ተጠናቋል።

ባለፉት 21ቀናት በመንግሥት እና ፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት እየተገመገመ ይገኛል !!!=========================ታህሳስ 12/2017ዓ/ምየሸኮ እና ሼህ ቤንች ወ...
21/12/2024

ባለፉት 21ቀናት በመንግሥት እና ፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት እየተገመገመ ይገኛል !!!
=========================
ታህሳስ 12/2017ዓ/ም
የሸኮ እና ሼህ ቤንች ወረዳ ክላስተር ባለፉት 21ቀናት በመንግሥት እና ፓርቲ ያከናወኗቸውን ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በሸኮ ወረዳ እየተገመገመ ነው።

የተግባራቱን አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ የመሩት የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ ማርቆስ ጎቢ እንደገለጹት መንግስትና ፓርቲ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል ።

በተከናወኑ ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን የገለጹት ረዳት የመንግስት ተጠሪው ህብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የተረጋጋ ፖለቲካ መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

ጤናማና የተረጋጋ ፖለቲካ መፍጠር በመቻሉ በዞኑ በርካታ የልማት ስራዎች ማከናወን መቻሉን በመጠቆም ፖለቲካ ሰላም ጸጥታን ማጽናት ልማት ማስበጠል በመሆኑ አመራሩ አዝማሚያዎችን በትኩረት መቃኘት እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

የፖርቲ አባላት መዋጮ፣የበልግ ስራ ቅድመ ዝግጅት ፣የበሽታ ቅድመ መከላከል ስራ፣የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን አባልነት እድሳት ፣የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ ቢስት ባር እንዲሁም የሸኮ ብሄር ዘመን መለወጫ ቲከሻ ቤንጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም የሚገኙት ሁኔታና ሌሎች ተግባራቶች ሪፖርት በደጋፊ አመራሮች ቀርቦ
አፈጻጸሙ እየተገመገመ ይገኛል ።

ትናንት የተጀመረው የአመራርና አባላት ማጥራት የፖሊስ ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ  እንደቀጠለ ነው!!!==========================ታህሳስ 11/2017 ዓ/ምከከልል ጀምሮ በተዋ...
20/12/2024

ትናንት የተጀመረው የአመራርና አባላት ማጥራት የፖሊስ ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው!!!
==========================
ታህሳስ 11/2017 ዓ/ም
ከከልል ጀምሮ በተዋረድ በሚገኙ በሁሉም የፖሊስ መዋቅሮች እየተካሄደ የሚገኘው የፖሊስ አመራርና አባላት ማጥራት ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ በሸኮ ወረዳና ከተማ አስተዳደሩ ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

እየተካሄደ ያለው ግምገማና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ጥራት ያለው አመራር እና አባላት በመገንባት ጠንካራ የፖሊስ ተቋም በመፍጠር ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መሆኑ ተመላክቷል።

ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ግምገማ መድረክ የወረዳው እና ከተማ አስተዳደሩ የፖሊስ አመራሮች ግምገማ ተካሂዷል ።

አሁን ጥራት ያለው አባላት ለመፍጠር በአመለካከት ፣ስነ ምግባርና ተግባር አፈጻምን መሰረት በማድረግ የፖሊስ አባላቱ እየተገማገሙ ይገኛሉ።

በወታደራዊ ስነ ምግባር የታነጸና  ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ የፖሊስ አመራርና አባላት ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ!!!===========================ታህሳስ 1...
19/12/2024

በወታደራዊ ስነ ምግባር የታነጸና ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ የፖሊስ አመራርና አባላት ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ!!!
===========================
ታህሳስ 10/2017ዓ/ም
አጠቃላይ የፖሊስ አመራር እና አባላት ማጥራት ግምገማና ሂስና ግለሂስ መድረክ በወረዳው እና ከተማ አስተዳደሩ በመካሄድ ላይ ነው።

የግምገማና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ዓላማ ወታደራዊ ስነምግባር የተላበሰ የፖሊስ አመራርና አባላት በመፍጠር የፖሊስ ተቋምን ማጠናከር እና ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት መስጠት መሆኑ ተጠቁሟል።

ፖሊስ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግሮች ሳቢያ ለህዝቡ ሰላምና ደህንነት ከአካል ጉዳት እስከ ህይወት መስዋዕትነት የሚደርስ ዋጋ በመክፈል ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን አሳይተዋል ።

እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ስነ ምግባር እና ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው ፖሊስ እንፈጠር ግምገማና ሂስ ግለሂስ መድረክ የተገኙት የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ምክትል ኮማንደር አለማየሁ ድረስ እንደገለፁት ሙያዊ ስነምግባር የተላበሰ ፣ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ ህዝባዊ ወገንተኝነት የተላበሰ የፖሊስ አመራርና አባላት ለመፍጠር ከክልል ጀምሮ የማጥራት ግምገማ በትኩረት እየተካሄደ እንደመመገኝ አብራርተዋል ።

የፖሊስ አመራርና አባላት በተለያዩ ምክያቶች ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ የሚሉት ምክትል ኮማንደ አለማየሁ ችግር ውስጥ የገቡ አባላትን ማረምና ወደ ቀድሞ ስብዕናቸው መመለስ ይገባል ብለዋል።

አባላትን ከችግር ፈጥነው እንዲወጡ ለማስቻል ከአቅም ግምባታ ስራዎች ባሻገር ግምገማና ሂስ ግለሂስ መድረኮች ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ እንደሚኙ በመጠቆም ከአትንካኝ አልካ አስተሳብ የጸዳ ግምገማ በማካሄድ በአባላትን እና አመራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክስ ንግድ ነክ ወንጀል ምርመራ ዲቭጅን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አለማየሁ አማረ እንደገለጹት ፖሊስነት ጥብቅ ዲሲፕሊያን ያለው በመሆኑ ሙያዊ ስነ ምግባር ደምቦች ሳይሸራረፉ በተቋሙ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

ፖሊስ ህዝዊነትን ተላብሶ የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅ ማህበረሰቡ በሰላም ወጥቶና በሰላም እንዲገባ እያደረገ ያለውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ወታደራዊ መርህዎችን መተግበር እንዲሁም ተልዕኮን በብቃት መፈጸም እንደሚገባ ገልጸዋል ።የፖሊስነት ሙያው ጥንቃቄን የሚጠይቅ በመሆኑ ዲሲፕሊንና ተልዕኮን በብቃት ለመፈጸም ምንጊዜም ንቁና ዝግጁ መሆን ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ሰላም ጸጥታና ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ ቴርካ እንደገለፁት ህዝባዋነትን የተላበሰ ፖሊስ ለዘላቂ ሰላምና ጸጥታ ያለው ሚና የላቀ መሆኑን በመጠቆም ፖሊስ ሙያው የሚጠይቀውን ምግባርና ተግባር የመፈጸም ተልዕኮን ማክበርና መፈጸም እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል ።

ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገቡ ከማድረግ ባለፈ የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻውን በማክበርና እንዲከበሩ በማድረግ ዜጎች ያለስጋት ሰርተው ሀብትና ንብረት እንዲያፈሩ በማድረግ ሰላሙ የተረጋጠ ብሎም በኢኮኖሚ የዳበረ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ የፖሊስ መዋቅር ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑም አክለዋል።

የግምገማና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ላይ የተገኙት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መሰረት ወገስ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት
የሂስ ግለ ሂስ ግምገማው በአመለካከት፣ በተግባር አፈጻጸም፣ በወታደራዊ ዲሲፕሊን እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማጥራት በሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ እንዲሁም ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው አባላት ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።

ከወንጀል የጸዳ አካባቢ ለመፍጠር በሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ እንዲሁም ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው አመራር እና አባላት ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው በወረዳው ተፈጥሮ የነበሩት የጸጥታ ችግሮች እንዲፈቱና አሁን ለተገኘው ሰላምና ጸጥታ የፖሊስ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበረ ገልጸዋል ።

ለአመራሮችና አባላት ግምገማና ሂስ ግለሂስ መድረክ ነባራዊ ሁኔታዎችን የዳሰሰ ሰነድ ቀርቧል።የቀረበው ሰነድ በትክክል የፖሊስ መዋቅሩን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ መሆኑ መግባባት ላይ ተደርሶበታል።

የፖሊስ አመራርና አባላቱ በአመለካከት ፣ስነ ምግባርና ተልዕኮ የመፈጸም ብቃትን መሰረት በማድረግ እየተገማገሙ ይገኛሉ ።

የፖሊስ አመራርና አባላት ማጥራት ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ  መካሄድ ጀመረ!!!==========================ታህሳስ 10/2017 ዓ/ምከከልል ጀምሮ በተዋረድ በሚገኙ በሁሉም የ...
19/12/2024

የፖሊስ አመራርና አባላት ማጥራት ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ!!!
==========================
ታህሳስ 10/2017 ዓ/ም
ከከልል ጀምሮ በተዋረድ በሚገኙ በሁሉም የፖሊስ መዋቅሮች እየተካሄደ የሚገኘው የፖሊስ አመራርና አባላት ማጥራት ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ መካሄድ ጀምሯል ።

የሸኮ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤትና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን እያካሄዱ በሚገኙት የፖሊስ አመራርና አባላት ሂስ ግለ ሂስ መድረክ የወረዳው እና የከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል ።

የግምገማና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ዓላማ ወታደራዊ ስነምግባር የተላበሰ የፖሊስ አመራርና አባላት በመፍጠር የፖሊስ ተቋምን ማጠናከር እና ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት መስጠት መሆኑ ተጠቁሟል።

የግምገማና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ላይ የተገኙት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መሰረት ወገስ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት
የሂስ ግለ ሂስ ግምገማው በአመለካከት፣ በተግባር አፈጻጸም፣ በወታደራዊ ዲሲፕሊን እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማጥራት በሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ እንዲሁም ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው አባላት ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።

ከወንጀል የጸዳ አካባቢ ለመፍጠር በሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ እንዲሁም ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት ያለው አመራር እና አባላት ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው በወረዳው ተፈጥሮ የነበሩት የጸጥታ ችግሮች እንዲፈቱና አሁን ለተገኘው ሰላምና ጸጥታ የፖሊስ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበረ ገልጸዋል ።

ለአመራሮችና አባላት ግምገማና ሂስ ግለሂስ መድረክ ነባራዊ ሁኔታዎችን የዳሰሰ ሰነድ ቀርቧል።የቀረበው ሰነድ በትክክል የፖሊስ መዋቅሩን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ መሆኑ መግባባት ላይ ተደርሶበት ግምገማው ተጀምሯል ።

በግምገማው የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ምክትል ኮማንደር አለማየሁ ድረስ፣ረዳት ኢንስፔክተር አለማሁ አማረ እንዲሁም የወረዳውና ከተማ አስተዳደር ፖሊስና የጸጥታ አመራሮች ተገኝተዋል ።

ግምገማው ለተከታታይ 2 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከመርሃ ግብሩ ለመረዳት ተችሏል።

ጤናማ የግብር ስርዓት ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው============================ታህሳስ 9/2017ዓ/ምየሸኮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤ...
18/12/2024

ጤናማ የግብር ስርዓት ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው
============================
ታህሳስ 9/2017ዓ/ም
የሸኮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በስራቸው ለሚገኙ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮቻቸው የደረሰኝ አጠቃቀም እና አቆራረጥ እንዲሁም አዲሱ እሴት ታክስ አዋጅ ለውጦችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የሸኮ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ መርፌ እንደገለጹት መንግስት እንደ አገር ከግብር ከፋዮቹ በሚሰበስበው ግብር በርካታ ልማቶችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩም በርካታ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ሲሳይ የተጀመሩ ልማቶችን ከዳር ለማድረስ ግብር ከፋዮች ከሚያከናወኑት ሺያጭ ወይም ለማህበረሰቡ ከሚሰጡት አገልግሎት ላይ ከሚያገኙት ገቢ ግብራቸውን በታማኝነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል ።

ታማኝ ግብር ከፋዮችን በመፍጠር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት የሸኮ ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ንጉሴ ዱደብ በበኩላቸው ለዚሁም ስኬታማነት ለንግዱ ማህበረሰብ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ስራዎች ባሻገር የግንዛቤና አቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

ያደጉና የበለጸጉ አገሮች ጠንክሮ መስራት በመቻላቸው እና በገቢያቸው ልክ ለአገራቸው ግብር በታማኝነት መክፈል በመቻላቸው ነው የሚሉት አቶ ንጉሴ በርካታ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ግብርን በታማኝነት በመክፈል የተጀመሩትን ልማት ማስቀጠል ይገባም ብለዋል።

ለግብር ከፋዮች ስልጠናውን የሰጡት የቤንች ሸኮ ዞን ገቢዎች መምሪያ የትምህርት ስልጠናና ኮሙኒኬሽን ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መሃመድ አህመድ እንደገለጹት ጤናማ የግብር ስርዓት ለመፍጠር የግብር ፍትኃዊነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የግብር ፍትኃዊነቱን ለማረጋገጥ በእውቀትና ክህሎት የዳበረ ግብር ከፋዮችን ለመፍጠር እየተከናወኑ ባሉት ተግባራት አበረታች ውጤት መገኘቱንም ጠቁመዋል ።

አያይዘውም የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች አዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ ለውጦች በመደረጋቸው ደረሰኝ አለመቁረጥ ከ50ሺህ እስከ 100ሺህ ብር የሚያሰቀጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች በሚሰጡት አገልግሎትና በሚያከናውኑት ሺያጭ ደረሰኝ በመቁረጥ ከአላስፈላጊ ቅጣት የራሳቸውን መከላከል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።

በስልጠናው ላይ የተገኙት ግብር ከፋዮች መካከል አቶ መካ ዳርገባ፣አቶ ገብረ መስቀልና ወ/ሮ አለሚቱ አበባው በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት ከስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ በመግለጽ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመው መድረኩ ተጠናቋል ።

የሸኮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በስራቸው ለሚገኙ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች  የደረሰኝ አጠቃቀም እና አቆራረጥ እንዱሁም በአዲሱ ...
18/12/2024

የሸኮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በስራቸው ለሚገኙ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች የደረሰኝ አጠቃቀም እና አቆራረጥ እንዱሁም በአዲሱ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ ለነጋዴዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

17/12/2024
ሚሊተሪ የለበሱ አጠቃላይ የፖሊስ አባላት በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ  የትራፊክና መንገድ ደህንነት ህጎችን እንዲያስከብሩ ትዕዛዝ ተሰጣቸው !!!====================ይህ ኃላፊነት ...
17/12/2024

ሚሊተሪ የለበሱ አጠቃላይ የፖሊስ አባላት በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ የትራፊክና መንገድ ደህንነት ህጎችን እንዲያስከብሩ ትዕዛዝ ተሰጣቸው !!!
====================
ይህ ኃላፊነት የተሰጣቸው የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ፖሊስ የመንገድ ደህንነት ህጎችን ማስከበር ባለመቻላቸው ህብረተሰቡን ከሚደርስባቸው የመንገድ ትራንስፖርት ብዝበዛ ለመታደግ መሆኑ ተመላክቷል።

የሸኮ ወረዳና የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ እየደረሱ ያሉትን እንግልትና ብዝበዛ ለማስቆም ዛሬ ታህሳስ 8ቀን 2017ዓ/ም ውይይት አካሂደዋል ።

የገንዘብ ቅጣት አሽከርካሪዎችን ደምብ ከመተላለፍ እንዲሁም ህብረተሰቡን ከእንግልትና ብዝበዛ እየታደገ አለመሆኑን የገለጹት የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ታምራት ምናሴ እንደገለጹት የገንዘብ መቀጮ የማያስተምራቸው አሽከርካሪዎች ላይ ሌሎች ጠንከር ያሉ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ገልጸዋል ።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ ክፍያ እየከፈለ መሆኑና እንደ እቃ ታጉሮ እየተጫኑ በመሆናቸው በተለያዩ መድረኮች "የመንግስት ያለ ሲሉ"ቅሬታዎችን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ከንቲባው ጉዳዩ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል ።

የህብረተሰቡ ቅሬታ ትክክልና ተገቢ መሆኑን የገለጹት የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አሪ ጉርሙ በበኩላቸው ወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመሆን ስርዓት አልበኞችን ህግ በማስከበር ስርዓት ያሲዛል ህብረተሰቡን ከብዝበዛ ይታደጋልም ብለዋል ።

ህብረተሰቡ ሲንገላታና ሲበዘበዝ እንደዋዛ የሚመለከት የመንገድም ሆነ ትራፊክ መዋቅር በስራው እንደማይቀጥልም አሳስበዋል ።

የመንገድና ትራፊክ ፖሊሶች ቸልተኝነት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር እና የአሽከርካሪዎች ራስወዳድነት ተደማምሮ ችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ማድረሱ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን ተናግረዋል።

የመንገድና የትራፊክ ህጎችን እንተግብር ህብረተሰቡን ከበደል እንታደግ ውይይት መድረክ የትራፊክና መንገድ ትራንስፖርት አካላት በጎሪጥ መተያየት እና ተቀናጅቶ አለመስራት ፣ኪራይ ሰብሳቢነት፣ደምብ መተላለፎችን የመንገድና ትራፊክ ፖሊስ ድርሻ አድርጎ መመልከት ፣ከተማና ወረዳ በሚል በመከፋፈል ህጎች ሲጣሱ መመልከት እንዲሁም የመናኸሪያ አገልግሎት ችግሮች ተለይተዋል ።

የመንገድ ደህንነት ህጎችን ለማሰከበር የመናኸሪያ መሪት ማሻሻል ፣ኪራይ ሰብሳቢነትን ማስቆም ፣ድምበር የለሽ ወንጀል መከላከያ ስራ መስራት ፣ተቀናጅቶና የጋራ አቋም በመያዝ የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶበታል።

በመጨረሻም ህገወጥ ቤንዝን ዝውውርን ለማስቆም እንዲሁም የመንገድ ደህነት ህጎችን ለማስከበር አጠቃላይ በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የፖሊስ አባላት ከዛሬ ጀምሮ የትራፊክና መንገድ ደህንነት ህጎችን እንዲያስከብሩ ትዕዛዝ ተሰቷቸው መድረኩ ተጠናቋል ።

የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እየተሰራ ነው!!!=========================ታህሳስ 8/2017ዓ/ምየሸኮ ወረዳና የሸኮ  ከ...
17/12/2024

የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እየተሰራ ነው!!!
=========================
ታህሳስ 8/2017ዓ/ም
የሸኮ ወረዳና የሸኮ ከተማ አስተዳደር በገጠሩና ከተማው አስተዳደሩ ከመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ላይ እየደረሱ ያሉትን እንግልትና ብዝበዛ ለማስቆም ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ ።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ ክፍያና ታጉሮ በመጫናቸው በተለያዩ መድረኮች የሚያሰሙትን ቅሬታዎችን መፍትሔ ለመስጠት እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ የመንገድ ትራንስፖርት ፣የትሪፊክ ፖሊስና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።
በተጨማሪ መረጃ እንመለስበታለን ።

የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስፋት እየታየ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ብድር አመላለስ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!=====...
17/12/2024

የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስፋት እየታየ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ብድር አመላለስ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!
========================
ይህም የተገለጸው የሸኮ ወረዳ ስራ ክህሎት ንግድ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ዛሬ ታህሳስ 8ቀን 2017ዓ/ም ባካሄደው የብድር አመላለስ ንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።

የብድር አመላለሱን በተመለከተ ሰነድ ያቀረቡት የወረዳው ስራ ክህሎት ንግድ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ኤሊያስ እንደገለጹት መንግስት በሀገር ደረጃ የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ወጣቱን በዘርፉ በማሰማራት የእድሉ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ የስራ አጥ ወጣቶች ልየታ ስራ 2 ሺህ 2መቶ 50 ወጣቶች መለየታቸውን ጠቁመዋል።

ብድር ተበድረው በተለያዩ ምክንያቶች ያልመለሱ አካላት እስከ መጋቢት 30/2017ዓ/ም ድረስ በመክፈል ቅጣት መነሳቱን የገለጹት ኃላፊው ተበዳሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ቀድሞ የተሰራጩ ውዝፍ ብድሮችን ማስመለስ ይገባል የሚሉት አቶ ዳግም ብድሩን ማስመለስ የስራ እድል ፈጣራ ህልውና በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል ።

የሸኮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ መጫሎ አለማየሁ በበኩላቸው የኢኮኖሚ ችግርን ለመፍታትና የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

በመደበኛና በተዘዋዋሪ ፈንድ በርካታ ብሮችን በማስመሰል ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ወረዳው በትኩረት እየሰራ መሆኑን በመጠቆም ለተግባሩ ስኬታማነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባልም ብለዋል።

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት ወገስ እንደገለጹት መረጃ በማጥራት ብድር የወሰዱ አካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ብድራቸውን እንዲመልሱ ይሰራል ብለዋል።ኦሞ ባንክና ስራ ክህሎት በዚህ ረገድ ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

መንግስት ስራ አጥ ወጣቶችን በመለየት የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉን የተናገሩት አቶ መሠረት ሆኖም ብድር ከወሰዱ በኃላ ያልመለሱ አካላት ለሌሎች ወጣቶች ስራ ለመፍጠር ተግዳሮት መሆን እንደማይገባቸው ገልጸዋል ።

በስራ እድል ፈጠራ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ የተጠቀሙ ወጣቶች እንደአገር ራሳቸውን በኢኮኖሚ ከመቻል ባለፈ ለአገር ልማት የበኩላቸውን አሻራ በማሳረፍ ላይ የሚገኙበትን ሁኔታም አክለዋል ።

በወረዳው እና ከተማ አስተዳደሩ ከ2006ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016ዓ/ም ድረስ 8 ሚሊዮን 325ሺህ 911 ከ36 ሳንቲም ብድር እንዳልተመለ የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል ።

በመጨረሻም ብድር አመላለሱን በአጭር ጊዜ ለማሳካት በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶበት መድረኩ ተጠናቋል ።

የተሰራጩ ብድሮችን በማስመለስ ለተለዩ ስራ ፈላጊዎች  ስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው!!!============================ታህሳስ 8/2017የሸኮ ወረዳ ስራ ክህሎት ን...
17/12/2024

የተሰራጩ ብድሮችን በማስመለስ ለተለዩ ስራ ፈላጊዎች ስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው!!!
============================
ታህሳስ 8/2017
የሸኮ ወረዳ ስራ ክህሎት ንግድ ገበያ ልማት ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የብድር አመላለስ ንቅናቄ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።

የተሰራጩ ብድሮችን በማስመለስ ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል እንፍጠር በሚል እየተካሄደ በሚገኘው ንቅናቄ መድረክ ላይ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መሠረት ወገስ እንደገለጹት መንግስት ስራ አጥ ወጣቶችንና ሴቶችን በመለየት የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉን ገልጸዋል ።

በመሆኑም በስራ እድል ፈጠራ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ የተጠቀሙ ወጣቶች እንደአገር ራሳቸውን በኢኮኖሚ ከመቻል ባለፈ ለአገር ልማት የበኩላቸውን አሻራ በማሳረፍ ላይ የሚገኙበትን ሁኔታ ጠቁመዋል።

የተሰራጩ ብድሮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስመለስ ለስራ ፈላጊዎች ስራ እንዲፈጠርላቸው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመላክተው ለስኬታማነቱ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።

አሁን የብድር አመላለስ ንቅናቄ ሰነድ በወረዳው ስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልምት ጽ/ቤቱ ኃላፊ በአቶ ዳግም ኤሊያስ በመቅረብ ላይ ይገኛል ።
መድረኩን በመከታተል በተጨማሪ መረጃ እንመለስበታለን ።

የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ተቋቋመ !!!==========================ታህሳስ 7/2017ዓ/ምየሸኮ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ተቋቋመ ።...
16/12/2024

የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ተቋቋመ !!!
==========================
ታህሳስ 7/2017ዓ/ም
የሸኮ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ተቋቋመ ።

የሸኮ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት እንደገለጸው የሀገር ሽማግሌዎች ባህላዊ የግጭት አፈታትን በማዳበር ለሰላምና ዴሞክራሲያዊ አንድነት መጠናከር ረገድ ያላቸው አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።

የሸኮ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ሰባት አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት አቋቁሟል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተክሌ ቡይትን እንደገለጹት ዛሬ የተቋቋመው የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት የተቋሙ ባለድርሻ አካላት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት መቋቋም ጽ/ቤቱ ለባህል እሴት ግምባታ እያከናወነ የሚገኙት ተግባራትን በማገዝ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከባህል እሴት ግምባታ በተጨመሪ የሀገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት አባላት ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም በአካቢያቸው ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።

የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት አባላት በመሆን የተመረጡት የሃገር ሽማግሌዎች እንደገለጹት ባህል፣ቋንቋና ታሪክ ሳይበረዝ ለትውልዱ ለማስተላፍ እንዲሁም በሰላም እሴት ግምባታ ላይ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ።

በዚህም መሠረት አቶ ባንኩ ኢሩሳ፣አቶ ገምታ ያጺኮምስ፣አቶ ካይሳ ታፋ፣አቶ ቢረጋ ሱብሳ፣አቶ ኮምቱ አይበራ፣አቶ ኮምቱ ጃርካብ እና አቶ ጢሞቴዎስ ሼና የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት አባል በመሆን ተመርጠዋል ።

የሸኮ ብሄር የጎሳዎች መሪ በረምበራስ ኮምቱ በዲ እና ሌሎች የተጓደሉ ጎሳ መሪዎች ባህላዊ ንግስና ስርዓት ተጠብቆ እንዲከናወን የሃገር ሽማግሌዎች እየመከሩ ነው!!!=================...
16/12/2024

የሸኮ ብሄር የጎሳዎች መሪ በረምበራስ ኮምቱ በዲ እና ሌሎች የተጓደሉ ጎሳ መሪዎች ባህላዊ ንግስና ስርዓት ተጠብቆ እንዲከናወን የሃገር ሽማግሌዎች እየመከሩ ነው!!!
===========================
ታህሳስ 7/2017ዓ/ም
የሸኮ ንጉስ በረምበራስ ኮምቱ በዲ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም መስከረም 13ቀን 2017ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ ባህላዊ ስርዓቱ ተጠብቆ የኮምቱ በዲ ንግስና እንዲከናወን የሸኮ ሃገር ሽማግሌዎች እየመከሩበት ይገኛሉ ።

ባህላዊ የሸኮ ብሄር ንግስና ስርዓት ባሻገር ሌሎች የተጓደሉ የጎሳ መሪዎች ባህላዊ ንግስና በሚካሄድበት አግባብም መክረውበታል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሸኮ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ቡይትን እንደገለጹት ቀጣይ የሸኮ ብሄር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል ቲከሻ ቤንጊ በወረዳው በድምቀት እንደሚከበር አመላክተዋል ።

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ከወዲሁ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው ከበዓሉ በፊት ባህላዊ ስርዓቱ ተጠብቆ የሸኮ ንጉስ በረምበራስ ኮምቱ በዲና ሌሎችም የተጓደሉ የጎሳ መሪዎች ንግስና ስርዓት እንዲፈጸም ጽ/ቤታቸው ከሀገር ሽማግሌዎች ጎን በመሆን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።

የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ትግሬ ባሻ በበኩላቸው ባህልና ታሪክን ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ የባህል አደራጃጀትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ከኮምቱ በዲ በተጨማሪ ኮኒያብ ፣ዱደብ፣ጎተብና ፋጅንሽ ተኪ ጎሳ መሪዎች ባህላዊ ንግስና እንደሚከናወን ለመረዳት ተችሏል ።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የሃገር ሽማግሌዎች መካከል አቶ ቢረጋ ሱብሳ፣አቶ ባንኩ ያሩሳና አቶ ገምታ ያጺኮምስ እንደገለጹት ቅድሚያ የኮምቱ በዲ ንግስና ከተካሄደ በኃላ ሌሎች የጎሳ መሪዎች ስርዓት ማስኬድ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
አሁን የሃገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ለማቋቋም ውይይቱ እንደቀጠለ ሲሆን በተጨማሪ መረጃ እንመለስበታለን ።

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር በሸኮ ወረዳ የዳማ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።=======================ታህሳስ 7/2017ዓ/ምበቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳ...
16/12/2024

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር በሸኮ ወረዳ የዳማ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
=======================
ታህሳስ 7/2017ዓ/ም
በቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ሀብታሙ ካፍትን የተመራ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በሸኮ ወረዳ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘውን የዳማ ወንዝ ድልድይ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተለያዩ ልማቶች እየተሰሩ መሆኑ ይታወቃል ።ዋና አስተዳዳሪው የዞኑ መንግስት ከዚህ ቀደም ድጋፍ ካደረገው ባሻገር ዛሬም የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

የዞኑ መንግስት በዳማ ወንዝ ድልድይ የመሰሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ላይ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ተጨማሪ የ1 ሚሊየን ድጋፍ አድርጓል ።

የዳማ ወንዝ ድልድይ በ22 ሚሊየን ብር ወጪ የሚሰራ 22 ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር ርዝመት ያለው ነው።

ኪስ አውላቂው እጅ ከፍንጅ በመያዙ በእስራት ተቀጣ!!!============================ከገበያ ዉስጥ ከግለሰብ ኪስ ዉስጥ የገንዘብ ስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይ...
15/12/2024

ኪስ አውላቂው እጅ ከፍንጅ በመያዙ በእስራት ተቀጣ!!!
============================ከገበያ ዉስጥ ከግለሰብ ኪስ ዉስጥ የገንዘብ ስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በእስራት ተቀጣ።

የአመያ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር መንክሮ ታመኔ እንደገለፁት በአመያ ከተማ አስተዳደር በሚዉለዉ ቅዳሜ ገበያ ከብት ተራ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተከሳሽ አዱኛ ዶኖቾ ከግል ተበዳይ ኪስ ዉስጥ 2,150 ብር ሲያወጣ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በፖሊስ ምርመራ ተጣርቶበት ፍርድ ቤት መቅረቡን ተናግረዋል።

የፍትህ አሰጣጡን በማቀላጠፍ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ በመላክ የአመያ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ በስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶበት እንደመሠረተበት ገልፀዋል።

በዚሁ መሠረት የአመያ ከተማ አስተዳደር የመጀመረያ ደርጃ ፍርድ ቤት እጅ ከፍንጅ ችሎት እግዚቭቱን አስቀርቦ የምስክሮችን ቃል አድምጦ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ አዱኛ ዶኖቾ በሁለት ዓመት እስራት እንድቀጣ እንደተወሰነበት አስረድተዋል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ተማሪዎችን በስነ ልቦና እየገነባ ነው!!!============================የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ባለ ልዩ  ተሰጥኦ አዳሪ ትምህርት ቤት ከሚዛን ቴፒ...
15/12/2024

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ተማሪዎችን በስነ ልቦና እየገነባ ነው!!!
============================
የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ባለ ልዩ ተሰጥኦ አዳሪ ትምህርት ቤት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለተማሪዎች የህይወት ክህሎት ፣የስነ ልቦና (ሳይኮሎጂ) ስልጠና ሰጥቷል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የትምህርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ታምራት ከበደ እንደገለፁት ማህበሩ ከሚሰራቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አንዱ የትምህርት ሥራው መሆኑን ተናግረዋል።

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን በዞኑ ውስጥ በተዘጋጀ ስታንዳርድ ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎች በመማር ማስተማሩ ሂደት ውጤታማ እንዲሆኑ የተሻሉ መምህራን እንዲያስተምሯቸው ከማድረግ ባሻገር የተለያዩ ድጋፍ እየተደረጉላቸው መሆኑን ተናግረዋል ።

በሚቀጥለው ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የተሻለ ውጤት ተማሪዎቻችን እንዲያስመዘግቡ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የምርምር የህትመት ና ስነ ምግባር ስርፀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አስካለ ገብረሚካኤል እንደገለፁት ተማሪዎች የስነ ልቦና ተግዳሮቶች ተቀርፈውላቸው መነቃቃትን በመያዝ ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ የህይወት ክህሎት ስልጠና ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

ተማሪ ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት በመሆኑ ለትምህርት ጥራት አጋዥ የሆነ ስራ ወደኃላ ማለት አይገባም ብለዋል።

ዶ/ር ረጋሳ ቤኛ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ፣ የማቴሪያል ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ከትምህርት ጋር ያላቸው ቁርኝት እንዲጨምር በስነ ልቦና ስልጠና ማገዝ ራዕያቸውን እንዲያሳኩ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

መምህር ሀብቱ ዝናቤ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር እንደገለፁት ተማሪዎች በዕድሜያቸው ፣በትምህርት ፣ በግል ህይወታቸው ሊገጥሟቸው የሚችሉ ፈተናዎችን አልፎ ውጤት ላይ ለመድረስ መሰረታዊ የሚባሉ የችግር መፍቻ ዘዴዎችን ማወቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ችግርን ና ጭንቀትን መፍታት ከሰው ሰው ፣ከዕድሜ ዕድሜ ፣ ከሁኔታ ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ የተለያየ ቢሆንም መሠረታዊ የሚባሉትን የችግር መፍቻ በመጠቀም ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለዋል።

ስልጠናውን እየተከታተሉ ካሉ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ስጦታ ግርማ፣ በእምነት ጌታሁን ፣በረከት ውበቱ እና ፂዮን ግርማ በሰጡት አስተያየት የሚገጥሙንን ችግሮች እንዴት መፍታት እንዳለብን ፣ ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባንና የመፍትሄ ሰው መሆን እንደሚገባን ግንዛቤ አገኝተንበታል ብለዋል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ባለ ልዩ ተሰጥኦ አዳሪ ትምህርት ቤት ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ከ160 በላይ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ሲል ቤሸኮ ዘግቧል ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sheko Wereda Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share