Tikus zena ትኩስ ዜና

  • Home
  • Tikus zena ትኩስ ዜና

Tikus zena ትኩስ ዜና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tikus zena ትኩስ ዜና, Digital creator, .

06/05/2024

መላው የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሰን ፣ አደረሳችሁ ።

የክርስትና አስተምህሮት እንደሚያስረዳን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ህይወቱን የሰጠው ስለ ሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ነዉ። እኛም አርዓያውን ተከትለን በፍቅር እንድንኖር እና መስጠትን የህይወታችን አካል እንድናደርግ ነው ።

ስለሆነም የፋሲካ በዓል የመስዋዕትነት፣የይቅርታ ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ነው።

በመሆኑም ይህን ታላቅ ሐይማኖታዊ በዓል ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም የአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ጥሪ አቀርባለሁ ።ንፁህ ሆነን እንደተፈጠርነው ሁሉ በንፅህናና በቅንነት መኖር እና ህዝባችንን ከልብ ማገልገል ይጠበቅብናል።

በድጋሚ መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ።

አቶ መገርሳ ገላና
በብልፅግና ፓርቲ የየካ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

በመንገድ ኮሪደር ልማት የተነሱ ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ቤት እንዳገኙ ገለጹ።ሚያዝያ 13/2016ዓ.ም የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ስ...
21/04/2024

በመንገድ ኮሪደር ልማት የተነሱ ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ቤት እንዳገኙ ገለጹ።

ሚያዝያ 13/2016ዓ.ም የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ስራ የተነሱ ነዋሪዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ የምልከታ ጉብኝት በአስተዳደሩ ተደርጓል።

የልማት ተነሺዎች በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በፈረንሳይ እና ጉራራ እንደየ ምርጫቸው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ መደረጉ በጉብኝቱ ተመላክቷል፡፡

በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 04 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እሱባለው መንደዶ የልማት ተነሺዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ካሉ በቅርበት ለመፍታት አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን በመግለፅ ነዋሪዎቹ አሁን ባሉበት አካባቢ ማንኛውንም አገልግሎት በየካ ወረዳ 2 አስተዳደር በኩል ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል ።

የወረዳው የዲሞክራሲ ሰረዓተ ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፉ ክንዴ ነዋሪው እንደ ከተማ እየተከናወነ ላለው የኮሪደር ልማት ስራ ቁርጠኛ መሆኑ ያስመሰግነዋል ብለዋል፡፡

የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ሙሉነህ ሲሳይ መንግስት አካባቢ ሲያለማ ነዋሪውንም አብሮ እያለማ መሆኑ በዚህ ጉብኝት ማረጋገጥ ችለናል በማለት የሚያጋጥሙ ጥቃቅን ችግሮችም ከአመራሩ ጋር በቅርበት በመስራት እየተፈቱ መሆኑን ተናግረዋል።

የልማት ተነሺዎቹ አሁን ያሉበት መኖሪያ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ በመሆኑ አስተዳደሩ ለነዋሪው የገባውን ቃል በፍጥነት መተግበሩ እንዳስደሰታቸው አስረድተዋል፡፡

መረሃ ግብር ላይ የወረዳው አስተባባሪዎች፤ አመራሮች፤ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲሁም የቀበና አካባቢ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን በጎብኝት ተደርጓል ።

ስራን መገምገም ለተሻለ አፈፃፀም !!ሚያዝያ 08/2016 የካ ወረዳ 04 ፓርቲ ሚዲያበየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፓርቲ ፅ/ቤት ግምገማ ተደረገ በግምገማዉ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ...
16/04/2024

ስራን መገምገም ለተሻለ አፈፃፀም !!

ሚያዝያ 08/2016 የካ ወረዳ 04 ፓርቲ ሚዲያ

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፓርቲ ፅ/ቤት ግምገማ ተደረገ በግምገማዉ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ የክ/ከተማዉ ምክትል አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መለስ ከበደ እንዲሁም የአስራ ሁለቱም ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊዎች በተገኙበት ግምገማዉን አካሂደዋል።
የወረዳ 04 ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፉ ክንዴ የ እንኳን ደህና መጣቹ መልክት ካስተላለፉ ቡሀላ የወረዳዉ የፓርቲ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ተረፈ ምርጥ ተሞክሮ አቅርበዋል በመጨረሻም የክፈለ ከተማዉ የ ፓርቲ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ የቀረበዉ ምርጥ ተሞክሮ ሊበረታታ የሚገባ መሆኑን ጠቁመዉ እና ሌሎችም ወረዳዎች ከዚ ትምህርት መውሰድ አንዳለባቸዉ አሳስበዋል

20/03/2024
ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!  በየካ ወረዳ 4 የብልፅግና ፓርቲ ኮንፍረንሱን"ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል ውይይቱ ቀጥሏል።
17/03/2024

ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!

በየካ ወረዳ 4 የብልፅግና ፓርቲ ኮንፍረንሱን"ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል ውይይቱ ቀጥሏል።

06/02/2024

#ማብራሪያ _1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች ‼

👉 የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ አንኳር ጉዳዮች የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የሚኬድባቸው መንገዶች ችግር ያለባቸው መሆኑ ነው፤

👉 ማንኛውም ችግር ሲያጋጥም ያንን ችግር ለመፍታት በንግግር ለመፍታት ያለን ልምምድ እየቀነሰ መምጣትም ሌላው ችግር ነው፤

👉 ለሰላም ለሚደረግን ጉዞ ወጥመድ የሚቀመጥበት ልምምዱም የሰፋ መሆኑ ሌላ ችግር ነው፤

👉 እነዚህ ችግሮች አብዛኛው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርጎ የሚነሳ አይደለም፤ ቢሆን ኖሮ ለቀይ ባህር እድል ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ባልተቃወሙት ነበር፤

👉 ታንዛኒያ ከሸኔ ጋር የነበረውን ድርድር ስንጀምር ለመላው ህዝብ ነግረን አሳውቀን ሳንደብቅ ነው፤ ውጤቱ ግን ምንም የሚጨበጥ ስላልሆነ ምንም ማለት አልቻልንም፤

👉 ሸኔ በአስመራ በነበረው ድርድር ቃል የተገባው ሳይፈጸም ቀርቶ ከሆነ ጫካ የገባው፤ እታገላለሁ የሚልለትን ህዝብ ማገትና ማሰቃየት ላይ ነው፤ የራስን ህዝብ እያሰቃዩ እታገልልሃለሁ ማለት ዋጋ የለውም፤

👉 ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በጠበንጃ ስልጣን መያዝ አይቻልም፤ የሚቻለው በሰላም በንግግር ነው፤

👉 በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ከከሚሴ በስተቀር ከህዝብ ጋር ለመነጋገር እድል አግኝቻለሁ፤ ጥያቄያቸው የልማት፣ የወሰን ይገባኛል እና የህገ መንግስት ነው፤

👉 በአማራ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 3 ሺህ 200 ኪሎሜትር መንግድ ጀምረነ እየሰራን ነው፤

👉 ይህ መንገድ በክልሉ ውስጥ ዞንን ከዞን ወረዳን ከወረዳ ጋር የሚያገናኝ ነው፤

👉 ይህ መንገድ አንድ ሽሮ ፈሰስ የሚባል አይደለምዐ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ነው፤

👉 ከአማራ ክልል የተነሳውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ መንግስት የሄደበትን ርቀት አመላካች ነው፤ በቂ አይደለም፤

👉 ከመንገድ ባሻገር በቱሪዝም መስክም የጎርጎራ ፕሮጀክት በአይነትና በደረጃው የትም ያልተሰራ ፕሮጀክት ሆኖ እየተሰራ ነው፤

👉 የላሊበላን ቅርስም ለማደስ የፈረንሳይን ፕሬዝዳንት ሳይቀር ይዘን ሄደነ አሳይተነ እያሰራን ነው፤ በሰላም ምክንያት ወጣ ገባ ቢልም፤

👉 ፋሲልንም የፈረሰውን ማስጎብኘት ተገቢ አይደለም ብለን፤ ስራውን ለማስጀመር ሙከራ አድረገነ ነበር፤ ነገር ግን በተለያዩ አሉባልታዎች ስራውን አስቁመውታል፤

ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tikus zena ትኩስ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share