Ethio 724

Ethio 724 ታማኝና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግነት ገፃችንን ላይክ እና ፎሎው ማድረግ አይርሱ ።

ጨዋታ ነውመርካቶ አካባቢ ነው ሌሎች ቪዲዮዎችንም አይተናል ተቃቅፈው እየተሳሳቁ እና አረጋጉት።ሰላሙን ሁሉ ለሀገራችን ይሁን።
19/04/2024

ጨዋታ ነው
መርካቶ አካባቢ ነው ሌሎች ቪዲዮዎችንም አይተናል ተቃቅፈው እየተሳሳቁ እና አረጋጉት።
ሰላሙን ሁሉ ለሀገራችን ይሁን።

18/04/2024

አንጀቴ ተላወሰ አባቴ ቢሆንስ😭😭😭
ፋኖ የሚዋጋበት ምክኒያት ከገባችሁ ይህንን ለመከላከል እና ለማስቀረት ነው።

08/04/2024

ለባለሀብቱ ወርቁ አይተነው መልክት አለኝ
ደህና ልጅ መስለከኝ 🤣🤣🤣

ባህርዳር ከተማ አባት ከሶስት ልጆቻቸውና አንድ ጎረቤታቸው ጋር በጥይት መገደላቸው ተሰምቷል።   ትናንት መጋቢት 29/2016 ምሽት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ 14 መስ...
08/04/2024

ባህርዳር ከተማ አባት ከሶስት ልጆቻቸውና አንድ ጎረቤታቸው ጋር በጥይት መገደላቸው ተሰምቷል።

ትናንት መጋቢት 29/2016 ምሽት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ 14 መስጅድ ከሚባለው መስጅድ የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲወጡ የነበሩ አባት እና ሶስት ልጆችን ጨምሮ 5 ሰዎች በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

አቶ ሙሄ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ፣ሽኩር ሙሄ፣ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉት እነኝህ 5 ሰዎች ከጥቃቱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም መትረፍ አለመቻላቸው ታውቋል።

ከመስጅድ ሲወጡ በጥይት የተመቱት 5 ሰዎች ግድያ በማን ለምን እንደተፈጸመ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።በክልሉ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ መሰል ተግባራት መበራከታቸው ተሰምቷል።መረጃው ከ Link Ethiopia የተወሰደ ነው።

08/04/2024

ልጆች እባካችሁ ቀስ ብላቹ እደጉ

08/04/2024

አርሰናሎች

የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?የ   በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ  ማታ ከታየች  #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ  #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋ...
06/04/2024

የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

የ በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ******************ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወ...
06/04/2024

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
******************
ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ወንጀሉን የፈፀሙ አካላትን ለመቆጣጠር የምርመራና የክትትል ቡድኑ ሌት ከቀን በመስራት ውጤት ማምጣት መቻሉን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አሽከርካዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት ተገድሎ ይገኛል፡፡
የወጣቱ መገደል ሪፖርት የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እና የክትትል ቡድኖችን በማዋቀር የገዳዮቹን ማንነት ለማወቅ ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሷል፡፡
ሟች ወጣት ሶፎኒያስ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በግል በተደረገ ስምምነተ ያለአፕልኬሽን ምዝገባ በኮድ 2 ቪትዝ አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው የምርመራና የክትትል ቡድን አባላት ባሰባሰቡት ማስረጃ ማረጋገጣቸውን ፖለስ አክሏል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ካሳፈራቸው በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው መሰወራቸው ተጠቁሟል፡፡
ፖሊስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ ቀን ከሌት ባደረገው ብርቱ ክትትል ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ፣ ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች እና የሰረቁትን መኪና እንዲሁም ሶስት አባሪዎቻቸውን መያዙን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ላይ ባለቤታቸው የማን እንደሆኑ የማይታወቁ 7 የስልክ ሲም ካርዶችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ጨምሮ ገልፆል፡፡
ምንም እንኳን ወንጀሉ በስውር የተፈፀመና ማንነታቸው የማይታወቁ ቢሆንም በተደረገ ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በመለየት ሦስት ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችን እና ሦስት ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
ለዚህ ስራ ስኬታማነት ቀና ትብብር ላደረጉ አካላት አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ፤ የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ህጉን ጠብቀው አገልግሎት ሲሰጡ በአፕልኬሽኑ ተመዝግበው እንዲሆን ፖሊስ አሳስቧል።

የፍኖተ ጽድቅ መስራችና የስራ ኃላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ ጠየቁ‼ፍኖተ ጽድቅ አገልግሎትና የማህበሩ ሚዲያ በአሠራጫቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዐተ አምል...
06/04/2024

የፍኖተ ጽድቅ መስራችና የስራ ኃላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ ጠየቁ‼

ፍኖተ ጽድቅ አገልግሎትና የማህበሩ ሚዲያ በአሠራጫቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዐተ አምልኮና የትውፊት ጥያቄዎች ሲቀርቡበትም ነበር።
በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ጉባኤና በጉባኤው በሚመደቡ መምህራንና መዘምራን፣ በጉባኤው በሚሰጡ ትምሀርቶችና በሚዘመሩ መዝሙራት፣ በመዝሙር መሣሪያዎች አጠቃቀምና የአዘማመር ስልቶች ላይ ጥያቄዎች ሲነሡና አንዳንድ ጊዜም የቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የልዩነትና የውዝግብ ምክንያት ሲሆንም ታይቷል።
ይህን ተከትሎም የፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ብቻ ማዕከል አድርጎ ማገልገል በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምሀራነ ወንጌልና በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወንድሞች፤ የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከማኅበሩ አመራሮች ጋር ለበርካታ ጊዜያት ውይይትና ምክክርም ሲያደርጉም ቆይተዋል።
በውይይቱም መሰረት ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል
👉 በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር በመደበኛ መምህርነት ተቀጥረው የሚያስተምሩ መምሀራን ማስተማር አቁመው በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳም ሔደው ጥሞና እንዲወስዱና በሚመደቡላቸው ኦርቶዶክሳውያን መምሀራን ሥልጠና እንዲወስዱ።
👉 ከኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና ትውፊት ያፈነገጡ መዝሙራትም ሆኑ ያልሆኑ ከፍኖተ ጽድቅ የዩቱብ ቻናል ሙሉ በሙሉ እንዲወርዱ።
👉 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለመዝሙር አገልግሎት ከምትጠቀማቸው የዜማ መሣሪያዎች ወጭ ያሉት የሙዚቃ መሣሪያዎችና ማቀናበሪያዎች በሙሉ እንዲወገዱ።
👉 በኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የዜማ መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ የፍኖተ ጽድቅ የጎብረት ዘማርያንና የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾች ሥልጠና እንዲወስዱ።
👉 ፍኖተ ጽድቅ ወደፊት በሚሰጣቸው የትምሀርትና የመዝሙር አገልግሎቶች ኦርቶዶክሳውያን መምሀራንና ዘማረያን ብቻ እንዲያገለግሉ።
👉 የፍኖተ ጽድቅ መስራችና የስራ ኃላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ እንዲጠይቁ።
👉 በፍኖተ ጽድቅና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ላይ አተኮረው የሰሩ ቲክቶከሮች የሰሯቸውን ቪዲዮዎች እንደያወርዱ፤ መምሀራኑም እንዲሁ እንዲያደርጉ።
በእነዚሀ የጋራ ስምምነት መሠረትና የወደፊቱን አገልግሎት በማሰብ ፍኖተ ጽድቅ ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነት ፣ ሥርዓት እምልኮ ፣ ትውፊት የተላለፋም ሆኑ ያልተላለፋ መዝመሮች በሙሉ ከዩቱብ ቻናል እንዲውርድ ተደርጓል።

06/04/2024
06/04/2024

የሞተ ሰው በልቶ ህይወቱን ያተረፈው

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ  እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት ታገደዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን፣ አሰያየምን፣ እና አጠቃቀምን በተመለከተ የተሟላ የ...
05/04/2024

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት ታገደ
ዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን፣ አሰያየምን፣ እና አጠቃቀምን በተመለከተ የተሟላ የአካሄድ መረጃ የሚሰጥ መመሪያ ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ተገለፆል ።
ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው ::
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የክብር ዶክትሬት ሽልማትን በተመለከተ ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ባቀረቡት ሰፊ የጥናት ፅሑፍ የክብር ዶ/ር ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም:: እንዲሁም ረ/ፕ ወይም ተ/ፕ የሚለውም ስያሜም ለመጠራያነት አይውልም በማለት ተናግረዋል::
ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት ዲግሪን አሰጣጥ በተመለከተ መመርያ ማውጣት እንደሚገባው ፕ/ር ማስረሻ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብዙ የዶክትሬት ትምህርት ተማሪዎች ያሉ ቢሆንም ለትምህርቱ የሚያስፈልገው ግብዓት አለመሟላት እና በቂ ዝግጅት አለመኖር ተግዳሮት መሆኑን በማንሳት ይህን ያገናዘበ የትምህርት ፕሮግራም መዘጋጀት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት መታገዱን ገልፀዋል፡፡

05/04/2024

ህጉ ምን ይላል
ንግድ ባንክ ፎቶ በለጠፍ ይችላል አይችልም?

ኤርትራ 60 በመቶ የሚሆነው የኢሮብ ብሄረሰብ መሬት በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተነገረ፡፡በትግራይ ክልል የሚገኘው የኢሮብ ብሄረሰብ 60 በመቶ  መሬት በኤርትራ ቁጥጥር ስር ተይዟል  መባሉን ኢትዮ ...
04/04/2024

ኤርትራ 60 በመቶ የሚሆነው የኢሮብ ብሄረሰብ መሬት በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተነገረ፡፡
በትግራይ ክልል የሚገኘው የኢሮብ ብሄረሰብ 60 በመቶ መሬት በኤርትራ ቁጥጥር ስር ተይዟል መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
ይህንን ያለው ደግሞ ኢሮብ አኒና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡
የድርጅቱ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተስፋይ አብዓላ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳስታወቁት ከሆነ በወረዳው ካሉ ስድስት ቀበሌዎች ሁለቱ በከፊል ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርትራ መጠቅላሉን ተናግረዋል፡፡
የኤርትራ መንግስት መሬቱን መውሰዱም ብቻ ሳይሆን በብሄረሰቡ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳቶችን እያደረሰ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተለይም መንገዱን በመዝጋቱ የተነሳ ምንም ዓይነት እርዳታ ወደ አካባቢው እንዳይደርስ በማድረጉ ብሄረሰቡ ለከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ህዝቡ ምንም ዓይነት ማህበራዊ አገልግሎት እያገኘ አይደለም የሚሉት አቶ ተስፋይ ከዛ ባለፈም በግዴታ ኤርትራዊ ናችሁ እየተባሉ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡
"አከባቢው ወደ ኤርትራ ተጠቃሏል ከዚህ ወዲህ ኤርትራዊ ናችሁ ልጆቻቹም አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት መላክ ይኖርባችሃል" እየተባሉ ማስገደድ መጀመራቸውንም አንስተዋል፡፡
የኤሮብ መሬት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የኤርትራ አካል ሆኖ አያውቅም ይሁን እንጂ የኤርትራ መንግስት ድንበር ተሻግሮ መሬት መውረሩ የፌደራል መንግስት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ከ2013 ዓ.ም ጦርነቱ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ ምንም ዓይነት ሰብዓዊ እርዳታ ያላገሳ ህዝብ በዚህ ሁኔታ ውስጥ መገኘቱ አሳዝኖናል ብለውናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም ተወሮ የሚገኘውን መሬት በማስለቀቅ ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ  ከ...
04/04/2024

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ።
ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B21705 አ.አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት የኩላሊት ታማሚ ነው ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ሲሆን በተያዙበት ወቅት ከአምስት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፤ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት የማታለል ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ በሚያደርግበት ወቅት ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ብልፅግና ፓርቲ በፕሪቶሪያ ውል መሰረት ፓለቲካዊ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ።ህወሓት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ  ባሰራጨው መረጃ...
02/04/2024

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ብልፅግና ፓርቲ በፕሪቶሪያ ውል መሰረት ፓለቲካዊ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ።

ህወሓት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ ፥ በብልፅግና ምክትል ፕረዚደንት አቶ አደም ፋራህ የሚመራ ቡድን ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም በመቐለ ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይቷል።

የሁለቱም ፓለቲካዊ ፓርቲዎች የፓለቲካ ውይይት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ቀደም ብሎ መጀመር እንደነበረበት በመተማመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲጀምሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ህወሓት ገልጿል

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለየታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ...
02/04/2024

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ
የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታውቀዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት አስመልክቶ በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ይህንን ያስታወቁት።
ኢንጅነር ክፍሌ የግድቡ ግንባታ አሁን ስለደረሰበት ደረጃ ሲያብራሩም፤ የህዳሴ ግድብ የኮንክሪት ሙሌት ግንባታ 99 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
በዚህም ከ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ውስጥ የ10 ነጥብ 65 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ሙሌት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት የግድቡ የሲቪል ሥራዎች 99 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች አፈፃፀም 79 በመቶ መድረሱንም ነው ሥራ አስኪያጁ ያስታወቁት።
እንደ ኢንጂነር ክፍሌ ገለፃ የውሃ ማስተላለፊያና መቆጣጠሪያ የብረታብረት ሥራዎች አጠቃላይ አፈፃፀም 90 በመቶ ተከናውኗል።
እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም ድረስ ለፕሮጀክቱ ግንባታ 191 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉነ ያስታወቁት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ቀሪ የግድቡን የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅም 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪካ ኃይል መረጃ ያመለክታል።
የኮንትራት ማሻሻያ መደረጉ፣ የተጣበበ የፕሮጀክት ጊዜ ሰሌዳና በግንባታ ወቅት በግድቡ መሠረት ላይ ያጋጠመ ልል ድንጋይ መኖሩ እንዲሁም የልምድ ማነስ እና የጥራትና ልኬት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ከዚሀ ቀደም ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ግድቡ በቀጣዩ ዓመት ማለትም በ2017 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠቃሎ ተገንብቶ ኢትዮጵያውያንና ጎረቤቶቿን ማገልገል እንደሚጀምር መግለጻው ይታወሳል።
እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ ፕሮጀክቱ በቀጣይ ተጠናቆ የሚጠበቅበትን 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል። ይህም የኢትዮጵያን አጠቃላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም በእጥፍ የሚያሳድግ ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዛሬ 13 ዓመታት በፊት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር በይፋ የተጀመረው።
ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ሁለት ተርባይኖች ሀይል በማመንጨት ላይ ናቸው።
የካቲት ወር 2014 ዓ.ም ግድቡ ካሉት ተርባይኖች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ዩኒት 10 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 270 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።
በነሃሴ ወር 2014 ላይ ደግሞ ዩኒት 9 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 270 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 540 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨም ይገኛል።
ዘገባው የዐል ዐይን ነው

ሜቴክ 6.5 ሚልየን ብር እንዲከፍለኝ ብከስም፤ ጭራሽ 1.5 ሚልየን ብር እንድከፍል ተፈርዶብኛል- ቅሬታ “ፍትህ በስልጣን ተሸፍናለች” ሲል ቅሬታውን ለአዲስ ማለዳ ያቀረበው እሱባለው ተካልኝ፤...
02/04/2024

ሜቴክ 6.5 ሚልየን ብር እንዲከፍለኝ ብከስም፤ ጭራሽ 1.5 ሚልየን ብር እንድከፍል ተፈርዶብኛል- ቅሬታ

“ፍትህ በስልጣን ተሸፍናለች” ሲል ቅሬታውን ለአዲስ ማለዳ ያቀረበው እሱባለው ተካልኝ፤ በቀድሞ መጠሪያ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አሁን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከተባለው ተቋም ያልተከፈውን 6.5 ሚልየን ብር በፍርድ ቤት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ 1.5 ሚልየን ብር ለድርጅቱ እንዲከፍል ተፈርዶብኛል ብሏል።

01/04/2024

ትዝታ እውነታውን ተናገረችው

01/04/2024

ድንበር እንጠብቅ

አለልኝ አዘነ ህልፈትየሳውዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየን ተጫዋች አለልኝ አዘነን ህልፈት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የሀዘ...
01/04/2024

አለልኝ አዘነ ህልፈት
የሳውዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየን ተጫዋች አለልኝ አዘነን ህልፈት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የሀዘን መግለጫ ደብዳቤ ልኳል።

ሰላም ነው የምንፈልገው ‼በኮረም፣ ዛታ፣ ወፍላ  ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ትህነግ የሚፈፅመው ትንኮሳ እንዲቆም፣ የሕዝብ ምርጫ እንዲከበር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል። ለዳግም ባርነት ተላልፈን አንሰ...
01/04/2024

ሰላም ነው የምንፈልገው ‼
በኮረም፣ ዛታ፣ ወፍላ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ትህነግ የሚፈፅመው ትንኮሳ እንዲቆም፣ የሕዝብ ምርጫ እንዲከበር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል። ለዳግም ባርነት ተላልፈን አንሰጥም ብሏል። በአላማጣና ሌሎች አካባቢዎችም በተመሳሳይ በርካታ ሕዝብ የተገኘባቸው ሰልፎች ሲደረጉ ሰንብተዋል።

01/04/2024

በኦሮሚያ ክልል ከለውጡ በኋላ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ''ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን'' በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል።

ቮልቮ የተሰኘው የመኪና አምራች ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት አቆመ‼️ቮልቮ ዋና ቢሮውን ጎተንበርግ ስዊድን ያደረገ የዓለማችን መኪና አምራች ኩባንያ ነው    ዋና መቀመጫውን ጉተን...
01/04/2024

ቮልቮ የተሰኘው የመኪና አምራች ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት አቆመ‼️
ቮልቮ ዋና ቢሮውን ጎተንበርግ ስዊድን ያደረገ የዓለማችን መኪና አምራች ኩባንያ ነው

ዋና መቀመጫውን ጉተንበርግ ስዊድን በማድረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል ቮልቮ ኩባንያ፡፡

ኩባንያው የመጨረሻዬ ናት ያላትን በነዳጅ የምትሰራ ተሽከርካሪ ምርትን ለገበያ ያስተዋወቀ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በቀጣይም ሙሉ ትኩረቱን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማምረት ላይ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በ2030 በአህጉሪቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ለሙሉ የማገድ እቅድ እንዳለው ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች ትኩረታቸውን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ ላይ መሆናቸው አልአይን በዘገባው አመልክቷል።

 #አሳዛኝ ዜና‼️👉ጅቦች በልጆች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ መጥቷል‼️✅ መጋቢት 22/2016 ዓ.ም ጉባ በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ማለደ የወጣው ጅብ በ6 ዓመት ህፃን ለይ ጉዳት በ...
01/04/2024

#አሳዛኝ ዜና‼️
👉ጅቦች በልጆች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ መጥቷል‼️
✅ መጋቢት 22/2016 ዓ.ም ጉባ በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ማለደ የወጣው ጅብ በ6 ዓመት ህፃን ለይ ጉዳት በመድረሱ ህይወቱ አልፏል።

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በጉባ ከተማ ትናንት ጠዋት የወጣው ጅብ በአንድ በ6 ዓመት ህፃን ልጅ ጉዳት በመድረሱ ህይወቱ አልፏል ።

✅ ጅቡ ህፃኑን አንጠልጥሎ ስሮጥ የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ የህፃኑ አስከሬን ማስጣል የተቻለ ሲሆን በጅቡ ላይም ፖሊስ እርምጃ ወስዶባታል።

✅ የተራቡ ጅቦች በየአካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ሲል የወረዳው ፖሊስ ገልጿል

አዋርድ አሸነፈበግራም ፒብልስ ዳይሬክት የተደረገው "አሁንም በሕይወት አለን፦ በኢትዮጵያ በአማራ ላይ የሚደረግ የዘር ማጥፋት" በሚለው የተሰራው ልዩ አጭር ዘጋቢ ፊልም ሁለት ታዋቂ የፊልም ሽ...
01/04/2024

አዋርድ አሸነፈ
በግራም ፒብልስ ዳይሬክት የተደረገው "አሁንም በሕይወት አለን፦ በኢትዮጵያ በአማራ ላይ የሚደረግ የዘር ማጥፋት" በሚለው የተሰራው ልዩ አጭር ዘጋቢ ፊልም ሁለት ታዋቂ የፊልም ሽልማቶች አሸንፏል:: ሽልማቶቹም በዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Global Film Festival) ቤስት ዘጋቢ ፊልም በሚል እና የዓለም ፊልም ፌስቲቫል በካንስ (World Film Festival in Cannes) ቤስት የሰብዓዊ መብት ላይ የተሰራ ፊልም በሚል ያገኘው ናቸው::

 #አዲስአበባ  #ነዳጅየኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ...
01/04/2024

#አዲስአበባ #ነዳጅ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል።

የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ " ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ውስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ? የተባሉት አቶ ደሳለኝ፤ " ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነው እየተጫነ ያለዉ ፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ " ብለው " መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች እየተስተዋሉ ይገኛል።

ይህ መረጃ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

በአክሱም በጭንቅላት የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ።ሴት መንትዮቹ  (Conjoined twins) እንዲሁም እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ይገኛሉ ተብሏል።መጋቢት 22 /2016 ሌሊት በሪፈር የተላከ...
01/04/2024

በአክሱም
በጭንቅላት የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ።

ሴት መንትዮቹ (Conjoined twins) እንዲሁም እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ይገኛሉ ተብሏል።

መጋቢት 22 /2016 ሌሊት በሪፈር የተላከች እናት በቆዶ ጥገና 5 ኪሎ የሚመዘኑ በጭንቅላት የተጣበቁ ሴት መንትዮች እንደተገላገለች የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገልጿል።

ወላጅ እናት ለአዋላጅ ሃኪም የሰጠችው መረጃ በመጥቀስ ባለሙያዎች እንዳሉት ፥ እናቲቱ የፅንስ ክትትል በአቅራቢያዋ በሚገኝ የጤና ማእከል ውስጥ ስታደርግ የቆየች ብትሆንም የአልትራሳውንድ ምርመራ ባለማድረግዋ በማህፀንዋ የነበሩት መንትዮች ሁኔታ ቀድማ ማወቅ አልቻለችም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ያገኘው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio 724 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share