Ghion press

Ghion press Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ghion press, Media/News Company, .

23/04/2024
16/04/2024

Welcome to our channel If you subscribe our channel you get more Information’s about Amhara, Ethiopia and World News, News Release, Programs, Documentary and...

16/04/2024

በ250 ሚሊዮን ብር የተገነባው አግማስ ውኋ ፋብሪካ የአማራ ክልልና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ በተገኙበት ተመረቀ።
*********
በቃሉ ወረዳ በ250 ሚሊዮን ብር የተገነባው አግማስ ውኋ ፋብሪካ የአማራ ክልልና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ በተገኙበት ተመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱም የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኋላፊ አቶ ኢንድሪስ አብዱ፣የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንንና የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኋላፊ አቶ ተስፉ ዳኛው ተገኝተው መርቀዋል።

ፋብሪካው 200 ለሚሆኑ ሥራ ፈላጊዎች በጊዛዊና በቋሚ የሥራ እድል መፍጠሩን ባለሐብቱ ሀጂ ኑሩ አህመድ ተናግረዋል። የውኋ ፋብሪካው በአዲስአበባ ዙሪያ ከአሁን በፊት የነበረና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረ አሁን ላይ ደቡብ ወሎ ዞን ባመቻቸላቸው ቦታ ገንብተው ማስመረቃቸውን ገልጸዋል። ከዚህ ሌላ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሠማራታቸውን አክለዋል። ዞኑ ላደረገው እገዛና ድጋፍ አመስግነዋል።

የዞኑ አስተዳደር ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ካለው ፍላጎትና ተነሳሽነት ማነቆ ከሆኑት መካከል የኋይል ችግርን በመፈታቱ ፋብሪካው ለምረቃ መብቃት ችሏል ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ናቸው።በቀጣይም ማነቆዎችን በመፍታት በዘርፉ የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት ይሠራልም ብለዋል።

South Wollo Zone Gov. Communication Dept.
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Website: https://www.amharacomm.gov.et

16/04/2024

ቀድመው ዘር በሚጀምሩ አካባቢዎች ማዳበሪያ የማስገባት ሥራ እየተሠራ መኾኑን ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በአማራ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን 5 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል በመሸፈን 169 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዷል።

እቅዱን ለማሳካትም 8 ነጥብ 05 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል።

👉 ለመኾኑ የተገዛው ግብዓት ለምን ያህል አርሶ አደሮች ተደራሽ እየተደረገ ነው?

አርሶ አደር ማንዴ መኳንንት የፎገራ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡ አርሶ አደሩ እንደገለጹልን በየዓመቱ በሁለት ሄክታር መሬታቸው ላይ ሰብል ያመርታሉ። ለዚህም 10 ኩንታል ማዳበሪያ እጠቀማለሁ ነው ያሉት።

በዚህ ዓመትም ከ2 ሄክታር በላይ መሬት በሰብል ለመሸፈን እየሠሩ ይገኛሉ። ከ10 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለመጠቀምም አቅደዋል። ይሁን እንጂ እስከ አሁን ማግኘት የቻሉት ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ ብቻ ነው።

በ2015/16 የምርት ዘመን በቂ ግብዓት ባለመቅረቡ የምርት መቀነስ እንዳጋጠማቸው ያነሱት አርሶ አደር ማንዴ በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥማቸው መንግሥት የዘር ወቅት ከመድረሱ ቀድሞ በቂ ግብዓት እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።

አርሶ አደር ማንዴ አሁን ላይ ማሳቸውን የማለስለስ ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ነግረውናል።

በ2016/17 የምርት ዘመን ግዥ ከተፈጸመው 8 ነጥብ 05 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታሉ ወደብ ላይ መድረሱን በምክትል ርእስ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታሉ ደግሞ ወደ ዩኒየኖች ገብቷል፤ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚኾነው የአፈር ማዳበሪያ ደግሞ አርሶ አደሮች እጅ መግባቱን ገልጸዋል፡፡ በተለይ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎችን ቀድመው ዘር በሚጀምሩ እንደ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ቀድሞ የማስገባት ሥራ እየተሠራ ይገኛል ነው ያሉት።

ይሁን እንጅ በአንዳንድ አካባቢዎች በዩኒየኖች የቀረበውን ግብዓት በትራንስፖርት እጥረት ወደ መሠረታዊ ማኅበራት የማጓጓዝ ችግር በማጋጠሙ አርሶ አደሮች ዩኒየኖች ላይ እንዲገዙ መደረጉን ገልጸዋል።

ይህም በአርሶ አደሮች ላይ ያልተገባ መጨናነቅ እና መዘግየት እየፈጠረ መኾኑን ገልጸዋል። ችግሩን ለመፍታትም አካባቢያዊ አጓጓዦች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

እጥረት ባጋጠማቸው አካባቢዎች በወቅቱ ለማድረስ ወደብ ላይ የደረሰውን ማዳበሪያም የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ መኾኑን ነው የተናገሩት። በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በክልሉ የተሻለ ሥርጭት እንደሚኖር ገልጸዋል። በምርት ዘመኑ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈለገውን ያህል ባይኾንም ከሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም የሚያስችል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።

በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታየው የሰላም ሁኔታ አኳያ ካልኾነ በስተቀር በዚህ ዓመት የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር እንደማያጋጥም ገልጸዋል።

በሕገ ወጥ የማዳበሪያ ግብይት ላይ ተሳትፎ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ንብረቱን መወረስ ብቻ ሳይኾን በወንጀል የሚጠየቅ መኾኑን ገልጸዋል። ማኅበረሰቡ ችግሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አርሶ አደሮችም ያገኙትን ግብዓት በግብርና ምክረ ሃሳብ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ከዚህም ባለፈ ክልሉ ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተባዝቶ እየተዘጋጀ መኾኑን ነው ዶክተር ድረስ የነገሩን። ከዚህ ውስጥ ከ102 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ዘር ተዘጋጅቶ ወደ ዞኖች እየተሰራጨ መኾኑን አንስተዋል።

Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ghion press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share