Loomii nasru

Loomii nasru Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Loomii nasru, Digital creator, .

08/11/2024
08/11/2024
08/11/2024

የሴቶች እና የህፃናት መብትና ደህንነትን ማስጠበቅ የምናልመውን ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው:- አቶ ኦርዲን በድሪ
**************
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የበጀት አመቱ የሩብ አመት ግምገማ በማህበራዊ ዘርፍ የክልሉ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አፈፃፀምን ተመልክቷል።

በሪፖርቱ ውይይት ላይ ተካሂዶ የማጠቃለያ አቅጣጫ የሰጡት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በዘርፉ የሚካሄዱ ስራዎችን በማጠናከር በተለይም የጎዳና ተዳዳሪነትና የመንገድ ዳር ላይ ልመናን ለማስቀረት መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

የወጣቶች፣ የሴቶችና የህፃናት ደህንነት ጋር የሚያያዝም በመሆኑ የጎዳና ተዳዳሪነትን ለመቀነስ መስራት ይገባል ብለዋል።

የሴቶች እና የህፃናት መብትና ደህንነትን ማስጠበቅ የምናልመውን ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በዘርፉ ሪፖርትም በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ፣ የሴቶች መብትና ደህንነትና ተሳትፎና ተጠባሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የተካሄዱ ስራዎች ቀርበዋል።

በተለይም ከአቅመ ደካማ ቤቶች ዕድሳት ጋር በተያያዘ በክልሉ የሚገኙ ሴክተሮች ጋር በጋራ በመሆን ከ100 በላይ ቤቶችን ማደስ መቻሉ ተገልጿል።

በክልሉ በሚገኙ የወጣት ማዕከላት ወጣቶች ስልጠናን ጨምሮ የስፖርት፣ የኪነጥበብ እና የመዝናኛ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉ ተገልፆ በሪፖርቱ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በተጨማሪም በመድረኩ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ የሩብ አመት አፈፃፀምም ተገምግሟል።

ዘጋቢ ዳኛቸው ደምሴ
29 / 02 / 2017

08/11/2024
08/11/2024

በጤናው ዘርፍ የመከላከልና አክሞ የማዳን አቅምን ውጤታማነት ማረጋገጥ ቁልፍ ስራ ሆኖ ይቀጥላል:- አቶ ኦርዲን በድሪ
**************
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የሩብ አመት አፈፃፀም ግምገማ በማህበራዊ ዘርፍ የክልሉ ጤና ቢሮ አፈፃፀምን ገምግሟል።

የዘርፉ ሪፖርት አፈፃፀም ላይ የማጠቃለያ አቅጣጫ ያስቀመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በጤና ተቋማትና የጤና ባለሞያዎች አክሞ የማዳን አቅምን ማጎልበት ይጠበቃል ብለዋል።

በተለይም በጤናው ዘርፍ ማነቆ የሆኑ ደላሎችን በማስቀረት ህብረተሰቡ በመረጠው እና በፈለገው ተቋም መገልገል እንዲችል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስነምግባር ፣ ክህሎት ፣አክሞ የማዳን እውቀት እና ብቃትን ተላብሰው መስራት እንደሚገባቸው አክለው ገልፀዋል።

በሩብ አመቱ በጤና ዘርፍ የተካሄዱ ስራዎችን በማስመልከት በቀረበው ሪፖርትም በመደበኛ ጤና ስርአትን ጨምሮ የምርመራና ህክምና አገልግሎት የማሻሻል፣ የጤና መሰረተ ልማት ማሻሻል እና አጠቃላይ የዘርፉን አገልግሎት ጥራት ከማሳደግ አኳያ የተካሄዱ ስራዎት ሪፖርት ቀርበዋል።

በገዛኸኝ አራጌ
29 / 02 / 2017

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Loomii nasru posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share