Bench Media Network -BMN

  • Home
  • Bench Media Network -BMN

Bench Media Network -BMN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bench Media Network -BMN, Media/News Company, .

ወጣት ምሁር ዶክተር ተክሌማርያም እርገት እንኳን ደስ አለህ።በተማረከዎ ትምህርት ህዝብህን እና ሀገርህን በስፋት ለመገለል መማር ትልቁ ቁልፍ ነው።እንኳን ለዚህ ሰኬት አደረስህ።
16/06/2024

ወጣት ምሁር ዶክተር ተክሌማርያም እርገት እንኳን ደስ አለህ።በተማረከዎ ትምህርት ህዝብህን እና ሀገርህን በስፋት ለመገለል መማር ትልቁ ቁልፍ ነው።እንኳን ለዚህ ሰኬት አደረስህ።

13/06/2024

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! Moka Jesus, Kifle Woldetsadik, Mastewal Tsegaye Mammo, Kinfe Hailu, Tinsaye Aberham, Abraraw Chale, Lij Aklilu Yosef, Tamerat Alemayehu Adello Kocha, ይዳቅ ወዳጆ, Milkias Demise Galileo, Mitiku Mohammed Zeleke, Assefa Wodajo Gontet, Dawit Wasihun Turiyat, Banchayhu Turjum, Kel Zewede, ዘብድዮስ አብርሃም, Sadenur Abdulkader, Yohannes Melaku, Andinet H. Mariam, Kenubesh Kero, Qaroo Qaroo Keessa ED, Aklilu Beyene

በኢፌዲሪ ጤና  ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ ዶ/ር  ደረጀ ዱጉማ የተመራ የጤና ልዑካን  ሚዛን አማን ከተማ ገቡ።ልዑኩን የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች   ተቀብለዋቸዋል ። ነገ በሚኖራቸው  ...
13/06/2024

በኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የጤና ልዑካን ሚዛን አማን ከተማ ገቡ።

ልዑኩን የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተቀብለዋቸዋል ።

ነገ በሚኖራቸው ቆይታ ሀገር አቀፍ የወባ ወረርሽኝ የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን የሚካሄድ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቤንች ሸኮ ዞን ወባ በሽታ የቡዙ ሰዎች ሕይወት እየቀጠፉ ነው።በቤንች ሸኮ ዞን በሁሉም ወረዳዎች እና በአጎራባች ዞንዎች የወባ ወረርሽኝ የአከባቢው መንግሰት መቆጣጠር አልቻለም ።ዛሬ ዛሬ በ...
13/06/2024

በቤንች ሸኮ ዞን ወባ በሽታ የቡዙ ሰዎች ሕይወት እየቀጠፉ ነው።

በቤንች ሸኮ ዞን በሁሉም ወረዳዎች እና በአጎራባች ዞንዎች የወባ ወረርሽኝ የአከባቢው መንግሰት መቆጣጠር አልቻለም ።ዛሬ ዛሬ በቀን በወባ በሽታ የምሞተው የማህበረሰብ ቁጥር አስደንጋጭ ነው።በዚህ ወቅት አንድ ሰው ብያንስ በሳምንት ውስጥ ሶስት ጊዜ ይታመማል ገንዘብ ያለው ሶስት ጊዜ ይተከማለ።ገንዘብ የሌለው እቤቱ ተኝቶ እየሞተ ነው።

ጉዳዩን እጅግ በጣም አስደንጋጭ የሚያደረገው የገጠሩ ማህበረሰብ ጎረቤቶች በበሽታው ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ በመደዳ እያለቁ በመሆነ አብዛኞቹ አካበቢውን ጥሎ ጠፍቷል ። የከተማ ማህበረሰብ ጉዳዩ ከምችለው በላይ ሰለሆነ ወደ ማን አቤት ይባላል በማለት አልጋቸው ላይ ተጋድሞ ተኝቷል።በአሁኑ ወቅት የትኛኝም የመንግሰት ሆስፒታል ;ጤና ጣቢያዎች እና የግል ክልሊንኮች በጣም ተጫናንቋል።በለፉት ሁለት አመታት ብቻ እጅግ በጣም ቡዙ ወላድ እናት በወባ ሕይወቷ ማለፍ አልፏል ።

በጣም ቡዙ አባት እና እናቶች በዚህ ሁለት አማታት ብቻ የሞቱት የህዝብ ቀጥሩ ባለፈው 10 አመታት የወባ በሽታ እና ሌሎችን ጨምሮ ከሞቱት ይለቅ በዚህ ሁለት አመታት ብቻ በወባ በሽታ የሞቱት ቁጥር አስደንጋጭ ነው።ቡዙ እናቶች;ብዙ ህጻነት;ትላልቅ አባቶች ተጠራርገው አልቋል ።
BMN

ከ250 ሚሊየን ዶላር በላይ በኾነ ወጭ  2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ። በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴር እ...
12/06/2024

ከ250 ሚሊየን ዶላር በላይ በኾነ ወጭ 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ።

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ሦስት ተቋማት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የጤና ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እና የሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ተወካዮች ፈርመውታል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በሥምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይና 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ማዕከላቱ በዋናነት በእናቶች እና ሕጻናት ጤና፣ በአረጋውያን፣ በወጣቶች እንዲሁም በወሊድ፣ በክትባት፣ በቤተሰበ እቅድ እና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተጠቁሟል።

ይኽም ለማኅበረሰቡ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ነው ያሉት።

የሚገነቡት የጤና ማዕከላት እያንዳንዳቸው ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ የሚጠጉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

ማዕከላቱን ለመገንባት ከ250 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደሚወጣ እና ወጪውም በሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የሚሸፈን መኾኑን ጠቁመዋል።

የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው ሥምምነቱ የእናቶችን ብሎም የህፃናትን ጤና ለመጠበቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
በመኾኑም ሚኒስቴሩ ለፕሮጀክቱ እውን መኾን የሚጠበቅበትን ሚና ይጫወታል ነው ያሉት።

የሩስያ የፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት ግብረ-ሰናይ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦክሳና ማዮሮቫ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የዜጎችን ጤናማ ሕይዎት ለማስጠበቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ይህን ፕሮጀክት ወደ ሀገሪቱ እንዲመጣ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ እውን መኾኑን የገለጹት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ (ዶ.ር) ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

BMN-Mizan

12/06/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Kedir Mersha Tesfaye, ይዳቅ ወዳጆ, Tinsaye Aberham, Mudesir Yasin, ጌታ ያዳነው ሰው, Moka Jesus

08/06/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Qaroo Qaroo Keessa ED, Biruk Abdisa, Adama Tinpaye, Kassahun Maleto

የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ እድገት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።የደቡብ  ም...
06/06/2024

የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ እድገት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።

የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ጸጋዬ ማሞ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት የቤንች ብሔር ቋንቋና ባህል እንዳይታወቅ ሲደረግ ቢቆይም ከለውጡ ወዲህ በርካታ አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ገለፀዋል፡፡

ለረጅም ዓመት ተቋርጦ የቆየው የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓልን ዳግም በተደራጀ መንገድ ለማክበር እንቅስቃሴ መጀመሩም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በዓሉን መሰረት ያደረገ የቤንች ብሔር የቋንቋና ባህል ፓናል ውይይት መደረጉም የብሔሩን ቋንቋና ባህል ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው የተለያዩ የአለም ሀገራት የዘመን መለወጫ በዓል እንዳላቸው ገልፀዋል።

አክለውም የቤንች ብሔር ለረዥም አመታት ተቋርጦ የቆየውን በዓል ለማክበር ሰፊ ስራዎች መሠራታቸውን ገልፀው የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ እንዲያድግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

የቤንች ህዝብ ዞኖችና ወረዳዎች ከሚገኙ ህዝቦች ጋር ተዋድዶ ፣ ተፋቅሮ ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ እየኖረ ያለ ህዝብ ነው ብለዋል።

ይህንን ወንድማማችነትን በማጠናከር የተጀመረው ለውጥ እናስቀጥላለን ብለዋል።

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ባህልን ከፍ አድርጎ በማክበር በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ብሎም የቱሪሰቶች በዓሉን መጥተው እንዲያከብሩ ለማስቻል በጋራ እንሰራለንም ነው ያሉት።

የቤንች ብሄር ባህልና ቋንቋ ላይ ያተኮረ ለፓናል ውይይት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ መምህር እጪ ዶክተር ትዕዛዙ አቱሞ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ሜርቴት ሻሽየመር ቲያት / ንጉስ /  መልዕክት                        እንኳን ለመጀመሪያ ግዘ በዞን ደረጃ በድምቀት ለሚከበረዉ የቤንች ብሄረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን ...
05/06/2024

ሜርቴት ሻሽ
የመር ቲያት / ንጉስ / መልዕክት

እንኳን ለመጀመሪያ ግዘ በዞን ደረጃ በድምቀት ለሚከበረዉ የቤንች ብሄረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን የ " ቢስት ባር " አደረሳችሁ ! አደረሰን ለማለት እወዳለሁ ።

የቤንች ብሄረሰብ በልዩ ዝግጅትና በድምቀት ከሚያከብራቸዉ 3 ትላልቅ በዓላቶች መካከል አንዱና የጥጋብ ፣ የተስፋ እና የበረከት ተምሳለት እንድሁም የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን የሆነዉ የ " ቢስት ባር " በዞናችን በታላቅ ድምቀት የብሄረሰቡ ባላባቶች እና ተወላጆች ባሉበት ቦታ ታርካዊ ይዘቱን ጠብቆ በመከበሩ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ ።

" ቢስት ባር " ማለት የእህል ወቅትን ተከትሎ በአካባቢዉ አባቶች የበኩር / የመጀመሪያው እሼት የሚቀመስበት ሪሃብና ድርቅ እንድሁም በሽታ ከአካባቢዉ እንድጠፋ አባቶች ተሰብስበዉ የሚመርቁበት ፤ ለፈጣር ምስጋና የሚቸርበት ባህላዊ ሥርዓት ነዉ ።

በዓሉም ( ቢስት ባር ) በቲያት/ በባላባቶች ምርቃት የሚመራ ሥሆን በዕለቱም የእርድ ሥርዓትን በማከናዉን ቦርዴ ተጠምቆ ከጎሳ መርዎች በመጀመር የመብላትና የመጠጣት ሂደቱ ከተከናወነ ቦኃላ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በጨረቃ ብርሃን በደሥታ ይጨፍራሉ ።

" ቢስት ባር " ከጥንት ጀምሮ ቤንቾች በድምቀት የሚያከብሩትና የማንነታቸዉ መገለጫና መድመቅያቸዉ ሥሆን በዓሉም ከመንግስታት የሥርዓት መቀያየር ጋር ተያይዞ የነበረዉ ፖለቲካ ምህዳር የብሄረሰቡ ተወላጆች በአደባባይ ወጥቶ በዓላቸዉን እንዳያከብሩ ጫና ማሳደሩንና በዝህም ለረዥም ግዜ በዓሉ ሳይከበር ተቋርጦ መቆየቱንና አሁን የተፈጠረዉ የለዉጥ ህደትን ተከትሎ ብሄረሰቡ በዓላቸዉን በአደባባይ እንድናከብር ታርካችንና ማንነታችንን በአደባባይ እንድናከብር ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ።

ስለሆነም ይህንን በዓል ለመጀመሪያ ግዜ የአካባቢው ቲያቶች/ ባላባቶች እንድሁም የሃገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች በአብሮነትና በታላቅ ድምቀት አክብረዉት ሳይ ሂደቱን ለመሩት የአካባቢዉ አመራሮች ምስጋና አቀርባለሁ ።

" ቢስት ባር " አንድ ግዜ አክብረን የምንተወው ሳይሆን በአሉን ቀጣይ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ቃላችንን ዳግም የሚናድስበት ፤ በቀጣይ ባህላችንና ታርካችንን ለማሳደግ በአንድነት የምንቆምበት እንድሆን እየጠየኩኝ በዓሉ የፍቅር የሰላምና የደስታ እንድሁም ዘመኑ የጥጋብና የበረከት ቸነፈርና በሽታ ከአካባቢው የሚጠፋበት እንድሆን በራሴና በህዝቤ ስም ምኞቴን እገልፃለሁ ።

የቤንችቲያት  /ንጉስ/ መልዕክት እንኳን ለ "ቢስት ባር " የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን በሠላም አደረሳችሁ ! አደረሰን !የቤንች ብሄረሰብ ከጥንት ጀምሮ ማንነቱን የሚገልፅበ...
05/06/2024

የቤንችቲያት /ንጉስ/ መልዕክት
እንኳን ለ "ቢስት ባር " የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን በሠላም አደረሳችሁ ! አደረሰን !

የቤንች ብሄረሰብ ከጥንት ጀምሮ ማንነቱን የሚገልፅበት የራሱ የንግስና ሥርዓት እና አስተዳደራዊ እንድሁም የራሱ ባህላዊ የኪነ-ጥበብ እዉቀት አለዉ፡፡

"ቢስት ባር" ከብሄረሰቡ ባህላዊ ዕዉቀቶች አንዱ ስሆን የክረምት ወራት አልፎ አዝመራ (እሸት) በሚደርስበት ወይም ማር የሚቆረጥበትን ወቅት ተከትሎ የእርድ ስርዓቱ ከተፈጸመ በኋላ ታላላቆችን / አባቶችን በማስቀደም የመቅመስ ፤ በጋራ የመብላትና የመጠጣት እንድሁም ፈጣር የሚመሰግንበት በዓል ነው ።

የ "ቢስት ባር" በቲያቶ / በንጉሱ መርነት የአካባቢው አባቶችና የጎሳ መርዎች በተሰባሰቡበት ቦታ የሚከበር ስሆን በዕለቱም ያመረተው ብቻ ሳይሆን መንገደኛ ሁሉ ከተዘጋጀው እሸት የሚቀምስበትና አብሮነት የሚገለፅበት ፣ ታላላቆችን ማክበርና በጋራ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ታላቅ ባህላዊ ክዋኔ ነዉ ።
በቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል (ቢስት ባር) የተጣላ የሚታረቅበት ፣ የበደለ የሚክስበት ፣ ክፉዉ ነገር ተወግዶ ማህበረሰቡ ሠላሙ የሚጠበቅበት ነው።

"ቢስት ባር " ማለት በኩር ወይም የመጀመሪያ ማለት ስሆን በበዓሉ የሚሳተፉ ሰዎችም የመጀመርያዉን ወይም የእህልን በኩር በመቅመስ ወደ ህዝቡ ሊተላለፉ የሚችሉትን እርግማኖችን ለማስወገድና በረከት እንዲገኝ ምርቃት የሚደረግበት ከዘመን ዘመን መሸጋገሪያም ነዉ ።
ይህን በዓል አያቶችና አባቶቻችን በድምቀት ሲያከብሩና ከትውልድ ወደ ትውልድ እያሻገሩ ለበርካታ ዘመናት እያከበሩት የመጡና ከተወሰኑ አመታት በፊት ተቋርጦ የቆየ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይ መንግስት ፣ የብሔሩ ተወላጆች እና የዞኑ ነዋሪዎች በድምቀት ሊያከብሩና ተቋርጦ የነበረውን ሊያስቀጥሉ መሆኑን ስሰማ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።

ከምንም በላይ ሞት ሳይቀድመኝ "ቢስት ባር" ሲከበር በማየቴና በዓሉ ላይ ለመታደም በመብቃቴ በጣም ደስ ብሎኛል። እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓላችን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በዓሉ የሠላም ፣ የብልጽግና ፣ የመተባበርና ሕዝባችን ከሚመጣዉ መቅሰፍት የሚጠበቅበት አመት ፈጣር ያድርግልን ። ይህን ላዘጋጁ አካላትም በራሴና በህዝቤ ስም ምስጋና አቀርባለሁ ።

  Bist Bareshn Yint Hatsasise!እንኳን አደረሳችሁ
05/06/2024

Bist Bareshn Yint Hatsasise!
እንኳን አደረሳችሁ

መልካም የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] ! Digám Benć Bíst  Báreśhn Yínť  Hátsaśise !የ [ ቢስ ባር ] ቅድመ ዝግጅት ፤ የኮምትኬስ ካርጉ ምድር !
05/06/2024

መልካም የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] !

Digám Benć Bíst Báreśhn Yínť Hátsaśise !

የ [ ቢስ ባር ] ቅድመ ዝግጅት ፤ የኮምትኬስ ካርጉ ምድር !

የህዝብ ዩኒቨርስቲ ,ከህዝብ እና ለህዘብ የሆነው የቦንጋ  ዩኒቨርስቲ  እንኳን ለቤንች በሔር ለዘመን መለወጫ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብሏል።
04/06/2024

የህዝብ ዩኒቨርስቲ ,ከህዝብ እና ለህዘብ የሆነው የቦንጋ ዩኒቨርስቲ እንኳን ለቤንች በሔር ለዘመን መለወጫ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብሏል።

እንኳን ለቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] በዓል በሰላም አደረሰን ፤  አደረሳችሁ  ወጣት ተማሪ ማስተዋል ጸጋዬ ማሞ ከሩቅ ምስራቅ ! ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የ 5,0...
04/06/2024

እንኳን ለቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ

ወጣት ተማሪ ማስተዋል ጸጋዬ ማሞ ከሩቅ ምስራቅ !

ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የ 5,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

Digám Benć Bíst Báreśhn Yínť Hátsaśise !

ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" ድጋፍ አድርገዋል። ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" እንኳን አ...
04/06/2024

ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" ድጋፍ አድርገዋል።

ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" እንኳን አደረሳችሁ በማለት የ10 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልሉ ባህል አድገት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ለቤንች ብሄር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" በሰላም አደረሳችሁ ብለው የ10 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ስላደረጋችሁት ድጋፍ በህዝባችን ስም እናመሠግናለን ቢስት ባርን አንድ ላይ በጋራ ሆነን እናከብራለን።

የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ''ቢስት ባር'' በአንድነት ለማክበር በተጀመረው ሥራ ድጋፍ ቀጥሏል።

Digam Bist Bareshn Yint Hatsasise!
እንኳን አደረሳችሁ አካውንት ቁጥር ንግድ ባንክ:- 1000628020047
Swift Code:- CBETETAA

ኢሳ ሜር ትያት
04/06/2024

ኢሳ ሜር ትያት

የካፋ ልማት ማህበር ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።የከፋ ልማት ማህበር እንኳን ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] በሰላም አደረሳችሁ በ...
04/06/2024

የካፋ ልማት ማህበር ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የከፋ ልማት ማህበር እንኳን ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ [ ቢስት ባር ] በሰላም አደረሳችሁ በማለት የ30
ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓዋል።

የቤንች ህዝብ ለዘመናት ከወንድሙ ካፋ ህዝብ ጋር የተቆራኘ ህዝብ ነው። ይህንን የዘለቀ ወንድማማችነት በባህላችን ይጠናከራል።

ስላደረጋችሁት ድጋፍ በህዝባችን ስም እናመሠግናለን ቢስት ባርን አንድ ላይ በጋራ ሆነን እናከብራለን።

እንኳን ለቢስት ባር በሰላም አደረሰን ።
03/06/2024

እንኳን ለቢስት ባር በሰላም አደረሰን ።

31/05/2024

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ስርዓት እንዲዘረጋ ወሰነ

የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ሲፈልጉ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት አልነበረም። ምክር ቤቱ ውሳኔው ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

31/05/2024

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! ሀብታሙ አየሌ, Kinfe Hailu, Daniel Marnanis

የቤንች  ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን ፤ በዓል የሚከበርበት የቦታ እና የቅድመ ዝግጅት ፤  ሥራዎችን ምልከታ ፤  የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና ሌሎች የአብይ ኮምቴ አባላት የተገኙበት ...
31/05/2024

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን ፤ በዓል የሚከበርበት የቦታ እና የቅድመ ዝግጅት ፤ ሥራዎችን ምልከታ ፤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና ሌሎች የአብይ ኮምቴ አባላት የተገኙበት ጉብኝት በዣዥ ለይ እያደረጉ ነው።

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን ፤ በዓልን ከግንቦት 30 ጀምሮ የብሔሩ መነሻ በሆነችው ሼይ ቤንች ወረዳ ዣዥ ቀበሌ ጋስ ለማክበር በርካታ የቅድመ ፤ ዝግጅት ሥራ እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም በዓሉን ባህላዊ ይዘቱንና ሥርዓቱን አስጠብቆ ለማክበር በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ሂደቱ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተደርጓል።

በምልከታቸው የጥንት የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን በዓል የሚከበርበት ቦታና ይዞታን ከነ ቅርሱ ጠብቆ ያቆዩትን አመስግነው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መልካም መሆናቸውን ገልጿል።

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን [ ቢስት ባር ]  ባህላዊ መገለጫው  ከሆኑት የባህል  ምግቦችና መጠጦች ።ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ ና የምስጋና  ቀን በዓል  የባህላዊ መጠ...
30/05/2024

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን [ ቢስት ባር ] ባህላዊ መገለጫው ከሆኑት የባህል ምግቦችና መጠጦች ።

ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ ና የምስጋና ቀን በዓል የባህላዊ መጠጥ የበቆሎ ቦርዴ የሚሆን የበቆሎ ቂጣ (ጢልቡድ) ዝግጅት ተጀምሯል።

ከደቡብ ቤንች ወረዳ ከቂጤ አካባቢ የተውጣጡ ከ60 በላይ የባህላዊ ምግብ አዘጋጅ እናቶች የበቆሎ ቂጣ (ጢል ቡድ) በባህላዊ ጭፈራ ታጅበው እያዘጋጁ ነው።

ለቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ''ቢስት ባር'' በዓል አከባበር የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ  በማድረጌ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ ነኝ / አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ /ቢር...
29/05/2024

ለቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ''ቢስት ባር'' በዓል አከባበር የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በማድረጌ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ ነኝ / አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ /

ቢር ፦ 21/2016 በሰሜን ቤንች ወረዳ በዳክን ቀበሌ መሀል ካሽማር መንደር ነዋሪ የሆኑት አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ / ለቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ''ቢስት ባር'' በዓል አከባበር የሚሆን አንድ በሬ ድጋፍ አድርጋል፡፡

አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ / እንዳሉት ባለፉት ጊዜያት በአመራሩ ፣ በምሁራን ፣ በሀገር ሽማግሌዎች ደረጃ በተለያዩ ጊዜያት መድረኮች መካሄዳቸው በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ / በአሉ መከበሩ ከምንም በላይ እንዳስደሰታቸው ተናግረው የብሔረሰቡን የዘመን መለወጫ በዓል ለማክበር ባህሉን ለትውልድ ለማሻገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ በማድረግ ድጋፋቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

"ቢስት ባር" በዞኑ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ መከበሩ መጠን ልዩ ትኩረትና ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አሰፋ ጃምቴት /ባርጊናስ / ዘንድሮ በወካይ ቀን ተከብሮ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ በበዓሉ መደበኛ ቀን ለሚከበረው "ቢስት ባር" አሁን ከሰጡት ድጋፍ በተጨማሪ በራቸው ሁልጊዜ ክፍት መሆኑን ና ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

Digam Bist Bareshn Yint Hatsasise!
እንኳን አደረሳችሁ

የሰሜን ቤንች መንግስት ኮምኒኬሽን

የቢስት ባር (የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል) መለያ ምልክት የሆነው  የቤንች ነገስታት የጥንትት  የንግስና ዘውድ ትርጉሞች1ኛ: የዘውዱ  ትርጉም : -  ዘውድ  (Crown) በ...
25/05/2024

የቢስት ባር (የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል) መለያ ምልክት የሆነው የቤንች ነገስታት የጥንትት የንግስና ዘውድ ትርጉሞች

1ኛ: የዘውዱ ትርጉም : - ዘውድ (Crown) በዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ የንግስና ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የቤንች ህዝብም ለየት ያለ የራሱ የሆነ ገፅታ ያለው ለነገስታት የሚጠቀምበት ዘውድ (Crown) መኖሩን የሚያሳይ ሲሆን ከዘውድነት አልፎ የቤንች ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የራሱ አስተዳደራዊ ስርዓት እና ንጉስ ያለው መሆኑን የሚያሳያረጋግጥ ነው።

2ኛ) ከዘውዱ ፊትለፍት ካለው ገፅታ ከስር ቀጥ ብሎ የሚነሳውና አንድ ወፍራም ዘንግ ሆኖ ጫፉ ላይ ለሶስት ተከፍለው የሚታየው የተሾሉ ጦሮች ያሉበት ዋና ግንድ የሆነው ዘንግ ትርጉምን በተመለከተ:-

ከስር አንድ እና ወፍራም ቀጥ ብሎ የወጣው ዋናው ግንድ (ዘንግ) መላው የቤንች ህዝብ ምንጩ ከአንድ አባት ተወልደው የሰፉ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ የሚያሳይ ልዩ መገለጫ ነው።

3ኛ) ከዋናው ግንድ ላይ በቅለው የወጡ ሶስቱ ቅርንጫፎች ትርጉም:-
ከአንድ አባት ተወልደው በሶስት ዋና ዋና ግዛቶች የተከፋፈሉ ሶስቱን የቤንች ነገዶች (ማለትም ሜር፣ሼይ እና ቤንች ከነ ነገስታታቸው ሜርቴት፣ ሼይቴት እና ቤንችቴትን ) የሚወክል ሲሆን ሶስቱ ቅርንጫፎች የአንድ ግንድ ቅርንጫፎች እንደሆኑና የተሾለ የጦር ቅርፅ ያለቻው የሶስቱ ቅርንጫፎች ጫፎች የሚወክለው ሶስት ጦሮችን ነው። ሶስቱ ጦሮች የቤንች ህዝብ ጀግና እና ባህልና ወጉን በጀግንነቱ በጦሩ ጠብቆ ያቆየ ህዝብ መሆኑን ያሳያል።

4ኛ) የጦሩ መሰረት ደጋፊ ሆኖ የተቀመጠው ክቡ ነገር:-
ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የቤንች የጥንት የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ልዩ ጥበብ መገለጫ ሲሆን በዋናነት ሁሉም ነገስታት የሚጠቀሙት የመናገሻ ወይም ቤተመንግስት ጊቢ በር (በብሄሩ ቋንቋ ፖርት(Port) በመባል የሚታወቀው) የነገስታት ጊቢ መጊቢያና መውጫ በር ዲዛይን ነው። ይህም ቤንች ከጥንት ጀምሮ የራሱ የሆነ ባህላዊ ልዩ ኪነጥበብ እንደነበረው የሚያሳይ ነው።

5ኛ) ከነገስታቱ የክብር ዘውድ ጎን የተሰካኩ ላባዎች ( ፒህ):-
በባህሉ መሰረት የነገስታት ዘውድ የሚጌጥበትና ለንግስና የተመረጠ ልዩ ሰው ብቻ የሚያደርገው ሲሆን በአንዳንድ የብሄሩ ዋና ዋና የነገድ አካባቢዎች በዓይነቷ ለየት ያለች ረዥም ላባ ያላት "ዛይፕ" የሚትባል ወፍ ዝርያ ላባ እና የአውራ ዶሮም ረዥም ላባ ጥቅም ላይ እንደሚውል ለማሳየት ነው። ላባ ልዩ የንግስና ምልክት ሲሆን አምበር (ዱም) ስልጣንና ኃይል ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው መተላለፉን የሚያረጋግጥ ምልክት ነው።

6ኛ) ዋናውን የጦር ግንድ በግራና ቀኝ አቅፎ የያዘው ክብ መሳይ ቅርፅ:-

ዱም (ወይም በእጅ የሚጠለቅ አምበር) ቅርፅን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በቤንች ስርወመንግስት ነገስታት የስልጣን ሽግግርን ለተመረጠ ልጃቸው የሚያሸጋግሩበት ልዩ ምልክት ሲሆን ነገስታቱ በህይወት እያሉ (ከመሞታቸው በፊት) ለቀጣይ ስልጣን ተረካቢ ማረጋገጫ እንዲሆን በእጃቸው ክንድ የሚያጠልቁት ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ልዩ የስልጣንና ኃይል ሽግግር ምልክት እና ለንግስና በተለዩ ንጉሳዊ ጎሳዎች እና ቤተሰቦች ብቻ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ የሚቀጥል መሆኑን የሚያረጋግጥ ልዩ ምልክት ነው።

7ኛ) ከዱም (አምበር) ወይም ክቡ የነገስታት ቤተመንግስት ጊቢ መግቢያ በር ግራና ቀኝ ያሉ ሁለቱ ቀስቶች በቤንች ብሄር "ዳይ" በመባል የሚታወቁ ሲሆኑ በህዝቡ ላይ የሚመጣውን የባዕድ ኃይልን ከመመከት አልፎ ጠላትን ለማጥቃት እና የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የነገስታቱን ዙፋን ለማስጠበቅ ሲዋጉበት የነበረው ልዩ ባህላዊ የጦር መሳሪያቸው ነው።

8ኛ) የክቡ አምበር (ዱም ) እና ሁለቱ ቀስቶች ውህደት የነገስታቱን ዙፋን ቅርፅ የሚያሳይ ሲሆኑ ሶስቱ የቤንች ነገስታት ስርወመንግስት (ማለትም ቤንችቴት፣ ሜርቴት እና ሼይቴት ) ከትውልድ ትውልድ የጎሳ መስመሩን (ማለትም ባይኬስ፣ ዛንግንድ እና ኮይንኬስ መስመርን) ጠብቆ ከቤተሰብ ቤተሰብ የሚሸጋገርበትረ -ስልጣንና ዙፋንን የሚወኪል ነው።

9ኛ) ከዘውዱ ዙሪያ ያሸበረቁ ቀለማት የቤንች እናቶችና ልጃገረዶች በነገስታት ንግስና ወቅት፣ በጋቢቻ/ሰርግ/ ወቅት እና በዓመት በዓላት ወቅት የቤቶቻቸውን ዙሪያ የሚያስዋቡበት ልዪ የጋራ መገለጫ (በብሄሩ "ጎይግን" በመባል የሚታወቅ) ሲሆን ቀለማቱም:- ሐምራዊ(ቦይ)፣ ቡኒና አርንጓዴ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያሉ የቤንች ብሔር ብሄራዊ ምልክት በመሆን በባህል አልባሳት ላይ የሚታተሙ መለያ ቀለማት ናቸው ።

10ኛ) አርንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ህብረ ቀለማት ትርጉም በአሁኑ ሰዓት የሀገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቀለማት ሆኖ እያገለገሉ ያሉና የፓን አፍሪካ ልዩ ምልክት ሆኖ ያሉ ከመሆናቸውም ባሻገር የአፍርካዊያንም ኩራት ምንጭ ሲሆን የቤንች ህዝብም አንዱ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት ታሪክ አካል መሆኑን የሚገልፅ ነው።

(ካናንስ)

እስክ አሰታያታችሁን አክሉበት
25/05/2024

እስክ አሰታያታችሁን አክሉበት

ኢንጂነር ፍቅሩ ገብሬ ሳይማሩ ላሰተማሩህ ማህበረሰብ እያደርክ ላሌው ተግባር ትልቅ ምስጋና ይገባሃል።ይህንን የህዝብ መገለጫ የሆነውን ሎጓ ሰረትህ ለዚህ ታላቅ ህዝብ ለደረከው ህዝቡ ያመሰገናሀ...
25/05/2024

ኢንጂነር ፍቅሩ ገብሬ

ሳይማሩ ላሰተማሩህ ማህበረሰብ እያደርክ ላሌው ተግባር ትልቅ ምስጋና ይገባሃል።ይህንን የህዝብ መገለጫ የሆነውን ሎጓ ሰረትህ ለዚህ ታላቅ ህዝብ ለደረከው ህዝቡ ያመሰገናሀል

25/05/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tizazu Mersha, Yeredanos Shifraw

የብና እና ቅመማ ቅማም ማዕከል በቤንች ሸኮ ዞን ለመከፈት እቅድ መኖሩን የዞኑ ግብርናና መምሪያ ኃላፊ አስታወቀ ።የኢትዮጵያ የብና እና ሻይ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይርክተር ዶክተር አዱኝ ቤንች ...
22/05/2024

የብና እና ቅመማ ቅማም ማዕከል በቤንች ሸኮ ዞን ለመከፈት እቅድ መኖሩን የዞኑ ግብርናና መምሪያ ኃላፊ አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ የብና እና ሻይ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይርክተር ዶክተር አዱኝ ቤንች ሸኮ ዞን በክልሉ ትልቁ የብና ምሪት አቅራቢ መሆኑን ገልጾ የክልሉ መንግስት ድጋፍ የሚያደርግ ከሆነ በፍጥነት የማዕከል ግንባታ መገንባት እንደሚቻል ገልጾአል ።

የዞኑ እና የክልሉሉ አመራሮችም ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።

እንኳን አደረሳችሁ ብሏል የHA electronics ባለቤት አቶ አሊ መሀመድአቶ አሊ መሀመድ በሚዛን አማን ከተማ ኮሶኮል ህንፃ ፊት ለፊት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እያስመጣ በተመጣጣ...
19/05/2024

እንኳን አደረሳችሁ ብሏል የHA electronics ባለቤት አቶ አሊ መሀመድ

አቶ አሊ መሀመድ በሚዛን አማን ከተማ ኮሶኮል ህንፃ ፊት ለፊት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እያስመጣ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸጥ የከተማችን ድንቅ ወጣት ነጋዴ ነው።የልጅ አዋቅ!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Media Network -BMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share