16/05/2024
ስለዚህም የትናንቱ የወያኔ አቃጣፊ የዛሬው ያማራ ፋኖ ደጋፊ አቶ ግርማ ካሳ መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚሉትን ፋኖወች ባንተ በእስክንድር ነጋ ላይ አነሳስቶ በዛቻው መሠረት ከጀርባህ እንዲወጉህ ሊያደርግ እንደሚችል መጠርጠር አለብህ። ያ ባይሳካለት ደግሞ መነሻውም መድረሻውም ገንዘብ በሆነው በመረጃ ቲቪ አማካኝነት ለጭራቅ አሕመድ መረጃ ሽጦ ሊያስገድልህ እንደሚችል መጠርጠር አለበህ። በጥርጣሬህ መሠረት ደግሞ መውሰድ ያለብህን ጥንቃቄወች ሁሉ መውሰድ አለብህ፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ የጠረጠረ ቤቱን አጠረ ነውና።
የስልጣን አራራ (ጥም) ሌላው ቀርቶ ከራስ አብራክ የወጣን የራስ ልጅን እንደሚያስገድል ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪከ በደንብ ስለምታውቅ፣ እነ አቶ ግርማ ካሳና መሰሎቻችውአንተን እስክንደር ነጋን በሰላሳ ጠገራ ሽጠው ለወያኔና ለኦነግ አሳልፈው ከሰጡ በኋላ አማራን እንወክላለን ብለው ከወያኔና ከኦነግ ጋር ባሜሪቃ አደሪዳሪነት ለመደራደር ቆርጠው ቢነሱ ሊገርምህ አይገባም። https://ethioreference.com/archives/35588
የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ ፋኖወች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ አማራጭ የለሽነት!
ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳሳው በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።
https://ethioreference.com/archives/35588