ናቶ /Naato/ የጋሞ ወጣቶች ህብረት ለፍትህ፥ ለእኩልነት፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ

  • Home
  • ናቶ /Naato/ የጋሞ ወጣቶች ህብረት ለፍትህ፥ ለእኩልነት፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ

ናቶ /Naato/ የጋሞ ወጣቶች ህብረት ለፍትህ፥ ለእኩልነት፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ "በባርነት ከመኖር በነፃነት መሞት ለነፍስ ዕረፍት ነው!"
(1)

ከግንቦት ወር ጀምሮ የሰራነው የወር ደሞዛችን ይከፈለን በማለት ፍትህን ለካምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በጠየቀው በካምባ ወረዳ መምህሩ በጀግናው ማርቆስ...
02/08/2024

ከግንቦት ወር ጀምሮ የሰራነው የወር ደሞዛችን ይከፈለን በማለት ፍትህን ለካምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በጠየቀው በካምባ ወረዳ መምህሩ በጀግናው ማርቆስ ኮርቾቸ ላይ የተወሰደው የእስራት እርምጃ ኢሰብዓዊ የሆነ የገዥውም መንግስት አምባገነናዊነት በግልፅ ያሳየና በጥብቅ የሚወገዝ በመሆኑ መምህሩ በአፋጣኝ ይፈታ ዘንድ የጋሞ ናቶ ይጠይቃል።

አብዮት ሊቀጣጠል ይችላልአቶ ክቡር ገናመንግስት የወሰደውን የተሳሳተ የኢኮኖሚ እርምጃ ተከትሎ በኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ አቶ ክቡር ገና ተናገሩ
02/08/2024

አብዮት ሊቀጣጠል ይችላል
አቶ ክቡር ገና

መንግስት የወሰደውን የተሳሳተ የኢኮኖሚ እርምጃ ተከትሎ በኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ አቶ ክቡር ገና ተናገሩ

በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በመሬት ናዳ አደጋ በደረሰው አስከፊ የሆነ የወገኖቻችን ሞት የተሰማን ሀዘን ጥልቅ ነው።የወገኖቻችንን ነፍስ ይማርለሟች ቤተሰቦች እና ለመላው የጎፋ ዞን ህዝብ መፅናናትን...
23/07/2024

በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በመሬት ናዳ አደጋ በደረሰው አስከፊ የሆነ የወገኖቻችን ሞት የተሰማን ሀዘን ጥልቅ ነው።

የወገኖቻችንን ነፍስ ይማር
ለሟች ቤተሰቦች እና ለመላው የጎፋ ዞን ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን።

ብርሃኑ ነጋ ካልተቀበለ ብርሃኑ ጁላ ይቀበላቸዋልመንገድ እየሄድን ወደ ዩንቨርሲቲ የሚጏዙ የ12 ክፍል ተማሪዋች መንገድ ዘግተው እየጨፈሩ አገኘናቸው:: አብሮኝ የሚጏዘው "... ለፈተና እየሄዱ...
16/07/2024

ብርሃኑ ነጋ ካልተቀበለ ብርሃኑ ጁላ ይቀበላቸዋል

መንገድ እየሄድን ወደ ዩንቨርሲቲ የሚጏዙ የ12 ክፍል ተማሪዋች መንገድ ዘግተው እየጨፈሩ አገኘናቸው:: አብሮኝ የሚጏዘው "... ለፈተና እየሄዱ ምን ያስጨፍራቸዋል? ውጤቱ ሲመጣ ቢጨፍሩ አይሻልም?" አለ:: ሁለተኛው እየሳቀ "እነኝህ የሚጨፍሩት 100 ወጣቶች ናቸው ብለን ብንወስድ 3ቱ ብቻ እኮ ናቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት የሚመለሱት:: 97ቱ ልጆች አሁን በደንብ ይጨፍሩ ምክንያቱም ለመጀመሪያ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ ሊዶርሙ ነው::" እኔ በድንጋጤ "97% መውደቅ አሳሳቢ ነው መንግስት ለነዚህ ወጣቶች የሆነ ነገር ማዘጋጀት አለበት" አልኩ:: ሹፌራችን ፈጠን ብሎ "መንግስት አዘጋጅቷል ብርሃኑ ነጋ ካልተቀበለ ብርሃኑ ጁላ ይቀበላቸዋል ችግር የለም" አለ:: አይባልም:: ሁሉም ሳቀ 🤣🤣🤣 አያስቅም:: ጨዋታ ተቀየረ::

ወደፊት 3% ህዝባችን የዩንቨርስቲ ምሩቅ ሲሆን 97%ቱ ምንድነው የሚሆነው?
በዘመነ ብልፅግና የማይሰማ ጉድ የለም።
ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ህይወት እና ሰላም አንዳች ግድ ሳይለው ህዝብን እያስራበና እያጋደለ መብራት በማብለጭለጭ በስልጣን ለመቆየት የሚሞክር ጅል መንግስት።

«የተማሪዎቹ እገታ በብልጽግና የተቀነባበረ ነው»ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድንራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ፣መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ሰ...
12/07/2024

«የተማሪዎቹ እገታ በብልጽግና የተቀነባበረ ነው»ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ፣መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እግቷል መባሉን አስተባበለ። የኦሮምያ መንግሥት ኮምኒኬሽን ቢሮ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ያለውን ቡድኑን በአጋችነት ከሷል። እገታውን በገዥው የብልጽግና ፓርቲ አባላት የተቀነባበረ ያለው ቡድኑ ግን ለእገታው «የብልጽግና ካድሬዎች ፣ሰላዮች እና የፀጥታ ኅይሎች»ያላቸውን ተጠያቂ ማድረጉን አዲስ ስታንዳርድ የተባለው የሀገር ውስጥ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩት ከ160 በላይ ተማሪዎች የታገቱት ገርባ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ነበር። የኦሮምያ መንግሥት ከ167ቱ ታጋቾች መካከል 160ውን ማስለቀቅ መቻሉን እና ቀሪዎቹንም ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ ነበር ያስታወቀው ።ይሁንና ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የተማሪዎቹ ጓደኞችና ቤተሰቦች ግን እስከ ትናንት ድረስ ተማሪዎቹ አልተለቀቁም ብለዋል። ከእገታ ያመለጠ አንድ ተማሪም ትናንት እንደተናገረው ተማሪዎቹ አሁንም በአጋቾች እጅ ናቸው። ቤተሰቦች እንደሚሉት የሚገኙበት ሁኔታም አሰቃቂ ነው። አንድ የታጋች ተማሪ እህት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት አጋቾቹ ደውለውላቸው ብዙ ገንዘብ እንዲያመጡ ጠይቀዋቸዋል።

«የተማሪዎቹ እገታ በብልጽግና የተቀነባበረ ነው»ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ፣መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እግቷል መባሉን አስተባበለ። የኦሮምያ መንግሥት ኮምኒኬሽን ቢሮ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ያለውን ቡድኑን በአጋችነት ከሷል። እገታውን በገዥው የብልጽግና ፓርቲ አባላት የተቀነባበረ ያለው ቡድኑ ግን ለእገታው «የብልጽግና ካድሬዎች ፣ሰላዮች እና የፀጥታ ኅይሎች»ያላቸውን ተጠያቂ ማድረጉን አዲስ ስታንዳርድ የተባለው የሀገር ውስጥ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩት ከ160 በላይ ተማሪዎች የታገቱት ገርባ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ነበር። የኦሮምያ መንግሥት ከ167ቱ ታጋቾች መካከል 160ውን ማስለቀቅ መቻሉን እና ቀሪዎቹንም ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ ነበር ያስታወቀው ።ይሁንና ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የተማሪዎቹ ጓደኞችና ቤተሰቦች ግን እስከ ትናንት ድረስ ተማሪዎቹ አልተለቀቁም ብለዋል። ከእገታ ያመለጠ አንድ ተማሪም ትናንት እንደተናገረው ተማሪዎቹ አሁንም በአጋቾች እጅ ናቸው። ቤተሰቦች እንደሚሉት የሚገኙበት ሁኔታም አሰቃቂ ነው። አንድ የታጋች ተማሪ እህት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት አጋቾቹ ደውለውላቸው ብዙ ገንዘብ እንዲያመጡ ጠይቀዋቸዋል።

ሁሉም ነገሩ ውሸት የሆነ መንግስትይህን መንግስት የነገ አገር ተረካቢ ከሆኑ ህፃናቶች አጠገብ በማራቅ ኢትዮጵያን እንታደጋት።የታገቱት ተማሪዎች እንዳልተለቀቁ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች እየተናገሩ ይ...
11/07/2024

ሁሉም ነገሩ ውሸት የሆነ መንግስት
ይህን መንግስት የነገ አገር ተረካቢ ከሆኑ ህፃናቶች አጠገብ በማራቅ ኢትዮጵያን እንታደጋት።

የታገቱት ተማሪዎች እንዳልተለቀቁ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች እየተናገሩ ይገኛሉ። አጋቹ መንግስት እኔጋ ናቸው ያሉት ነገር ግን የተጠየቃቹትን ገንዘብ ክፈሉና ልጆቻችሁን እለቅላችኋለው እንዳለ የሚያሳብቀውን መረጃ ነው ትላንት በዜና መልክ ያወጣው።

‹‹ ተማሪዎቹ አልተለቀቁም የተሰራጨው ዜና ሀሰት ነው ›› - የታጋች ቤተሰቦች

‹‹ ተማሪዎቹ ተለቅቀዋል ›› - የኦሮሚያ ክልል

‹‹ እያጣራሁ ነው፤ አዲስ ነገር የለም ›› - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

አሻም ዜና | ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ከታገቱት 167 ተማሪዎች ውስጥ 160ዎች መፈታታቸውን ለአሻም ቢናገሩም ሦስት የታጋች ቤተሰቦች ግን መረጃውን ‹‹ ሀሰት ነው ›› ሲሉ ነቅፈውታል፡፡

የታጋቾች ቤተሰቦች እንደሚሉት ‹‹ የታገቱ ተማሪዎች ተፈተዋል ተብሎ በመገናኛ ብዙሀን የተሰራጨው ዜና ሀሰት ነው፤ ተማሪዎቹን ለመልቀቅ ከአምስት መቶ ሺህ እስከ 700ሺ ብር ›› ትናንት ተለቅቀዋል በተባለትም ሆነ በዛሬው ዕለት እየተጠየቁ መሆኑን ለአሻም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በበኩሉ ‹‹ ማጣራት እያደረገ ቢሆንም ተጨማሪ አዲስ መረጃ የለም ›› ሲል አጭር ምላሽ ለአሻም ሰጥቷል፡፡

አሻም የፌዴራል መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ብትደውልም ‹‹ ሰብሰባ ላይ ነኝ ›› ሲሉ፤ ሌላኛው ሚኒስትር ዲኤታ ከበደ ዴሲሳ ጋር ብትደውለም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለአሻም መረጃ የሰጧት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ‹‹ በትናንትናው እለት ታግተው ከነበሩ 167 ተማሪዎች መካከል 160 የሚሆኑት መለቀቃቸውን ቀሪወቹን ለማስፈታት እየተሰራ መሆኑን በድጋሚ ›› ለአሻም አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን አዲስ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

( በዚህ ዘገባ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምላሽ ተካትቶበታል)

(በምሽት የዜና እወጃችን ዝርዝር ዘገባውን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን)

ቴዎድሮስ ፍቅሩ

ፎቶ - ፋይል

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

አዳዲስ፣ ተዓማኒ ዜናዎችን እና ዝግጅቶችን በፍጥነት እንዲደርስዎት
የአሻም ቲቪን ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያድርጉ

Facebook :
https://www.facebook.com/AshamMedia
Telegram :
https://t.me/Asham_TV
You Tube : https://www.youtube.com/channel/UCdE5nyP9z2J4Tq_apRMtc0A
Tik Tok :
tiktok.com/?lang=en
https://youtu.be/SyhItmJF3Gk
https://youtu.be/SyhItmJF3Gk

"በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል"--- የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ "እውነት ይሆን?" ብዬ የታጋ...
10/07/2024

"በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል"--- የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ
"እውነት ይሆን?" ብዬ የታጋቾች ቤተሰቦችን፣ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረትን እና የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንትን ማምሻውን ጠየቅኩ። ምላሹ ይህን ይመስላል:
"አሁንም ልጆቻችን በእገታ ስር ናቸው፣ የማስለቀቂያ ገንዘብ ከህዝብ እየለመንን ነው። በዚህ ግዜ እንዲህ አይነት መረጃ ማውጣት የጭካኔ ስራ ነው"--- የታጋቾች ቤተሰቦች
"ታግተው ያሉ በርካታ ተማሪ አልተለቀቁም፣ ተለቀቁ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከየት እንደመጣ አናውቅም"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረት
"አንዴ መረጃ ሰጥቻለሁ፣ እኔ ጋር ለምን ትደውላላችሁ?"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ

Elias Meseret

·

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች የታገቱ አብዛኞቹ ተማሪዎች መለቀቃቸውን ቢገልጽም የታጋች ቤተሰቦች ግን ተማሪዎቹ አሁንም ታግተው እንዳሉ ተናገሩ።ከአማራ ክልል ተነስተው ወ...
10/07/2024

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች የታገቱ አብዛኞቹ ተማሪዎች መለቀቃቸውን ቢገልጽም የታጋች ቤተሰቦች ግን ተማሪዎቹ አሁንም ታግተው እንዳሉ ተናገሩ።
ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሦስት በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከ100 የሚበልጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም. ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ውስጥ በታጣቂዎች መታገታቸው ይታወሳል።
ታጋቾቹ አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ “ሸኔ” በተባሉ ታጣቂዎች መታገታቸውን ከእገታው ያመለጡ ተማሪዎች እና የታጋች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

BBC News Amharic

ስነቃባቸው የአገቷቸውን ተማርዎች መልቀቅ ጀመሩበኢትዮጵያ እየተፈጸሙ የሚገኙ የዜጎች እገታና ግድያ በዋናነት አገርቱን እየመራ በምገኘው መንግስት እና እሱ ባቋቋመው ኮሬ ነጌኛ በተሰኘ ቡድን መ...
10/07/2024

ስነቃባቸው የአገቷቸውን ተማርዎች መልቀቅ ጀመሩ

በኢትዮጵያ እየተፈጸሙ የሚገኙ የዜጎች እገታና ግድያ በዋናነት አገርቱን እየመራ በምገኘው መንግስት እና እሱ ባቋቋመው ኮሬ ነጌኛ በተሰኘ ቡድን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሸኔ ስም የምነግደው የኢትዮጵያው መንግስት ከቀናቶች በፍት ከዩንቨርሰቲ የሚመለሱት ተማርችዎችን አግቶ ከቤተሰቦቻቸው ማስለቀቂያ የምሆን ገንዘብ በእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ሚሊዮን ብር መጠየቅ ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን አሜሪካ በአምባሳደሯ በኩል ትላንትና መግለጫ ካወጣች በኋላ ተማርዎችን ያገተው መንግስታዊ ቡድን ተነቅቶብኛል ብሎ በዛሬው ዕለት ተማርዎቹን መልቀቅ ጀምሯል፡፡

አለም አቀፍ ማህበረሰቡን ቁማር ልትበላው አትችልምየሽመልስ አብዲሳ ወላጅ እናት ጊንጪ ላይ ታግተው 10 ሚልዮን ብር ከፍሎ ማስልቀቁንና ከዚህ ጋር በተያያዘም እናትየውን እንዲጠብቁ ተመድበውየነ...
10/07/2024

አለም አቀፍ ማህበረሰቡን ቁማር ልትበላው አትችልም

የሽመልስ አብዲሳ ወላጅ እናት ጊንጪ ላይ ታግተው 10 ሚልዮን ብር ከፍሎ ማስልቀቁንና ከዚህ ጋር በተያያዘም እናትየውን እንዲጠብቁ ተመድበውየነበሩ የኦሮሞ ልዮ ሀይል አባላት መታሰራቸውተነገረ:: ይህ ዜና የተፈበረከው በነሽመልስ አብዲሳ ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው፤ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ በተለይም የአሜሪካ መንግስት በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀሙ የሚገኙ ተደጋጋሚ አፈናዎችና እገታዎች እንዳሳሰበው ሰኞ እለት መግለፁ ይታወሳል። በዚህ እገታ ተግባር ላይ በዋናነት ተሳታፊው ደግሞ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን እንደሆነ አለም እየተረዳው መሆኑን አብይና ሽመልስ ተገንዝበዋል። ስለዚህም የአለምን ትኩረት ለማዛባትና እኛ የለንበትም ለማለት የሽመልስ አብዲሳ ወላጅ እናት ታግተው በ10 ሚሊዮን ብር ተለቀቁ የሚል የተፈበረከ ዜና በትላንትናው እለት ማስራጨት ጀምረዋል። እውነታው ሴትየዋ አልታገቱም ሽመልስ አብዲሳ ትኩረት ለማስቀየር የፈጠረው ዜና መሆኑን ኢትዮጵያውያንም ሆኑ አለም አቀፍ ማህበረስቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል።

የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚንስትር የአብይ አህመድን ንግግር ማዳመጥ "ከሆድ በስተቀር ጭንቅላት ባዶ ሲሆን አያስጠነቅቅህም" የሚለውን የአፍሪካ ምሳሌያዊ አባባል ያረጋግጣል። እሱ በተናገረ ቁጥር ...
04/07/2024

የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚንስትር የአብይ አህመድን ንግግር ማዳመጥ "ከሆድ በስተቀር ጭንቅላት ባዶ ሲሆን አያስጠነቅቅህም" የሚለውን የአፍሪካ ምሳሌያዊ አባባል ያረጋግጣል። እሱ በተናገረ ቁጥር ልቤ ለኢትዮጵያውያን ይታመማል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይናገርበት ጊዜ ኢትዮጵያ ይሻላታል!

Dr. Chepkiru Basilio

12ቱ  የብልፅግና ማኒፌስቶመድፈር መጨፍጨፍ መግደልመቆራረጥ መደፍጠጥመገዝገዝመደርመስመዋሸትመመንተፍመዝረፍመስረቅመቀጥቀጥ ።!!።
04/07/2024

12ቱ የብልፅግና ማኒፌስቶ

መድፈር
መጨፍጨፍ
መግደል
መቆራረጥ
መደፍጠጥ
መገዝገዝ
መደርመስ
መዋሸት
መመንተፍ
መዝረፍ
መስረቅ
መቀጥቀጥ

።!!።

ኬንያ፣ መሪዎቿ፣ ጋዜጠኞቿና ኬንያውያን ያስቀናሉ፦👉በኬንያ ፕሬዝዳንቱን ስልጣን ልቀቅ ማለት ይቻላል፤ አያሳስርምም።👉በኬንያ ጋዜጠኞች ቤተመንግስቱ ድረስ ዘልቀው በመግባት ፕሬዝደንቱን ውሸታም ...
04/07/2024

ኬንያ፣ መሪዎቿ፣ ጋዜጠኞቿና ኬንያውያን ያስቀናሉ፦
👉በኬንያ ፕሬዝዳንቱን ስልጣን ልቀቅ ማለት ይቻላል፤ አያሳስርምም።
👉በኬንያ ጋዜጠኞች ቤተመንግስቱ ድረስ ዘልቀው በመግባት ፕሬዝደንቱን ውሸታም ነህ በእጅህ ላይ የንጹሃን ደም አለ ብለው ተናግረው በሰላም ወጥተው መግባት ይችላሉ።
👉በኬንያ ጋዜጠኞች የቀዳማዊት እመቤቷ ቢሮ አባካኝ ነው ብለው ስለሞገቱ ቢሮው ይዘጋል።
👉በኬንያ ጋዜጠኞች መሪያቸውን ሀይማኖትን የፖለቲካ መስበኪያ አድረገሃል፤ ስላንተም ደግ ደጉን እንዲናገሩ ገንዘብ ደጉመሃል ብለው መጠየቅ ይቻላሉ። መሪውንም አስተካክላሁ የፖሊሲ ለውጥ አድርጋለሁ እንዲሉም ማድረግ ይቻላል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ሌላ የትም አይደለም እዚሁ ጎረቤታችን ኬንያ ነው።

የእኛው ጨቅላ መሪ በተግባር ዘረኝነትን ያስፋፋል በወሬ ሲፀየፍ ይታያል። በጀርባ ይገላል በፓርላማ መጥቶ በወሬ ንፁህ ነኝ ይላል። ህዝብን አደህይቶ የአገርን ህልውና አናግቶ እያለ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ እያስመዘገብን ነው ይላል። ውሃ ጠማን፣ ህጋዊ መሬታችን አይነካ ብለው አደባባይ የወጡትን በጥይት አናታቸውን እያለ ይገድላል ከዚያም አይኑን በጨው አጥቦ ዴማክራሲያዊ ነኝ ይላል። በእሱ ፈቃድ መፈንቅለ መንግስት የሚደረግ አድርጎ ጭንቀቱንና እንቅልፍ ማጣቱን ሳይጠይቁት ይቀባጥራል።

በአዳማ ከተማ በዛሬው እለት በአሮሬቲ እና ቶርበን ኦቦ ቀበሌዎች በነዋሪዎች ከተቀሰቀሰ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የ 7 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል ተቃውሞው በ...
03/07/2024

በአዳማ ከተማ በዛሬው እለት በአሮሬቲ እና ቶርበን ኦቦ ቀበሌዎች በነዋሪዎች ከተቀሰቀሰ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የ 7 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል
ተቃውሞው በነዋሪዎቹ የተቀሰቀሰው የከተማ አሥተዳደሩ በቀበሌዎቹ የሚገኙ 1,500 ደገማ ቤቶችን ሕገ ወጥ ብሎ የማፍረስ ሥራ ሲጀምር መሆኑን ዋዜማ ዘግቧል።
ነዋሪዎቹ መሬቱን በአካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች የገዙ መሆናቸውና ከ 2005 ዓ.ም አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ላለፉት 11 ዓመታት በሕጋዊ መንገድ ለአዳማ ከተማ መሥተዳድር ግብር ሲገብሩበት መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ሆኖም ቀደም ብሎ ይፈርሳሉ የተባሉትን ቤቶች እየዞሩ ቀለም ሲቀቡ መቆየታቸውንና ዛሬ ጠዋት ላይ ዶዘርና ሌሎች ማፍረሻ ማሽኖችን ይዘው ወደ ስፍራው መምጣታቸውን ተከትሎ አመጹ መቀስቀሱን ተናግረዋል።
በዚህም ሳቢያ የሰባት ሰዎች ሕይወት ወዲያው ማለፉን፣ ቀጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውንና ከሟቾች መካከልም አንዲት ነፍሰጡር ሴት እንደምትገኝበት ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ ባለፉት ጊዜያት ለጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ጭምር ቤቶቹ እንዳይፈርሱባቸው ግብር የከፈሉበትን ሕጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ መጠየቃቸውንና ጽ/ቤቱም ቤቱ እንዳይፈርስና ጉዳያቸው በይደር እንዲታይ ወስኖ እንደነበር ታውቋል።
ይህ ዘገባ እየተጠናቀረ እስካለበት ሰዓት ድረስ ተቃውሞው መቀጠሉንና ድባቡም አስፈሪ መሆኑን ዋዜማ የዘገበ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ሚሊሻ ተሳታፊዎች መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
Via Wazema Radio

02/07/2024
♦ በመብራት ለማብለጭለጭ 33 ቢሊየን ብር ➖➖➖➖➖በሰኔ በጀት መዝጊያ የተፈፀመ ከባድ ሙስናአዎ 33 ቢሊየን ብር ምን ላይ እንደዋለ ታውቃለህ..? ለሰሞኑ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት!33 ...
02/07/2024

♦ በመብራት ለማብለጭለጭ 33 ቢሊየን ብር
➖➖➖➖➖

በሰኔ በጀት መዝጊያ የተፈፀመ ከባድ ሙስና

አዎ 33 ቢሊየን ብር ምን ላይ እንደዋለ ታውቃለህ..? ለሰሞኑ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት!

33 ቢሊየን ብዙ ነገር ነው። ብዙ ሃብት ነው። ለአንዲት መናጢ ድሃ ሀገር ደግሞ እጅግ በ ጣ ም....ብዙ ነው።
እስኪ ግዝፈቱን በሌላ መልኩ ላስረዳህ...

◾️የንግድ ባንክ አዲሱ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በስንት እንደተሰራ ታውቃለህ...? 8 ቢሊየን ብር
◾️ሰሞኑን የተመረቀው ግዙፉ የዓባይ ድልድይ በጀት 4.1 ቢሊየን ብር ነው
◾️የሞጆ ሀዋሳ 92 ኪሜ ፈጣን መንገድ በጀቱ 6.3 ቢሊየን ብር ነው
◾️ለሸገር ቀለበት መንገድ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተያዘው በጀት 4.5 ቢሊየን ብር ነው

➖በክልል በጀት ደግሞ እንይ:

33 ቢሊየን ብር ማለት ለ 2016 የትግራይ ክልል ም/ቤት ካፀደቀው በጀት በሁለት እጥፍ ይበልጣል። ከ2016 የአፋር ክልል በጀት ደግሞ በሶስት እጥፍ ይበልጣል።

◾️ለ2017 ዓ.ም የፌዴራል መንግስት ለክልሎች ከያዘው የድጋፍ በጀት ውስጥ ከ33 ቢሊየን ብር በላይ የተመደበላቸው ለኦሮሚያ እና ለአማራ ክልል ብቻ ነው
◾️ለሌሎች የሚሰጠው ከ33 ቢሊየን በታች ነው

◾️ በሌላ መልኩ 33 ቢሊየን ብር ማለት 1870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ማለት ነው።
➖➖
እናም 33 ቢሊየን ብር ማለት ብዙ ፋብሪካ፣ የአዳማ-አአ አይነት ፈጣን መንገድ፣ የግልገል ጊቤ 3 አይነት የኃይል ማመንጫ ግድብ፣ ብዙ ሺህ ኮንዶሚኒየም፣ 4 የንግድ ባንክ ትልቁ ህንፃ፣ ብዙ ሺህ የስራ ዕድል...

ነበር ባይሰበር - ኮሪደሩ ባይደረደር
ጥላዬ ያሚ

የ5 ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈለን ጥያቄ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል
02/07/2024

የ5 ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈለን ጥያቄ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል

‹‹ በጉልበት ሥራና በሹፍርና ተሰማርተናል ›› - የዩኒቨርስቲ መምህራን ‹‹ ዩኒቨርስቲዎች ተጠሪነታቸው ለትምህርት ሚኒስቴር ነው  ›› - ገንዘብ ሚኒስቴር‹‹ በጉዳዩ ዙሪያ በቀጣይ ቀናት ም...
28/06/2024

‹‹ በጉልበት ሥራና በሹፍርና ተሰማርተናል ›› - የዩኒቨርስቲ መምህራን

‹‹ ዩኒቨርስቲዎች ተጠሪነታቸው ለትምህርት ሚኒስቴር ነው ›› - ገንዘብ ሚኒስቴር

‹‹ በጉዳዩ ዙሪያ በቀጣይ ቀናት ምላሽና ማብራሪያ እሰጥበታለሁ ›› - ትምህርት ሚኒስቴር

‹‹ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ መምህራን ወርሃዊ ደሞዛቸው ዝቅተኛ በመሆኑ በጉልበት ሥራና በሹፍርና መሰማራታቸውን ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የሚከፈላቸዉ የደሞዝ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑና ወቅቱንም ሆነ ዓለማቀፉን የደሞዝ እርከን ጠብቆ ያልተሸሻለ በመሆኑ ‹‹ መሰረታዊ ፍጆታዎቻችን እንኳን ለማሟላት ተቸግረናል ›› ሲሉ ነው መምህራኖቹ ለአሻም የነገሯት፡፡

በተለይም የጅግጅጋ ፣ ወልቂጤ ፣ጂንካና ዎላይታ ሶዶ ዪኒቨርስቲዎች መምህራን በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ በመገኘታቸዉ ህይወታቸዉን ለማቆየት ለተጨማሪ ስራ በሚወጡበት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች እንደሚበደሉም ጠቅሰዋል፡፡

አንድ ስማቸው አንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የጂንካ ዩኒቨርስቲ መምህር ለአሻም እንደነገሯት ከሆነ የመምህራኑን በኑሮ መጎሳቆል የተረዱ ተማሪዎች በመምህራኑ ላይ ‹‹ ሲሳለቁ ›› መመልከታቸዉን ጭምር አስረድተዋል፡፡

እነዚህ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በሚገኙና ተጠሪነታቸው ለፌደራሉ መንግስት በሆኑ አምስት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን የደሞዝ ማሻሻያ ከተደረገ በርካታ ዓመታትን በመሻገሩ ኑሮ ዉድነቱን መቋቋም ባለመቻላቸዉ በተጨማሪነት ‹ በጉልበት ስራና ሹፍርና › የተሰማሩ ስለመኖራቸዉ ለአሻም ነግረዋታል፡፡
መምህራኑ ይቀጥላሉ ‹‹ ቤት ኪራይ፣ ምግብና አልባሳት መግዛት አልቻልንም ብሎ ከዩኚቨርስቲ መምህራን ጥያቄ መነሳት ለአንድ አገር መንግስት ዉድቀት ነው ›› ሲሉ ይበይኑታል፡፡

በዚሁ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደሞዝ ሳይሻሻል 8 ዓመታትን ተሻግሯል ማለታቸዉን ያዳመጠችዉ አሻም በጉዳዩ ላይ ስለምን መሻሻያዉ አልተደረገም ስትል ‹ የገንዘብ ሚኒስቴር › የበጀት ቢሮ ዳይሬክተር ጥላሁን ወልዴን አነጋግራለች፡፡

ሚኒስቴሩ ይህን ለማድረግ ራሱን የቻለ የአሰራር ሂደት እንዳለዉ በማስታወስ ‹‹ ዩኒቨርስቲዎች ተጠሪነታቸው ለትምህርት ሚኒስቴር ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ስራ የሚያስከትለው የበጀት ጫና ምንድን ነው የሚለውን አስተያየት ከመስጠት ውጭ ኃላፊነት እንደሌለበት ›› ለአሻም አስረድተዋታል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ በቀጣይ ቀናት ምላሽና ማብራሪያ ለአሻም የሚመለከተዉ ክፍል እንደሚሰጣት አስታዉቆ፤ለጊዜዉ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

አሻም ቲቪ (የዚህን ዜና ዝርዝር ዘገባ በአሻም ይፋዊ የዜና ዩቱብ ቻናል ታግኙታለችሁ)

27/06/2024

''መንግስት አለ ብለን ስለማናምን ድርድር ብሎ ነገር የለም!!!''
ፋኖ

በ6 ዓመታት ውስጥ በርካታ መቶ ሺዎች የአማራ ህዝብን ጨፍጭፈውና አስጨፍጭፈው ከጨረሱ በኋላ በአንዲት ድልድይ ዳንኪራ እንደልቅ እያሉን ነው።ለነገሩ አንዳንድ አማራ ነን ባዮች የእስክስታ ዘፈን...
14/05/2024

በ6 ዓመታት ውስጥ በርካታ መቶ ሺዎች የአማራ ህዝብን ጨፍጭፈውና አስጨፍጭፈው ከጨረሱ በኋላ በአንዲት ድልድይ ዳንኪራ እንደልቅ እያሉን ነው።
ለነገሩ አንዳንድ አማራ ነን ባዮች የእስክስታ ዘፈን ከተከፈተላቸው ደስታቸው ወደር አልባ ይሆናል።

አስመሳይ ለስልጣንና ጥቅሙ ሲል የማይሆነው ምንም ነገር የለም። ወለጋ ሄዶ መቶ ዓመትን ሰበርን ይላልባህርዳር መጥቶ አንድነት ቅብርጥሴ ይላል።በዚህ ሰው የማስመሰል ጨዋታ የሚሸወድ አማራም ሆነ...
13/05/2024

አስመሳይ ለስልጣንና ጥቅሙ ሲል የማይሆነው ምንም ነገር የለም።

ወለጋ ሄዶ መቶ ዓመትን ሰበርን ይላል
ባህርዳር መጥቶ አንድነት ቅብርጥሴ ይላል።

በዚህ ሰው የማስመሰል ጨዋታ የሚሸወድ አማራም ሆነ ኦሮሞ ወይም ጋሞም ሆነ ወላይታ የለም።

29/04/2024

በፅዳት እና በተማሪ መፅሐፍ ግዢ ስም የሚደረግን ብዝበዛ እንቃወማለን። ለጥይት መግዣ የሚሆን ገንዘብን ባለማዋጣት ለአገራችን ሰላም የድርሻችንን እንወጣለን። ህዝብን ከጭፍጨፋ እንታደጋለን።

ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደአሻሮ ጠጋየገንዘብ እጥረት ፓለቲካውን ሊያፈርስበት የተቃረበው የብልግና አገዛዝ ባለሀብቶችን በማስገደድ በእገታና በዘረፋ ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ፅዱ ኢትዮጵያ በሚል ወቅ...
28/04/2024

ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደአሻሮ ጠጋ

የገንዘብ እጥረት ፓለቲካውን ሊያፈርስበት የተቃረበው የብልግና አገዛዝ ባለሀብቶችን በማስገደድ በእገታና በዘረፋ ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ፅዱ ኢትዮጵያ በሚል ወቅታዊ አጀንዳ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊመዘብር በአብይ አህመድ መሪነት ገንዘብ የማስባሰብንና ፖለቲካን የመታደግ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ጀምሯል።

ህዝብ ሆይ ንቃ
ግብር በመክፈል ከምታወጣው ውጪ በዘለለ ያውም በዚህን የአገሪቱ ሀብት ሁሉ ለመሳሪያ ግዢ፣ ለፓርክ ግንባታና ለካድሬ አበል እየዋለ ባለበት ሰዓት ላይ ተጨማሪ የሆነ ወጪ ገዳይና ዘራፊ ለሆነ ስርዓት እንድታወጣለት የሚያስገድድህ ህግና አሰራር የለም።

አበዳሪና ለጋሽ አገራት የከለከሉትን ገንዘብ በቀን ሁለቴ እንኳን መብላት ከተሳነው ህዝብ መቀማት ግፍ ነው!!!

ከህዝብና ከንግዱ ማህበረሰብ ግብር በመሰብሰብ፣ ከለጋሽና አበዳሪ አገራት ገንዘብ በማግኘት አገርን ማልማት፣ የህዝብን ደህንነት መጠበቅና ህዝብን በቀን ሶስት ጊዜ እንዲበላ ማድረግ የአንድ መንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ ነው።

መንግስትም:- በግልፅ > የሚሉት የቦዘኔ ዓይነት ፈለጣን በይፋ ጀምሯል።

ወይ ሃገሬ 😥

የኢሳን ቲቪ ምርመራ: ከእነ ጄነራል አሳምነው ፅጌ እስከ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ እንዲሁም የትናንቱ የኦነግ ከፍተኛ ኦፊሰር ድረስ የነበረውን ግድያ እንዲህ አጠናቅረነዋል‼➖➖➖ኮሬ ነገኛ፡ የተቋ...
12/04/2024

የኢሳን ቲቪ ምርመራ: ከእነ ጄነራል አሳምነው ፅጌ እስከ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ እንዲሁም የትናንቱ የኦነግ ከፍተኛ ኦፊሰር ድረስ የነበረውን ግድያ እንዲህ አጠናቅረነዋል‼
➖➖➖
ኮሬ ነገኛ፡ የተቋቋመው ዐብይ አህመድ ጠ/ሚኒስትር በሆኑ በነጋታው ነው። 2010 ዓ.ም ማለት ነው።

ኮሬ ነገኛ ግድያውን የጀመረው በቡራዩ የሚኖሩ ጋሞዎች ላይ ነበር። በድምፅ አልባ መሳሪያ (በቆንጨራ) ተጨፈጨፉ።

ኮሬ ነገኛ ሰኔ 15 በባህርዳር ጄነራል አሳምነው ፅጌ፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ ምግባሩ ከበደ፣ እዘዝ ዋሴን ገድሏል። ይህንን ግድያ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጨፌ ኦሮሚያ የተናገሩት ንግግር ድምፅ ሾልኮ መወጣቱ ይታወሳል። አቶ ሽመልስ አባይ ማዶ አደናግርናቸው፣ የማይደናገረውን ደግሞ አስወግደናቸዋል ማለታቸው የሚታወስ ነው። አቶ ሽመልስ የኮሬ ነገኛ ከፍተኛ አመራር ናቸው።

ኮሬ ነገኛ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድሏል። ሃጫሉ ኦሮሞ እርስ በእርሱ እየተላለቀ ነው። ጦርነት አይጠቅምም ሲል በOMN መናገሩን ተከትሎ፣ ይህ ሰው እየቆዬ ሲሔድ የእኛ ተቃዋሚ ይሆናል ብለው እነ አብይ አህመድ ገመገሙ ከዚያ ኮሬ ነገኛ ገደለው። ሌሎቹ የኦሮሞ ድምፃዊያን "ፀጥ ለጥ" ብለው እነ ዐብይ አህመድን ማገልገል ጀመሩ። ምክንያቱም ፈርገጥ ቢሉ የሃጫሉን ፅዋ ይጎነጫሉና።

ኮሬ ነገኛ የከረዩ አባገዳዎችን ጨፍጭፏል። እነዚህን አባገዳዎች ኮሬ ነገኛ እንደገደላቸው በተጨበጭ መረጃ ተመርኩዞ ዓለም አቀፉ ሚዲያ ሮይተርስ መዘገቡ ይታወሳል።

👉የህውሓት አመራሮች ዐብይ አህመድ ስልጣን ልስጣችሁ ሲላቸው ለምን እምቢ አሉ?

ከደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት በኋላ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለህውሓት አመራሮች ስልጣን ልስጣችሁ ብለው ነበር። ህውሓቶች የአንተ ስልጣን ጥንቅር ብሎ ይቅር ብለው እምቢ አሉ።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድም ባለፈው ከትግራይ ተወካይ ከተባሉት ጋር ሲወያዩ እንዲህ ብለው ነበር:- የህውሓትን አመራሮች ስልጣን ልስጣችሁ ስላቸው አልፈልግም አሉኝ ብለው ነበር።

በኋላ ላይ ህውሓቶች እምቢ ያሉበት ሚስጥር ሲወጣ፣ ህውሓት የደረጀ የስለላ መረብ አለው እናም የዐብይን እቅድ በደንብ ያውቃል፣ ስለዚህ ዐብይ አህመድ ለህውሓት ስልጣን ሰጥቶ በኮሬ ነገኛ ለማስገደል ነበር። ህውሓቶችም አፍንጫህን ላስ አሉት።

ኮሬ_ነገኛ ትናንት የኦነግ ከፍተኛ አመራር በመቂ ከተማ ኮሬ ነገኛ ገድሎ ጥሎት አስከሬኑ ተገኝቷል። አሜሪካ በፍጥነት ምርመራ እንዲጀመር ብላለች።

ኮሬ_ነገኛ መግደል ብቻ አይደለም ያፈናቅላል። በአዲስ አበባ እና ዙሪያውን የተደረጉ ቤት ማፍረሶች ይህ የገዳይ ቡድን እጅ አለበት። አማራ ድሃ መሆን አለበት በሚል ስሌት የሚሰራ ዘግናኝ ድርጅት ነው።

ኮሬ_ነገኛ ቀጣይ የሚገድላቸው ፖለቲከኞች መካከል፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ ይገኙበታል። ሰሞኑን አብዲ ኢሌ ከዕስር ተለቋል። የተለቀቀበት ሚስጥር ደግሞ ሙስጠፌን ከስልጣን አስወግዶ አብዲ ኢሌ እንዲተካ ለማድረግ ነው።

ሶማሌ ክልልን ከሶስት ለመክፈል ታቃዷል። ግማሹ የሶማሊ ክልል ወደ ኦሮሚያ በማካላል፣ ኦሮሚያን ሀገር ካደረግን በኋላ ከሶማሊላንድ ጋር ተዋግተን ወደብ እናገኛለን ስለዚህ የኢትዮጵያ ሶማሊ ግማሽ የሚሆነውን ወደ ኦሮሚያ ለማድረግ ታቅዷል።

የኦሮሞ ብልጽግና አንቀፅ 39 ተጠቅሞ ኦሮሚያን ለመገንጠል አቅዷል። ለዚህ መሰናክል የሆነ ሁሉ ከላይ የጠቀስናቸውን ፖለቲከኞች የደረሳቸው እጣ ፈንታ ይደርሳቸዋል። አሁን ተራው የሙስጠፌ ሊሆን ይችላል። ኮሬ ነገኛ ሙስጠፌን ከመግደል ወደ ኋላ አይልም! ሙስጠፌ ኢትዮጵያ ወዳድ ናቸው ይባላል።

አምባገነን መሪዎች በሚስጥር ገዳይ ቡድን ያቋቁማሉ። ለእነሱ እንቅፋት የሆኑትን ይገድላሉ! ይሔ የተለመደ ነው።

ለምሳሌ

👉ሒትለር 👉 ss
👉 ፑቲን 👉 ዋግነር
👉 አልበሽር 👉 ጃጃዊ
👉 ዐብይ አህመድ👉 ኮሬ ነገኛ

አሳዛኝ ነውይህ ሰው በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ጥበቃ ሁኖ የሚስራ ነበር በ29/7/2016 ዓ.ም የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ተብሎ ሰዎችን ንግድ ቤታችሁን ዝጉና ወደ ስልፉ ውጡ እየተባለ በግዳጅ...
11/04/2024

አሳዛኝ ነው

ይህ ሰው በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ጥበቃ ሁኖ የሚስራ ነበር በ29/7/2016 ዓ.ም የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ተብሎ ሰዎችን ንግድ ቤታችሁን ዝጉና ወደ ስልፉ ውጡ እየተባለ በግዳጅ ሰውን እያስወጡ ነበር፣ አንሄድም እሚለውን እየደበደቡ ነበር።
በዚህ ወቅት የዚህ እራሱን አንቆ የገደለው አባት ልጁ ፀጉር ቤት ነበር የሚሰራው በወቅቱ ዝጋና ወደ ስልፉ ውጣ ሲባል አልወጣም በማለቱ ተደብድቦ ከባድ የሆነ ጉዳት ደርሶበት ነበር ነገር ግን በህይወት ሊተርፍ ባለመቻሉ በቀን 30/7/2016 ህይወቱ ሲያልፍ አባትየውም ሞቱን እንደሰማ በምስል በምታዩት መልኩ ራሱን አንቆ ህይወቱን አጥፍቷል

ምንጭ: አዩዘሀበሻ

የመጋቢት 24 ድሎች
05/04/2024

የመጋቢት 24 ድሎች

05/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ መቀመጫ አርባምንጭ ይሆናል ብሎ የቀጠፈህን ዱርየ መንግስት ትደግፋለህ?

ገዳይና አምባገነን የሆነውን ፅንፈኛ ቡድን ለመደገፍ በነገው ዕለት የምንሰለፈው ምንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ የለም!!በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገደሉባት፣ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ በከፋ የኑ...
05/04/2024

ገዳይና አምባገነን የሆነውን ፅንፈኛ ቡድን ለመደገፍ በነገው ዕለት የምንሰለፈው ምንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ የለም!!

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገደሉባት፣ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ በከፋ የኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ባለባት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በርሃብ አለንጋ እየተገረፉ በሚኖሩባት፣ ዛሬም ድረስ የእርስ በእርስ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ባለባት አገር ላይ መላው የአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ነገ በሚደረገው የወንጀለኞች የድጋፍ ሰልፍ ላይ ባለመሳተፍ ለአገር አንድነት፣ እውነተኛ ለሆነ ዴሞክራሲ፣ ለፍትህና ለሰላም ያላችሁን አጋርነት ትገልፁ ዘንድ ናቶ የጋሞ ወጣቶች ህብረት ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።

በአዲስአበባ የተሰቀሉ ባነሮች
02/04/2024

በአዲስአበባ የተሰቀሉ ባነሮች

Address

Arba Minch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ናቶ /Naato/ የጋሞ ወጣቶች ህብረት ለፍትህ፥ ለእኩልነት፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share