Ra,uuf

Ra,uuf Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ra,uuf, Digital creator, .

11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024

ለዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን 23 ቀናት ይቀሩታል።
**********

11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
10/06/2024

ለዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን 24 ቀናት ይቀሩታል።
**********

10/06/2024

በሀረሪ ክልል ከነገ ጀምሮ ለ 2 ተከታታይ ቀናት የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መስጠት እንደሚጀመር ተገለፀ፡፡
***************
በሀረሪ ክልል ከነገ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መስጠት እንደሚጀምር የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዘካሪያ አብዱላዚዝ ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የፈተና ህትመቶች ተጠናቀው ርክክብ መደረጉን የገለፁት ምክትል ሀላፊው ከተማ እና ገጠርን ያማከለ 19 የፈተና ጣቢያዎች ዝግጅታቸውን መጨረሻቸውንም ገልፀዋል፡፡

በዚህም 3ሺ 51 ወንዶች ፣ 2 ሺ 624 ሴቶች ባጠቃላይ 5ሺህ 675 ተማሪ ሴቶች ከግል እና ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ፈተናውን እንደሚወስዱም ተናግረዋል፡፡

አክለውም ፈተናው ያለ ምንም ችግር ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ በሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በኩል ሙሉ ዝግጅቶች ማለቃቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ትምህርት ቢሮ የፈተና አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሪት ዙክራ ሙኽታር እንደገለፁት ኩረጃን ለማስቀረት ተማሪዎች ላይ ሰፊ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን ገልፀው ተማሪዎችን የማዘጋጀት እና በራስ መተማመናቸውን እንዲያዳብሩ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ፈታኞች እና የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎችን መልምሎ ቅድመ ዝግጅቶች የተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከነገ ሰኔ 4 እስከ 5 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ዘጋቢ ፡- አብስራ አሰግድ
03 / 10 / 2016

10/06/2024

በሐረር ከተማ ጎዳና ተዳዳሪነትን እና የጎዳና ላይ ልመናን ለማስቀረት በቅንጅት ይሰራል- አቶ ኦርዲን በድሪ
**************
በሀረር ከተማ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ችግር ለመፍታት በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ የተጀመሩ ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ለመደገፍ፣ የጉዳት ተጋላጭነታቸውን ለመከላከልና ቁጥጥር ለማድረግ ከተቋቋመው ግብረሃይል ጋር ተወያይተዋል።

በመድረኩም ግብረሃይሉ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት ተገምግሟል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በሐረር ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።

ይህም ዜጎቹ የወንጀል መንስኤና የትራፊክ አደጋ ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና የዜጎችን ጉዳትና ተጋላጭነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመናን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ማህበረሰብም እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ እንዲያጎለብት ግንዛቤ የማስፋት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አመላክተዋል።

አስፈጻሚ ተቋማትም የወጣው ደንብ በአግባብ አውቀው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍም አቅም የሌላቸው ዜጎችን የመደገፍና ማብቃት ስራን መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ ማንሳታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘገባ አመልክቷል።

ማህበረሰብም የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

03 / 10 / 2016

10/06/2024

ቴክኖሎጂን በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች መጠቀም ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብን ማሳደግ የሀገር እድገትን ለማፋጠን አስፈላጊ ነው ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ፎዚያ አሚን ገለፁ ፡፡
****************
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ፎዚያ አሚን ከሀረሪ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሀገሪቷ ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በጤና በግብርና በፀጥታ ዘርፍና ሌሎችንም በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ አቅም እንድትጠነክር እያደረጉ ያሉት ጥረት ከፍተኛ መነሳሳት የፈጠረ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ ስራ መስኮች ቴክኖሎጂን መጠቀም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ፋይዳ አለው ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ ህብረተሰቡም ቴክኖሎጂ የመጠቀም ልምዱ ጠንክሮ የተሻለ ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እድገት እስከ ሰው ሰራሽ አስተውሎት መጠቀም መድረሱን የገለፁት ሚኒስትር ድኤታዋ ይህ በትኩረት ከሰራንበት ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ቱራ አያና
3/10/2016

10/06/2024
10/06/2024

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ra,uuf posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share