Nami kiyya

Nami kiyya Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nami kiyya, Digital creator, .

19/04/2024
16/04/2024
11/03/2024

እንኳን ለዓብይ ፆም እና ለታላቁ ረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ!

ፆሙ ለሀገር ሰላም የምንፀልይበት ፣ካለን ላይ በማካፈል የተቸገሩትን የምንረዳበት እና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

05/03/2024
01/03/2024

የዓድዋን ድል ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ሁለንተናዊ ብልጽግናችን ለማረጋገጥ መጠቀም የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል!

የዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ተጋድሎና መስዋትነት ሀገራችንን ያስከበሩበት ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ አንፀባራቂ የሆነ ድል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በጋራ መታገል እና በጋራ ድል መቀዳጀት የካበተ ልምድ ያለን ህዝቦች መሆናችን የዓድዋ ድል ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ጀግኖች አባቶች በከፈሉት መሰዋእትነት ድልን አጎናጽፈውናል፤ ለዚህ ክብር ላበቁን አርበኞች ክብር ይገባቸዋል፡፡

ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአብሮነት፣ የአሸናፊነትና ፅናት ተምሳሌት ነው። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መግስታችን ደግሞ መስዋትነት ለከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ክብራቸውን የሚመጥን ትልቅ እና ማስተማሪያ የሆነ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በማቆም ሌላ ደማቅ የታሪክ አሻራ ማኖር ተችሏል።

እኛም የዛሬ ትውልዶች ለአርበኞቻችን ክብር እየሰጠን ዘመኑን በመዋጀት ከአባቶቻችን ልቀን እንጂ አንሰን እንዳንገኝ የዛሬውን የጋራ ጠላት የሆነዉን ድህንትን በማሸነፍ ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን የማስረከብ ሃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል።

01/03/2024

እንኳን ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡

እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡
የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አሳይቷል፡፡ የመጀመሪያው በጦርነቱ ዘመቻና ድል ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ በምናውቃት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች መካከል ወደ ዐድዋ ያልዘመተ ወገን የለም ብሎ መናገር እውነትን መናገር ነው፡፡ ሁለተኛው ክሥተት ደግሞ የዐድዋ ድል በተገኘ በሰባት ዓመቱ የዐድዋ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሲከበር ትርዒቱን ያቀረቡት ከተለያዩ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችች የመጡ የኢትዮጵያ ጦር አባላት ነበሩ፡፡ በዚህ ትርዒት ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት ሀገር መሆንዋን በዐደባባይ ሰልፈኛው አሳይቶ ነበር፡፡
ይሄንን በዐድዋ ዘመቻና በዓል የተንጸባረቀ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አጽንተን ልንይዘው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ኅብረ ብሔራዊ ማነነት ያላቸው ሕዝቦች በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ኅብረ ብሔራዊነታቸው ከፈጣሪ ሲያገኙት ነው፡፡ አንድነታቸውን ደግሞ እነርሱ ራሳቸው በዘመናት ትሥሥርና መሥዋዕትነት ገንብተውታል፡፡ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁለቱን፣ ነገር ግን አንዱ ከሌላው ጋር ሳይነጣጠል የሚኖሩትን መገለጫዎቿን ትታ ኢትዮጵያ አትሆንም፡፡ በእያንዳንዱ ጉዞዋ ይሄንን እያረጋገጠች መጓዝ አለባት፡፡
ሁለተኛው ዕሴት ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ሲባል ንኡስ ፍላጎቶችን መሠዋት ነው፡፡ ወደ ዐድዋ የዘመቱ ሁሉ በወቅቱ በነበረው ሥርዓተ መንግሥት የሚስማሙና የተደሰቱ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ግጭትም ቅራኔም ነበራቸው፡፡ አንዳንዶቹም በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ ቅር ተሰኝተው ከጠላት ጋር የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ነገሩ የሀገር ጉዳይ ሲሆንባቸው ግን ሁሉም ንኡስ ፍላጎቶቻቸውን ትተው፣ ለታላቁ ፍላጎት ለሀገር ህልውና መሥዋዕት ለመሆን መጡ፡፡ ማንኛውም ፍላጎት ከሀገር ፍላጎት በታች መሆኑንም አሳዩን፡፡
እንኳን ዛሬ ብዙ ዓይነት መረጃ፣ ዕውቀትና የሐሳብ መንገዶች ባሉበት ዘመን ቀርቶ ከመቶ ዓመት በፊትም ሰዎች ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ነበሯቸው፡፡ በፍላጎቶቻቸው የተነሣም ቅራኔዎችና ግጭቶች ነበሩ፡፡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ የምታስተሣሥር ዓላማ ሀገር የምትባለው ናት፡፡ ዛሬም ንኡስ ፍላጎቶቻችን ከኢትዮጵያ አይበልጡም፡፡ ኢትዮጵያን የሚያዳክም፣ የሚያሳንስና የሚያሳጣ መንገድ ከትልቁ ዓላማ የሚጋጭ መንገድ ነው፡፡ ጦርነት የትልቁ ዓላማ የኢትዮጵያ ህልውና ማስከበሪያ እንጂ የንኡስ አካባቢያዊና ግላዊ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ሊሆን አይገባም፡፡ ጦርነት ለትንሽ ነገር የሚወጣ ወጪ አይደለም፡፡ ዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉት ሁሉ ብዙ የመፍትሔ አማራጮችም አሉት፡፡ መከራከር፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ በሕግ መዳኘት፣ አንዱ ሌላው መሸከም፣ የትየለሌ አትራፊ መንገዶች አሉት፡፡ ትልቋ ዓላማ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ስንል ንኡስ ዓላማዎቻችንን እያመሙን እንኳን ቢሆን መሠዋት አለብን፡፡
ሦስተኛው ዕሴት የጦርነትን ምርቅና ፍትፍት ማወቅ ነው፡፡ ጦርነት ምንም ያህል በአሸናፊነት ቢጠናቀቅ የሚያስከፍለው ዋጋ አለው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ሀገር ሆኖባቸው፤ ሉዓላዊነት ሆኖባቸው፤ የታላቅ ዓላማ ጉዳይ ሆኖባቸው እንጂ ጦርነት የመጀመሪያ አማራጫቸው አልነበረም፡፡ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ነገሩ በሰላም እንዲቋጭ ደጋግመው ጽፈዋል፤ ለምነዋል፡፡ አልሆነም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዘማቾች ግን ከድል የተመለሱት በደስታ ብቻ አይደለም፡፡ ከፊታውራሪ ገበየሁ ጀምሮ አያሌ ጀግኖች ለትልቁ ዓላማ ለኢትዮጵያ ህልውና ሲሉ ተሠዉተዋል፡፡ የሄዱት ሁሉ አልተመለሱም፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በድልና በኀዘን ነው የተመለሰው፡፡ ብዙዎችም በየአካባቢያቸው በፌሽታ አልነበረም ድሉን ያከበሩት፡፡ እንኳን በራሳቸው ወገኖች፣ በጣልያኖች መሞት ኢትዮጵያውያን አዝነዋል፡፡
ጦርነት ተገድደን ብቻ ለትልቁ ዓላማ ስንል የምንገባበት የመጨረሻ አማራጭ እንጂ ከደረት ኪሳችን ቶሎ የምንመዘው አይደለም፡፡ እዚህም እዚያም የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በጠመንጃ ለመፍታት መነሣት የዐድዋ ዘማቾችን ኀዘን አለመጋራት ነው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ድልን ብቻ ሳይሆን ጦርነት የሚያስከትለውን መከራም ጭምር አስተምረውን አልፈዋል፡፡
አራተኛው ትዕግሥት፣ ዝግጅት እንጂ ፍርሐት አለመሆኑን ነው፡፡ ጣልያኖች ከሦስት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ሲገፏት ነበር፡፡ በሀገሪቱ የደረሰውን የእንስሳትና የሰዎች ማለቅ ምክንያት አድርገው ትንኮሳውን አባብሰው ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እየተገፋች እንኳን ቢሆን ታግሣለች፡፡ ትዕግሥቷ ግን ከዐቅመ ደካማነቷ የመጣ አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር እየተዘጋጀች ስለነበር እንጂ፡፡ እህል እስኪደርስ፣ ሰው እስኪያገገም፤ የተገዛው መሣሪያ እስኪደርስ፣ የደረሰው መሣሪያ ከጦሩ ጋር እስኪላመድ ታግሣለች፡፡ በመጨረሻ ግን የትዕግሥቷን ውጤት በዐድዋ ተራሮች ላይ አሳይታለች፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬም ትታገሣለች፡፡ እየተገፋችም እንኳን ቢሆን ትታገሣለች፡፡ የምትታገሠው ስለሚያቅታት አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር ስለምትዘጋጅ ነው፡፡ ያ የባሰው ነገር ሲመጣ የዐደዋውን ድል በብዙ እጥፍ ትደግመዋለች፡፡
እነዚህን ዕሴቶች ዘወትር ማሰብ፣ አስበን መተግበር እንድንችል የሚያስታውሰን ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ ዐድዋን የሚመጥን ታሪኩንም ዕሴቱንም የምናስብበት መታሰቢያ ዘመቻው በተጀመረበት ሥፍራ ባስገነባን ማግሥት ነው በዓሉን የምናከብረው፡፡ ይሄም ለዘንድሮው በዓል ሞገስና ክብር ጨምሮለታል፡፡ ዛሬ መታሰቢያውን በከበረ ሁኔታ አከናውነናል፡፡ ነገ ግን የአድዋን ዕሴቶች በሚገባ በመጠቀም እንደ ዐድዋ ተራሮች የጸናች ኢትዮጵያን መገንባት ይቀረናል፡፡ ያ ደግሞ የሁላችንንም ስክነት፣ ብስለትና ጥምረት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ መልካም የዐድዋ ድል በዓል ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ‍ በልጆቿ‍ ጥረት‍ ታፍራና‍ ተከብራ‍ ለዘላለም‍ ትኑር!!
ፈጣሪ‍ ኢትዮጵያና‍ ሕዝቦቿን‍ ይባርክ!
የካቲት 22/2016 ዓ.ም

15/02/2024

የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የወል ትርክት!

ሀገራችን ብዝሀ ማንነቶች ያሉባት ህብረ-ብሔራዊት ብትሆንም በደም የተሳሰረ፣ በባህል እና በቋንቋ የተወራረሰ፣ በጋራ መስዋዕትነት የፀና አንድነታች ከብረት የጠነከረ ነው።

በፈተናዎች ሁሉ ፀንቶ የዘለቀው የኢትዮጵያውያን አንድነት በየዘመኑ የተቃጡብንን ጦርነቶች በመመከት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገር እንድንወርስ አስችሎናል።

አርበኞቻችን ለሉዓላዊነታችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በመስዋዕትነታቸው ብሔራዊነትን ከፍ አድርገዋል።
ሀገራችን ሉዓላዊነቷ ባለመደፈሩ አንገታችንን ከፍ አድርገን መራመድ ብንችልም በድህነታችን ምክንያት ለዘመናት አንገታችንን ደፍተናል።

ፓርቲያችን ብልፅግናም የእኛን ትውልድ የአርበኝነት ተጋድሎ የሚጠይቀውን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ አቅጣጫዎችን ቀይሶ ለተግባራዊነቱ እየተረባረበ ይገኛል።
የላብ መስዋዕትነትን በሚጠይቀው የዘመኑ አርበኝነት ድልም መመዝገብ ጀምሯል። ለዚህ ደግሞ ከተማችን አዲስ አበባ ምሳሌ ናት።

በሰው ተኮር ፕሮግራሞቻችን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ ከተማችንን የኢትዮጵያ ብልፅግና ምሳሌ ማድረግ የጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶቻችን በተባበረ ክንዳችን ድህነትን ድል እንደምናደርገው አመላካች ናቸው።

የእኛ ዘመን አርበኝነት በህይወት መስዋዕትነት በአንዴ የሚጠናቀቅ ድል ሳይሆን በማያቋርጥ ትግል ላባችንን አፍስሰን ድህነትን በመንቀል የሚረጋገጥ የህዝባችን ህይወት መሻሻል ነው። የህይወት መስዋዕትነትን በሚጠይቀው የአገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ አርበኝነት በአብሮነት የቆምን ኢትዮጵያዊያን በነጠላ ትርክቶቻችን አንድነታችን ሊሸረሸር አይገባም።

ኢትዮጵያውያንን ብቻም ሳይሆን ሁሉንም ጥቁር ህዝቦች የሚያስተሳስሩ የአድዋ ድልን የመሳሰሉ አሰባሳቢ የወል ትርክቶች እያሉን ቁሞቀር ፖለቲከኞች እና ሀላፊነት የጎደላቸው አክቲቪስቶች በሚረጩት ከፋፋይ አጀንዳ እና በሬ ወለደ ወሬ በህብረ-ብሔራዊነት የተጋመደው የህዝባችን አንድነት አይነጣጠልም!

12/02/2024

ዓድዋ የሕብረ ብሔራዊ-አንድነት ዓርማ!

ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን በብሔራዊ ገዥ ሀሳብ ሲሰባሰቡ ጠንካራ የማስተባበር፤ የመምራት፤ የመደማመጥና ፈተናዎችን በአብሮነት የመሻገር ችሎታ እንዳላቸዉ ያስመሰከሩበት ታላቅ ታሪክ ነው!

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ የአርበኝነት አምድ የሆነ በእሳት ተፈትኖ የነጠረ በወጀብ የማይናወጥ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት የታነፀበት የብሔራዊ አርበኝነት ምሰሶ ነው! ዓድዋ የኢትዮጵያዊያን አይበገሬነት፤ ጀግንነት፣ ሕብረትና አንድነት በተግባር የተመሰከረበት የብሔራዊነት ምልክት፣ የወል ታሪካችን አርማ ነዉ!

ዓድዋ የብሔራዊነት ምሰሶ ነው ስንል ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ በወል ተምመዉ ያስመዘገቡት ድል የጋራ ትናንትን ከነገ ጋር ማስተሳሰሪያ ገመዳችን መሆኑን የሚገልጽ ሀቅ ስለሆነ ነው!

ብሔራዊ ገዥ ትርክት ልክ እንደ ዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ሲሆን ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ በተሰናሰነ የብሔር-ብሔረሰቦች ላብ እና ደም ድምር ዉጤት የተገነባችና በወል ጥረቶቻቸው የምትበለጽግ ሀገር ናት።

ዓድዋ ብዝሃነትን ያከበረ፣ አብሮነት ለሁለንተናዊ ድል ወሳኝ መሆኑን የሚያሳይ ለኢትዮጵያ ክብርና የግዛት አንድነት በተከፈለ የጋራ መስዋትነት የተገኘ የኢትዮጵያዊያን የወል ድል ነው።

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nami kiyya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share