Ethiopian daily news

  • Home
  • Ethiopian daily news

Ethiopian daily news Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian daily news, Media, .

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነአዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ...
27/01/2023

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/

በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁም አገልግሎቱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ተዋሃዱአዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ...
25/01/2023

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ተዋሃዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ተብለው በአንድ ተቋም ተዋሃዱ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛው አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷አውቶቡሶቹ የተዋሃዱት በተናጠል በሚሰሩበት ወቅት የሚፈጠርን የሃብት ብክነት ለመቀነሰ በማለም ነው፡፡

በተለይም ተቋማቱ ተመሳሳይ አገልግሎት እየሰጡ በየተለያየ የነዳጅ ዴፖ፣ የመለዋወጫ ማዕከል፣ የሰው ሃይል እና ሌሎች አገልግሎቶችን መጠቀማቸው ከፍተኛ የሃብት ብክነት ማስከተሉን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ውህደቱ አውቶቡሶቹ በመዲናዋ በሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት ላይ የሚፈጠርን አላስፈላጊ ድግግሞሽ በማስቀረት የተሳላጠ ትራንስፖርት መስጠት የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስለሆነም በተበጣጠሰ መልኩ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩት አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ተብለው መዋሃዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡

አውቶቡሶቹ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ስያሜምይዘው የሚቀጥሉ መሆኑን ነው ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian daily news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share