
11/06/2024
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን አሰመልክተው ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️
👉 ጀጎል ሲባል አጥሩ ብቻ አይደለም። በውስጥ የሚኖሩ ቤቶችን፣ በቤቶች ውስጥ ያሉ የአኗኗር ዘይቤዎችንና ባሕሎች እንዲሁም የሰዎች መስተጋብር ሁሉ እንደ ጀጎል ይታሰባል። የጀጎል ቅርስነትም ይህን ሁሉ የያዘ ነው፣
👉 ያለፈው አካሄድ የእኔ ብቻ ባሕል ተብሎ ለመከፋፋል መነሻ የሚሆን ትርክትን የፈጠረ ስለነበር ከዚያ ትርክትና እሳቤ ለመውጣት እንደ ክልል ጥረት አድርገናል፣
👉 የጋራ የሚያደርጉና የሚያስተሳስሩ ባሕሎች የበለጠ ለማጎልበት ሰርተናል፣
👉 የሌሎች ክልሎችን የባሕል ማዕክል እና የእንግዳ ማረፊያ በክልላችን እየገነባን ነው፤
👉 የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሳቤ መጎልበት ለዘላቂ ሠላም በጣም አስፈላጊ ነው፣
👉 ከአጅፕ እስከ ደከር” ያለው መንገድ ብቻ ሳይሆን የኮሪደር ልማትም እያከናወን ነው፣
👉 ኮሪደር ስንል ደግሞ ዝም ብሎ ኮሪደር አይደለም። የተመረጠ የጤና ኮሪደር እንጂ፣
👉 ሁለተኛ በዚህ አካባቢ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚሰጥ ከሆነ የሚሰጠው ፈቃድ በጤናው ዘርፍ ላይ ብቻ ነው፣
👉 አሁን ላይ ከሱማሌ ላንድ በርካታ ሰዎች ለሕክምና ወደ ሐረር ይመጣሉ፣
👉 ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት መስጠት ከቻልን የሜዲካል ቱሪዝሙን እውን ማድረግ እንችላለን፣
👉 የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስኬታማ ሆኖ ሲጠናቀቅ አሁን ካለው የውሃ ምርት በእጥፍ ይጨምራል፣
👉 በግብርናው ዘርፍ ለሌማት ትሩፋት ትኩረት ሰጥተን እየሠራን ነው፣
👉 አሁን ላይ ወደ 21 የሚጠጉ የወተት፤ 14 የሚሆኑ የዶሮ መንደሮችን መሥርተናል፣
👉 በሐረሪ ባሕል ቤት የእቃዎች አደራደር በምክንያት ነው፤
👉 የሐረሪ ሰዎች የትም ቦታ ቢሄዱ የሐረሪን ባሕል የሚያሳይ ቤት ይገነባሉ፣
ርዕሰ መስተዳድሩ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129664