Deema-Dhufee/ሂዱ መጣው /

  • Home
  • Deema-Dhufee/ሂዱ መጣው /

Deema-Dhufee/ሂዱ መጣው / Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Deema-Dhufee/ሂዱ መጣው /, Digital creator, .

18/06/2024

"አሻራ"

ዛሬ ምሽት ይጠብቁን!

18/06/2024
18/06/2024

ኢትዮጵያ፤ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት!

👉 የከተማ ልማት
በሀገሪቱ የሚታየው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማትና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አንዱ የከተሞች የልማት ገፅታ ነው። ከዚህ አኳያ ከተሞች የኢኮኖሚ ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ እንዲሆኑ በከተሞች ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለከተማ ግብርና፣ ለማዕድንና ለቱሪዝም ልማት ትኩረት ይሰጣል።

👉 ከተሞች ልማትን የሚያፋጥን እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩና ሚዛኑን የጠበቀና ያልተማከለ የአከታተም ሥርዓትን የሚያጠናክር ዕቅድና ትግበራ በሁሉም ደረጃ እንዲኖር በማድረግ በከተሞች የሚስተዋለውን የቤት ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ለማጥበብ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የተለያዩ የቤት ፕሮግራሞችና የፋይናንስ አቅርቦት አማራጮች እንዲኖሩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል።

👉 የከተማ ልማት ዋና ዓላማ የከተሞች ልማትንና የገጠር ዕድገትን የሚያፋጥን እንቅስቃሴ በከተማና በገጠር ተመጋጋቢ በሆነ መልኩ በመተግበር ከተማነትን ማሳደግ እንዲሁም ከተሞች አሳታፊና ዘላቂ ልማትን በሚያቀናጅ ተዋረድ ባለው የተሟላ ዕቅድና ባልተማከለ የከተማ አስተዳደር እንዲመሩ በማድረግ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕድገትን ማፋጠን ነው።

👉በቀዳሚነት መልማት የሚገባቸውና ሀገራዊ ዕድገቱን ከማፋጠን አንጻር ከፍተኛ ሚና ያላቸው ከተሞችና የልማት ቀጠናዎች ተለይተው የርብርብ ማዕከል የሚደረግባቸው ይሆናል። የተቀናጀ ልማትን ለማረጋገጥ የከተማና የአካባቢው ቅንጅት ዕቅድና ትግበራ እንዲኖር ይደረጋል።

👉 የከተማ ነዋሪው የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ የሚያስችል ተቋማዊ ሥርዓት ይተገበራል።

ከ10 ዓመት የልማት እቅድ ገፅ 128 የተወሰደ



18/06/2024

የብልጽግና ፓርቲ በብሪክስ ማዕቀፍ አማካኝነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት ግንባታ በቁርጠኝነት ይሰራል- አቶ አደም ፋራህ

የብልጽግና ፓርቲ በብሪክስ ማዕቀፍ አማካኝነት የዓለምን ስርዓት ፍትሐዊና አሳታፊ ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ትናንት በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ በተጀመረው የብሪክስና አጋር አገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ፎረሙ “ወርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።

አቶ አደም ፋራህ በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ፓርቲያቸው ብሪክስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በቅርበት ሲከታተለው እንደቆየ ገልጸው ማዕቀፉ የዓለም የኢኮኖሚና ፖለቲካ ምህዳር የመቀየር አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል አገራትና ከአሰራር ማዕቀፉ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት እየሰሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ራዕይና አመራር ሰጪነት እንደ አገርም እንደ ፓርቲም ላለን ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

ብሪክስ አዲስ አባል አገራትን ለማካተት በወሰደው ጠንካራ እርምጃ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ አደም ውሳኔው ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል እንድትሆን እድል ፈጥሯል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ በአፍሪካ የተስፋና የለውጥ ብርሃን ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በመደመር እሳቤ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ለማምጣት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ነጻነትና የዜጎች ክብር መሰረት አድርጎ መቋቋሙንና በፍጥነት እድገት በማሳየት ከ14 ሚሊዮን በላይ አባላትን ይዞ የአፍሪካ ትልቁ ፓርቲ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።

ፓርቲው ኢትዮጵያውያንን ተሳታፊ በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች አስደማሚ ውጤቶችን ማስመዘገቡንም ነው ያብራሩት።

በግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ለዘላቂ ልማት በማዋል እሳቤ ባለፉት 5 ዓመታት ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።

በዘንድሮው ዓመትም ከ7 ቢሊዮን ችግኝ በላይ ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል።

በኢንዱስትሪ ልማት፣ በኢንፎርሜሽንና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ቱሪዝምና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ጥራት ከማሳደግ አኳያም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት የማከናወን ስራ አንዱ የብልጽግና ፓርቲ መገለጫ መሆኑን የገለጹት አቶ አደም ለዚህም የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በዋና ማሳያነት አስቀምጠዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገራት አንዷ መሆኗንና በአፍሪካም አምስተኛ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ እንደሆነች ጠቅሰዋል።

ስኬቶቹ የተመዘገቡት ኢትዮጵያ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈተነች ባለበት ወቅት መሆኑንና ለውጤቱ መመዝብ ከፓርቲው አመራሮችና አባላት ያላሰለሰ ጥረት ባለፈ የኢትዮጵያ ሕዝብና አጋሮች ድጋፍ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተ ነው አቶ አደም የገለጹት።

ብልጽግና ፓርቲ በአገራት ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና በሰላም አብሮ የመኖር እንዲሁም የባለብዙ ወገን ትብብርና ፍትሐዊ ዓለም በሚሉት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው ብለዋል።

በኢኮኖሚና ንግድ ትብብር ዘላቂ ልማትን ማምጣት ፓርቲው የሚደግፈው ሀሳብ መሆኑን ገልጸዋል።

ዓለም በብዙ አቅጣጫዎች ፍትሐዊ አይደለችም ያሉት አቶ አደም የዓለም የፋይናንስና የፖለቲካ ስርዓትና የብዙሃን መገናኛዎች ትርክቶች የዓለምን ብዝሃነት የሚያንጻባርቁ አይደሉም ብለዋል።

ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው የአፍሪካና የላቲን አሜሪካ አህጉራት እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት አለመወከላቸው ተገቢነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም የአስተዳደር ስርዓት ይበልጥ አሳታፊና የዓለም ብዝሃነትን በማንጻባረቅ ሁሉን ያማከለ የብዝሃ ዓለም ስርዓት እንዲፈጠር ለሚደረጉ ማሻሻያዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

ብሪክስ በሰላም፣ ኢኖቬሽን፣ ቴክኖሎጂና የጋራ ብልጽግና እውን ለማድረግ በአገራት መካከል ለሚከናወኑ የትብብር ስራዎች ወሳኝ ሚና እንዳለውና በዚህ ረገድም አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው ምክትል ፕሬዝዳንቱ የገለጹት።

የብሪክስ አባል አገራትና ሌሎች አጋር አገራት ማዕቀፉን በመጠቀም የጋራ ትብብርና አንድነትን ይበልጥ በማጎልበት የጋራ ተጽእኖ መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የብሪክስ አላማዎች እውን እንዲሆኑና የጋራ ግቦቹ እንዲሳኩ የበከሉን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል።

በተጨማሪም ፓርቲው ብሪክስ የዓለም የፋይናንስ ስርዓት እንዲለወጥና ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ የዓለም ስርዓት እንዲፈጠር ለያዘው ግብ የበኩሉን ሚና ይወጣል ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሁለተኛ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ገልጸው በጉባኤውም ፓርቲው ባለፈው ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በመገመገም ለቀጣይ ስራዎች አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ጠቁመዋል።

አቶ አደም በፎረሙ ላይ እየተካፈሉ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውንም ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የብሪክስና አጋር አገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።



18/06/2024
18/06/2024

አስተማማኝ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ለህዝባችን ተጠቃሚነት ተናጠላዊ ፍላጎቶቻችንን መስዋዕት እናድርግ !

በህብረት በቆምንበት ጊዜ ድል አስመዝግበን ታሪክ ሰርተናል። ከተናጠል ፍላጎቶቻችን ይልቅ ለብሔራዊ ክብራችን ቅድሚያ በሰጠንበት የታሪክ ምዕራፍ ሁሉ የአሸናፊነት ደማቅ ታሪክ ተጎናፅፈናል።

በዓለም አቀም ደረጃ የሚጠቀሱ ታላላቅ ስልጣኔዎች የነበሩን ፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ከመስፋቱ በፊት አገር በቀል ስርዓትን የገነባን ፣ ተቻችሎ እና ተከባብሮ በመኖር አብነት የሆነን ፣ በየጊዜው የገጠሙንን ተግዳሮቶች በጋራ የመከትን እያልን ስለ ገናና ታሪካችን ብዙ መጠቃቀስ ብንችልም ታላቅ ነበርን ማለት ታላቅ አያደርግም ፤ ታላቅ ሆኖ መገኘት እንጂ።

ኢትዮጵያ በየዘመኑ የታሪክ ስብራቶቿን ልትጠግንባቸው የሚችሉትን መልካም አጋጣሚዎች አባክናለች። እንደ አለመታደል ሆኖ አንድነቷን እንደ ብረት ሊያጠናክርላት የሚገባው በደምና በአጥንት መስዋዕትነት የተገኘው የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራት የሆነው የአድዋ ድል አከባበር ጭምር የመሰባሰቢያ ሳይሆን የመለያያና የመገፋፊያ ምንጭ ሆኖ መቆየቱ አግራሞትን ያጭራል።

ምስጋና ለባለ ራዕይ መሪዎቻችን ይሁንና አሁን ላይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር የጥል ግድግዳ የሚፈጥርበት ምዕራፍ ተዘግቶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአብሮነትና በፍቅር የሚያከብርበት ብቻም ሳይሆን ድሉ ዓመቱን ሙሉ የሚዘከርበት ፣ ጥበብንና ቅርስን አጣምሮ የያዘው ፣ ከእኛ ትውልድ የታሪክ አሻራዎች ውስጥ ጎልቶ ሲጠቀስ የሚኖረው የአድዋ ድል መታሰቢያ ለከተማችንም መለያ ዓርማ ሆኗል::

በመሰባሰባችን የተገኘው ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነውን የአድዋ ድልን በአድዋ ድል መታሰቢያ ተሰባስበን በድምቀት ማክበር ብቻም ሳይሆን በችግር ጊዜ ጭምር የህብረታችን ሚስጢር ተናጠላዊ ፍላጎትን ለአገራዊ ድል በማስገዛት መሆኑ በጥናትና ምርምር እየዳበረ ለትውልድ መማሪያ ዕውቀት እንደሚገበይበትም ይጠበቃል።

የለውጡ መንግስት የህዝባችንን ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ነፃ ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ አገር የመምራት ሀላፊነት ስለተሰጠው የነበሩትን ውስብሰብ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እያቃለለ እንደ አገር የነበሩብንን ስብራቶች ለመጠገን ጥልቅ ሪፎርሞችን እያከናወነ ይገኛል።

ከሪፎርም ስራዎቻችን መካከልም ነፃ እና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተቋማትን ለመፍጠር የተደረገው አበረታች ጥረት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው::

ፓርቲያችን የዴሞክራሲ ስርዓትን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት እና የፖለቲካ ባህላችን ወደ ትብብር እና ፉክክር ለማምጣት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች ምንጫቸው የአገራችንን ውስብስብ ችግሮች በጥልቀት ከመረዳት እና አሻግሮ ከማየት ብቃት ነው።

ነፃ እና ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ተቋቁሞ በአገራችን ታሪክ ሲወሳ የሚኖር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መደረጉ ስልጣን በህዝብ ድምፅ እንጅ በሀይል የሚገኝበት የታሪክ ምዕራፍ መዘጋቱን የሚያመላክት የዛሬው ብቻም ሳይሆን የነገውም ትውልድ ብስራት ነው።

ሀገረ መንግስት ግንባታው የዕድሜውን ያህል እንዳይራመድ ተግዳሮት የነበሩ መግባባት ላይ ያልደረስንባቸውን አገራዊ ጉዳዮች በምክክር እና በውይይት ለመፍታትም ከማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

ሳንግባባቸው ያደርን ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች ሳያንሱን ለሰላም እንምከር ፣ ለልማት እንተባበር ፣ ዴሞክራሲን እናዳብር ስንል ተቃራኒውን የሚያስቡ እና የሚተገብሩ ፅንፈኛ አካላት የሀሳብ ድርቀታቸውን ለመሸፋፈን ጥረት ቢያደርጉም ህዝባችን ምርትና ገለባውን አብጠርጥሮ የሚለይበት ጥበብ ስላለው በጊዜ ሂደት እኩይ ድርጊታቸው እየተጋለጠ የበለፀገች እና አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ ዕውን መሆኗ የማይቀር ጉዳይ ነው::

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!



17/06/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሃ /አረፋ/በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት
ኢድ ሙባረክ!

15/06/2024

እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴቶቻችንን የሚያጎለብት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ

አቶ ሞገስ ባልቻ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ

15/06/2024

እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ አል አድሃ

ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

15/06/2024

ወንድማማችነት እና እህታማማችነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና!

ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን ማሳደግ ለሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት ነው። ሰዎች በአንድነት እና በትብብር መንፈስ ሲሰባሰቡ የሚደነቅ እመርታ ማስመዝገብ እና ፈተናዎችን በብቃት ማሸነፍ ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በልዩ ልዩ ማህበረሰቦች መካከል የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ስሜትን ማጎልበት በተለይ ሀገሪቱ ካላት የበለፀገ የባህል ዕሴት እና ታሪክ አንፃር እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህንን እሴቶቻችንን መቀበል ፣ መለያየትን ለመድፈን፣ መግባባትን ለማጎልበትና ለሀገር እድገት የሚያበረክተው አስተዋፅዖ ለማበርከት ይረዳል።

የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ተግዳሮቶች የሚፈቱ ውይይቶችን፣ የባህል ልውውጦችን እና ተነሳሽነቶችን ጨምሮ የአንድነትን ትስስር ለማጠናከር የሚደረጉ የቆዩ እሳቤዎቻችንን እያጎለበትን ልንሄድ ይገባል።

በእኛ ኢትዮጵያውያን መካከል መከባበርን፣ አብሮነትን እና መተሳሰብን ማበረታታት የሀገረ መንግስት ግንባታን በማፅናት ለዛሬና ነገዋ ኢትዬጵያ ፅኑ መሰረት የሚጥል ነው።

15/06/2024

ብልጽግና የብሔራዊነት ትርክትንና ሀገራዊ መግባባትን ለማጽናት እየሰራ ያለ ፓርቲ!

ብልፅግና ፓርቲ የነደፋቸው የፖለቲካ ተልዕኮና ዓላማዎች ይሳኩ ዘንድ በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች አንዱና ዋናው የሀገራዊ መግባባት ጉዳይ ነው። ፓርቲው ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ማበብና አጠቃላይ ሀገራዊ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት ይመጣ ዘንድ ከነጠላ ትርክት በመላቀቅ ገዥ ብሔራዊ ትርክትን በማጽናት ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በጽኑ እየሰራ ይገኛል።

በሀገራችን የተፈጠሩና እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ዋነኛው መነሻቸውና አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት መሆኑንና አንድ ሀገር የሚጸናው በአገሪቱ በተገነባው የጋራ ትርክት መሆኑን በመረዳት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቱ ትውልድ የተናጠል ትርክት ሰለባ እንዳይሆን ወላጆችና ማሕበረሰቡ ብዝሃነትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ለአሰባሳቢ ትርክት ቅድሚያ በመስጠት የሚያግባባንን አሰባሳቢ የጋራ ትርክት ማጉላት ይጠበቅብናል።

ፓርቲያችን ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ በሀገራችን የቂምና የጥላቻ ታሪክ ምዕራፍ እንዲዘጋና በብሔራዊ አርበኝነት የተገነባ ብዝሃነትን ያማከለ አካታች የፖለቲካ ስርዓት ይኖር ዘንድ ነው ።

የብልፅግና ፓርቲ በሀገራችን የምንፈጥረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የጠበቀና የሁሉም ማንነቶች ነፀብራቅ የሆነ፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ማንነት ያከበረ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል። ለዚህም ብሔራዊ አርበኝነትን የሚያፀና አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ወሳኝ ነው። ብሔራዊነት ስንፈልግ የምንይዘው ሳይመቸን የምንጥለው ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ከተቃርኖ የጠቅላይነትና የተገንጣይነት ነጠላ ትርክቶች ተላቀው ጠቃሚ የሆኑ የስልጣኔና የአብሮነት ዕሴቶቻቸውን በማዳበር የወል እውነትን በማጽናት በህብረ - ብሔራዊ አንድነት ፀንታ የምትበለጽግ የጋራ ሀገር ዕውን ማድረግ ይገባል።



Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deema-Dhufee/ሂዱ መጣው / posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share