Gerji media

Gerji media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gerji media, Media/News Company, .

07/06/2024
31/05/2024
25/04/2024

በመደመር እሳቤና በመደመር ትውልድ መካከል ያለው ትስስር ምንድነው?

መደመር ሁለንተናዊ ፍልስፍናችን ሲሆን የመደመር ትውልድ ደግሞ የሀገራችን ኢትዮጵያ ጥሪትና ዕዳን ተገንዝቦ ወደ ምንዳ የሚቀይር ትውልድ ነው፡፡ መደመር የማይዳስሳቸው ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች የሉም፡፡ መደመር ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ፣ ውጭ ግንኙነትና የሀገር ደህንነት የሚተነትንበትና የሚተገብርበት፣ ሀገር በቀል ፍልስፍናችን ነው።

መደመር ከነጠላ ቡድናዊ እውነት ወጥተን ወደ ሁለንተናዊ የወል እውነቶቻችን የምንሻገርበት ድልድያችን ነዉ፡፡ የመደመር ትዉልድ መደመርን ሁለንተናዊ በሆነ አኳኋን የሚፈጽም፣ ኢትዮጵያን ከዕዳ ወደ ምንዳ ማሸጋገር የሚችል ትውልድ ነው፡፡

25/04/2024
24/04/2024

ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ምን ማለት ነዉ?

ብልጽግና ምሉዕ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ግንኙነት ልህቀት ውጤት ነው፡፡ ከፖለቲካው አንጻር ብልጽግና መካከለኛና አካታች የፖለቲካ እይታን ይከተላል፡፡

ከዚህ አንጻር ሲታይ ብልጽግና በቀኝና በግራ ዋልታዎች መካከል ሚዛን በመበጠበቅ በመደመር እሳቤ የተቃኘ የተረጋጋ የፖለቲካ ሀይሎች አሰላለፍና መስተጋብር የሰፈነበት ምህዳር የበለጸገ ፖለቲካ ማሳያ ነው፡፡ ሁሉም ማንነቶችና ፍላጎቶች እውቅናና ክብር አግኝተው የሚደመጡበት፣ ህግና ስርዓት የሰፈነበት አውድ ነው።
ቅቡልነት የተጎናፀፈ ሀገረ መንግሥት የተረጋገጠበት ነው። ፍትህና ርትህ እውን የሆነበት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሰፈነበት ነው፡፡

በሌላ በኩል ሁለንተናዊ ብልፅግና የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ እውን የሆነበት ነው፡፡ ሁለንተናዊ የግብርናና ኢንዱስትሪ ልማትና ዕድገት የተሰናሰለበት ነው፡፡ ገቢ ምርቶች በብዛትና በጥራት የተተኩበት፣ የኤክስፖርት ምርቶችም በዚያው ልክ በብዛትና በጥራት የተመረቱበትና የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ የተቻለበት፣ ለሰፊ የተማረ የሰው ኃይል ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለበት ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማፋጠን የግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፉን ትስስር የሚያጠናክርና ሀገራችንን በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀዳሚ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችሉ ስራዎችን በስፋት እየሰራ የሚገኘውም ከዚሁ እሳቤ በመነሳት ነው፡፡

24/04/2024

ብልጸግና አሰባሳቢ ትርክትን በመቅረፅ የበለጸገች ኢትዮጵያ ይገነባል!

ሀገራችን ኢትዮጵያን የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ በመገንባት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር መሆን ይኖርባታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የቀደመ ሀገረ-መንግስት ባለቤት ብትሆንም አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ትርክቶቿ በስርዓታት ፖለቲካ ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሆነው በመቆየታቸው ስርዓታት በወጡ እና በወረዱ ቁጥር የሚገለባበጡ ነጠላ ትርክቶች ገዥ እየሆኑባት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ተግባሯን ያለ ተቃርኖ ለማስቀጠል አልታደለችም። በአንፃሩ የአሜሪካን፣ የቻይናን የፈረንሳይን ሀገራዊ ገዥ ትርክቶች የሚነግሩን ስርዓቶች ቢቀያየሩም ገዥ ሀገራዊ ትርክታቸው መሰረቱ ሀገረ-መንግስቱ ላይ በመገንባቱ በየወቅቱ የሚነሱ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አይለዋወጥም።

ሀገራት ህዝባቸውን ከየት እንደተነሱና ወዴት እንደሚደርሱ በአሰባሳቢ ገዥ ትርክት በመገንባት ከአስተዳደራዊ ወሰናቸው አልፈው በዓለም ላይ የበላይነታቸውን ቅቡልነት አረጋግጠዋል።
የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚዘውሩት የትርክት የበላይነት በያዙ ሀገራት እና ተቋማት ፍላጎት ነው። እነዚህ ሀገራትም ይሁኑ ተቋማት የትርክታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ዓይነት ሀይል የማስጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ትርክት ቻይናን ከወደቀችበት አንስቶ የዓለም ተፆዕኖ ፈጣሪ ሀገር አድርጎ ከፊት አስቀምጧታል። ትርክት ሶሪያ ከዓለም ቀደምት ሀገርነት ወደ ፍርስራሽነት ቀይሩታል። ትርክት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲነገር የሚኖረውን በቅኝ-ገዥዎች ቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንዲትሰራ አስችሏታል።

ትርክት በህዝብ ውስጥ ለጋራ ዓላማና ራዕይ በአብሮነት በማነሳሳትን በአርበኝነት እንዲፈፅሙ የሚያንቀሳቅስ ታላቅ ሀይል መሆኑን በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ በተራራቀ ዋልታ የሚገኙትን የሀገራችን ትርክቶች ወደ አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለማምጣት በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረት ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችን ገዥ ትርክት እንዲሆን እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችንን ያልፈውን የጉዞ ምዕራፍ ፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ እና የነገን መዳራሻ የምንመለከትበት የጋር አሰባሳቢ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብሎ ያምናል።

በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት ገዥ ትርክት የትላንቱን ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ መሰረት አድርጎ የዛሬውን አስተሳስሮ ነገን ማመልከት የሚችል የህዝባችንን ዋና ዋና የጋራ እሴቶችን፣ ፍላጎቶችንና ግቦችን የሚያሳካና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል።

ፓርቲያችን ህዝባችን የጋራ ታሪክ ያለው፣ ብዙ ትላንቶችን በጋራ የተሻገረ አሁን ስንቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ አያሌ ታሪኮችን እንዳሉት ያምናል።

በዚሁ አግባብ ብልፅግና በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ አማካይነት ነባር የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት፣ ታሪካዊ እሴቶችን አውጥቶ በማበልፅግ እና በማህበራዊ ካፒታላችንን በመጠቀምና በእነዚህ ላይ እሴቶችን በመጨመር ለነገ ብልጽግናችን በሚሆን መንገድ ማልማት በሰፊው ቀጥሏል።

ከትላንት የተሻለ ሀገራችንንና ህዝቡቿን የሚጠቅም ታሪክ እንድሰራ፣ የትውልዶችን ድካም በማረም ለትወልድ የበለፅገች ሀገር ለማስረከብ እንትጋ። ስለዚህ ትርክታችን ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የዛሬን ዕድል እና የገነን ተስፋ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

03/03/2024

እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

የአድዋ ድል ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት የፀናበት ካስማ ነው!

የአድዋ ድል አርበኞቻችን የግል ፍላጎቶቻቸውን ለአገር ሉዓላዊነት እና ለህዝብ ነፃነት በማስገዛት የአስተሳሰብ ከፍታቸውን ያሳዩበት፣ በእኛ ትውልድ ብቻም ሳይሆን በመጭው ትውልድም ተመራማሪዎች ሊፈልቁበት የሚችሉ ትምህርት ቤት ነው።

የአድዋ ድል የምዕራቡም የሰሜኑም የምስራቁም የደቡቡም የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የጋራ ድል ነው::

የአድዋ ድል ሲታወስ የመሰማማት እና የመዳማመጥ ዋጋ ይታወሳል። በመሪዎችና በተመሪዎች ፣ በመሪዎችና በመሪዎች እንዲሁም በተመሪዎችና በተመሪዎች መካከል መደማመጥ ነበር ፤ የወራሪው የጣሊያን ፕሮፖጋንዳ በባንዳዎች ተከሽኖ ቢቀርብም የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ አልሰጠውም። መከባበር የዚህ ግዙፍ ድል መለያው ነው፤ ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ መናናቅ አልነበረም፡፡

ከጦርነቱ በፊት የነበረውን እረጅም አድካሚ ጉዞ በእግር በፈረስ የተጓዙት አርበኞቻችን ከፊት ለፊታቸው የአሸናፊነት ስነ -ልቦና እና የአይደፈርባይነት ቁጭት ሰንቀው ስለነበር በዱር በገደሉ ሲወጡ ሲወርዱ ወደፊት መገስገስን እንጅ ወደ ኋል ማፈግፈግን ምርጫቸው አላደረጉም።

አድዋ በአባት እና በእናት አርበኞቻችን የተመዘገበ የኢትዮጵያውያን ድል በመሆኑ በየትኛውም የዓለም ጫፍ አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት እንጓዛለን።

አድዋ የኢትዮጵያዊያን ፣ የአፍሪካውያን ፣ የመላው ጥቁር ህዝቦች እና የፍትህ ወዳድ ህዝቦች ሁሉ ድል ነው።

የቀለም ልዩነት በሚቀነቀንባት ፣ ፍትህ በጠፋባት ጭቁን ህዝቦች በድቅድቅ ጨለማ በነበሩባት ዓለም የበራ ሻማ ነው የአድዋ ድል።

አድዋ ላይ የተከፈለው መስዋዕትነት የህይወት፣ የፈሰሰው ደግሞ ደም ፣ የተከሰከሰውም አጥንት ነው። የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን አሸናፊነት በመጠናቀቁ በደስታ ብናከብረውም ለተከፈለልን መስዋዕትነት ፣ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ከሉዓላዊነቷ ጋር ያወርሱንን አገር የላብ መስዋዕትነት ከፍለን ድህነትን ድል ባለማድረጋችን በቁጭት ጭምር ነው የዓድዋን ድል የምንዘክረው።

የዓድዋ ድል የዓላማ ፅናት ከያዝን ሁሉንም ችግሮቻችን እንደምንቀርፍ ፅኑ እምነት የምንሰንቅበት ለላቀ ድልም ቃል የምንገባበት ነው።

ከድልም በላይ የሆነው የዓድዋ ድል በሚገባው ልክ ሳይዛከር ፣ በክብሩ ልክ ሳይከብር ፣ በጋራ መስዋዕትነት የተገኘው ድል በዓል አከባበር ጭምር አንዳንዴ የልዩነት እና የግጭት ምክንያት ሆኖ 128 ዓመት መቆየቱ እንቆቅልሽ ብቻም ሳይሆን ቁጭትን ያጭራል።

ህብረብሔራዊ አንድነትን ለማፅናት ቆርጦ የተነሳው የለውጡ መንግስት የወል ታሪኮቻችን ላይ የተራገፈውን አቧራ ለማራገፍ ጊዜ አላባከነም።

መልካም ወረቶችን የማብዛት ፣ ስህተቶችን ፈጥኖ የማረም አቅጣጫን የተከተለው የመደመር መንገድ አሰባሳቢ ነው።

ከአሰባሰቢ ትርክቶቻችን አንዱ የሆነው የአድዋ ድል ተገቢውን ክብር እንዲያገኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈጻሚነት በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቅርብ ክትትል የኛ ትውልድ አሻራ ያረፈበት የአድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክን የሚዘክር ቅርስ ሆኖ ተጠናቋል።

የአድዋ ድል መታሰቢያ የከተማች ድምቀት፣ የህዝባችን ኩራት፣ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ቱሪስቶች መዳረሻ የሚሆን ታሪክንና ቅርስን አጣምሮ የያዘ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

የአድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክን መዘከር ብቻም ሳይሆን ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ ሬስቶራንቶች፣ ከ 1000 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ ፣ የልጆች መዝናኛ ፣ የኪነ-ጥበብ ማሳያ እና መሰል አገልግሎቶች የሚሰጡ ክፍሎች የተካተቱበት ከምንም በላይ ቱሪስቶች የሚጎርፉለት ለትውልድ የሚተላለፍ ቋሚ ሀብታችንም ነው፡፡

ወንድማማችነትን ፣ እህትማማችነትን እና አብሮነትን በሚዘክረው አገራዊና አህጉራዊ ትርጉም ባለው በአድዋ ድል መታሰቢያ የዓድዋ ድል በዓል እንዲከበር መደረጉ ጥላቻ ቦታውን እንዲያጣ አድርጓል፤ ከፋፋይነትንም የሚያስተናግደው አይኖርም።

መሪና ተመሪ ተደማምጦ የተመዘገበ አኩሪ ድል እንደመሆኑ በዓሉን ስናከብረም በመደማመጥ ፣ በመከባበር ፣ ህግና ስርዓትን በመከተል በመከራ ጊዜ ጭምር የማይላላውን የተጋመደ ማንነታችን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ግድ ይላል።

የዓድዋ ድል በፍቅር በመሰባሰብ እንጅ በጥላቻ በመገፋፋት የተገኘ ባለመሆኑ በዓሉን ስንዘክርም ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት የፀናበት ካስማ የበለጠ እንዲጠብቅ በማድረግ ሊሆን ይገባል !

እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

03/03/2024

እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡

የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አሳይቷል፡፡ የመጀመሪያው በጦርነቱ ዘመቻና ድል ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ በምናውቃት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች መካከል ወደ ዐድዋ ያልዘመተ ወገን የለም ብሎ መናገር እውነትን መናገር ነው፡፡

ሁለተኛው ክሥተት ደግሞ የዐድዋ ድል በተገኘ በሰባት ዓመቱ የዐድዋ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሲከበር ትርዒቱን ያቀረቡት ከተለያዩ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችች የመጡ የኢትዮጵያ ጦር አባላት ነበሩ፡፡ በዚህ ትርዒት ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት ሀገር መሆንዋን በዐደባባይ ሰልፈኛው አሳይቶ ነበር፡፡

ይሄንን በዐድዋ ዘመቻና በዓል የተንጸባረቀ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አጽንተን ልንይዘው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ኅብረ ብሔራዊ ማነነት ያላቸው ሕዝቦች በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ኅብረ ብሔራዊነታቸው ከፈጣሪ ያገኙት ነው፡፡ አንድነታቸውን ደግሞ እነርሱ ራሳቸው በዘመናት ትሥሥርና መሥዋዕትነት ገንብተውታል፡፡ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁለቱን፣ ነገር ግን አንዱ ከሌላው ጋር ሳይነጣጠል የሚኖሩትን መገለጫዎቿን ትታ ኢትዮጵያ አትሆንም፡፡ በእያንዳንዱ ጉዞዋ ይሄንን እያረጋገጠች መጓዝ አለባት፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

03/03/2024

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮጀክት ሳይሆን ታሪክ ነው!

ቀደምት አባቶችና እናቶቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና ብለን እንድንሄድ ያስቻለንን የዓድዋ ድልና ታሪክ አውርሰውናል፡፡ ድሉን ሊያጎናፅፉን የቻሉት በታጠቁት ዘመናዊ መሣሪያ ወይም አደረጃጀት ሳይሆን ለጋራ ዓላማ በፅናትና በአንድነት በመሰለፋቸው ነው። በመሆኑም የዓድዋ ድል ትውልድ ሊማርበት የሚገባው የዓላማ አንድነትና የፅናት ውጤት ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድም ታዲያ በዓድዋ መንፈስ ሆነን፤ በድሉ ብስራት ጠንክረን፣ ኢትዮጵያ የምትጠብቅብንን ደማቅ ታሪክ ዳግም መስራት መቻል አለብን፡፡ ብዙ ያልሰራነው ፣ ገና ያልፈጸምነው በርካታ የቤት ስራዎች አሉብን፡፡ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያወረሱን የዓድዋ ድል ፍሬ ከጫፍ እንዳይደርስ ብልፅግናችን በቅርበት እውን እንዳይሆን በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ ወደ ኋላ የሚጎትቱን ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ የዓድዋ ጀግኖች እንዳደረጉት ትልቁን መዳረሻችንን አልመን የስኬትን ማማ እንድንቆናጠጥ የብልፅግና ሳንካዎችን ከራሳችን በማራገፍና በመታገል በጋራ አብረን መቆም ይኖርብናል፡፡

የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት ከሚባል ታሪካዊና አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ፡፡

የመደመር ትውልድም ከአባቶቹ በመማር በዓለም አደባባይ እውቅና የተቸራቸውን በርካታ ስኬታማ ገድሎችን እየፈጸሙ ወደ ብልፅግና ማማ እየገሰገሱ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት፡- በጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አሕመድ ( ዶ/ር ) ሀሳብ አመንጪነት እና በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቅርብ ክትትል ዳግማዊ ዓድዋ የሆነውን የዓድዋ የድል መታሰቢያ እውን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮጀክት ሳይሆን ታሪክ ነው!

የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ያከበርነው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን ድሉን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ገንብተን የዓድዋን ጀግኖች እየዘከርን በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል፡፡ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ብቻም ሳይሆን የሁሉም አፍሪካዊያን እና ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በመሆኑ ሙዚየሙ በአለም አቀፍ ደረጃ ድሉን ለማስተዋወቅ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድም አንድ ሁነን እንደ ብዙ፣ ብዙ ሁነን እንደ አንድ በመሆን ልክ እንደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ በሌሎች የልማትና የሰላም መስኮች በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና በፖለቲካው መስክ የሀገራችንን ብልፅግና ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሌሎች የዓድዋን
ድል ፍሬ ደጋግመን ማሳካት ይኖርብናል፡፡

03/03/2024

ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶችን ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡

ከዚህም መካከል ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ሲባል ንኡስ ፍላጎቶችን መሠዋት አንዱ ነው፡፡ ወደ ዐድዋ የዘመቱ ሁሉ በወቅቱ በነበረው ሥርዓተ መንግሥት የሚስማሙና የተደሰቱ አልነበሩም፡፡

አንዳንዶቹ እንዲያውም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ግጭትም ቅራኔም ነበራቸው፡፡ አንዳንዶቹም በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ ቅር ተሰኝተው ከጠላት ጋር የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ነገሩ የሀገር ጉዳይ ሲሆንባቸው ግን ሁሉም ንኡስ ፍላጎቶቻቸውን ትተው፣ ለታላቁ ፍላጎት ለሀገር ህልውና መሥዋዕት ለመሆን መጡ፡፡ ማንኛውም ፍላጎት ከሀገር ፍላጎት በታች መሆኑንም አሳዩን፡፡

እንኳን ዛሬ ብዙ ዓይነት መረጃ፣ ዕውቀትና የሐሳብ መንገዶች ባሉበት ዘመን ቀርቶ ከመቶ ዓመት በፊትም ሰዎች ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ነበሯቸው፡፡ በፍላጎቶቻቸው የተነሣም ቅራኔዎችና ግጭቶች ነበሩ፡፡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ የምታስተሣሥር ዓላማ ሀገር የምትባለው ናት፡፡ ዛሬም ንኡስ ፍላጎቶቻችን ከኢትዮጵያ አይበልጡም፡፡

ኢትዮጵያን የሚያዳክም፣ የሚያሳንስና የሚያሳጣ መንገድ ከትልቁ ዓላማ የሚጋጭ መንገድ ነው፡፡ ጦርነት የትልቁ ዓላማ የኢትዮጵያ ህልውና ማስከበሪያ እንጂ የንኡስ አካባቢያዊና ግላዊ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ሊሆን አይገባም፡፡ ጦርነት ለትንሽ ነገር የሚወጣ ወጪ አይደለም፡፡ ዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉት ሁሉ ብዙ የመፍትሔ አማራጮችም አሉት፡፡

መከራከር፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ በሕግ መዳኘት፣ አንዱ ሌላው መሸከም፣ የትየለሌ አትራፊ መንገዶች አሉት፡፡ ትልቋ ዓላማ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ስንል ንኡስ ዓላማዎቻችንን እያመሙን እንኳን ቢሆን መሠዋት አለብን፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

28/02/2024

ብልፅግና ፓርቲ በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ፓርቲ ነው!

የፓርቲያችን ተራማጅ ሀሳቦች ወደ ተግባር ተተርጉመው የህዝባችን የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል፣ ከተማችንም የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅበትን በማበርከት ላይ ይገኛል።

የፓርቲያችንን ፕሮግራሞች እና እሳቤዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች የምትከታተሉ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎቻችንና በሀሳብ የበላይነት የምታምኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ወዳችሁና ፈቅዳችሁ ስለምትከተሉን እያመሰገን የበለጠ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን!

የውይይት እና የመደማመጥ ባህላችን እንዲጎለብት፣ የዴሞክራሲ ባህላችን እንዲያብብ አገር ገንቢ እሳቤዎችን ማበረታታት፣ እርስ በእርስ የሚያጣሉ አገር አፍራሽ ትርክቶችን ደግሞ በሀሳብ ትግል የማስተካከል ሁሉም ዜጋ አገራዊ ሀላፊነት አለበት።

ብልፅግና ፓርቲ በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ፓርቲ ነው። የፓርቲው ሀሳብ በህዝባችን ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት በማግኘቱም አገራችን እየተመራችበት ይገኛል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gerji media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share