Jemal Adame

Jemal Adame Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jemal Adame, Digital creator, .

03/06/2024
03/06/2024

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም የምግብ ዋስትናችንን እናረጋግጥ !

ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት የተረጂነት አስተሳሰብ ፈተና ሆኖባት ቆይታለች በተለይም ያሉንን የመሬት፣ የሰው ሀይል፣ የማእድንና የውሃ ሀብቶቻችን በአግባቡ ባለመጠቀማችን ምክንያት ለረጅም አመታት ከተረጂነት ለመላቀቅ አልተቻለም፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን እምቅ ሀብቶቻችን በአግባቡ በመጠቀም ተረጂነት አንገት የሚያስደፋ፣ የሚያዋርድ ብሎም የሀገር ሉአላዊነትን የሚያስደፍር ተግባር በመሆኑ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ለመዋጋት እና የስራ ባህልን ለመቀየር ፓርቲያችን ትኩረት ሰቶ እየሰራ ይገኛል።

በቀጣይ እነዚህ ሀብቶቻችን በአግባቡ ከተጠቀምን በአጭር ጊዜ መለወጥ እንደሚቻልና ለዚህም ወጣቱ ያለው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ የስራ ባህሉን በማሻሻል ፓርቲያችን በተለያዩ ጊዜያት በሚያመቻቸዉ የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በተገኙ አጋጣሚዎች እድልን ወደ ድል መቀየር ይገባል፡፡

የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናችን ለማረጋገጥ በግብርና ዘርፉ በትኩረት መስራት ግድ ይለናል፤ የአደጋ ጊዜ ስጋት ለመቋቋም እና ምላሽ ለመስጠት የሚሆኑ ስራዎቻችን ይበልጥ ለማጠናከር የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ የአብሮነት እሴታችን ይበልጥ ማዳበርና ፀጋዎቻችንን በመለየት ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅብናል ፡፡

በሌማት ትሩፋት ተግባራቶቻችን ያሳየነው ውጤት የይቻላል አስተሳሰብ በተጨባጭ ያሳየ እንደመሆኑ በቀጣይም በታቀዱ የልማት ስራዎቻችን ላይ አጠናክረን በማስቀጠል የተረጂነት አስተሳሰብ በመቅረፍ የብልጽግና ጉዞ ማረጋገጥ ይገባል ፡፡

17/05/2024
15/05/2024

"አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የምናረገው የምንለውን ሆነን ፣ አንፀባራቂ ውጤት አስመዝግበን ነው!"

ለህዝባችን የገባነውን ቃል በተጨባጭ የተግባር ውጤታማነት እያሳየን ነው። መሠረታዊው ጉዳይ በትውልድ ላይ በመስራት የተሻለች ነገን ፥ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት ላይ ነው።

አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ስንል ቃል በተግባር የተገለፀባቸው በርካታ አንፀባራቂ ውጤት የተመዘገበባቸው ለትውልድ አሻራ የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ፕሮጀክቶችንና መሰረተ_ልማቶችን በማሳካት ነው።

በተመሳሳይ ትውልድ ላይ በመስራት ከተማዋ ህጻናትን ለማሳደግ በአፍሪካ ታላቅ የተሞክሮ ማዕከልነቷን በማረጋገጥ መጭው የመደመር ትውልድ የሚታነፅባትና ለሀገራዊ ግንባታ ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ ነው።

በጥቅሉ የፓርቲያችን መሰረት የሆነው ''መደመር'' ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን አስቦ ትውልድን በኢትዮጵያ ልክ ትልቅ አድርጎ የሚሰራ የብልጽግና መንገድ ነው። ትውልድ ላይ እየገነባን ያለነው ሀገርን ለማሻገርና ከፍታዋን ለማጽናት ነው። የመደመር ትውልድ የነገዋን የተሻለች ኢትዮጵያ ለመገንባት በወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ የፀና ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚገነባ ነው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jemal Adame posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share