Lafee

Lafee Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lafee, Digital creator, .

02/05/2024
ቀን መጋቢት 29 / 2016 ዓ.ምየአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያደረገው የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት በስኬት መጠናቀቁን የብሔራዊ መ...
06/04/2024

ቀን መጋቢት 29 / 2016 ዓ.ም

የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያደረገው የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት በስኬት መጠናቀቁን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር (TSA) ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

የኦዲት ልዑክ ቡድኑ በቆይታው የመንገደኞች፣ የሻንጣ፣ የካርጎ ጭነቶች፣ የዙሪያ ጥበቃና ፍተሻ እንዲሁም የአውሮፕላን ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚወሰደው የሴኪዩሪቲ እርምጃ ከዓለም አቀፍ አሰራር አንጻር አጠቃላይ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ሁሉን አቀፍ ኦዲት አድርጓል፡፡

በኦዲቱ ጥልቅ የሠነድ ግምገማ እና የአካል ምልከታ የተደረገ ሲሆን፤ በልዑኩ በቀረበው የማጠቃለያ ሪፖርት ወደ አሜሪካ ሀገር በሚደረጉ በረራዎችም ሆነ አጠቃላይ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦፕሬሽናል ሂደቶች ላይ ምንም ዓይነት የደኅንነት ስጋት እንደሌለ በድጋሚ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ጠንካራ የሆነ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ስርዓት መገንባቱን እንዲሁም በቀጣይም በአፍሪካ ምርጥ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለመሆን የተያዘውን ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሰረት እንደተጣለ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር (TSA) ተወካይ የገለፁ ሲሆን፤ በሁለቱ ተቋማት ብሎም ሀገራት መካከል በዘርፉ የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጀላ የኦዲት ሪፖርቱ በቀረበበት መርሐ ግብር ባደረጉት ንግግር በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ የተደረገው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም፣ የተዘረጋው አሰራር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የቴክኖሎጂ እምርታ እና ከምንጊዜውም በላይ የተጠናከረው የኤርፖርት ባለድርሻ አካላት ቅንጅት የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደርን (TSA) እና ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሌሎች ተከታታይ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ምዘናዎችን ስኬት ለመጎናፀፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡

በኦዲቱም ለተገኘው ሀገራዊ ውጤት ሌት ተቀን ሲተጉ ለነበሩ የዋና መምሪያው ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም በኤርፖርት ለሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በቀጣይም በሚደረገው ሀገራዊ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ኦዲት ሁሉም በከፍተኛ ቅንጅት፣ ቁርጠኝነት እና ትብብር በመስራት ኢትዮጵያን በከፍታ ማስጠራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ለሀገራዊ ኦዲቱም ከወዲሁ ስራዎች ተለይተው እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር (Transportation Security Administration) ከሐምሌ 10 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ባካሄደው የበረራ ደኅንነት ልዩ ኦዲት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት ምንም አይነት የደኅንነት ክፍተት (ግኝት) እንደሌለበት መግለጹ ይታወሳል፡፡

የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር ሐላፊ ደቪድ ፕኮስኬ የኦዲት ውጤት መገኘቱን ተከትሎ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በተቋሙ ባደረጉት ጉብኝት ለኢትዮጵያ የበረራ ደኅንነት አጠባበቅ አድናቆታቸውን መግለጻቸ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share