ትኩስ ዜና Tikus Zena Ethiopian news

  • Home
  • ትኩስ ዜና Tikus Zena Ethiopian news

ትኩስ ዜና Tikus Zena Ethiopian news ትኩስ ዜና Tikus zena is Ethiopian Zena or news brocading media from original source only like and follow as.

we do not share and talk lies hate speech and annoying saying too.

22/07/2024

አብዛኛው የተቆራረጠ ነው ግን አወራሩ ብዙ ክፍተት አይፈጥርም እራሱን ጠብቆ ነው የተናገረው :: ( ፍኖ እና የእስክድር ግሩፕ ... ) አስተውለው ያዳምጡ

06/07/2024

ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መታገታቸው ተነገረ።
አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው የተባሉት መንገደኛ በታጣቂዎች የታገቱት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ መሆኑን የዐይን እማኖች እና የታጋች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን 155 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከተፈጸመው እገታ የተወሰኑ ተማሪዎች ሲያመልጡ ሌሎች ደግሞ መለቀቃቸው ተነግሯል።
ተማሪዎቹ መነሻቸውን ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እና ከባሕር ዳር ያደረጉ ሲሆን፣ ሲጓዙባቸው ከነበሩ “ታታ” ከሚባሉ ሦስት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ረቡዕ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም. “ሸኔ” ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች መታገታቸው ተነግሯል።
https://bbc.in/3VVHgDV

20/05/2024
08/04/2024

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆታ በተባለ አካባቢ 43 ንፁሃን ተጨፈጨፉ።
*********************************
ኦነግ ሸኔ መጋቢት 26/2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆታ በተባለ አካባቢ 43 ንፁሃን በግፍ ጨፍጨፈ።

በዚሁ ቦታ በ24/07/2016 ዓ.ም ንጋት 11:30 በታጣቂ ቡድኑ በተፈጸመው ጥቃት ኦርቶዶክሳውያን በተለየ መልኩ ኢላማ የተደረጉ ሲሆን እስከ አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት 22 የተገደሉ ሲሆን ከሟቾቹ ውስጥ 3 ህጻናት 1 ነፍሰ ጡር እንዳሉበትና ገዳዮቹ በአንገታቸው ላይ ያለው ማህተብ እያዩ ያለምንም ርህራሄ ገላዋቸዋል። ከነዚህም ሟቾች ውስጥ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሙሉ በሙሉ የተገደሉ ሲሆን 12 የሚሆኑ ኦርቶዶክሳዊያን በአንድ ጉድጓድ እንደተቀበሩ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

28/03/2024

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ የአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
*****************************************************************

ታጣቂዎች የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም እሁድ ንጋት ላይ ካህናቱ ጸሎተ ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ኦርቶዶክሳውያንን አግተው የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 5ቱ ካህናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ 8ቱ ደግሞ ምእመናን ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱን ምእመናን እና አስተዳዳሪውን የጠየቁት ገንዘብ ተከፍሎዋቸው የለቀቋዋቸው ሲሆን የተቀሩትን አገልጋይ ካህናት ገንዘብ ቢከፈልም ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል።

በታጣቂዎች የተገደሉት አገልጋዮች ስም:-
1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ
2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን
3.መሪጌታ ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም
4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው።

በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ሌሎችም አገልጋዮች በተመሳሳይ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም በቾ ወረዳ ሶየማ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ቀሲስ መልአኩ የተባሉ አንድ ካህን መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ታግተው ተወስደዋል። ቶሌ ወረዳ ላይ እንዲሁ አንድ ዲያቆን በመውሰድ ለመልቀቅ አንድ ሚልዮን ብር እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል።

በመላው ሃገሪቱ ባለው ጦርነትምም ይሁን በታጣቂዎች በሚደረጉ ጥቃቶች አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በተለየ መልኩ ጥቃት እየደረሰባቸው ሲሆን ችግሩን ለማስቆምም ይሁን ታግተው ያሉ ካህናትና ምእመናንን ለማስለቀቅ የሚደረግ መንግስታዊ ጥረት አለመኖሩ መንግስት ራሱ ከአጥቂዎች ወገን መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው። ስለሆነም ምእመናን የተከበረችና የታፈረች ቤተ ክስርቲያንን ለትውልድ ለማሻገር ይቻል ዘንድ ለሰማዕነት ልንዘጋጅና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ልንነሣ ይገባል።

16 shi lekenale TPLF
22/03/2024

16 shi lekenale TPLF

በትግራይ ጦርነት “ምርኮኞች ነበሩ” የተባሉ 112 የመከላከያ ሰራዊት አባላት “በምህረት” ተለቀቁ

በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት “ተማርከው ነበር” የተባሉ 112 የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ በዛሬው ዕለት “በምህረት” መፈታታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። በዛሬው ፍቺ ያልተካተቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይም “በአጭር ጊዜ ውስጥ” መፍትሔ እንደሚያገኝም አስተዳደሩ ገልጿል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፤ የፌደራል መንግስት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት የተማረኩ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከ16 ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መለቀቃቸውን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውሷል።

ዛሬ አርብ መጋቢት 13፤ 2016 የተለቀቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ “በከባድ ወንጀል” ተጠርጥረው “በቁጥጥር ስር የቆዩ” መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለእነዚህ የሰራዊት አባላት “ምህረት” ያደረገው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ “በተደረሰው መግግባት” መሆኑንም አክሏል።

* ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:- https://ethiopiainsider.com/2024/12815/

18/03/2024

በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር ውለዋል!

ያቀረብኩት መረጃው ውሸት እንደሆነ ጠቅሰው ሲያጣጥሉ ለነበሩት ይድረስ። እውነት ሊቆይ ይችላል እንጂ መውጣቱ አይቀርም።

Good job, Ethiopian Airlines

16/03/2024

ትናንት ለሊት ከንግድ ባንክ የሌላችሁን ገንዘብ ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣

በማወቅም ይሆን ባለማወቅ የወሰዳችሁትን ብር መልሱ አለበለዚያ ግን ተጠያቂ ትሆናላችሁ እየተባላችሁ ነው።

ግር የሚለው ግን ንግድ ባንክ እስካሁን ይህን በርካቶች የሌላቸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ያወጡበትን ድርጊት በይፋ አለማሳወቁ ነው። "የሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም" የሚል መግለጫ አሁን አውጥቷል።

የተፈፀመበት ዝርፊያስ?

ሌላው አለም ላይ ቢሆን መጀመርያ ድርጊቱ ይፋ ይደረጋል፣ ከዛም ምን ያህል ገንዘብ፣ በየትኛው አካባቢ ካሉ ተገልጋዮች፣ በምን መልኩ፣ የወሰዱ ሰዎች ላይ የሚወሰዱ አካሄዶች... ወዘተ የሚሉ መረጃዎች ቢያንስ ለደንበኞች ይነገራል።

ምስል: ማህበራዊ ሚድያ

18/01/2024
16/01/2024

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ በተደርገ ማሻሻያ ቀደም ሲል ሲሰጥ ከነበረው የድጎማ መጠን ዝቅ አንዲል መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ የተደረገው በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች አና ፐብሊክ ባስ አንዲሁም ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በየስድስት ወሩ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች የድጎማ መጠን ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን÷ ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ለቤንዚን ተጠቃሚ አገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች እና ፐብሊክ ባስ ብር 22.36 በሊትር ሲሰጥ የነበረውን ድጎማ ወደ 19.16 በሊትር ዝቅ እንዲል፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲሰጥ የነበረው ብር 23.21 በሊትር ድጎማ በሊትር 19.89 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

እንዲሁም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር የሚሰጠው ድጎማ በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ ለቤንዚን ተጠቃሚዎች ሲስጥ የነበረው ብር 12.78 በሊትር ድጎማ ወደ 6.39 በሊትር፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲስጥ የበነረው የብር 13.27 ድጎማ ወደ ብር 6.63 በሊትር ተቀናሽ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

11/12/2023

ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

Kabajamoo Muummicha Ministeeraa Abiyyi Ahimadiif

Yaada Ida’amuu dubbattee fi barreessite amanee isin hordofe. Dhawaata garuu nama waan dubbatu hin jiraanne qofa otoo hin taane cubbamaa dhiiga namaatiin taphatu ta’uu keessanin hubadhe. Gaafan dhugaa sehee waraana bilaasha maqaa walabummaa biyyaatiin bantan, isa Itoophiyaanota wal-nyaachise, fi diinagdee biyyaa kuffise gegeessaa turtan deeggaretti na faarsaa turtan. Hardha gaafan dubbii argee gara nagaa goruun wal-ajjeechaan obboleeyyanii haa dhaabatu jennaan aangoo narraa fudhattan. Otoon shira Oromoo Oromoodhaan balleessuu fi obboleeyyan isaatiin walitti buusuuf kaatan argaa callisuu dhabuu kootii baayyeen gammada. Turtii waliin qabaannef galatoomaa!

Hagan jirutti qabsoon nagaa fi obbolummaa ummataatiif godhu itti fufa!

04/12/2023

ዮሃንስ ቧ ያለው

22/11/2023

ዘወትር ረቡዕ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ አሁን በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
----------||----------
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com

21/11/2023

በሸኔና በመንግስት መካከል በታዛኒያ ሲደርግ የነበረው ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን አቶ ርድዋን ሁሴን በቲዊተር ገፃቸው አሳወቁ።

ያልተስማሙት በየትኛው የድርድር ነጥቦች ላይ እንደሆነ አልገለፁም።

በአባቱ መረቀ

06/11/2023

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትን አንደኛ ዓመት በተመለከተ ከኢፌዴሪ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️

የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ለሰላም ባላቸው የጸና አቋም የተነሣ የውጭም ሆኑ የውስጥ ጠላቶች በተነሡ ጊዜ ሁሉ እየተጠቁም ቢሆን አስቀድመው የሰላምን አማራጭ ይፈልጋሉ፡፡

የፈሩ፣ ዐቅመ ቢሶችና ደካሞች መስለው እስከሚታዩ ድረስ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት እስከጥግ ድረስ ይሄዳሉ፡፡ መንግሥት የሰላም አማራጭን አብዝቶ የሚፈልገው ጦርነትየኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ ሰላም፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና ብልጽግና ስለማያመጣ ነው።

እነዚህ የሰላም አማራጮች ተሟጥተው ማለቃቸውን ሲመለከቱ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት እንደ አራስ ነብር ተነሥተው ጠላቶቻቸውን አደብ ያስገዛሉ፡፡ የጥንትም የቅርብም ታሪካችን ይሄንን ይመሰክራል፡፡

በትግራይ ከሁለት ዓመታት በፊት የተፈጠረው ሁኔታ ወደ ጦርነት ከማምራቱ በፊት መንግሥት የሰላም አማራጮችን ሁሉ ሞክሯል፡፡ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሞክረዋል፡፡ እናቶች እያለቀሱ ለምነዋል፡፡ የጦርነት ነጋሪት ከልክ በላይ እየተጎሰመ እንኳን ከትግራይ ክልል ጋር የነበረው ግንኙነት እንዳይቋረጥ ትዕግሥት አስጨራሽ መንገድ መንግሥት ተጉዟል፡፡

የተለያዩ ወገኖች መንግሥት በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲጠቀም እየወተወቱት እንኳን ለውይይትና ለፖለቲካዊ ንግግር ቅድሚያ በመስጠት ከልክ በላይ ትችቶችን አስተናግዷል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት የኃይል የበላይነት እንዳለው እያረጋገጠ እንኳን ለትግራይ ሕዝብ ሲል ጦርነትን ለማቆምና ከጦርነት ቦታዎች ለመውጣት ቆራጥ ውሳኔ ወስኖ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በጦርነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እርዳታ ለትግራይ ሕዝብ እንዲደርስ መንገዶችን ከፍቶ አሳልፏል፡፡ እርዳታ የጫኑ መኪኖች በሄዱበት እየቀሩ እንኳን ከሕዝብ የሚበልጥ የለም በሚል ችግሩን ተቋቁሞ እርዳታ እንዳይቋረጥ አድርጓል፡፡

ይህ ሁሉ ተደርጎ የሚፈለገው ሰላም ባለመምጣቱ ወደ ግጭት ተገባ፡፡ በዚህም የተነሣ ሕግ የማስከበር ሥራውን እንዲፈጽም መንግሥት ተገድዷል፡፡ መንግሥት ተገድዶ በገባበት በዚያ ጦርነት የደረሰውን ኪሣራ ከትግራይ ሕዝብና ከክልሉ መንግሥት በላይ የሚያውቀውየለም፡፡

ጦርነትን ብቸኛ አማራጫቸው ያደረጉ ኃይሎች የትግራይን ወጣቶች ለእሳት ማግደዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያን እናቶች በሃዘን እሳት ጠብሰዋቸዋል፡፡ የክልሉን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ አውድመዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የነበረውን ዘመናት የተሻገረ ወገናዊነት አበላሽተዋል፡፡

በጦርነቱ መጨረሻ የፌዴራል መንግሥት ሁሉን ነገር በኃይል ለመፈጸም የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ነበረው፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ቢቋጭ ሀገርን አትራፊ የሚያደርግ መሆኑ ስለታመነበት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም አድርጓል፡፡

ይሄንን ያደረገበት ከመርሑ የመነጨ ምክንያት ነበረው፤ በምንም መልኩ ለትውልድ ቂምና በቀልን ማውረስ የለብንም፤ ጦርነት አሸናፊና ተሸናፊን ይፈጥራል፤ ሰላም ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል፤ መጪው ትውልድ በአሸናፊና ተሸናፊ ትርክት ውስጥ ከሚያድግ ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርገው የሰላም ትርክት ውስጥ ቢያድግ ይሻላል በሚል የተደረገ ነው፡፡

ለተጎዱ የተለያዩ ማኅበረሰቦች የሚያገግሙበት ፋታ ለመስጠት የተሰጠ ዕድልም ነው፡፡ ይህ ውሳኔ ሀገርን ለመገንባትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ሲባል የተከፈለ መሥዋዕትነት ነው፡፡

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መንግሥት በሆደ ሰፊነትና ቁስሉ እንዲሽር ካለው ፍላጎት ረጅም ርቀት ተጉዟል፡፡ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ የጥላቻውን ጉም በመግፈፍ ወደ ትግራይ በግንባር ቀደምነት የተጓዘው በአፈ ጉባኤው የተመራው የፌዴራል መንግሥቱ ልዑክ ነበር፡፡ ይህ ልዑክ ከተጓዘ በኋላ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የባንክና የአውሮፕላን አልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀምሩ ተደርገዋል፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተመሠረተ ጊዜ መሳሳብና መጓተትን ለማስቀረት ሲባል የአመራሩን ድርሻ ክልሉ እንዲወስድ በማድረግ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፋታ አግኝቶ ፊቱን ወደ ሰላምና ልማት እንዲያዞር ተደርጓል፡፡

የግብርና ሥራውን ለማገዝ የሚመለከተው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በክልል ደረጃ ከሚጠበቅበት በላይ ሠርቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችንና ትምህርት ቤቶችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የትምህርት ሚኒስቴር ከተልዕኮ በላይ ተጉዟል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ከራሱ በጀት ቀንሶ አያሌ ተግባራት አከናውኗል፡፡ የሰላም ስምምነቱን እንደ ዕድል በጠቀም ሕዝብን ከችግር በማዳን፣ መንግሥታዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማስመጀር ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

አንዳንድ ነገሮችን እያገዘ፤ አንዳንድ ነገሮችን ችሎ እያለፈ፤ አንዳንድ ነገሮችን እየመከረ፤ አንዳንድ ነገሮችንም ራሱ እየሠራ የሰላም ስምምነቱ በተሟላ ልኩ በሂደት እንዲፈጸም ለማድረግ ሞክሯል፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ ነገሮች ወደኋላ እየቀረና ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ሳይፈጽም እያነከሰ እንኳን ለክልሉ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ የፌዴራል መንግሥቱ አላቋረጠም፡፡

ከፌዴራል መንግሥቱም አልፎ ክልሎች ከአነስተኛ በጀታቸውና ገቢያቸው በመቀነስ የትግራይ ክልልን ደግፈዋል፡፡ አከራካሪ የሚባሉ አካባቢዎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ አቋም ወስዶ ሠርቷል፡፡ የፌዴራል መንግሥት በዚህ ረገድ ያለው አቋም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ፣ ሁሉንም ወገን በሚጠቅም መንገድ ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ብልጽግናን በሚያረጋግጥ መንገድ መፍትሔ መሰጠት አለበት፡፡

ክረምት ደርሶ የእርሻ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፤ የአካባቢ ነዋሪዎች በመረጧቸው አካላት እንዲተዳደሩ፤ በመጨረሻም ደረጃ በደረጃ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ እነዚህን ሁሉ አቋሞችና ተግባራት የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ በሚገባ ያውቃል፡፡

ይህ ሁሉ ቢደረግም እንኳን በዚያኛው ወገን እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል፡፡ ይህ ግን ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናንና የሕዝቦችን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አያረጋግጥም፡፡

የፌዴራል መንግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በተመለከተ ከሚጠበቅበት በላይ ተጉዟል፡፡ በዚህም ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም ደጋግሞ አሳይቷል፡፡

የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር መንግስት አሁንም ቁርጠኛ አቋም አለው፡፡ ሁሉም አካላት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት በማሳየት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል፡፡

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

20/09/2023

በምዕራብ ጎጃም በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ‘ከ30 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን’ ነዋሪዎች ተናገሩ

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ከተማ እና ቋሪት ወረዳ ከትናንት በስቲያ መስከረም 6/2016 ዓ.ም በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ነዋሪነታቸው በቋሪት ወረዳ የሆኑ እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪ ሁለት ስፍራዎች ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል ብለዋል።

በአንደኛው ጥቃት “በብዛት ተሰባስበው ይጓዙ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ኢላማ ተደርገዋል” ያሉት እኚህ ነዋሪ በጥቃቱ “ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል” ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የድሮን ጥቃት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎችን እንደጎበኙም እኚሁ ነዋሪ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

ጥቃቱ የደረሰው ውጊያ ከሚደረግበት አካባቢ የራቀ እና ለጊዜው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ባልነበረበት ቦታ መሆኑንም እኚሁ ነዋሪ አስረድተዋል።

በሁለተኛው ስፍራ የደረሰው የድሮን ጥቃት ግን ጉዳት አለማድረሱን ገልጸዋል።

“ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገው ጥቃት ጫካ ላይ ነው ያረፈው፣ በመሆኑም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም” ብለዋል።

በሌላኛዋ የምዕራብ ጎጃም ከተማ ደምበጫ ከተማ ተፈጽሟል በተባለ የድሮን ጥቃት በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ ጥቃቱ የተፈጸመው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው ብለዋል።

ነዋሪው ቢያንስ 18 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው በአካባቢው አስከሬን በማንሳት መሳተፋቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ በቋሪት እንዲሁም በደምበጫ አካባቢ ተፈጽሟል ስለተባለው የድሮን ጥቃት መረጃ ለማግኘት የመንግሥት አካላትን ለማነጋገር ቢሞክርም ምላሽ አላገኘም።

ከአንድ ወር በፊት በፍኖተ ሰላም ከተማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቁጥራቸው 30 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንዲያጣራ በተባበሩት መንግሥታት የተቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች የባለሙያዎች ቡድን ትናንት መስከረም 7/2015 ዓ.ም ባወጣው ሁለተኛው ሪፖርት በክልሉ ቢያንስ አንድ የድሮን ጥቃት ስለመፈጸሙ ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል።

በከተማው መውጫ አካባቢ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ተኩስ መኖሩን የተናገሩት እኚሁ ነዋሪ ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ ግን ምንም አይነት የታጣቂ እንቅስቃሴ አልነበረም ሲሉም አስረድተዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማዋ ውጭ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ ነዋሪዎችን “መሣሪያ አምጡ” እያሉ በማስጨነቃቸው ምክንያት ጦርነቱ እንደገና ማገርሸቱንም እኚሁ ነዋሪ ይናገራሉ።

አሁንም በከተማዋ ምዕራባዊ አቅጣጫ ጦርነት እየተደረገ መሆኑን እና ከተማዋ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደማይታይባት አክለው ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ መግለጹ ይታወሳል።

በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች እጅግ አሳሳቢም እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መስከረም 4/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሙሉ ዘገባው፡ https://bbc.in/3RseQRf

የጌታቸው ረዳ ምርጫ
19/09/2023

የጌታቸው ረዳ ምርጫ

762 likes, 186 comments. “ #ፕሮፌሰርብርሀኑነጋ #አብይአሕመድ ゚viral ...

13/09/2023

ትናንት ➡️ ከጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋሮቢት እና አዋሽ አርባ ውጭ የማቆያ ቦታ የለም

ዛሬ ➡️ በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል የማቆያ ስፍራዎች አሉ

ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጩ ከነበሩ ምስሎች ጀርባ ያለው እውነታ እዚሁ ጋር ይገኛል።

¿?????¿¿
25/08/2023

¿?????¿¿

24/08/2023

The 15th BRICS Summit decided to invite Saudi Arabia, Egypt, the UAE, Argentina, Iran and Ethiopia as full members. CONGRATS & WARMLY WELCOME for joining the family! A stronger BRICS will have a bigger voice.

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትኩስ ዜና Tikus Zena Ethiopian news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

ትኩስ ዜና Ethiopian news tikuse Zena https://t.me/ethiozena

ትኩስ ዜና Ethiopian news tikuse Zena https://t.me/ethiozena