05/05/2024
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በክርስትና አስተምሮት በክርስቶስ ትንሳኤ ጥላቻ በፍቅር፣ ጨለማ በብርሃን፣ ልዩትነት በአብሮነት ድል ተነስተዋል፤ ሁላችንም ኢትዮጵያዊ አንድነታችንንና ህብረታችንን የሚሸረሽሩ አጀንዳዎችን፣ ጉስቁልናን እና ድህነትን ድል በመንሳት ህብረ ብሔራዊ አብሮነታችንን እና አንድነታችንን ከፍ በማድረግ በዓሉን ልናከብር ይገባል።
በዓሉንም እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ በህብረት ልናከብር ይገባል፡፡
መልካም የትንሰኤ በዓል!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ