Mekane-Selam Media - MSM

  • Home
  • Mekane-Selam Media - MSM

Mekane-Selam Media - MSM Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mekane-Selam Media - MSM, Media/News Company, .

13/07/2023

S○UTHERN AFRICAN C○UNTRIES T○P FACTS ✅
🇲🇼 🇿🇲 🇿🇼 🇦🇴 🇱🇸 🇸🇿 🇲🇿 🇧🇼 🇳🇦 🇿🇦 🇲🇬

1. Madagascar 🇲🇬 is the fourth largest island in the world.

2. Madagascar 🇲🇬 has the largest coastline in Africa.

3. South Africa 🇿🇦 is the only Country to have hosted FIFA World cup in Africa.

4. Eswatini 🇸🇿 is a kingdom ruled by a Monarch.

5. South Africa 🇿🇦 has the largest GDP in the region.

6. South Africa 🇿🇦, cape Town city was ranked the best in 2019.

7. Namibia 🇳🇦 has the largest desert in the region known as namib desert that meets The Atlantic Ocean.

8. Lesotho 🇱🇸 is the only Landlocked country inside a country in Africa.

9. In Madagascar 🇲🇬 All houses should face west

10. Madagascar 🇲🇬 The head of the bed must face north

11. People in Madagascar 🇲🇬 Never have a funeral on a Thursday.

12. Nearly 40% of Botswana 🇧🇼 is made up of national parks and wildlife reserves which provide plenty of large areas for animals to roam.

13. Botswana 🇧🇼 is home to the world's largest concentration of African elephants, of which the highest concentration is found in Chobe National Park.

14. 🇧🇼 The world’s second-largest gem quality diamond was discovered in Botswana last year. It is the biggest diamond to be discovered in Botswana and the largest find in more than a century.

15 Botswana 🇧🇼 holds a number of world records including the world’s largest salt pans, the world’s largest inland delta and the world’s shortest border.

16. Half the people in Mozambique 🇲🇿 are under-17.More than half the women have their first child before they are 19.

17. Mozambique 🇲🇿 is the only country with a single word name that includes all five vowels.

18. Mozambique is the only country in the Commonwealth never to have been part of the British Empire.

19. Termite hills in Zambia 🇿🇲 can grow as big as a small house. With room for a pony. The termite hills are the size of a house.

20. In Zambia 🇿🇲 Victoria Falls is double the height of Niagara Falls -Victoria Falls is 108 metres in height. It’s almost double the height of Niagara Falls in Canada.The traditional name for Victoria Falls is Mosi-oa-Tunya, Mosi-oa-tunya means the ‘Smoke that Thunders’ and, as you can imagine, Victoria Falls truly lives up to its name.

21. In Zimbabwe 🇿🇼 There’s a massive man-made lake that sustains life to the country, Lake Kariba is the world’s biggest man-made lake and is used for commercial fishing operations and to supply electric hydropower to Zambia and Zimbabwe.

22. In Zimbabwe 🇿🇼 The noise of the Victoria Falls can be heard as far as 40 kilometers away.

23. Zimbabwe 🇿🇼 has five UNESCO World heritage sites; these are Khami Ruins, Great Zimbabwe Ruins, Victoria Falls, Mana Pools and Matobo Hills. Now that’s a good reason to come and visit. Find out more about these sites.

24. Angola 🇦🇴, there are many Portuguese speakers in Angola than Portugal itself.
25. Namibia 🇳🇦 is home to the world’s oldest desert.

26. In Namibia 🇳🇦 The himba rive of Namibia is the most famous tribe in the region. The Himba tribe in the Kunene region of the country have strongly clung to their traditional ways and beliefs. They wear traditional clothes, eat traditional foods and even practice traditional religions. The women wear skirts and leave their upper body bare.

27. In Malawi 🇲🇼 Lake Malawi contains the largest number of fish species of any lake in the world.

28. South Africa 🇿🇦 has the best Healthcare in Africa that matches Europe and international standards.

29. South Africa 🇿🇦 is the second leading tourist destination in Africa after Morocco.

30. South Africa 🇿🇦 is the most popular country in Africa after Nigeria 🇳🇬

31. South Africa 🇿🇦 Rovos Rail & Blue Trains Are Considered The Most Luxurious Trains In Africa

32.South African 🇿🇦Table Mountain Is One Of The Oldest Mountains In The World & Has More Species Of Flowers Than Some Countries In Europe

33. CapeTown South Africa 🇿🇦 Is Ranked Number 7 Most Beautiful City In The World.

34. South Africa 🇿🇦 South Africa is the first country in the world to carry out a successful heart transplant in capetown.

📸 An Interchange in South Africa.

23/06/2023
በዛሬው የፓርላማ ውሎ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ጫላ ዋታ፤  ከፖርላማ እንደወጡ  በጏደኛቸው መኪና ቢሰወሩም በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታው...
04/04/2023

በዛሬው የፓርላማ ውሎ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ጫላ ዋታ፤ ከፖርላማ እንደወጡ በጏደኛቸው መኪና ቢሰወሩም በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል :: ዶ/ር ጫላ በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው ነው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት:
ባለግዜ እንዴት ይታሰራል 😉😏

ቦረና መካነ ሰላም ምን እየተፈጠረ ነው ያለው? መካነ ሰላም ተሾመ ዳኜን የገደለውን የማይረቡ የከተማ ሰዎች ደበቁት፣ ዛሬ አዲሱ ደጀንን የገደለ ግን በገጠሩ የዋህ አርሶ አደር ተይዞ ለህግ አ...
31/03/2023

ቦረና መካነ ሰላም ምን እየተፈጠረ ነው ያለው? መካነ ሰላም ተሾመ ዳኜን የገደለውን የማይረቡ የከተማ ሰዎች ደበቁት፣ ዛሬ አዲሱ ደጀንን የገደለ ግን በገጠሩ የዋህ አርሶ አደር ተይዞ ለህግ አካል አስተላልፈው ሰጥተዋል። ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።
ምን አይነት ዓመት ነው። ሁለቱንም ባልረባና በማይረቡ ገዳዮች አጣናቸው። እሺ አስከመቼ? ቀጣይስ 😭😭😭😭😭

ህይወት አንተ የምትፈልገዉን ሰዉ ለክታ አትሰጥህም።የሚረዳህ፣የሚጎዳህ፣የሚወድህ፤ጥሎህ የሚሄድ እንዲሁም ትልቅ እንድትሆን መንገዱን የሚያመቻችልህን አስፈላጊ ሰዉ ግን ትሰጥሃለች፡፡• ማንኛዉም ...
20/03/2023

ህይወት አንተ የምትፈልገዉን ሰዉ ለክታ
አትሰጥህም።

የሚረዳህ፣የሚጎዳህ፣የሚወድህ፤ጥሎህ የሚሄድ እንዲሁም ትልቅ እንድትሆን መንገዱን የሚያመቻችልህን አስፈላጊ ሰዉ ግን ትሰጥሃለች፡፡
• ማንኛዉም እንድትሰላች የሚያደርግህ ነገር ካለ እሱ ነገር ትእግስት እንዲኖርህ እያስተማረህ ነዉ፡፡ጥሎህ የሔደ ማንኛዉም ሰዉ በሁለት እግሮችህ ቆመህ በራስህ እንድትሄድ እያስተማረህ ነዉ፤ማንኛዉም የሚያናድድህ ነገር ይቅርታንና ደግነትን እያስተማረህ ነዉ፡፡ማንኛዉም ባንተ ላይ ሃይል ያለዉ ነገር የራስህን ጉልበትና ሃይል እንድትቆጣጠር እያስተማረህ ነዉ፡፡
ማንኛዉም የምትጠላዉ ነገር ያለቅድመ ሁኔታ እንድትወድ እያስተማረህ ነዉ፡፡ማንኛዉም የምትፈራዉ ነገር ፍርሃትህን አሸንፈህ እንድትራመድ እያስተማረህ ነዉ፡፡መቆጣጠር የማትችለዉ ነገር ሲደርስብህ ከእጅህ እንድትለቀዉ እያስተማረህ ነዉ፡፡
• በህይወትህ ያለዉ አስቸጋሪ ሁኔታ አንተን ለመጥፋት የተሰራ ሳይሆን ዉስጥህ ያለዉን እምቅ አቅምና ችሎታ እንድትረዳ የሚያግዝህ ነዉ፡፡ችግሮችህ ከነሱ በላይ ችግር እንደሆንክባቸዉ ይወቁ!
• እርካታ ያለዉ ህይወት ስኬታማ ከሆነ ህይወት ይሻሻላል፡፡ምክንያቱም ስኬትህ በሌሎች ሰዎች ሲለካ እርካታህ ግን በራስህ ነፍስ፣አእምሮና ልብ ይለካል፡፡
• ትላልቅ ነገሮች በምቾት የሚገኙ አይደሉም፡፡
• ሃላፊነት ዉሰድ፡፡ካሸነፍክ ደስተኛ ትሆናለህ፤ከተሸነፍክ ደግሞ ብልህ ትሆናለህ፡፡
• ነገሮችን ሁልጊዜ ሰዉ ሳያጨበጭብልህ በትክክል መስራት ከባድ ነዉ፡፡በእነዚህ ጊዜያት ለራስህ አጨብጭብለት፣የራስህ ደጋፊ እራስህ መሆን ይኖርብሃል፡፡
👍 እዉነተኛ ሀብታም ለመሆን ባንክ ቡክህ ዉስጥ ያለዉ የገንዘብ ብዛት ሳይሆን ልብህ ዉስጥ ያለዉ ማንነት ይወስናል፡፡
• ፍቅር፣ሀብትና ስኬትን አታሳድድ፡፡ይልቁንም ከትላንቱ የተሻለ ማንነትን ገንባ፣ከዛማ እራሳቸዉ ያሳድዱሃል!
• በሃሳብ የምንሰቃየዉ በእዉነታዉ ከምንሰቃየዉ ይበልጣል፡፡
• አንዳንድ ቤተሰቦች ስኬታማ ለመሆን እርስ በርሳቸዉ መረዳዳት እንዳለባቸዉ ገና አልገባቸዉም፡፡
• ዋናዉ ችግራችን የሰአት ማነስ ሳይሆን የአቅጣጫ መጥፋት ነዉ፡፡ ሁላችንም 24 ሰአት ተሰጥቶናል፡፡
• አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ የምትሆንባትን አንዷን አመት ለማግኘት ሌላ አስር አመት ሊፈጅብህ ይችላል፡፡
• በህይወትህ ዋናዉን ሃላፊነት የሚወስደዉ እራስህ ብቻ ነህ፡፡
• በምድር ላይ ስትኖር ባደረከዉ ስራ ልክ ይከፈልሃል!
NNur TypingTNur Typing..

ስሟ ወርቄ ቅባቴ ይባላል የአባቷ ስም ቅባቴ አስፌ የእናቷ  ስም ደግሞ  ሙመር ናየሁ  እንድሁም  ሀብታሙ ቅባቴ እና ሲሳይ ቅባቴ የሚባሉ ወንድሞች .ፋሲካ ቅባቴና ጌጤ ቅባቴ የተባሉ እህቶች ...
17/03/2023

ስሟ ወርቄ ቅባቴ ይባላል

የአባቷ ስም ቅባቴ አስፌ የእናቷ ስም ደግሞ ሙመር ናየሁ እንድሁም ሀብታሙ ቅባቴ እና ሲሳይ ቅባቴ የሚባሉ ወንድሞች .ፋሲካ ቅባቴና ጌጤ ቅባቴ የተባሉ እህቶች እንዳሏት ተናግራ የመጣችው ግን በተፈጠረው ሀገራዊ ችግር ከሰሜን ወሎ ከላሊበላ ከተማ አካባቢ ከምትገኝ አይና ከተማ ልዩ ቦታው ተከወይ መንደር እንደመጣች ተናግራለች ነገር ግን የበለጠ መረጃ ለማግኘት ትንሽ የመደናገር ስሜት ሰለነበረባት ማጣራት አልቻልንም ሆኖም ግን ይችን ከታች በፎቶው ላይ የምትመለከቷትን ህፃን በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ መካነ ሰላም ከተማ ስለምትገኝ ለቤተሰቦቿ ወይም ወዳጅ ዘመዶቿ ይህንን በማጋራት ተባበሯት እኛም ከምናውቃቸው የላሊበላ ልጆች ጋር እየተደዋወልን ጥረት ላይ ነን።

የቦረና ሳይንት ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሽማግሌ እና መሪ በሆኑት በጋሽ ደመቀ አዳነ የተጻፈው የወሎ ቦረናን ባህልና ትውፊት የያዘ መጽሐፍ ለማሳተም ዝግጂቱ ተጠናቋል። የመጽሐፉ ሽያጭ ገቢ ለአካ...
09/01/2023

የቦረና ሳይንት ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሽማግሌ እና መሪ በሆኑት በጋሽ ደመቀ አዳነ የተጻፈው የወሎ ቦረናን ባህልና ትውፊት የያዘ መጽሐፍ ለማሳተም ዝግጂቱ ተጠናቋል።

የመጽሐፉ ሽያጭ ገቢ ለአካባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ማሳለጫ እንዲሆን አባታችን ቃል ገብተዋል። ለህትመቱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000519869881 ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።

ዋና አስተባባሪው በደሴ ከተማ የቦረናና አካባቢው የልማትና መረዳጃ ማህበር ነው።

Ayalew Talema

ሀርቡ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በምስራቅ አቅጣጫ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በስተ ደቡብ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰሜን የኮምቦልቻ ከተማ ያዋሥናታል። ሀርቡ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን የተዘ...
04/12/2022

ሀርቡ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በምስራቅ አቅጣጫ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በስተ ደቡብ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰሜን የኮምቦልቻ ከተማ ያዋሥናታል። ሀርቡ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን የተዘረጋዉን ትልቁ መንገድ መሀል ለማሀል ያቋርጣታል።

ይህች በመቆርቆር እረጅም እድሜ ያስቆጠረች ታሪካዊ ከተማ በመልከአ ምድር አቀማመጧና ዉስጥ ባላት የተፈጥሮ ሀብት የብዙዎችን ቀልብ ትማርካለች ለምሳሌ ያክል የሀርቡ ፉልዉሀ፤ የቦርከና ወንዝ፤ የፈላና፤ የመልካ ኤላ (ሀርቡ ወንዝ)፤ የዲርማ ወንዞች መገኛ ናት።

በእነዚህ ተፈጥሮ ባፈራቸዉ ወንዞች ተከትሎ የተለያዩ የፍራፍሬና የሰብል ምርቶች ወደ ተለያዩ ቦታ ትልካለች ለምሳሌ ሸንኮራ አገዳ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ብርቱካን፣ ማንጎና ሙዝ እንዲሁም ከሰብል ሰሊጥ፣ ማሾ፣ ጤፍ እና ማሽላ ይገኙባታል።

ሀርቡ የተለያዩ የአማራ፣የኦሮሞ እና የአርጎባ ብሔረሰብ ህዝቦች ተከባብረውና ተዋደው ይኖሩባታል። ከዚች ውብና ለመኖር ተስማሚ ከሆነች ከተማ መዋዕለ ንዋየዎን ያፍስሱ!!!

እሴቶቻችንን ለመሸርሸር  የመሰሩ ሀይሎችን በጋራ ልንታገል ይገባል ሲሉ የሀይማኖት ፍረም አባለት ተናገሩ፡፡==========================መካነ ሰላም፣ ህዳር 23/2015ዓ.ም (መካ...
02/12/2022

እሴቶቻችንን ለመሸርሸር የመሰሩ ሀይሎችን በጋራ ልንታገል ይገባል ሲሉ የሀይማኖት ፍረም አባለት ተናገሩ፡፡
==========================
መካነ ሰላም፣ ህዳር 23/2015ዓ.ም (መካነ ሰላም ኮሙኒኬሽን) የመካነ ሰላም ከተማና የቦረና ወረዳ ሀይማኖት ፎረም አባላት በአካባቢ ሰላምና ደህንነት ዙሪያ ውይይት አድረገዋል፡፡

በየእምነት ተቋማቱ አብሮነታችንን በመስበክ እሴቶቻችንን ለመሸርሸር የመሰሩ ሀይሎችን በጋራ ልንታገል ይገባል ሲሉ የፎረሙ አባላት ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የእምነት ተቋማት መልካምን ነገር ይሰብካሉ እንጅ አብሮነትን የሚሸረሽርሩ አዥንዳዎችን እንደማያራምድዱ በመግለጽ የሀይማኖት አዥንዳ በማሲያዝ ህዝቡን ለግጭት የሚያነሳሱ ሀይሎችን ከመንግስት ጎን በመቆም ልንታገል ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሰሞኑን በመካነ ሰላም ከተማ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጠረውን ጥቃት የሀይማኖት ፎረም አባላቱአውግዘዋል፡፡

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሠረት ጣይ ተምሳሌትወግዲ ወረዳ ኮየ✍️ የሀገሬ ልጅ ደራሲ ዶክተር መሐመድ ዐሊ ኢድሪስ - የወይራ ስር ድርሰቱን ሲጽፍ ገጸ-ባህሪያቱን እንዳይረሱ አድርጎ ነው የሳላቸው...
29/11/2022

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሠረት ጣይ ተምሳሌት

ወግዲ ወረዳ ኮየ

✍️ የሀገሬ ልጅ ደራሲ ዶክተር መሐመድ ዐሊ ኢድሪስ - የወይራ ስር ድርሰቱን ሲጽፍ ገጸ-ባህሪያቱን እንዳይረሱ አድርጎ ነው የሳላቸው ። የአካባቢውን የተበችሳ ባህል ለሚያውቅ ሰው ሁለመናቸው በአካል ይታዩታል ። በዚያ ላይ ደግሞ መጽሀፉ በሬድዮ ባማረ ሁኔታ ስለተተረከ ምስሉ ከአእምሮ አይጠፋም

ደራሲው በመጽሀፉ ውስጥ የኮየ መንደር ሰወችን በገጸ ባህሪያትነት ተጠቅሟል ። የአካባቢው ነዋሪወች እነኝህን ሰወች በመጽሀፉ ስናነብ ምን ያክል እንደምንደሰትና በባህላችን ምን ያክል እንደምንኮራ ልነግራችሁ አልችልም ።
በመጽሀፉ ውስጥ የተጠቀሱ ሰወችን እኔ ራሴ በተጨባጭ በአካል የማውቃቸው ሰወች አሉ ። ይሄ በመሆኑ ደስ ይለኛል ። ባህላችንም እንዳይረሳ ይጠቅማል የሚል እምነትም አለኝ ። በወረዳችን በባህል ዙሪያ ለሚሰሩ አካላትም ጥሩ መስረት ይሆናል የሚልም ሀሳብ አለኝ ።

ለዛሬ ይሄን የተበችሳ ግጥም እንድትሰሙት በአክብሮቶ እጋብዛለሁ ። ( የቀረበው በጽሁፍ ቢሆንም ዜማና ስልተ-ምቱ በጆሮም የሚንቆረቆር ስለሆነ ከመስማት አይተናነስም ብየ ነው ፣ ስሙት የምላችሁ !! .......)
እንደዚህ ... ቀርቧል !!

ለሚ - (ኮየ) በተባለ መንደር ውሰጥ የተበችሳ አቀንቃኟ ተጓዳ አወሉ የሰርገኛውን መውጣት እንደሰማች አታሞዋን እየመታች፣ ከዚህ ቀደም በጋብቻ ምክንያት የተለዩዋቸውን ጓደኞቻቸውን ጭምር እያስታወሰች የመለየት ግጥሞችን፣ በዜማ ተቀባይ ባልንጀሮቿ ታጅባ እንድህ ታወራርዳለች ።

".... አበቡ ሙህየ እንውረድ እንጨት
ልክነሽ አያሌው እንውረድ እንጨት
ሀውዬ ሙህየ እንውረድ እንጨት
የኔ ዝሀራ አህመድ እንውረድ እንጨት
ልጅነት ቀረ አሉ ውሃ መራጨት
ልጅነት ልጅነት ልጅነት ዓለም
በብር አይገዛ በሠላሳ ላም
እንኳን በሠላሳ ቢገዛ በመቶ
እኔ እገዛው ነበር ልጅነት ተገኝቶ ..."
ትላለች !!

በጣም ደስ ይላል ። የአካባቢያችንን ባህል በድርሰቱ ስላስተዋወቀልን ደራሲውን ከልብ አመሰግናለሁ ።

Gashaw Mekonnen



#ወሎየነት

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሠረት ጣይ ተምሳሌትየከንፈር ወዳጅ!!"አረንዛው ቦረና ናና በአስኮ ጫማ ማርዬ ቦረና ናና በአስኮ ጫማ ሸግዬ ላንተ ስል... እንደ አሞራ ልብረር እንደ ጨው ልሟሟ።"  ...
29/11/2022

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሠረት ጣይ ተምሳሌት
የከንፈር ወዳጅ!!

"አረንዛው ቦረና ናና በአስኮ ጫማ
ማርዬ ቦረና ናና በአስኮ ጫማ
ሸግዬ ላንተ ስል...
እንደ አሞራ ልብረር እንደ ጨው ልሟሟ።"

የለገማራን እርጥብ ሰርዶ የሚመስሉቱ የወሎ አማራ ሳይንት ልጃገረዶች ለአስኮ ጫማ ለባሽ የከንፈር ወዳጆቻቸው የቋጠሩት ስንኝ ነው። እኛም ዘናጭ አስኮ ጫማ ለባሾች ዘፈኑን ስንሰማ አለንበት ላይ ሆነን ምድር እስኪናድ ደልቀናል።

አስኮ የተባለው ጫማ ከታች በፎቶው ላይ ወንዱ አድርጎት የምታዩት ሲሆን በእኛ ጊዜ እሱን ያደረገ ጎረምሳ ሞጃ የሞጃ ልጅ ነበር። በአሁኑ ናይክ ፑማ አዲዳስ በሉት አብዛኞቹ ባልንጀሮቻችን ቸርኬ ነዋ የሚለብሱት ህእ😁 (ቸርኬን ለማታውቁ በየአካባቢው የተለያየ ስያሜ አለው በረባሶ፣ ጅብ አይበላሽ፣ ሸረፈዴ፣ ሞጋ ጫማ... እኛ ግድም ቸርኬ ነው የምንለው)።

የከንፈር ወዳጅ በአብዛኛው የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ክፍል ያለ ባህል ሲሆን ትዳር ሳይመሰረት በፊት ያለ የእጮኝነት ጊዜ ነው። በእኛ በወሎ አማራ ሳይንት አካባቢ ደግሞ የከንፈር ወዳጅ ማለት :- የእጮኝነት ጊዜ፣ የፍቅርና የታማኝነት መለኪያ ሚዛን፣ የባልንጀርነትና የአብሮ አደግነት ትስስር፣ የቤተሰብ ክብርና የሀገሬው ውብ ባህል ሲሆን እጮኝነቱ ካልተሳካ በከንፈር ብቻ የሚጠናቀቅ ወዳጅነትም ነው። እኛ አካባቢ የከንፈር ወዳጅ የራሱ የሆነ የጨዋታ ወቅትና ክዋኔ አለው እርሱም የሠርግ ሰሞን ጨዋታ (አጫዋች) ላይ ብቻ ሲሆን በአዘቦት ቀን ደግሞ በተለያዩ በዓላት ላይ፣ በእንጨት ሰበራ፣ በደቦ፣ በገበያ፣ በእረኝነትና በኩበት ለቀማ፣ በአክርማ ቀጨታና በጨርቅ አጠባ... ላይ ደግሞ መወዳደሱ መሞጋገሱና እሱ የኔ እሷ የኔ መባባሉ አለ።

"...መቼም ወሎየ ሁሉም የጁና ወረኢሉ
ወሎን ያላማ የለም ቆንጆ ናቸው እያሉ"... እንዲል ድምጻዊ አበባየሁ ደምሴ የወሎ ከንፈር ወዳጅ ሲባል ከቁንጅናቸው ባሻገር ውስጠ ታዋቂ ሀሜት አለች። ይህንን አስተሳሰብ ያመጣው አብዛኛውን የወሎ ገጣሚ የዘምዘም ዓይኖች ውበት፣ የጠጄ ዘንፋላ ፀጉር፣ ያልማዝ ሞንዳላ ጅስም. . . አይነት ስለሆነ የስነ ልቦና ስሪቱ ሁሉ ይህ ብቻ እንደሆነ የሚያስቡ ብዙ ናቸው።

እኛ አካባቢ ግና ይሄ አይነት አስተሳሰብ ዋጋ ያስከፍላል ወዳጄ ወደድኩ ላለው ሁሉ መቀነት የምትፈታ እንስት የለችንም ያለቀው ቢያልቅ የተንገላታውን ያህል ቢንገላታ እልሁ እያነሳ ቢያፈርጠው ወይ ፍንክች!! ለዚያም ነው አጫዋች ላይ እንኳን አሳዳሪ ስንሆን አይ እንግዲህ በጅም አላለይህ የበለል ስጣት የምንለው። በነገራችን ላይ የወሎ አማራ ሳይንት ስነልቦና ማንንም አይመስልም አሁን ድረስ ወሎየነት ሌላ ትርጉም ነበረው ከጊንባ ወዲያ ያለውን አገር ነው ወሎ እንል የነበረው በየቀበሌውም ወሎ መንደር የምንለውም አለ። (እዚህ ላይ በሌላ ጊዜ በሰፊው እንመለስበታለን)

በእኛ አካባቢ የከንፈር ወዳጅ የነበራት ማንኛዋም የሀገራችን ልጃገረድ ክብሩዋን ጠብቃ ነው የምታገባው "ቁንጅና አላት ወይ? ክብርት (ጠብቆ ይነበብ) አላት ወይ?" ተብሎ በሶስተኛ ቀኑ ጫጉላ ይጠየቃል ደንብ አለ። ሳት ብሎ ባይኖራት እንኳ ማን እንደወሰደው ይጠይቃል ያ የከንፈር ወዳጇ ከሆነ በማህበረሰቡ የተገለለ ይሆናል በባሏ አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል ቅጣቱ ሌላ ሰውም ቢሆን አይቀርለት ዱለኛው ቦረኔ ደም በነሰረው የሰፋ ሽመል ቢያሻው መሃል ሶዬ ገበያ ላይ ቢያሻው ውረድ እንውረድ ብሎ መልእክተኛ ልኮ ከወንዶቹ ቦታ ነውረኛውን የወንድ እጅ ያሳየዋል።

አብዛኛዉን ግዜ የከንፈር ወዳጅ የነበሩ ወጣቶች ለትዳር አይበቁም ምክንያቱ የቤተሰብ አለመስማማት ነው።
"ቢጠቁር ቢነጣ ኑግ አይሆንም ጠላ
ልጅ እየወደደ አባት እየጠላ " ይላሉ ተፈላልገው የተነጣጠሉ የልብ ባለቤቶች ሲዘፍኑ።

!
!
𝐌𝐞𝐤𝐚𝐧𝐞𝐬𝐞𝐥𝐚𝐦 𝐓𝐮𝐛𝐞

_____💚💛❤_____



#ወሎየነት

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሰረት ጣይ ተምሳሌት“ኧረ ባቲ ባቲ…”በድሮው ቃሉ አውራጃ በአሁኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ የምትገኘው ስመ ገናናዋ ባቲ ብዙ ነገሮች የተባሉላት ግን ደግሞ ያል...
27/11/2022

ወሎ የነገዋ ኢትዮጲያ መሰረት ጣይ ተምሳሌት
“ኧረ ባቲ ባቲ…”

በድሮው ቃሉ አውራጃ በአሁኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ የምትገኘው ስመ ገናናዋ ባቲ ብዙ ነገሮች የተባሉላት ግን ደግሞ ያልተባለላት የሚበዛ ውብ ከተማ ናት:: ስለ ባቲ ሲነሳ ከሀገሪቱ የሙዚቃ ቅኝቶች ማለትም አንቺ ሆዬ፣ ትዝታ፣ አምባሰል እና ባቲ አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል:: ይሄንን ጉዳይ ወደ ኋላ ላይ እንመለስበታለን::

ባቲ ፍቅሯን ዘልቀው የሚያውቁት አፋሮች፣ አርጐባዎች፣ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች እና የሌሎች ብሔረሰብ ነዋሪዎችም በፍቅር የሚኖሩባት የደጋጐች እና የውቦች ሀገር ናት:: “ውበት ሲለካ፣ ባቲ ነው ለካ” መባሉም የዚሁ እውነታ ማስረገጫ ነው::

ባቲ ላይ ተገኝተው በባቲ ቆነጃጅት ውበት ልብዎ አልሸፍትም ካለዎት እርስዎ ዐይንዎን ይመረመሩ ዘንድ ከመምከር ውጭ ምንም ሊባሉ አይችሉም:: የባቲ ቆነጃጅት በድሪያ /ሽቲ/ እና ሂጃብ ውበታቸውን ቢደብቁት እንኳን ያልተደበቀው የሰውነት ክፍላቸው የተደበቀውን ውበታቸውን እያሳበቀ ለቁንጅናቸው እጅ መንሳት ግድ ያስብላሉ::

የባቲ ቆነጃጅት ውበት በዘመን አመጣሽ የመዋቢያ ቁሳቁሶች የተዥጐረጐረ አይደለም:: ለባቲዋ ቆንጆ ‘ሎሽን’ ምኗም አይደለም፤ እሷ የምትዋበው ከአያት እና ቅድመ አያቶቿ በወረሰቻቸው የወይባ እና ሌሎች ባህላዊ የመዋቢያ ቁሶች ነው::

ባቲ ላይ ዶዶራንት፣ የሱዳን ወይም የፈረንሳይ ሽቶ አፍንጫዎትን አይሰነፍጥዎትም:: ይልቁንም የባቲ ኮረዳዎች እና ወይዛዝርት በአጠገብዎ ሲያልፉ አፍንጫዎ መልካም መዓዛን ያሸታል:: እንዴት? ካሉ የባቲ ውቦች መዋቢያዎች ሀገር በቀል ጢሳ ጢሶች ናቸውና! ነው መልሳችን::

የበለጠ ትኩረትን ስለሚስቡት፣ ዐይንን ስለሚያሸፍቱት፣ አፍንጫን በመልካም መዓዛቸው ስለማያውዱት የወሎ /ባቲ/ ቆነጃጅት ማውጋቱ ደሰ ስለሚል እንጂ የባቲ ወንዶችም ውበታቸው መስፈሪያ ላይ ቢቀመጥ በሌላ አካባቢ ከምንገኝ ወንዶች በእጥፍ ይልቃል:: በዘመን አመጣሽ የጥርስ ሳሙና ሳይሆን በአካባቢያቸው የተለያዩ የጥርስ መፋቂያዎች የሚያፀዱት የባቲ ወጣቶች ጥርስ ከወተት ቢነጣ እንጂ አይተናነስም::

ስለ ባቲ ከተማ እና በውስጧ ስለሚገኙት ውቦች በርካታ ድምፃዊያን በርካታ መወድሶችን አቅርበዋል:: እኛም የጥቂቶቹን ስንኞች እየገለጽን ምን ለማለት ፈልገው ነው? የሚል መላ ምታዊ አስተያየት እናቀርባለን::

ኧረ ባቲ ባቲ ባቲ ገንደልዩ
ይመሻል ይነጋል ቆንጆ ልጅ እያዩ
አዎ፣ ከባቲ ከተማ ውስጥ እግርዎትን አስኪደክመዎ ድረስ ቢጓዙ የሚያዩት ቆንጆዎችን ብቻ ነው:: በእርግጥ የባቲ ቆንጆዎችን መግነጢሳዊ ቁንጅና እያዩ እግርዎት ብዙ አልጓዝ ካላለዎት በቀር መሽቶ እስኪነጋ ቢጓዙ ባቲ ውስጥ የሚያዩት ቁንጅናን እና ቁንጅናን ብቻ ነው::

ኧረ ባቲ ባቲ ባቲ ከተማው
ከሚበላ በቀር የሚጣል የለው
ለኔ በዚህ ስንኝ ውስጥ የሚበላ ተብሎ የተገለፀው የፈረደበት የባቲዎች ውበት ነው:: የባቲዎች ውበት ደግሞ ከሚታይ በቀር የሚተው/ከሚበላ በቀር የሚጣል/ የለውም እንደተባለው ነው::
ባቲ ገበያ ላይ ቅል ይዤ እንደለማኝ
አንቺን አላገኘሁ ወይ ገበያው አልቀናኝ
የባቲን ቆንጆ ከጅሎ ያልቀናው ሰው ካለ እሱ በእርግጥ ለምኖ ከማጣት በላይ የተጐዳ ነው:: ልመና በሰው ዐይን የሚያስገርፍ ከችግር ሁሉ ችግር በመሆኑ የከጀሏትን የባቲ ጉብል አለማግኘት ለምኖ ከማጣትም የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም::

እንደ ባቲ መንገድ አንደ ወዲያኛው
በዓመት አንድ ቀን ነው የምትገኝው
የባቲን ቆንጆ እንደ መስቀል ወፍ በዓመት አንዴ ብቻ ማየት በእጅጉ ያሳምማል:: ሲያዩዋት ውለው ሲያዩዋት ቢያድሩ የማትጠገበውን የባቲ ውብ በዓመት አንዴ ብቻ ማየት ከዐይን ረሀብም አልፎ ህመም መሆኑ አይቀሬ ነው::

እንደ ባቲ መንገድ አንደ ቁልቁለቱ
ይሄን ያህል ነወይ የፍቅርሽ ጽናቱ
በባቲዋ ጉብል ልቡ የሸፈተ ሰው ፍቅሯ በልቡ መጽናቱ ሳይታለም የተፈታ ነው:: ቀድሞ አለመለከፍ እንጂ በባቲዎች ውበት ከተነደፉ በኋላ ቁንጅናቸውን ከዐይኔ ገለል በልልኝ ማለት አይቻልም:: ሰው ወዳዶቹን ባቲዎች የልብን በር ከፍቶ ካስገቡ በኋላ ውጡልኝ ማለት ይቸግራል:: መፍትሄው ፍቅርን ከባቲዎች ጋር ማጽናት ብቻ ነው::

ሰው ሁሉ በሽታው ራስ ወገቡን ነው
እኔስ በሽታዬ ባቴ ነው ባቴን ነው
የዚህ ዘፈን ቅኔው የባቲን ውቦች ብቻ ሳይሆን ራሷን ባቲንም አለመወደድ አይቻልም የሚል አንድምታ ያለው ነው:: በእርግጥም የባቲ ከተማ የውቦች መፍለቂያ ሆና እያለ ከማህፀኗ የወጡትን ውቦች ብቻ እያደነቁ ራሷን ውቦቹን ፈጣሪዋን ባቲን አለማድነቅ አይቻልም:: የብዙ ሰው በሽታው ራስ እና ወገቡን ሲሆን የዘፋኙ በሽታ ግን “ባቱን” ባቲን የመሆኑ ቅኔም ለዚሁ ነው::

እኛ ለአብነት ያህል እነዚህን አነሳን እንጂ የባቲ ከተማን እና በውስጧ ያሉትን ውቦች ለማወደስ ብዙ ድምፃዊያን ብዙ ነገሮችን ብለዋል:: የባቲዎቹ ደግነት እና ቁንጅና አሁንም ድረስ እንደ ዥረት እየፈሰሰ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ አየተሸጋገረ በመሆኑ ነገም ስለ ባቲ እና ስለ ቁንጅናዋ ገና ብዙ ይባላል::

ከሀገራችን የሙዚቃ ቅኝቶች አንዱን “ባቲን” በስሟ የያዘችው የባቲ ከተማ ሕዝቧ እንግዳ ተቀባይ እና ሰው ወዳድ ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፤ እኛም ለሥራ ጉዳይ ወደ ውቦቹ መንደር ባቲ ሄደን ያረጋግጥነው ይሄንኑ ነው::

ከባቲ ነዋሪዎች ውስጥ አንዳንዶቹን በከተማቸው ስም ስለሚጠራው የባቲ ቅኝት ያውቁ እንደሆነ ጠይቀናቸዋል:: አቶ አደም ሙሄ የባቲ ከተማ የረዥም ጊዜ ነዋሪ ሲሆኑ “የባቲ ቅኝት ሲባል እሰማለሁ፤ የትኛው የሙዚቃ ቅኝት የባቲ እንደሆነ ግን አላውቅም” ሲሉ መልሰውልናል:: አቶ አደም ከባቲ ቅኝት ይልቅ ስለ ባቲ የተዘፈኑ ብዙ ዘፈኖችን እንደሚውቁም ነው ያጫወቱን::

ሌላኛዋ የባቲ ተወላጇ ማህደር ጌታሰው ስለ ባቲ ቅኝት ምን እንደምታውቅ ጠይቀናት የባቲ ቅኝት ከአራቱ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ እና ቀሪዎቹ አንቺ ሆዬ፣ አምባሰል እና ትዝታ መሆናቸውን ገልፃልናለች:: የባቲ ቅኝት ከአራቱ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝቶች አንዱ ስለመሆኑ እንጂ በትክክል የትኛው ቅኝት የባቲ እንደሆነ አለማወቋንም ነው ማህደር የነገረችን::

አቶ ሁሴን ኢብራሂም በባቲ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ ናቸው:: ባቲ ከተማ ስሟን ያገኘችው “ባቴ” ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሲሆን የአማርኛ ትርጓሜውም ወጣህ? እንደማለት ነው ብለውናል:: የባቲ ከተማ እንዳሁኑ ከተማ ከመሆኗ በፊት ጫካ የዋጣት መንደር ስለነበረች የአካባቢው ነዋሪዎች በዚያ ጫካ ውስጥ ገብተው እንጨት ሲለቅሙ ከዋሉ በኋላ ከጫካው ወጥተው ገላጣ ቦታ ላይ ሲገናኙ “ባቴ?” ከጫካው ወጣህ? ተባብለው መጠያየቃቸውን ተከትሎ ያሁኗ ባቲ ባቴ ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ስሟን ስለማግኘቷ አፈ ታሪኮች እንደሚናገሩ ነው አቶ ሁሴን የገለፁልን::

የባቲ ስያሜ ባቴ ከሚለው በኦሮምኛ ለጨረቃ ከተሰጠው ስያሜ የተወሰደ ነው የሚል ሁለተኛ መላ ምት እንዳለም ነው አቶ ሁሴን የነገሩን:: ባቲ ከነዚህ ሁለት በአፈ ታሪክ ከሚነገሩ ቃላት ስሟን ወስዳ ዛሬ ላይ ባቲ ሆናለች::

ስለ ባቲ ቅኝት አብዛኛው የአካባቢያችን ሰው ያውቃል የሚል ግምቱ አለኝ የሚሉት አቶ ሁሴን እንኳንስ የባቲ ነዋሪዎች ይቅሩና ከባቲ ውጪ ያሉ ነዋሪዎችም ባቲ የሚለውን ቃል ሲሰሙ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደሯ የባቲ ከተማ በተጨማሪ ፈጥኖ ወደ አእምሮሯቸው የሚመጣው የባቲ ቅኝት የሚባለው የሙዚቃ የቅኝት ዓይነት እንደሆነ አንጠራጠርም ብለዋል::

የባቲ ከተማ አስተዳደር የራሱ የሆነ የባህል ኪነት ቡድን እንዳለው የነገሩን አቶ ሁሴን የባህል ቡድኑ በአብዛኛው የሚጫወታቸው የባቲ ቅኝት የሆኑ ሙዚቃዎችን እንደሆነም ገልፀውልናል:: የባቲ ቅኝት ሲነሳ በአብዛኛው የሙዚቃ አድማጭ ዘንድ ማሪቱ ለገሰ እና ሌሎችም ወደ ምናባችን ይመጣሉ ያሉት አቶ ሁሴን የባቲ ቅኝት አፈጣጠርን እና ከሌሎች ቅኝቶች የሚለይባቸውን ነገሮች ለሙዚቃ ባለሙያዎች ከመተው በቀር እሳቸውን ጨምሮ ጽ/ቤታቸውም መረጃዎቹ እንደሌሉት ነው የባቲ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪው አቶ ሁሴን ኢብራሂም የገለፁልን::


(እሱባለው ይርጋ)
ኅዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም

ተፈትኖ በወደቀ የዘውግ ፌደራሊዝም የኢትዮጵያ አትፈወስም!---------------------ይህንን ጽሑፍ እንዳጋራ ያነሳሳኝ ሰሞንን የብልጽግና ሹማምንት በበደል ትርክት ተጠንስሶ ዘውጌ ማንነት...
17/10/2022

ተፈትኖ በወደቀ የዘውግ ፌደራሊዝም የኢትዮጵያ አትፈወስም!
---------------------

ይህንን ጽሑፍ እንዳጋራ ያነሳሳኝ ሰሞንን የብልጽግና ሹማምንት በበደል ትርክት ተጠንስሶ ዘውጌ ማንነት ላይ የተንጠለጠለውን "የፌደራል ሥርዓት" ከችግራችን መውጪያ "መድኃኒት" አድርገው ሲሰብኩ በማየቴ ነው።

ፌደራሊዝም የሚለው ቃል ሥረወ ቃሉ የላቲኑ ፌደስ (Feodus) ሲሆን ትጓሜውም ‹‹ቃል ኪዳን›› ማለት ነው፡፡ (እንደ አላዛር እና ኦስተሮም ጥናት) የፌደራል ሥርዓት በዓለማችን ከተዋወቀ 230 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን በአሜሪካ በ1789፣ በስዊዘርላንድ በ1848፣ በካናዳ 1867፣ አውስትራሊያ ከ1901 ጀምሮ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ካናዳዊው የፌደራሊዝም ተመራማሪ ዋትስ “Federalism, Federal Political Systems, and Federations” በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናት ‹‹በምሥራቅ የአውሮፓ ሀገሮች እና በሦስተኛው ዓለም ሀገሮች ፌደራሊዝም እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ወድቋል›› ብለዋል (Watts1998)፡፡ ሽናይደር የተባሉ ሌላ አጥኚ በበኩላቸው የዩጎዝላቪያን እና የታላቋ ሶቪየት ኅብረት መፈረካካስ ምንጩ የተከተሉት የፌደራል ሥርዓት መሆኑን በጥናታቸው ሞግተዋል (Snyder 1999)፡፡

ሶቭየት ኅብረትና ዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበረው ፌዴራሊዝም ከላይ ወደታች የተጫነ እንጂ የህዝቦች ቃልኪዳን ውጤት አልነበረም። ለዚህ ነው ሁለቱም ፈራርሰዉ ለብዙ ጥቃቅን ሉዓላዊ መንግሥታት መፈጠር ምክንያት የሆኑት።

በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ፌደራሊዝም ሥርዓት በሁለት መንገዶች ሊዋቀር ይችላል፡፡ (ጋሽ ኤፍሬም ማዴቦ ‹‹አብረን እንኑር›› እና ‹‹ሀገር እናድን›› ሲል ይፈታቸዋል) (Stephan 2001)

የመጀመሪያው አማራጭ ሉዓላዊ የሆኑ ሀገሮች በደኅንነት ወይንም በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ወደ አንድ ስብስብ ለመምጣት (Coming Together) ሲወስኑ የሚፈጠር ሲሆን ሁለተኛው በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች መካከል የብሔር ወይንም የቡድኖች ፍላጎቶችን ለማቻቻል ሲባል የሚፈጠር ነው፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አሠፋ ፍሰሐ “Federalism and the Accommodation of Diversity in Ethiopia: A Comparative Study’’ በሚል ርእስ ባሳተሙት ጥናት እንደሚጠቁሙት የአፍሪካ ፌደራሊዝም ቅኝ ግዛትን ተከትሎ አፍሪካውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት የመጣ ሥርዓት ነው፡፡ ጋናዊው ክዋሜ ንኩሩማን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮች ፌደራል ሥርዓትን አምርረው የተቃወሙት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡

በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ የመረጡት የአስተዳደር ዘይቤ በቅኝ ገዢዎች የተጫነባቸውን በዘውግ ማንነት (በብሔር) ላይ የተዋቀረ ፌደራሊዝም አሽቀንጥው በመጣል አንድነታቸውን ለማጠንከር አሀዳዊ ሥርዓት ማስፈንን መርጠዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በርካታ አፍሪካውያን "ፌደራሊዝም ጠባብ ብሔርተኝነትን ያስፋፋል" በማለት አምርረው ይቃወሙታል። (Kimenyi 1998)

ቅኝ ገዢዎች ለአፍሪካ ምንም ጥሩ ነገር ይዘው አልመጡም፡፡ ጥሩ ነገር ካመጡም ለነሱ በጣም ጠቅሟቸዋል ማለት ነው፡፡ ፌዴራሊዝምን የአፍሪካን ሕዝብ ከፋፍለው ለመግዛት ተጠቅመውበታል፡፡

በናይጄሪያ የፌደራል ሥርዓት ላይ ጥናት በማቅረብ የሚታወቁት J.Isawa Elaigwu “ፌደራሊዝም በአፍሪካ ግጭት ማርገቢያ ሳይሆን የግጭት መንስኤ ነው” ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች በሕገመንግሥቶቻቸው የፖለቲካ ፓርቲን በብሔር ማደራጀትን ክልከላ እስከመጣል መድረሳቸው ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ጨምሮ 10 ያህል የአፍሪካ ሀገሮች የፌደራል ሥርዓትን ተከታይ ሲሆኑ የተቀሩት ከ40 በላይ ሀገራት አሀዳዊ ሥርዓት ተከታዮች ናቸው፡፡

የደርግ ሥርዓትን በማስወገድ መንበረ ሥልጣኑን የወረሰው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ የተከተለው ዘውግን (ብሔርን) መሠረት ያደረገው የፌደራል ሥርዓት አወቃቀር ምንም እንኳን "ለህዝቦች ሰላም እና አንድነት ያመጣል" ቢባልም በተግባር እንደታየው ባለፉት ሠላሳ ዓመታት የግጭት እና የቀውስ ምንጭ ሆኗል።

አሁን በሥራ ላይ ያለው የፌዴራል ሥርዓት አንደኛ በህሕዝብ መልካም ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በጉልበትና በኃይል የተጫነ ፌዴራሊዝም ነው፡፡ ሁለተኛ መሠረቱ በየትም ያልታየ ብሔር እና ቋንቋ ብቻ ነው፣ ሦስተኛ የፌዴራል ክልሎቹ ሉዓላዊነት የተረጋገጠ አይደለም፡፡ አራተኛ- ከዲሞክራሲ ጋር የማይተዋወቅ ፌዴራሊዝም ነው።

በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ይተተበተበውን የዘውግ ፌዴራል ሥርዓት ነው እንግዲህ ሰሞኑን "ኢትዮጵያን ከግጭት የሚያወጣት ክትባት ነው" እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት። ይህንን የፌደራል ሥርዓት ታቅፈን የግጭት እና የድህነት ምንጭ መሆኑ ሊገርመን አይገባም፡፡

Monahan እና Biyant የተባሉ አጥኚዎች በጥናታቸው እንደሚገልጡት በዓለማችን ከሚገኙ ከ89 ሕገ መንግሥታት መገንጠልን የሚፈቅዱት ሰባቱ (ኦስትሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፣ ሲንጋፖር፣ ቅዱስ ክርሰቶፈርና ኔቪስ፣ የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እና ቸኮዝሎቫኪያ) ብቻ ሲሆኑ ከሰባቱ ሁለቱ ሀገሮች (ሶቪየት እና ቸኮዝሎቫኪያ) ብትንትናቸው ወጥቷል።

ከላይ የጠቀስኩት የተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አሠፋ ፍሰሐ ጥናት ማጠቃለያ እደሚመሰክረው ኢትዮጵያ ውስጥ የተተከለው የጎሳ (የብሔር) ፌደራሊዝም በተግባር ተፈትኖ ወድቋል፡፡ (Asefa 2007)
በህወሓት የተዘጋጀልን እና በሥራ ላይ ያለው የሀገራችን ሕገ መንግሥት ሀገሪቱን የዜጎች ሳትሆን የዘውጌዎች (የብሔሮች) አክስዮን አድርጎ ቀርጿታል። በዚህ ስሌትም የሀገሪቱን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የደኅንነት ተቋማትን በጎሳ ለተደራጁ በማስረከቡ በብሔር ከረጢት የማይመደቡ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር እና አድርጓቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴራሊዝም ያስፈልጋል ተብሎ የሚታመነው ብዝኀነትን ያቀፈ ሀገራዊ አንድነት እንዲፈጠር፣ ለዘመናት የተጠየቀውን ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ስለሚመልስ ኅዳጣንን (አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን) እንዳይበድል ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም መሠረቱን ያደረገው የልዩነት ምልክት በሆነው በብሔር ላይ በመሆኑ ያስወግዳል የተባለውን ዋናውን የአገሪቱን ችግር አባባሰው እንጂ አልፈታውም፣ ሁሉንም ነገር ከብሔር ጋር አያያዞ ሀገራዊ አንድነትን አዳከመው እንጂ ጠንካራ አንድነት አላመጣም፣ አብዛኛው አናሳውን እንዲረግጥ መንገድ ከፈተ እንጂ ዲሞክራሲን አላመጣም፡፡

አሁን ባለው ሕገመንግሥት ማህቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያን ችግሮች መፍታት በፍጹም አይቻልም፡፡ ይህንን የሀገርን ሉዓላዊነት ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝቦች ለሚባሉ ልዩነታቸውና አንድነታቸው በውል ለማይታወቅ ስብስቦች የሰጠውንና በተለይ ለብሔሮች ገደብ የለሽ መብት እንጂ መብታቸውን ከምንም ዓይነት ግዴታ ጋር የማይያያዘውን ሕገመንግሥት ይዘን እስካሁንም እንደ ሀገር መዝለቃችንም በራሱ አስገራሚ ነው።

ከላይ ከጠቃቀስኳቸው እና ሌሎች ጥናቶች በመነሳት ሀገራችን ኢትዮጵያ የተከተለችው ዘውግን (ብሔርን) መሠረቱ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት አደረጃት ተፈትኖ የወደቀ እና በተጨባጭ የሚከተሉት ሀገራዊ ችግሮች አስከትሏል እላለሁ፡፡

1) ዜጎች ከክልል ወደ ክልል በነጻነት እና በሰላም ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ ስለማያበረታታ ሀብት ፈጣሪዎችን በማብዛት ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ የምናደርገው ጥረት ከንቱ ልፋት አድርጎታል፡፡

2) ዕውቀት እና ሀብት ያላቸው የሀገሪቱ ዜጎች በመላዋ ሀገሪቱ ያለሰቀቀን ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዳይፈጥሩ እና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይሰፍን አድርጓል፡፡

3) በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት እንደታዘብነው የክልል ከተሞች ጎብኚዎች እና ሥራ ፈጣሪ ባለሀብቶች በማጣታቸው በከፍተኛ ፍጥነት እየተዳከሙ እና እየተፋዘዙ እንዲመጡ አድርጓቸዋል፡፡

4) በክልል ከተሞች ሀብት በመፍጠር እና ቀጣሪ በመሆን የሚታወቁ የሀገሪቱ ዜጎች ከክልሎቹ ትብብር እና ድጋፍ በማጣት አልፎ አልፎ በሚነሱ ብሔርን መሠረት ባደረጉ ግጭቶችም ሰለባ በመሆናቸው ሥራቸውን እየተዉ ወደ ማዕከል (አዲስ አበባ) ስለሚሰበሰቡ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመላ ሀገሪቱ እየተዳከሙ ሄደዋል፡፡

5) ከግብር ከፋይ ዜጎች የተሰበሰቡ፣ በብድር እና በልመና የተገኙ የሀገሪቱ ውሱን ሀብቶች የፈሰሰባቸው የፌደራል ተቋማት በየውቅቱ የሚገነፍሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች የጥቃት ዒላማ ስለሚሆኑ ለትውልድ የሚተርፍ እዳ እና ኪሳራ ምክንያት ሆኗል፡፡

የመፍትሔ ሀሳቦች!

መፍትሔው የዝግጅት ሂደቱን በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ በመሻገር ላይ ባለው ሀገራዊ ምክክር ሁሉንም ባለድርሻዎች ያሳተፈ የሰከነ እና እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ሲሆን ምክክሩ የሚከተሉትን ውጤት ያስገኛል ብዬ ተሥፋ አደርጋለሁ፦

1) የችግሮቻን ምንጭ የሆነውን የዘውግ (የብሔር) ፌደራሊዝም በዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም መተካት፤

2) የሀገር ባለቤትነትን ሁላችንንም እኩል በሚያደርገን እና በሚያመሳስለን የጋራ እሴት በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ ማቆም፤

3) የሀገሪቱን የመንግሥት አወቃቀር የብሔሮችን ባህል፣ ቋንቋ እና ሌሎች የቡድን መብቶችን በሚያከብር ነገር ግን መሠረቱን ዜግነት ባደረገ ፍልስፍና መተካት !

4) የኢኮኖሚ መዋቅራችንን በሂደት ማኅበራዊ ፍትህ በሚያሰፍን (ለሁሉም ዜጎች እኩል እድል በሚሰጥ እና የተለየ ድጋፍ የሚያሻቸውን በማገዝ) ሥርዓት መተካት !

ሠላም !

አርክቲኬት ዮሀንስ መኮነን
የኢዜማ ምክትል መሪ

Via Fan Man Addisየተፈጠረው ምንድን ነው?[ብዙ ስራዎች አሉብን፤ ብዥታውም መጥራት አለብት።]""""""""""""""""""""“"""""" "የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ  የተጣለበትን ሃገ...
13/10/2022

Via Fan Man Addis

የተፈጠረው ምንድን ነው?
[ብዙ ስራዎች አሉብን፤ ብዥታውም መጥራት አለብት።]
""""""""""""""""""""“"""""" "
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተጣለበትን ሃገራዊ ግዴታ እንዲወጣ ቀንም ማታም ሁሉም ሰራተኛ በሚባል ደረጃ በርብርብ ሰርቷል፤ ለሁለተኛው ምዕራፍም ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ለ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከተመደለት የተማሪዎች ቁጥር አንፃር፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በተጨማሪ ዩኒበርሲቲው ተማሪዎቹ በአቅራቢያቸው መፈተን እንዲችሉ አስቸኳይ ዝግጅት አድርጓል። ለዚህም የጤና ካምፓስ የፈተና ማዕከል አንዱ ነው። ከአሁን በፊት ለ ሀገር አቀፍ የህልውና ዘመቻ ስልጠና በተለያየ ዙር አገልግሎት ሲሰጥ ስለነበር በአጭር ጊዜ ማዘጋጀት ሰፊና አድካሚ ስራ የሚጠይቅ ነበር።
“
ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች ራቅ ወዳሉ ቦታዎችና ሌሎች ክልሎች ሂደው እንዳይፈተኑ ለአላስፈላጊ እንግልት እንዳይዳረጉ ሲባል በተወሰደው ቆራጥ ውሳኔ የወደሙት ተጠግነው: ቆሻሻው ተጸድቶ እና ከባዶ ተነስቶ ከ4ሺ (4000) በላይ ፍራሽ፣ ችፑድ እና አልጋ ገዝቶ ዶርሚተሪዋችን አደራጅቷል። ዩኒቨርስቲው ለካምፓሱ ውሃ በፋጥነት አስገብቷል። የተማሪ ምግብ ቤት (ካፋቴሪያ) አዘጋጅቷል።
“
ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር (መምህራን ኮሌጅ: ከፓሊስ ኮሌጅ እና የተለያዩ የግል ኮሌጆች) የመፈተኛ ወንበር በመስብስብ አንድ ክላስ ውስጥ 36 ተማሪ የሚይዝ 122 የመፈተኛ ክፍሎችን ተዘጋጀ።
በዩኒቨርስቲው የማኔጅመንት አባላት ቅርብ ክትትል ተገምግሞ የተመደቡ 4333 ተማሪዋችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑ ተረጋገጠ። ከ26/01/2015 ጀምሮም ተማሪዋችን ተቀበለ።
“
በ29/01/2015 የዩኒቨርስቲውን አካዳሚክ ምክትል ፕረዘዳንትን ጨምሮ ከትምህርት ሚኒስተር በመጡ አስተባባሪዎች ስለፈተናው ገለጻ ተደረገ።
በ30/01/2015 ዓ.መ የመጀመሪያው ፈተና ተጀመረ። ፈተናው እንደተጀመረ አልፎ አልፎ ጬኽት የሚያሰሙ ጥቂት ሴት ተማሪዎች ነበሩ። ምናልባት የጭንቀት ስሜት ሊሆን ይችላል። በርግጥ ሆን ብሎ የሚያደርግም አልታጣም ወይም ነበር። ይንንም በብዙ ርብርብ በተለይ በተማሪ ህብረት አባላትና ድጋፍ ሰጭዎች ብርቱ ስራ ለመቀነስ ተችሎ ያለምንም እንከን ፈተናው ቀጠለ።
“
የሁለተኛውን ፈተናም ከሰዓት በኋላ ሁሉም ተማሪ ባለበት ተጀመረ። ፈተናው ሂሳብ ትምህርት ነበር፤ የተሰጠውም ሰዓት 3፡00 ሠዓት። ሆኖም በርከት ያለ ቁጥር ያለው ተማሪ በ30 ደቂቃ ውስጥ መልስ ሞልቶ ወጣ። በጣም ስላስገረመን አንዳንድ ተማሪዎችን ለምን ወጣችሁ ብለን ጠይቀን ነበር። 4 ፈታኝ ከፊታችን ቆሞ ኦክስጅንም አጠረን እኮ የሚል የፌዝ መልስ መለሱልን። ነገርግን ይህ ኩረጃ የማስወገድ ስራው አካል ነው። በየክፍሉ ቁጭ ብለው እስከመጨረሻው የሚፋለሙ ተማሪዎች ግን ነበሩ፤ ሰዓታቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ፈተናቸውን የጨረሱ!፡፡ እስከ ምሽቱ 3:00 አምሽተን፣ አረጋግተን ሰላም መሆናቸውን ስናረጋግጥ ወደቤታችን ተመልሰን። ዕለት አንድ!
“
በሁተኛው የፈተና ቀን ሊነጋጋ ሲል 11:00 ስዓት ላይ ከትምህርት ሚኒስተር ከተላከው የፈተና አስተባባሪ ስልክ ተደወለልን። አነሳን።ተማሪዎች ጭፈራ እንደጀመሩና ለመውጣት ወደ በር እየተጠጉ እንደነበር ተነገረን። ተደዋወልንና በድንጋጤ ፊታችንን እንኳ በወጉ ሳንታጠብ አጠገባችን ያገኘነውን ልብስ እየለበስን ወደ ካምፓሱ አቀናን።
“
ተማሪዋችም ጸጥታ ሃይሉ ብዙ ተለምነው አንፈተንም ወደቤት እንሄዳለን ብለው ጥሰው ግቢውን ለቀው እየጨፈሩ በጋራ ሲጓዙ መንገድ ላይ ተገጣጠምን።እዚህ ላይ የ ፀጥታ ሀይሉ ጥረት የሚደነቅ ነበር፤ በንብረትና በሰው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሀላፊነቱን ተወጥቷልና። ለአዲስ መንገድ መስሪያነት የተደፋ ብዙ ድንጋይ ባለበት አካባቢ ስለነበር አንስተው ይመቱን ይሆን የሚል ፍርሃትና ጥርጣሬ እንዳደረብን ግን አልደብቅም። ነገርግን ምንም ይፈጠር ብለን የዩኒቨርስቲውን ፕረዚዳንት ጨምሮ ፊትለፊታቸው ቆመን ለመናቸው።
“
ብዙ የውሸት መፈክር እየፎከሩ እና እየጨፈሩ እንደቆምን ጥለውን ሄዱ። ድካማችን ከንቱ ሆነ።
በቀጥታ የወጡትን ትተን ግቢ ውስጥ ወዳሉ ተማሪዋች አመራን። ሰብሰብ ያሉትን እንደሁኔታው በድምጽ ማጉያ እንዲሁም በየግል ለመናቸው። እነሱም አንፈተንም አሉን። ያቀረቡት ተጨባጭ ምክንያት የለም። በመጨረሻ ግን የቀሩትን ተማሪዋች ከብዙ ልመና በኋላ ተሳክቶልን የፈተና ጊዜው ሳያልፍ ወደ መፈተኛ ክፍላቸው እንዲገቡ አደረግን። እየዞርን ስንቆጥርም ከ2700 በላይ ተፈታኝ ፈተና ላይ ተቀምጧል። በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናቸውንም ጨረሱ። 1200 አካባቢ የሚሆኑ ተማሪዎች ግን ወደየመጡበት ተበተነው ፈተናውን ሳይጨርሱ ሄደዋል።
“
ከቀሩ ተማሪዋች መረጃ ስናጣራ ችግሩን የፈጠሩትና ሲያስተባብሩ የነበሩት ባለፈው ዓመት ተፈትነው ያላለፋ ነገር ግን ድጋሜ ለመፈተን የተፈቀደላቸው ናቸው።
ሲሉት የነበረውም ለዚህ ማስረጃ ነው። "ተፈተነን የማናልፍ ከሆነማ መውደቃችንን የሚገልጽ ሁለተኛ ካርድ ምን ያደርግልናል" ይሉ ነበር። ከነዚህ ተማሪዎች ጋር ምንም ሳይገባው የሄደ የድሃ ልጅ ብዙ እንደሚሆንም ከቀሩ ተማሪዋች ተረድተናል።
በሄዱ ተማሪዎች እናዝናለን: አንገት ያስደፋል። ውርደትም ነው😪 ብዙ መስራት ያስፈልጋል። ትምህርት ቤት ድረስ ወርዶ መምህራንና ተማሪዎች ጋር መስራት! የትውልድ ግንባታ!
“
የመጀመሪያው ዙር ፈተና ክስተት ይኸው ነው። ሌላ ነገር የለም። እያንዳንዱ ሰው ያልገባውን፣ ያላየውንና ያልተጣራ ወሬ ማራገብ የለበትም። ማገዝ ሲገባን ልጆቻችንንስ ለምን እንረብሻቸዋለን። በራሱ የሚተማመን እና መንፈሰ-ጠንካራ፣ በአሉባልታ የማይነዳ ትውልድ መፍጠር አለብን። ተማሪዎችም የወላጆቻችሁን የዓመታት ልፋት መና ማስቀረት የለባችሁም። የሁለተኛ ዙር ተፈታኞ ከዚህ ብዙ ተምረው በተረጋጋ መንፈስ ለመፈተን እንደሚመጡ እምነታችን ነው። ራዕይ የሚሳካው በምክንያታዊነትና ጠንካራ ስራ ብቻ ነው። መረበሽና አብዝቶ መጨነቅ አያስፈልግም።በናንተ ውስጥ የሀገር ተስፋ ስላለ ሙሉ እንክብካቤ ይደረግላችኋል።
መልካም ዕድል!

የበላይ ዘለቀ እና የፋሺስት ኢጣሊያ ድርድር ታሪከበላይ ዘለቀ ከውስጥም ከውጭም ጠላቶች ነበሩአቸው ለምሳሌ ቀኛዝማች ሰማነባዋ የተባሉት የኢጣሊያ የባንዳ አለቃ ስለነበሩ በቂ መሣሪያ እና 500...
11/10/2022

የበላይ ዘለቀ እና የፋሺስት ኢጣሊያ ድርድር ታሪከ

በላይ ዘለቀ ከውስጥም ከውጭም ጠላቶች ነበሩአቸው ለምሳሌ ቀኛዝማች ሰማነባዋ የተባሉት የኢጣሊያ የባንዳ አለቃ ስለነበሩ በቂ መሣሪያ እና 500 ወታደር ይዘው በቢቸና አውራጃ በሸበል በረንታ ወረዳ ልዩ ስሙ አባራ ጊዮርጊስ ከተባለው ቦታ ገጥመዋቸው ነበር ። በተደረገው ውጊያ ቀኛዝማች ሶማ ነገዎን ገድለው፣ ከሞት የተረፉትን ጀሌዎቻቸውን በሙሉ ከነመሣሪያዠው ማርከው ካስቀሩ በኋላ በላይ ዘለቀ እንዲህ አሉ፡- “እናንተ ከኢጣሊያ ታዛችሁ ከአገራችሁ በመክዳት በዛው ቀን በተደረገው ጦርነት ከሞት ተርፋችሁ የተማረካችሁ ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ ወገኖቼ ሁሉ፣ አሁን በእኔ በኩል ምሬአችኋለሁ።

እናት ሀገራችሁን የምትወዱ ተከተሉኝ። ወይም አርሳችሁ ብሉ። ነገር ግን ሁለተኛ ለጠላት ገብታችሁ ብትገኙ እኔ የዘለቀ ለጅ ነገ እመጣለሁ” በማለት መክረው አሰናበቷቸው። በላይ ዘለቀ ሊወጋቸው የመጣውን የኢጣሊያ ጦር ከመመከት አልፈው ድልን መቀናጀት ዋናው መለያቸው እየሆነ መጣ። የኢጣሊያ ጦር ሁሌም እየተሸነፈ በመሄዱ ተስፋ በመቁረጥ የበላይ ዘለቀን ባለቤት ወ/ሮ ሸክሚቱ አለማየሁን እና የባለቤታቸውን እህት ወ/ሮ ዘውዲቱ አለማየሁን ገድሎ ልጃቸው ወ/ት የሻሽወርቅ በላይን ማርኮ ሄደ። ከዚህ በኋላም የበላይ ዘለቀ እልህም እያየለ በመምጣት ብዙ የኢጣሊያ ወታደሮችን ድል አደረጉ። በመጨረሻም ጠላት ከበላይ ዘለቀ ጋር ታርቆ፣ ሠላም ፈጥሮ መኖር ፈለገና የሚከተለውን መልዕክት ላከላቸው።
“ይድረስ ለልጅ በላይ ዘለቀ። ለኢጣሊያ መንግስት ብትገባ ጥቅም እንጂ ጉዳት አያገኝህም። ጐጃምን በእንደራሴነት ይሰጥሃል። ስለዚህ በሰላም ግባ የኢጣሊያ መንግስት መሀሪ ነውና በአጠቃላይ ሙሉ ምህረት ያደርግልሃል” የሚል ነበር። በዚህ ግዜ ጀግናው በላይ ዘለቀም ይህንን የኢጣሊያ ደብዳቤ በሰሙ ጊዜ ለተፃፈው ደብዳቤ መልስ ሲፅፉ እንዲህ አሉ፡-
“ይድረስ ለኢጣሊያ መንግሥት፣ ከሁሉ አስቀድሜ ሁልጊዜ ሰላም ላንተ ይሁን እያልኩ የማክበር ሰላምታዬን አቀርባለሁ። ከሰላምታዬ ቀጥዬ የምገልፅልህ ነገር ቢኖር ከኢጣሊያ መንግሥት የተፃፈልኝ ደብዳቤ ደርሶኛል። በአክብሮት ተቀብያለሁ። ተመልክቸዋለሁ። በደብዳቤው ላይ ያለውን ቁም ነገር ያዘለ ቃል ስመለከተው እጅግ በጣም የሚያስደስት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ስለዚህ ልጄን ከመለስክልኝ ጐጃምን ያህል ሀገር በእንደራሴነት ከሰጠኸኝ ከዚህ የበለጠ ሌላ ምን እፈልጋለሁ። ስለዚህ የኢጣሊያ መንግስት የሚያምናቸውን ታማኞቹን ይላክልኝና በእነሱ አማካኝነት አገባለሁ” የሚል ደብዳቤ መልሰው ፃፉለት።

በዚህን ጊዜ የኢጣሊያን መንግስት የበላይ ዘለቀን ደብዳቤ እንደደረሰው ሲመለከተው አስደሳች ሆኖ ስለአገኘው በላይ ዘለቀን በእርቅ አታሎ በእጁ ለማስገባት የዘወትር ምኞቱ ስለነበር በጉጉት ይጠብቀው የነበረው ሃሳብ የተሳካ መስሎት የራሱ የፍርድ ቤት ዳኞች ሆነው በታማኝነት ሲያገለግሉት የነበሩትን፣ በኢትዮጵያዊያን ወገናቸው በአርበኛው ላይ ይሰቀል ይገረፍ እያሉ ሲፈርዱና አርበኛ ያለበትን ቦታ ሲጠቁሙና መርተው በማሳየት ይረዱ የነበሩትን ታማኞችን እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማንና እነ ቀኛዝማች አደራው የተባሉትን ከነ አስተርጓሚ ጭምር ሆነው በላይ ዘለቀን በእርቅ አታለውና አባብለው በእጁ እንዲያስገቡለት ላካቸው። በኢጣሊያ መንግሥትና በጀግናው በላይ ዘለቀ መካከል በእርቅ መልክ ለማስማማት የተላኩት ሽማግሌዎችም መድረስ አይቀርምና እንደ እመጫት ነብር ከሚያስፈራው ኮስትር ፊት ቀረቡ። በዚህ ግዜ ጀግናው በላይ ዘለቀም ከፊታቸው ለተሰለፈው ጀግና አርበኛ እንዲህ ሲሉ ስለ እንግዶቹ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ።

“ጐበዝ ያገሬ ጀግና ሆይ፣ አንድ ግዜ አዳምጠኝ፤ እነዚህ እኔንና የኢጣሊያን መንግስት ለማስታረቅ የመጡ እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማ የተባሉት ሐገራቸውን ከድተው እዚሁ እላይዋ ላይ ሆነው ለኢጣሊያ ፋሽስት ለማያውቁት ለማይወለዱት፣ ለማይመሳሰላቸው በገንዘብ፣ በጊዜያዊ ጥቅም በመደለል ለጠላት መሣሪያ በመሆን በሐቅና በእውነት ለውድ እናት ሀገራቸው የሚዋደቁትን ንፁህ ኢትዮጵያዊያንን ሲያሰቅሉ፣ ሲያሳስሩ፣ ሲያንገላቱና ሲያስረሽኑ ከመቆየታቸው በላይ አሁን እኔንም በዕርቅ መልክ አስገብተው ለማስረሸንና አገሪቱ ተከላካይ ልጅ እንዳይኖራት የሚጥሩ ናቸው። ስለዚህ ምን ውሣኔ ማግኘት እንደሚገባቸው ጀግናው አርበኛ ሃሳብህን ስጥበት” ሲሉ ተናገሩ። በዚህ ጊዜ ጀግናው አርበኛም የመሪውን አነጋገር በጥሞና ካዳመጠ በኋላ እንዲገደሉ ተወሰነ።

በዚህ ጊዜ በአስታራቂነት የመጡት እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማ እነሱ በሌላ ሲፈርዱ ኖረው በእነሱ ላይ ይግባኝ የሌለው የአርበኛ ፍርድ በማግኘት ፅዋው ስለደረሳቸው በጥይት ተረሽነው በዛፍ ላይ ተሰቀሉ።

ከዚያም በኋላ ጀግናው በላይ ዘለቀም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢጣሊያ መንግሥት ፃፈ፡-
“ይድረስ ለኢጣሊያ መንግሥት፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ የላክልኝን እንግዶች እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማን በአክብሮት ተቀብዬ በማስተናገድ ሥፍራ ወይም ቦታ ሰጥቻቸዋለሁ። ላንተ ግን ትርጁማን (አስተርጓሚ) ብለህ የላከውን ሌላ ቦታ ስትልክ እንዳይቸግርህ ልኬልሃለሁ። ልጅህን እመልስልሃለሁ ለምትለው ለአንድ ልጅ ብዬ እናት ሀገሬን ኢትዮጵያን ከድቼ ከአንተ ጋር በእርቅ መልክ አልደራደርም። ከዛሬ ጀምረህ በእኔ በኩል ያለውን ምኞትህን አንሳ። እኔን ፈልገህ ማጥፋት እንጂ አንዲት ልጅ ወስዶ ማስጨነቅና ማጉላላት ደስ የሚልህ ከሆነ እንደፈለክ አድርጋት።

ሲሆን ለሷም የፈጠራት አምላክ እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ከአንተው እጅ ላመጣት እችል ይሆናል። ጐጃምን በእንደራሴነት ልስጥህ ለምትለው አንተ የሰው ሀገር ሰው ከምትሰጠኝ እኔው ሀገሬን በሥሬ አድርጌ አስተዳድረው የለም ወይ? የኢትዮጵያን አርበኛ እየቆማመጠ ለአሞራ በመስጠት በየዱር ገደሉ ወድቀህ ከመቅረት በመጣህበት መንገድ አገርህ ከመግባት በስተቀር አማራጭ የሌለህ መሆንህን በዚህ አጋጣሚ ልነግርህ እወዳለሁ” ሲሉ በላይ ዘለቀ ለኢጣሊያ መንግሥት ደብዳቤ ልከዋል።
በመጨረሻም የተማረከችውን ልጃቸውን የሻሽወርቅን እንደገና ተዋግተው ከኢጣሊያኖች እጅ ከነህይወቷ ለመማረክ ችለዋል። በአጠቃላይ በላይ ዘለቀ በአምስቱ ዓመት የነፃነት ተጋድሎ ውስጥ ከፊት የሚሰለፉ ታላቅ አርበኛ ናቸው።

ከ ሠንደቅ ጋዜጣ የተወሠደ

የቦረና ወረዳ አስተዳደር  በራያ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ።*********ወልዲያ - መስከረም 25/2015 (ቦረና ኮሙኒኬሽን) በቦረና ወረዳ የሚገኙ  ሁሉም ...
07/10/2022

የቦረና ወረዳ አስተዳደር በራያ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ።
*********

ወልዲያ - መስከረም 25/2015 (ቦረና ኮሙኒኬሽን)
በቦረና ወረዳ የሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ቡድን የከፈተብንን ጦርነት በአስተማማኝ ብቃት እየመከተና ድል እያስመዘገበ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ጥምር ጦር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሎጀስቲክ ድጋፍ አድርጓል።

በግንባር በመገኘት ድጋፋን ያስረከቡት የቦረና ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኡመር አሰፋ እንደገለፁት 123 የእርድ በጎች ፣50 ካርቶን ተምር፣90 ኩንታል በሶ እና 70 ደርዘን ውሀ በአጠቃላይ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሎጀስቲክ ከህዝባችን በማሰባሠብ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

አቶ ኡመር አያይዘውም ህዝባችን የሠጠንን ተልዕኮ የተሠበሠበውን ድጋፍ በአካል በመሄድ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦር አድርሱልን ጦርነቱ እስካልተቋጨ ድረስ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ባሉን መሠረት በቆቦ ከተማ ተገኝተን አስረክበናል ብለዋል።

በመጨረሻም አቶ ኡመር ይህንን ጦርነት ለመመከት የመጀመሪያው አማራጫችን አንድነታችንን ማጠናከር ነው ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጥምር ጦሩ ተወካይዮችም በህብረተሠቡ ደጀንነት እጅግ በጣም ኮርተናል እኛም የአገርን ሉአላዊነትን ለማስከበርና የህዝባችንን ሰላም ለማረጋገጥ ይህንን ጁንታ ወራሪ ቡድን ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመሆን ኢትዮጲያን ለማፍረስ ቢሞክርም እንደማይሳካለት በተግባር እያሳየነው እንገኛለን ብለዋል።

በተቃርኖ የተሞላች እናት ሀገር!! በአንድ በኩል የጎሳ ፖለቲካ ባመጣብን ቀውስ ምክኒያት በሰሜን በኩል ህዋሃትና የውጭ አጋሮቹ በከፈቱብን  ጦርነት እንደ አገር የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ...
04/10/2022

በተቃርኖ የተሞላች እናት ሀገር!!

በአንድ በኩል የጎሳ ፖለቲካ ባመጣብን ቀውስ ምክኒያት በሰሜን በኩል ህዋሃትና የውጭ አጋሮቹ በከፈቱብን ጦርነት እንደ አገር የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለማስወገድ እማማ ኢትዮጵያ በእኔ ግምት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶቿን እየገበረች ትገኛለች፣ ለባሰ ክፋ ጊዜ መከታ ሊሆኑ የሚችሉ icon የሆኑ ወጣቶቿን ለመስዋዕትነት ታቀርባለች ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ንፁሃን ዜጎች ያለምንም ከልካይ በታጣቂወች ይታረዳሉ።

በሌላ በኩል በማዕከሏ አአ በፉክክር በሚመስል ከመቸውም በበለጠ ቸበርቻቻ ፣ዓለምን ጉድ ባስባለ ሁኔታ የአደባባይ በዓላትን ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ታከብራለች። ዓለም አድንቆን ወይ ስቆብን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም።

በእኔ አመለካከት ይህ ድርጊት በፍፁም የሞራል ከፍታችንን አያሳይም።
እንደኔ መንፈስ ቢሆን ቀዝቀዝ ባለመልኩ በፍፁም ፀሎትና ምህላ ውስጥ ሆነን ብናሳልፈው የበለጠ ፈሪሃ ፈጣሪ ያለን ህዝብ መሆናችንን እናሳይ ነበር።

እሱ አንድየ አይናችንን ያብራልን!

ተስፋው ሙሐመድ

ለሰላም ዕድል ለመስጠት ሲል እየደፈረ፣እየዘረፈና እየገደለ ከመቀሌ ሰሜን ሸዋ የደረሰው የወያኔ ጉጅሌ እንደገና ለሰላም እድል ለመስጠት እየሞተና እየተወገረ  ከሰሜን ሸዋ መቀሌ መግባቱ የምታስ...
02/10/2022

ለሰላም ዕድል ለመስጠት ሲል እየደፈረ፣እየዘረፈና እየገደለ ከመቀሌ ሰሜን ሸዋ የደረሰው የወያኔ ጉጅሌ እንደገና ለሰላም እድል ለመስጠት እየሞተና እየተወገረ ከሰሜን ሸዋ መቀሌ መግባቱ የምታስታውሱት ሀቅ ነው🤣....

ባለፉት ጥቅት ወራት እንደገና ለሰላም ዕድል ለመስጠት ከመቀሌ ተመልሶ በአማራ ክልል ጥቂት ወረዳዎች ላይ ሲደፍር። ሲገድልና ሲዘርፍ የቆየው ይሄው የወያኔ ጉጅሌ ደግሞ እንደገና ለሰላም ዕድል ለመስጠት እየተቀጠቀጠና እንደ ቅጠል እየረገፈ ወደ መቀሌ እየተመለሰ መሆኑን የተለያዩ የወያኔ ቃል አቀባዮች እየተናገሩ ነው🤣

አሁን ጥያቄው ለሰላም እድል ለመስጠት ከመቀሌ እስከ ሲዖል አሸኛኘት የሚደረግላቸው መቼ ነው ነው?🤣

ከ 6000 በላይ በራሪ ወረቀት ታትሟል    ከመካነሰላም ወደ ግሸን ማርያም የተናጠል ጉዞ ተጀምሯል:: ለቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ገቢ ለማሰባሰብ በሚል በግሸን ደብረ ከርቤ አቅራቢ...
29/09/2022

ከ 6000 በላይ በራሪ ወረቀት ታትሟል

ከመካነሰላም ወደ ግሸን ማርያም የተናጠል ጉዞ ተጀምሯል:: ለቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ገቢ ለማሰባሰብ በሚል በግሸን ደብረ ከርቤ አቅራቢያ መግቢያው አካባቢ መንገድ ለመታው ምዕመን ውሀና ምግብ ለማቅረብ ዝግጅት የተደረገና የቤት ኪራይ እንድሁም የምግብ ግብአት ማሟላት ስራው ተጠናቆ ወንበር እና የማገዶ እንጨት እንድሁም የማብሰያ ቁሳቁሶች እና ዱቄት ከሌሎች ማቴሪያሎች ጋር በሁለት መኪና በመጫን የጉዞ ልዑኩ ወደ ግሸን ማርያም እየተመመ እያለ መስከረም 10 ቀን ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ያ የሰማችሁት ዜና ሊሰማ ችሏል::

አምስት ወንድሞቻችንንም በአደጋው አጥተናል:: የቆሰሉና አሁን ላይ ሆስፒታል ውስጥ ያሉም አሉ:: እግዚአብሔር የወደደውን ወሰደ:: ይሆናል ያለውም ሆነ:: የአምስቱ ሰማዕታት ህልፈት የፅድቅ ስለሆነ ፅድቅ ነው ብለን መውሰድ እና የሞቱለትን ጅምር ስራ መጨረስ እንጅ ዝም ብለን እጃችንን አጣጥፈን መብሰክሰክ እንደሌለብን ይሰማኛል:: የቆሰሉትን ማሳከም ደግሞ አሁናዊ ግደታችን ነው:: በህንፃ ኮሚቴው በኩል አባላቱና ሌሎች የገብርኤል ወዳጆች እየተመላለሱ የተጎጅ ቤተሰቦችን ማፅናናታቸውን እንድሁም በፀሎት መትጋታቸውንና ከባድ ሀዘን ውስጥ እንዳሉ ሰምቻለሁ::

የሁላችንንም ልብ የሰበረ አስደንጋጭ ክስተት ነው:: ኮሚቴው ደግሞ ምርጥ አባቶቻችን የሚመሩት እና ሀቀኛይቱ እህታችን እቴጌ እየሩስ አንተነህ ያለችበት ነው:: ይህ ኮሚቴ አምስት ልጆቹን እንዳጣ ከፍተኛ ስብራት ላይ ወድቋል:: የኮሚቴው አባላት እኛን ማጠንከር ሲገባቸው እነሱው ቀድመው በመሰበራቸው ሰው በሀዘን ብዛት እንዳይጎዳብን ስጋት አለኝ::

ይግባኝ የሌለው ጉዳይ ነውና የአምስቱን ወንድሞች የልብ ወዳጆችና ቤተሰቦቻቸውን እንድሁም የስራ ባልደረቦቻቸውን ብሎም በቅዱስ ገብርኤል ጉዳይ ሌት ተቀን በመስራታቸው የሚያውቋቸውን ያገራችን ልጆች ከአደጋው ወዲህ ያላቸውን ስሜት ሁላችንም የምንረዳውና እኛም ያለንበት ነው:: በጣም ከባድ ስሜት ነው ግን ምን ይደረጋል? በማማረር እና በሀዘን ብዛት አይመለሱልንም:: ስለዚህ ሀዘን ቀንሰን ፀሎት እናድርግላቸው::

የቅርብ ቤተሰቦቻቸውንም በደጃቸው እየተገኙ ማፅናናቱ እና ማበርታቱ ይቀጥል: ይህ በኮሚቴው አባላትም እየተደረገ ያለ ከትልቅ ሰው እንድሁም ከሁሉም ወንድም እህቶች የሚጠበቅ ሰውኛ እና ክርስቲያናዊ ተግባር ነው:: አባቶቻችን እና እቴጌ እየሩስን ከልብ ማመስገን እወዳለሁ::

በህክምና ላይ ያሉትንም የአደጋው ተጎጅዎች እነ ወንድም ሳለአምላክ ተፈራ ከኪሳቸው እያወጡ እንክብካቤ እና ህክምና እንድያገኙ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል:: እግዚአብሔር ይስጣችሁ ከማለት ውጭ ምንስ ይባላል...?በጥቅሉ የደረሰው አደጋ የሁላችንንም ልብ የሰበረ ድንገተኛ ዱብዳ መሆኑ ይታወቃል:: ሆኖም ይህ አደጋ የተከሰተው በእግዚአብሔር እንጅ በሆነ ግለሰብ ወይም ስብስብ ትዕዛዝና ፍላጎት አይደለም የሚል አረዳድ ሁላችንም ሊኖረን ግድ ነው::

አንዳንድ ስክነት የሌላቸው የቤተክህነት ሰዎችም ግለሰቦችን ከዚህ ጋር አያይዘው ጉዞ መከልከላቸው አሳዝኖኛል:: ግለሰብን በአደጋው የሚወቅሱ በጣም መርዘኛ እና ሴረኛ የተወሰኑ ያገራችን ልጆች እንዳሉም ሰምቻለሁ::

ይህ አይነቱ እሳቤ ስራ የሚሰራን እና እግዚአብሔርን የሚታዘዝን የእውነት ሰው ለማሳቀቅና ተስፋ ለማስቆረጥ ወይም ልብ ለመስበር የሚደረግ ሰይጣን ያደረባቸው ግለሰቦች ብቻ የሚያራምዱት ሲሆን የቅዱስ ገብርኤል አገልጋይ እህት ወንድሞች ሆይ በማንም የሰይጣን ጉረንቶ አሉባልታ እንዳትፈቱ የሚል ወንድማዊ ማሳሰቢያ አለኝ::

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekane-Selam Media - MSM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share