Amhara Fano in Gondar

  • Home
  • Amhara Fano in Gondar

Amhara Fano in Gondar Amhara politics,music,entertainment, history/culture & analysis on the current Amhara struggle
(3)

ይሄ ብርጌድ በሻለቃ ከፍያለው የሚመራው የጉና ክ/ጦር አካል ነው፡፡ የራሱን መንግስት መስርቶ ነውኮ ስእሉ እንደሚያሳየው፡፡ እስቴ መካነየሱስ ከተማ
19/09/2024

ይሄ ብርጌድ በሻለቃ ከፍያለው የሚመራው የጉና ክ/ጦር አካል ነው፡፡ የራሱን መንግስት መስርቶ ነውኮ ስእሉ እንደሚያሳየው፡፡ እስቴ መካነየሱስ ከተማ

የአማራ ፋ*ኖ በጎንደር የገብርዬ ክፍለ- ጦር ከ700 በላይ  አዳዲስ ሰልጣኞችን አስመረቀ። በምረቃው ስነ ስርዓት የጉና ክፍለ- ጦር ዋና አዛዥ ሻንበል አምሣሉ ማዘንጊያ ፣ ሁለቱ ምሁራን እና...
16/09/2024

የአማራ ፋ*ኖ በጎንደር የገብርዬ ክፍለ- ጦር ከ700 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞችን አስመረቀ። በምረቃው ስነ ስርዓት የጉና ክፍለ- ጦር ዋና አዛዥ ሻንበል አምሣሉ ማዘንጊያ ፣ ሁለቱ ምሁራን እና ተመራማሪዎች የአማራ የመከራ ቀን ደራሽ ፕሮፌሰሮች ጌታ አስራደ እና ኢያሡ አባተ ተገኝተዋል።

16/09/2024

ደባርቅ ፣ዳባት፣ አምባ ጊዮርጊስ አመራሮች እጅ መስጠት ጀምረዋል።
እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
ጎንደር አማራ ኢትዮጵያ!!!

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በጠቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ===================================
03/09/2024

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በጠቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ
===================================

የአማራ ፋኖ በጎንደር አገዛዙ የሚፈጽመውን እገታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ==========================================
03/09/2024

የአማራ ፋኖ በጎንደር አገዛዙ የሚፈጽመውን እገታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
==========================================

17/08/2024

ጎንደር
======
በሶስት ቀናት ውስጥ ፋ*ኖ የጨበጣቸው አካባቢዎች ዝርዝር፡፡
ማሰሮ ደንብ፣
ሶሮቃ፣
አሸሬ፣
ሙሴባንብ ሙሉ በሙሉ፣
የሳንጃ ገጠር ቀበሌዎች፤
አርባያ በለሳ፣
ጉሃላ፣
የምዕራብ በለሳ እና የምስራቅ በለሳ የገጠር ቀበሌወች፣
ደልጊ፣
ሙሉ የደንቢያ የገጠር ቀበሌዎች፣
አይንባ፣
ብሆና፣
የቆላ ወገራ ገጠር ቀበሌዎች፣
ሙሉ የቋራ ገጠር ቀበሌዎች፣
ሙሉ የአለፋ ቀበሌወች::

12/08/2024

ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
====================================
የደም ዋጋ የተከፈለበት የነፃነት መዋቅር በጠላት ሰርጎ ገቦችና ባንዳዎች አይፈርስም!

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ የማንነትና ወሰን ትግል ዛሬ ላይ በእጃችን የገባውን አማራዊ ነጻነት ለማግኘት ሁለት ትውልድ የተቆጠረበት መራር መሥዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡ እስካሁን በመጣንበት የትግል መንገድ፤ ከከፋኝ የአርበኞች ተጋድሎ እስከ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴው ሰላማዊ የትግል መስመር፤ የሰሜን ዕዝ ከጀርባ መታረድን ተከትሎ በሕግ-ማስከበር ዘመቻው እንደአገር ኢትዮጵያን ከጥቃት፣ እንደ ወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ደግሞ ከወያኔ-ግፈኛ የባርነት አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ክቡር መሥዋዕትነት ከፍለናል፡፡

በዚህም በእጃችን በገባው ነጻነት እስከ አሁን ድረስ የዘለቀው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምሥረታና ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል በጋራ መሥዋዕትነታችን፣ በትግል ዓላማ ጽናታችን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ወልቃይት-ጠገዴ በመላ አማራ ትግል ከጠላት ነጻ ወጥቶ፣ ሕዝባችንም የተነጠቀ ማንነቱን ዳግም በግፈኞች እንዳይነጠቅ ከምን ጊዜውም በላይ ራሱን አደራጅቶ እየጠበቀ ይገኛል፡፡

የትግሉ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ፣ ከፍትሐዊው የማንነት ትግላችን ጎን የቆሙ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ዓለማቀፉ ማኀበረሰብ እንደሚያውቀው ዞናችን መደበኛ በጀት የሌለው ነገር ግን ‹ነጻነታችን በጀታችን› በሚል ወኔ፣ቁጭት፣እልህና ተስፋን የትግላችን ማዕከል አድርገን ከሕዝብ፤ ለሕዝብ፤ በሕዝብ፤ የሆነ አስተዳደራዊ የነፃነት መዋቅር ዘርግተን ለዘላቂ የህግ አሸናፊነት ትግል ላይ እንገኛለን፡፡

በጀት የማይበግረው፤ ወራሪ የማይደፍረው ማኀበረሰብ መገንባት የተቻለው፤ የማንነት ኮሚቴው፣ የዞኑ አስተዳደር እና ሕዝቡ አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ መሆን በመቻላችን ነው፡፡

ሆኖም ግን የጥፋት መንገዱ ብዙ የሆነው ወያኔ ዞኑን መልሶ በግፍ ለመውረር ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሙከራዎችን አድርጓል፡፡ ጥቃቱ የተልዕኮና ቀጥታ፤ የተቀናጀና የዕቅድ ደረጃዎች (Plan A, B, C) ያሉት ሆኖ ታይቷል፡፡

የወያኔ ወታደዊና የደህንነት ክንፍ በቀጥታ የወረራ ሙከራዎቹ በሱዳንና በተከዜ በኩል ተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ አከርካሪውን እየተመታ በተደጋጋሚ ተመልሷል፡፡ በዚህ መልኩ እንደማይሳካለት ያወቀው ጠላት፥ በአንድ በኩል፣ የብረት በር የሆኑበትን የማንነት ኮሚቴና አስተዳደር ቁልፍ አመራሮች ከሕዝብ ለመነጠል በተደራጀ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ስም ማጠልሸት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለፖለቲካ ዓላማ በልዩ ሁኔታ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ ገዳይ ቡድን ከትግራይ መልምሎ ወደዞኑ በማስገባት ኮር አመራሩን የማጥቃት፣ ወዘተ... የጥፋት ሙከራዎቹን ቢያደርግም የእውነት አምላክ ከሕዝባችን ጎን በመቆሙ፣ በአመራሩና በጥምሩ የፀጥታ ሀይላችን ጥንካሬ በሕዝቡ አማራዊ አንድነት ብርታት የታቀዱ የጠላት ሴራዎች ሁሉ ከሽፈዋል፡፡

እነዚህ ሁሉ ሲሉ ሙከራዎቹ ሲከሽፉ፣ በክልላችን የተከሰተውን እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ችግር፣ የአማራ ሕዝብን ፈተና ላይ መውደቅን እንደዕድል በመጠቀም ወያኔ ወልቃይት-ጠገዴን ዳግም ለመውረር ያመቸው ዘንድ ለጥፋት ዓላማው ስምሪት ላይ ከርሟል፡፡

በዚህም አጠቃላይ ሕዝብና መዋቅራችን ላይ ያነጣጠረ የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመክፈት በትጥቅ፣ በገንዘብና በፕሮፖጋንዳ ድጋፍና የግንኙነት አመራር በመስጠት ነጻ በወጣ ምድራችን ላይ ቅጥረኞቹን/ባንዳዎችን መልምሎ ለጥፋት ዓላማ ማሰማራቱን ከኀብረተሰቡ ጋር ባደረግነው ውይይትና የመረጃ ክትትል አረጋግጠናል፡፡ ስለሆነም ከወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ የማንነት ሁለንተናዊ ትግል ፍላጎትና ስምሪት በተፃራሪ የግፈኛው-የወያኔ ቡድን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎት የሆኑትን:-

1) አስተዳደሩ ጠላቱን የሚከላከልበትን ለአከባቢው ነዋሪዎች ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ማስፈታት፤

2) የማንነትና የወሰን አስተዳደር መዋቅርን ማፍረስና ፀረ-ማንነት ትግል ሁኖ መታየት

3) በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተደራጀውን የማንነት አደረጃጀት ዶክመንቶችን፣ ፋይሎችንና ልዩ ልዩ ሰነዶችን ማቃጠል/ማውደም፤

4) በትግራይ በኩል በተከዜ ወሰን የወያኔ ታጣቂ ለወረራ ወሰን እንዳይሻገር የወልቃይት-ጠገዴ ተከዜ ዘብ ከሚጠብቅበት፤ በሱዳን የሚገኘው የታጣቂው ኃይል አካል የሆነው ‹የሳምሪ ገዳይ ቡድን› የአገር ዳር-ድንበር ሰብሮ ለወረራ እንዳይገባ ዘብ ሆኖ እየጠበቀ ባለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ምንም ዓይነት ትንኮሳ እንዳይደረግ በዞናችን አስተዳደርና ሕዝብ የጋራ አቋም የተወሰደበትን ስምምነት በመጣስ በአውራ ወረዳ ሎሚ ወንዝ ቀበሌ ፣ ጠገዴ ወረዳ አዳይጦ እና በቃብትያ ሁመራ ወረዳ በእድሪስ ቀበሌዎች ባሉ ቀይመስመሮች በሕዝባችንና በፀጥታ ኃይሉ ላይ ትንኮሳ አድርገዋል፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ፀረ-አማራነት ተግባራት እና ይህን የሚያስፈጽሙ የታጠቁ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ድርጊታቸው የጠላት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎት እንደሆነ፣ ለዚህም ከወያኔ ውክልና የወሰዱ መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠናል፡፡

ለዚህም ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ እያረጋገጥን የመጣንበት በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተደራጀው የማንነት አደረጃጀት፣ የዞኑ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት፣ ከዋናው የማንነትና ወሰን ኮሚቴው ጋር በመቀናጀት በየደረጃው ካለው የኀብረተሰብ ክፍል ጋር በተደረገው ውይይትና ሕዝባዊ የመረጃ ልውውጥ ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡

ስለሆነም የጠላትን ተልዕኮ በወሰዱ የሰርጎ ገቦች የጥቃት ሰለባ ከሆኑ ወገኖቻችን ጉዳትና ከሕዝባችን ተጨባጭ መረጃ በመነሳት፣ ከዚህ በፊት ከክልላዊ፣ አገራዊና ቀጠናዊ ሁኔታዎች በመነሳት ስትራቴጂካዊ ግምገማ በማድረግ እንዳይነኩ አቋም የወሰድንባቸው ወሳኝ ጉዳዩች ቀይ መስመሩ ታልፎ ሕዝባችንን ለዳግም ባርነት፤ ኢትዮጵያንም ለፍርሰት የሚዳርግ የምድር በሩን የማፍረስ ሙከራ በጠላት ሰርጎ ገቦች መሞከሩን አረጋግጠናል፡፡

የወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ከሚታገልለት ሕዝብ ባሻገር፣ የመላው አማራ የትግል አስኳል የሆነውን ትግል፣ የኢትዮጵያን የምድር በር ብሔራዊ ደህንነቷን የመጠበቅ መልክዓምድራዊና ታሪካዊ የትግል አደራ ያለበትና በዚህም ብዙ መከራ ያሳለፈ መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ይገነዘባል፡፡

ችግራችን ውስብስብ፣ የሁሉንም ወገን አገራዊ ትብብር የሚጠይቅ፣ ጊዜ የማይሰጥ፤ ምንም ዓይነት ስህተት ሊታይበት የማይገባ በመሆኑ፤ የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የትርምስ ቀጠና እንዳይሆን የፋኖ ኃይሎች ወደ ዞኑ ከመግባት ተቆጥበው ያሉ መሆኑ እየታወቀ፤ የወቅቱን የክልላችንን ሁኔታ እንደዕድል በመጠቀም ወያኔ ለወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶቹ መሳካት ሲል በትጥቅ፣ በገንዘብ፣ በፕሮፖጋንዳና የግንኙነት አመራር በመስጠት የሚደግፈው ሰርጎ ገብ ኃይል ስለመሆኑ እንዲታወቅልን እናሳስባለን፡፡

እነዚህ የጠላትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለማሳካት የወልቃይት-ጠገዴ አማራ ሕዝባችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተልዕኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች፡-

ከዚህ ታሪክ ይቅር ከማይለው የፀረ-አማራነት ድርጊት፤ ለወያኔ የ‹‹ታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክ›› ምሥረታ አገር አፍራሽ መንገድ ጠራጊነታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ሕዝባችን ወደዳግም ባርነት ላለመመለስ፤ የደም ዋጋ የከፈለበትን አስተዳደራዊ መዋቅሩን በመጠበቅ አማራዊ ነፃነቱን ለማስከበር ሲል ሰርጎ ገቦችንና ባንዳዎችን በይፋ ይታገላል፡፡ እምቢ ለባርነት በማለት ሁሉም ሰው፣ ሁልጊዜምና በሁሉም ቦታ መታገል አስፈልጓል። የሰማዕታት አደራ አለብን!

መላ የወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ የዞኑ አስተዳደርን ከጠላት ሰርጎ ገቦችና ባንዳዎች ለመጠበቅ ሕግ የማስከበር እርምጃ እንዲሚወሰድ የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤቱ ወስኗል።

በመጨረሻም፤

በደም የፈካው ነጻነታችንን፤ እስከሞት የምንታመንለት አማራነታችንን የሚያፀናልንን የማንነት አስተዳደር እንዲፈርስ መቼውንም ቢሆን የሚፈቅድ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ የለም! ሕዝባችን በደምና አጥንቱ ያመጣውን ድል ራሱ ይጠብቀዋል እንጂ በጠላት የሴራ መንገድ አይራመድም! ወልቃይት-ጠገዴ በመላ አማራና በፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ትግል ከጠላት ነጻ ወጥቷል፤ ለዘላቂ የሕግ አሸናፊነት ፀንቶ ይቆማል፡፡ በየትኛውም ሁኔታ ወደዳግም ባርነት ሊመልሱት ተልዕኮ የወሰዱ የጠላት ሰርጎ ገቦችንነ‍ኣ ባንዳዎችን አይታገስም! የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ አስተዳደር የለንም!

በሌላ በኩል እጅግ ጥቂት የሚዲያ አካላት የጠላትን ተልዕኮ የወሰዱ ሰርጎ ገቦችን እንቅስቃሴ ከእውነታው ተቃራኒ በሆነ መንገድ መዘገባቸውን ተመልክተናል፡፡ በጠላት የተገዙ እንዳሉ ብናውቅም እውነታውን ባለማወቅ የተሳሳተ መረጃ ያሰራጫችሁ የሚዲያ አካላት ከዚህ በኋላ ላለው ዘገባችሁ ከእውነት ጎን እንድትቆሙ በትግሉ ሰማዕታት ስም አደራ እያልን፤ የጠላት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ማሽን የሆኑትን ሚዲያዎች የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲታገሏቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን በዘላቂነት የማስከበር ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ ሕዝባዊ አንድነትና ስትራቴጂካዊ አመራር ይጠይቃል፡፡ በወልቃይት ጠገዴ ነጻ ምድር ከጠላት ሰርጎ ገብና ባንዳ ቀጠናውን ለመጠበቅ ሁላችንም፣ ሁልጊዜምነ‍ኣ በሁሉም ቦታ ዝግጁ ሆኖ መገኘትና መታገል ነው:- የተከዜ ዘብ መርሁ እንጂ የተገኘውን ነፃነት ለጠላቶቻችን አሳልፎ መስጠት አይደለም።

ወልቃይት-ጠገዴ ቀይ መስመር ነው!

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር

ነሐሴ 06፤ 2016 ዓ.ም.
ሁመራ-አማራ፤ ኢትዮጵያ!

08/08/2024

የጀግናው የውቤ ልጆች ታረክ ሰሩ
==================
1)አማራ ፋኖ በጎንደር የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር መላኩ ደስታ ብርጌድ
2)አማራ ፋኖ በጎንደር የአጼዎቹ ክፍለ ጦር አዘዞ ድማዛ ብርጌድ
3)አማራ ፋኖ በጎንደር የበጌምድር ክፍለጦር አይሸሽም ብርጌድ
4)አማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ

በጋራ በመሆኑ ጎንደር ኤርፖርት ስር ከአገዛዙ ሠራዊት ዲሽቃ ብሬና ስናይፐር በርካታ ጥቁር ክላሽ ማርከዋል። ዲሽቃ ተኳሹን ጨምሮ ብዙ ምርኮኛም አለ።

07/08/2024
06/08/2024

ምርጫው
======
(1) ከብአዴን ጋር ሆኖ “ኢትዮጵያኒስቱን” መታገል እና
(2) ከኢትዮጵያኒስቱ ጋር ሆኖ ብአዴንን መታገል ነበር፡፡

የብአዴን አገልጋይ ፋኖ ከምንሆን እና ብአዴንን ለሌላ ሶስት አስርት አመት አናነግስም የሚሉ ሀይሎች ከእስክንድር ጋር ሆኖ ብአዴንን መታገል መርጠዋል፡፡ በአኩራፊ ብአዴኖች የሚዘወሩት ፋኖዎች ደግሞ ከብአዴን ጋር ሆነው እውነተኛውን ፋኖ ማሳደድ ጀመሩ፡፡
ምርጫው እንግዲህ የብአዴን አገልጋይ በመሆን እና የአማራ ህዝብ አገልጋይ በመሆን መካከል ነበር፡፡ ምርጫችን ትክክል ነው፡፡ ቀድሞውንም ከፊል ብአዴን የነበረው የፋኖ አደረጃጀት አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ብአዴንነት አድጓል፡፡ በእውነተኛው የአማራ ህዝብ ጠበቃ ፋኖ ላይም የተቀነባበር ዘመቻ ከፍቷል፡፡ ዘመቻውም በሚዲያ ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ በማሳደድ እና በመግደል የተደገፈ ነው፡፡
እዚህ ውስጥ መረሳት የሌለበት የወያኔ ሚና ነው፡፡ ወያኔ ከዚህ የብአዴን ፋኖ ጋር ሆኖ የጥምር መንግስት እንዲፈጥር ምአራባዊያን ይፈልጋሉ፡፡ ወያኔ ደግሞ ወልቃይት እና ራያ ላይ ጥያቄ ከሚያነሳው ሀይል ጋር አብሮ መስራት አይፈልግም፡፡ ወያኔ ሽዋ የትግሬ ዘላለማዊ ጠላት ነው ብሎ ስለሚያምን ከሸዋ ሀይል ጋር አብሮ መስራት አይፈልግም፡፡ ይሄ ደግሞ የብአዴን መስመር ነው፤ የቀድሞ አለቃና ምንዝር አንድ ላይ ተሰልፈዋል፡፡ የብአዴኑ ሀይል ዋናው የአማራ ሀይል ላይ ዘመቻ የከፈተበትም ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ለአብነት ሰሞኑን ሚዲያው ላይ የሚካሄደውን የለቅሶ ዘመቻ ብታዩ አንዱን የፋኖ ክንፍ የብልጽግና የፕሮፓጋንዳ ክንፍ በደንብ እያገዘው እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ የአማራ ህልውና የሚከበረው ብአዴንን መልሶ በማንገስ ሳይሆን በእውነተኛ የአማራ ልጆች ብቻ ነው፡፡

ይነበብ!!!
03/08/2024

ይነበብ!!!

ዝክረ ናሁሰናይ አንዳርጌ!የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ!°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°በዘመናችን ጀግንነትን በምግባር ከገለጡ እንቁዎች አንዱ ሻለቃ ፋኖ ናሁ...
14/04/2024

ዝክረ ናሁሰናይ አንዳርጌ!
የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በዘመናችን ጀግንነትን በምግባር ከገለጡ እንቁዎች አንዱ ሻለቃ ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ ነው። ሞትን የናቀ ለአማራ ሕዝብ ክብር እራሱን መስዋእት ያደረገ የአባቶቹ ልጅ ነው።

ከትውልድ ሲቀዳ...
===========
ናሁሰናይ የ27 አመት አፍላ ወጣት ነው። የተወለደው እስከ ሞ*ት በታመናት፣ አቆላምጦ በሚጠራት፣ እሷም አቀማጥላ በእቅፏ ባሳደገችው በታሪካዊቷ ጎንደር ነው። ለእናቱ ምትክ የሌለው አንድያ ልጅ ነው። በእናት እና አባቱ ቤት ሲያድግ በረከት ሞልቶ የተትረፈረፈላቸው ናቸውና አቀማጥለው በስስት አይን ነበር። አባቱ መምህር አንዳርጌ በመላው ጎንደር የተመሰከረላቸው ኢንቨስተር አራሽ አንደፋራሽ ባለ ትልቅ ፎቅ ባለቤት ናቸው። ወጣት ናሁሰናይንም በስራ እና ምግባር ኮትኩተው ስላሳደጉት ቀልጣፋ የስራ ሰው እንደነበር የቅርብ ጓደኞቹ ይመሰክሩለታል።

ለሕዝብ ነፃነት የተኖረ ወጣትነት...
====================
ወጣት ናሁሰናይ ሕዝቡን ከጭቆና የማወጣው እኔም ውትድርና ሰልጥኜ ብቁ ስሆን ነው በማለት ገና በለግላጋ እድሜው መከላከያ ተቋም ውስጥ ገብቶ የሞያ ክህሎት እየተማረ ነበር። ነገር ግን አይበገሬነቱን ያዩ፣ በማንነቱ አንገቱን የማይደፋ መሆኑን የተረዱ በዘመኑ ተረኞች የነበሩት የት*ህነግ አንጋቾች "ፅን*ፈኛ ትም*ክህተኛ" ነህ ብለው በግፍ አባረሩት። ነገር ግን በእልህ የተንቀለቀለው የነፃነት ጥማቱን ይበልጥ አናረው እንጅ አንገት አልደፋም። በዛ መሃል ነው ጎንደር ላይ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ 2008 ላይ የተቀ*ጣጠለው።

ጀግናው ኮ/ል ደመቀ ሐምሌ 5 ላይ የነፃነት አብሪ ጥ*ይት ጎንደር ላይ ሲተኩ*ስ እነ ወጣት ናሁሰናይ የጎንደርን ወጣት እያደራጁ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያቀጣጥሉት ነበር። ታድያ ይህ ጀግና ልክ ጎንደር እንደ ተለኮሰችው አብሪ ጥ*ይት መሃል አዲስ አበባ ላይ አዲስ የነፃነት ችቦ ለኮ*ሰ።

ናሁሰናይ እና የት*ህነግ ወረራ...
=================
ከአራት ኪሎ መንበር በሕዝብ እምቢተንነት ተገፍ*ትሮ መቀሌ መሽጎ የነበረው ትህ*ነግ በእ*ብሪት እና በማናለብኝነት የአማራን ሕዝብ ለዳግም ወረ*ራ ሲዳርገው እልፍ አእላፍት ሆኖ እንደተመ*መው የአማራ ወጣት መካከል ናሁሰናይ እንደ አንዱ ቢሆንም የተላበሰው ስብእናው እንደ ብዙ አስቆጠረው። የቤት መኪናው የነበረችውን ተሽከርካሪ ሸጦ ስና*ይፐር ገዝቶ ወደ ግ*ንባር ዘ*መተ። ናሁሰናይ ቁመናው የቆፍጣና ወታደር ነው። ትጥቁ በሙሉ አብሮ የበቀለ ወይ ለእሱ ብቻ ተለክቶ የተሰራለት ይመስላል።

ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ የትህ*ነግን ወ*ረራ መክቶ ለመመለስ ያልዘመተበት ግን*ባር ያልተንከራተተበት ጎራ፣ ያልከተመበት ም*ሽግ፣ ያልወጣው ያልወረደው ተራራ አልነበረም። በወልቃይት ግንባር፣ በንፋስ መውጫ ግንባር፣ በማይጠምሪ ግንባር፣ በጋሸና እና ቆቦ ግንባር፣ ብቻ ወንድማለም ሕዝብን ከእ*ልቂት ከታደጉ የቁርጥ ልጆች አንዱ ሆነ። ከጎኑ የነበሩ እነ ህርያቆስ እነ ያየሽ ብዙዎቹ ሲ*ሰው ናሁሰናይ ቃል ኪዳናቸውን ተሸክሞ እስከ ቀራንዮ ተከተላቸው። ታድያ በዛ የትህነግ ወረራ ልበ ሙሉ ደፋሩ ጀግና ናሁሰናይ ብዙ ጀብ*ዶች ፈፅሟል። ስና*ይፐር ማራኪ ነው። ለወልቃይት እና ራያ የአማራ ማንነት ብሎም አፅ*መ ርስት ማስመለስ እነ ናሁሰናይ በለግላጋ እድሜያቸው በደ*ማቸው ታሪክ ሰሩ። ቀሪው አደራው ለጓዶቹ፣ ለትውልዱ፣ ለእኔ እና እናንተ ነው።

ለአማራ ሕዝብ ህልውና የተከፈለ መስዋእትነት...
============================
የአማራ ሕዝብ ከወለጋ እስከ ሻሸመኔ፣ ከሐረር እስከ ቤንሻንጉል፣ ከሽዋሮቢት እስከ አዲስ አበባ መሳ*ደዱ እና መታ*ረዱ አልበቃ ብሎ፤ የአማራ ክልል ተብሎ በተሰፈረለት ቀየ ሁሉ የእል*ቂት ድግስ ተላከበት። የአብይ የጥላቻ እና የክፋት በት*ር በጅምላ በአማራ ሕዝብ ላይ ማረፍ ጀመረ። ያኔ ጀግናው ናሁሰናይ ላይመለስ ከቤቱ ወጣ። ስምንት ወራት በበርሃ እየተንከራተተ የፋኖ አብሪ ኮከብ ሆነ። አደራጄ! አጀገነ! አስ*ታጠቀ! መራ! ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ በትግል ተኮትኩቶ ያደገው በስመ ገናናዋ እና ቀደምቷ የጎንደር "ቴዎድሮስ ብርጌድ" ነው። ይህ ጀግና ብዙዎችን ከጎኑ በማሰለፍ "ጃንተከል ብርጌድ"ን አቋቋመ። ከአንጡራ ሃብቱ አውጥቶ ብዙዎችን ስና*ይፐር ገዝቶ ማስ*ታጠቁን የትግል ጓዶቹ ህያው ምስክር ናቸው።

ናሁሰናይ የሚመራው ብርጌድ ከሌሎች ጋር በጋራ ሆነው ነው "የአፄዎቹ ክፍለ ጦ*ር" ን ያቋቋሙት። ይህ ክፍለ ጦ*ር ሰፊ በሆነው ማእከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ጀብ*ዱ እየፈፀመ ይገኛል። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰሎሞን አጠና ደግሞ የናሁሰናይ አጎቱ ጭምር ነው። በየ ቤቱ፣ በየ ቤተሰቡ፣ የሚከፈል ድርብርብ መስዋእትነት። ሻለቃ ሰሎሞን ሐምሌ/ነሐሴ ላይ በነበረው የጎንደሩ ከባድ ው*ጊያ ቆስሎ በደንብ ሳያገግም ነው ወደ ት*ግል ተመልሶ የተቀላቀለው። የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና ግብግብ ከዚህ በላይ በምን ሊገለጥ?!

የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ...
=========================
ሚያዝያ 4, 2016! በታሪክ ተመዝግባ ትቀመጥ!
ሽቅርቅሩ፣ መልከኛው፣ ደርባባው፣ ወንድማለም፣ ናሁሰናይ፣ ባበይ፣ የአማራ ሕዝብ ጠላ*ቶች ዋና ሴራ መጎንጎኛ ምሽግ ወደ አደረጓት አዲስ አበባ ዘልቆ ጠላ*ትን ማሸ*በር መቅ*ጣት ወሰነ። ከባድ ውሳኔ የሚያደርገው ከጎንደር አዲስ አበባ ከ700 ኪሜ በላይ ብዙ እጅግ ብዙ መሰናክል አልፎ መድረስን እና ተልእኮ መፈፀምን ይጠይቃል። ድፍረት ይጠይቃል። ወኔ ይጠይቃል። መጀገን ይጠይቃል። ያ ናሁሰናይ መሆንን ይጠይቃል። የመይሳው ታሪክ ስንቅ ሆነው፣ የጎቤ ጀግንነት በወኔ ሞላው፣ የውባንተ ቆራጥነት በውስጡ ተላበሰው። ናሁሰናይነት!

ከእምየ ጎንደር ተነስቶ አቆራርጦ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዘልቆ ደርሶ ለታላቅ የፋኖ ተልእኮ ከሽዋ አናብስት ጋር መከረ ዘከረ። ቆረጡ! የአገዛዙ ባለስልጣናት መናህሪያ በሆነችው ቦሌ ላይ በቁጥር ጥቂት ሆነው በጀግንነታቸው ግን እንደ ብዙ ሆነው ተፋ*ለሙ። አገዛዙ ምን ያክል እንደተናጠ ከዚህ በኋላ ፍጥጥ ብሎ የሚገለጥ ነው።

በፋኖ ታሪክ አዲስ አበባ ላይ አዲስ ምእራፍ ተጀምሯል። በአማራ ሕዝብ የሚቆምሩ የአገዛዙ ተላላ*ኪዎች ከአሁን በኋላ አዲስ አበባ ተሸሽገው አያመልጡም። የአራት ኪሎ ዘን*ዶዎች በየጎዳናው በየፓርኩ በነፃነት አይጥመለመሉም። ብርክ ይይዛቸዋል። የፋኖ አመራሮች ከአሁን በኋላ የተጠኑ እና በይዘታቸው ከፍ ያሉ ኦፕ*ሬሽኖች #ዘመቻናሁሰናይ ስም እንደሚቀጣጠሉ አጠንክረው እየገለፁ ነው። ናሁሰናይ እና ቁርጠኛ ጓዶቹ የፋኖን አዲሱን የትግል ምእራፍ ወለል አድርገው ከፍተው በክብር ተሰው*ተዋል። ቀሪው እዳ የእያንዳንዳችን ነው። የአማራ ሕዝብ በልጆቹ ቆራጥ ትግል ነፃነቱን ይጎናፀፋል። ህልውናውን ያረጋግጣል። አልፎ ተርፎም ለሃገረ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። እኩልነት! ክብር! በትግል እንጅ በልመና አይመጣም! ድርሻህን ተወጣ!
ናሁሰናይን ተላበሰው! ናሁሰናይ ሁን! ናሁሰናይነት!
ወንድማለም አንተ በሰላም እረፍ!
አንድያ ልጅህን በአደራ እንረከባለን!
የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ!
ሙሉነህ ዮሐንስ
[4/13, 5:00 AM] +41 78 738 03 35: ዝክረ ናሁሰናይ አንዳርጌ!
የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በዘመናችን ጀግንነትን በምግባር ከገለጡ እንቁዎች አንዱ ሻለቃ ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ ነው። ሞትን የናቀ ለአማራ ሕዝብ ክብር እራሱን መስዋእት ያደረገ የአባቶቹ ልጅ ነው።

ከትውልድ ሲቀዳ...💚💛❤️
===========
ናሁሰናይ የ27 አመት አፍላ ወጣት ነው። የተወለደው እስከ ሞ*ት በታመናት፣ አቆላምጦ በሚጠራት፣ እሷም አቀማጥላ በእቅፏ ባሳደገችው በታሪካዊቷ ጎንደር ነው። ለእናቱ ምትክ የሌለው አንድያ ልጅ ነው። በእናት እና አባቱ ቤት ሲያድግ በረከት ሞልቶ የተትረፈረፈላቸው ናቸውና አቀማጥለው በስስት አይን ነበር። አባቱ መምህር አንዳርጌ በመላው ጎንደር የተመሰከረላቸው ኢንቨስተር አራሽ አንደፋራሽ ባለ ትልቅ ፎቅ ባለቤት ናቸው። ወጣት ናሁሰናይንም በስራ እና ምግባር ኮትኩተው ስላሳደጉት ቀልጣፋ የስራ ሰው እንደነበር የቅርብ ጓደኞቹ ይመሰክሩለታል።

ለሕዝብ ነፃነት የተኖረ ወጣትነት...💚💛❤️
====================
ወጣት ናሁሰናይ ሕዝቡን ከጭቆና የማወጣው እኔም ውትድርና ሰልጥኜ ብቁ ስሆን ነው በማለት ገና በለግላጋ እድሜው መከላከያ ተቋም ውስጥ ገብቶ የሞያ ክህሎት እየተማረ ነበር። ነገር ግን አይበገሬነቱን ያዩ፣ በማንነቱ አንገቱን የማይደፋ መሆኑን የተረዱ በዘመኑ ተረኞች የነበሩት የት*ህነግ አንጋቾች "ፅን*ፈኛ ትም*ክህተኛ" ነህ ብለው በግፍ አባረሩት። ነገር ግን በእልህ የተንቀለቀለው የነፃነት ጥማቱን ይበልጥ አናረው እንጅ አንገት አልደፋም። በዛ መሃል ነው ጎንደር ላይ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ 2008 ላይ የተቀ*ጣጠለው።

ጀግናው ኮ/ል ደመቀ ሐምሌ 5 ላይ የነፃነት አብሪ ጥ*ይት ጎንደር ላይ ሲተኩ*ስ እነ ወጣት ናሁሰናይ የጎንደርን ወጣት እያደራጁ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያቀጣጥሉት ነበር። ታድያ ይህ ጀግና ልክ ጎንደር እንደ ተለኮሰችው አብሪ ጥ*ይት መሃል አዲስ አበባ ላይ አዲስ የነፃነት ችቦ ለኮ*ሰ።

ናሁሰናይ እና የት*ህነግ ወረራ...
=================
ከአራት ኪሎ መንበር በሕዝብ እምቢተንነት ተገፍ*ትሮ መቀሌ መሽጎ የነበረው ትህ*ነግ በእ*ብሪት እና በማናለብኝነት የአማራን ሕዝብ ለዳግም ወረ*ራ ሲዳርገው እልፍ አእላፍት ሆኖ እንደተመ*መው የአማራ ወጣት መካከል ናሁሰናይ እንደ አንዱ ቢሆንም የተላበሰው ስብእናው እንደ ብዙ አስቆጠረው። የቤት መኪናው የነበረችውን ተሽከርካሪ ሸጦ ስና*ይፐር ገዝቶ ወደ ግ*ንባር ዘ*መተ። ናሁሰናይ ቁመናው የቆፍጣና ወታደር ነው። ትጥቁ በሙሉ አብሮ የበቀለ ወይ ለእሱ ብቻ ተለክቶ የተሰራለት ይመስላል።

ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ የትህ*ነግን ወ*ረራ መክቶ ለመመለስ ያልዘመተበት ግን*ባር ያልተንከራተተበት ጎራ፣ ያልከተመበት ም*ሽግ፣ ያልወጣው ያልወረደው ተራራ አልነበረም። በወልቃይት ግንባር፣ በንፋስ መውጫ ግንባር፣ በማይጠምሪ ግንባር፣ በጋሸና እና ቆቦ ግንባር፣ ብቻ ወንድማለም ሕዝብን ከእ*ልቂት ከታደጉ የቁርጥ ልጆች አንዱ ሆነ። ከጎኑ የነበሩ እነ ህርያቆስ እነ ያየሽ ብዙዎቹ ሲ*ሰው ናሁሰናይ ቃል ኪዳናቸውን ተሸክሞ እስከ ቀራንዮ ተከተላቸው። ታድያ በዛ የትህነግ ወረራ ልበ ሙሉ ደፋሩ ጀግና ናሁሰናይ ብዙ ጀብ*ዶች ፈፅሟል። ስና*ይፐር ማራኪ ነው። ለወልቃይት እና ራያ የአማራ ማንነት ብሎም አፅ*መ ርስት ማስመለስ እነ ናሁሰናይ በለግላጋ እድሜያቸው በደ*ማቸው ታሪክ ሰሩ። ቀሪው አደራው ለጓዶቹ፣ ለትውልዱ፣ ለእኔ እና እናንተ ነው።

ለአማራ ሕዝብ ህልውና የተከፈለ መስዋእትነት...💚💛❤️
============================
የአማራ ሕዝብ ከወለጋ እስከ ሻሸመኔ፣ ከሐረር እስከ ቤንሻንጉል፣ ከሽዋሮቢት እስከ አዲስ አበባ መሳ*ደዱ እና መታ*ረዱ አልበቃ ብሎ፤ የአማራ ክልል ተብሎ በተሰፈረለት ቀየ ሁሉ የእል*ቂት ድግስ ተላከበት። የአብይ የጥላቻ እና የክፋት በት*ር በጅምላ በአማራ ሕዝብ ላይ ማረፍ ጀመረ። ያኔ ጀግናው ናሁሰናይ ላይመለስ ከቤቱ ወጣ። ስምንት ወራት በበርሃ እየተንከራተተ የፋኖ አብሪ ኮከብ ሆነ። አደራጄ! አጀገነ! አስ*ታጠቀ! መራ! ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ በትግል ተኮትኩቶ ያደገው በስመ ገናናዋ እና ቀደምቷ የጎንደር "ቴዎድሮስ ብርጌድ" ነው። ይህ ጀግና ብዙዎችን ከጎኑ በማሰለፍ "ጃንተከል ብርጌድ"ን አቋቋመ። ከአንጡራ ሃብቱ አውጥቶ ብዙዎችን ስና*ይፐር ገዝቶ ማስ*ታጠቁን የትግል ጓዶቹ ህያው ምስክር ናቸው።

ናሁሰናይ የሚመራው ብርጌድ ከሌሎች ጋር በጋራ ሆነው ነው "የአፄዎቹ ክፍለ ጦ*ር" ን ያቋቋሙት። ይህ ክፍለ ጦ*ር ሰፊ በሆነው ማእከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ጀብ*ዱ እየፈፀመ ይገኛል። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰሎሞን አጠና ደግሞ የናሁሰናይ አጎቱ ጭምር ነው። በየ ቤቱ፣ በየ ቤተሰቡ፣ የሚከፈል ድርብርብ መስዋእትነት። ሻለቃ ሰሎሞን ሐምሌ/ነሐሴ ላይ በነበረው የጎንደሩ ከባድ ው*ጊያ ቆስሎ በደንብ ሳያገግም ነው ወደ ት*ግል ተመልሶ የተቀላቀለው። የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና ግብግብ ከዚህ በላይ በምን ሊገለጥ?!

የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ...💚💛❤️💚💛❤️‼️
=========================
ሚያዝያ 4, 2016! በታሪክ ተመዝግባ ትቀመጥ!
ሽቅርቅሩ፣ መልከኛው፣ ደርባባው፣ ወንድማለም፣ ናሁሰናይ፣ ባበይ፣ የአማራ ሕዝብ ጠላ*ቶች ዋና ሴራ መጎንጎኛ ምሽግ ወደ አደረጓት አዲስ አበባ ዘልቆ ጠላ*ትን ማሸ*በር መቅ*ጣት ወሰነ። ከባድ ውሳኔ የሚያደርገው ከጎንደር አዲስ አበባ ከ700 ኪሜ በላይ ብዙ እጅግ ብዙ መሰናክል አልፎ መድረስን እና ተልእኮ መፈፀምን ይጠይቃል። ድፍረት ይጠይቃል። ወኔ ይጠይቃል። መጀገን ይጠይቃል። ያ ናሁሰናይ መሆንን ይጠይቃል። የመይሳው ታሪክ ስንቅ ሆነው፣ የጎቤ ጀግንነት በወኔ ሞላው፣ የውባንተ ቆራጥነት በውስጡ ተላበሰው። ናሁሰናይነት!

ከእምየ ጎንደር ተነስቶ አቆራርጦ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዘልቆ ደርሶ ለታላቅ የፋኖ ተልእኮ ከሽዋ አናብስት ጋር መከረ ዘከረ። ቆረጡ! የአገዛዙ ባለስልጣናት መናህሪያ በሆነችው ቦሌ ላይ በቁጥር ጥቂት ሆነው በጀግንነታቸው ግን እንደ ብዙ ሆነው ተፋ*ለሙ። አገዛዙ ምን ያክል እንደተናጠ ከዚህ በኋላ ፍጥጥ ብሎ የሚገለጥ ነው።

በፋኖ ታሪክ አዲስ አበባ ላይ አዲስ ምእራፍ ተጀምሯል። በአማራ ሕዝብ የሚቆምሩ የአገዛዙ ተላላ*ኪዎች ከአሁን በኋላ አዲስ አበባ ተሸሽገው አያመልጡም። የአራት ኪሎ ዘን*ዶዎች በየጎዳናው በየፓርኩ በነፃነት አይጥመለመሉም። ብርክ ይይዛቸዋል። የፋኖ አመራሮች ከአሁን በኋላ የተጠኑ እና በይዘታቸው ከፍ ያሉ ኦፕ*ሬሽኖች #ዘመቻናሁሰናይ ስም እንደሚቀጣጠሉ አጠንክረው እየገለፁ ነው። ናሁሰናይ እና ቁርጠኛ ጓዶቹ የፋኖን አዲሱን የትግል ምእራፍ ወለል አድርገው ከፍተው በክብር ተሰው*ተዋል። ቀሪው እዳ የእያንዳንዳችን ነው። የአማራ ሕዝብ በልጆቹ ቆራጥ ትግል ነፃነቱን ይጎናፀፋል። ህልውናውን ያረጋግጣል። አልፎ ተርፎም ለሃገረ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። እኩልነት! ክብር! በትግል እንጅ በልመና አይመጣም! ድርሻህን ተወጣ!
ናሁሰናይን ተላበሰው! ናሁሰናይ ሁን! ናሁሰናይነት!
ወንድማለም አንተ በሰላም እረፍ!
አንድያ ልጅህን በአደራ እንረከባለን!
የጎንደሩ እጮኛ የአዲስ አበባው ሙሽራ!💚💛❤️💚💛❤️
💚💛❤️ ድል ለጀግናው አማራ ፋኖ

የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ*ጦር የምሥረታ መግለጫ!=============እንደሚታወቀው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የአማራን ሕዝብ በጠላ*ትነት ፈርጀው የሚንቀሣቁሡ አካላት በኢ...
11/04/2024

የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ*ጦር
የምሥረታ መግለጫ!
=============
እንደሚታወቀው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የአማራን ሕዝብ በጠላ*ትነት ፈርጀው የሚንቀሣቁሡ አካላት በኢትዮጵያ ስርዓተ መንግሥት መንበር ላይ ተፈናጥጠው በተጠናና መዋቅራዊ ሁኔታ አማራ ሀገር አልባ ለማድረግ እና ከምድረ ገጽ ለማጥ*ፋት ያለ እረፍት ሲሰሩ ኖረዋል እየሠሩም ነው። ይሄ እኩይ ተግባር ደግሞ ከ1983 ዓ.ም እስከ 2010 አጋማሽ ዓ.ም ድርስ በህ*ወሓት መሩ ኢህ*አዴግ ፊትአውራሪነት የተመራ ሲሆን አያሌ ጀግኖቻችን ዋጋ ከፍለዋል። ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እስከ ካህናት አባቶች፣ ከገበሬ እስከ ምሁር፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ የአካል የሞራል የሀብት እንዲሁም ውድ የህይወት ዋጋ ተከፍሎበታል።

ይኼውም ሆኖ አገዛዙን እረፍት የነሡ ብርቅዬ ጀግኖቻችን ለአማራ ህዝብ ታምነው ታግለው ወ*ያኔ ቢወገድም ድጋሜ ለዐቢይ መሩ ቁጥር ሁለት ኢህ*አዴግ ተሸጠ። በዐቢይ አህመድ የሚመራው አሸባሪ አገዛዝ በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ስፋት እና ፍጥነት አማራ እና አማራነትን ከምድረ ገጽ ለማ*ጥፋት በጥድፊያ ያለምንም ማስተባባል እና ይሉኝታ የሙሉ ጊዜ የአገዛዙ ስራው አደረገው። በዐደባባይ ሰበር*ናቸው ከማለት፣ በመላው ኢትዮጵያ ከማሠደድ እና ከማፈናቀል፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ከማገት እና ከመጨ*ፍጨፍ፣ መብት ጠያቂዎችን ከማሠር፣ በተጠና መልኩ አማራ በ3 ዙር እንዲወረር ከማድረግ፣ የኢትዮጵያ ዋስትና የአማራ ብርቱ ክንድ የነበረውን ልዩ*ኃይል በግ*ፍ ከመበተን ያለፈ እና የከፋ አማራን በየቀየው እና በየቤቱ ለማ*ረድ ዐቢይ አህመድ ክተት አውጆ ጦርነት ከፈተ።

ጀግና የማይነጥፍበት የአማራ ምድርም ድጋሜ እልፍ ጀግኖች ከሞቀ ቤታቸው እየወጡ የህልውና ትግሉን ተቀላቀሉ። ለዘመናት ማኅበራዊ እረፍት እንዳይኖረው ተፈርዶበት ከትላንት ተጋድ*ሏቸው ሳያርፉ ወደሌላ ዙሩ መታገል እና ማታገል ከመጡት መካከልም የክፍለ ዘመኑ ክስተት የአማራው ጀኔራል አባታችን ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ግንባር ቀደሙ ነው። አባታችን ለዘመናት ግፍን ተጸይፎ ለአማራ ክብር ታግሏል፣ አታግሏል፣ ትህ*ነግ በግ*ፍ በወ*ረረን ጊዜም የስርዓቱ ሠራዊት የፈራውን የጋሸናን ም*ሽግ ሰ*ብሮ ከሁመራ እስከ ቆቦ ድል በትከሻው የተጻፈ እስኪመስል ድረስ የወራ*ሪውን ጦር በገባቡት ሁሉ ድል ተቀዳጅቶበታል። በመጨረሻም በከባዱ ቆ*ስሎ 6 ጥ*ይት በአካሉ ውስጥ ተሸክሞ የህክምና ጊዜ ሳያገኝ በጎንደር ምድር በመጀሪያ ከአ*ሸባሪው ዐቢይ አህመድ ጦ*ር ጋር ፊት ለፊት ገጠመ። ትግሉ ቅርጽ እና መልክ ይኖረው ዘንድም በአማራ ምድር የመጀመሪያውን ክፍለ*ጦር ጉና ክፍለ ጦ*ርን አቋቋመ። የተማረውን በገፍ የተበተነውን ልዩ*ኃይል እያሰባሰበ፣ ደጉን የአማራ ገበሬ በሰላ አንደበቱ እያስተማረ በላቀ ብስለት ነገሮችን እየተመለከተ ጎንደርን ለማደራጀት ሞከረ፤ ከጎንደር ከተማ ደብረታቦር፤ ከደብረታቦር ጎንደር እየተመላለሠ ድል በድል መሆኑን የምናውቅ ልጆቹ " ገብርዬ" እያልን እንጠራዋለን!!!

አባታችን ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ከ30 በላይ መደበኛ ውጊ*ያዎችን አድርጎ በቀን 10/07/2016 ዓ.ም. ደራ ገላውዴዎስ ላይ ከአፉ የማይለየውን አማራነት በደሙ ጽፎ አልፏል። እኛ ልጆቹም የአባታችን የእውነት መንገድ ላይ ቆመን በስሙ ህልሙን ለማሣካት ከትላንት በበለጠ ሞራል እና ብርታት ላይ እንገኛለን። ከጉና ክፍለ ጦር በተጨማሪ በስሙ "ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ*ጦር" የመሠረትን መሆኑን ለመላው አማራ በኩራት ማብሠር እንወዳለን። ክፍለ*ጦሩ በአብራኩ ክፋይ እና የበኩር ልጁ ሻለቃ ተመስገን ውባንተ እና በመንፈስ ልጆቹ እና ህልም ተጋሪዎቹ የሚመራ ሲሆን አባታችን ሜጀር ጀኔራል ውባንተ ጦርነት በበረታበት ሁሉ የሚገኝ በመሆኑ ጦ*ር በበረታበት የአማራ ምድር ሁሉ ተገኝተን ህልሙን ለማሣካት ከእርሱ የቀሰምናቸው ባሕሪያት እና ጀግንነት ለትውልዱ ለማውረስ እና ህልሙን ለማሣካት የጀመረውን ለመፈጸም በአማራ ፋኖ በጎንደር ስር ባቋቋምነው ክፍለ*ጦር የምንገኝ ልጆቹ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ ነጥቦች ማስተላፍ እንወዳለን:-
1. ለአባታችን ለሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ:-
አባታችን ሁሌም የተመኜኸው የአማራ ነጻነት ሳይረጋገጥ ክንዳችን አይዝልም። ዛሬም ግን ፈገግታህ እሰይ ልጆቼ የሚለው ድምጽህ፤ በመካከላችን የሚጎማለለው ግርማ ሞገስህ ብርታታችን ነው ። ገብርዬ ሆይ ለናኖ ሰከንድ ከልባችን ከዐይናችንም አትጠፋም እኛ ልጆችህ በስምህ ተማምለን ከመንገድህ ላናፈገፍግ እልፍ ሆነን ህልምህን ልናሳካ ቆመናል እና ነፍስህ በሰላም ትረፍ!

2.ለመላው የአማራ ሕዝብ እና የፋ*ኖ ሠ*ራዊት:-
መላው አማራ እና ታጋዩ በአባታችን መሰ*ዋእትነት ማዘኑን ልቡ መሠበሩን እናውቃለን። ዳሩ ግን አባታችን በአምሣሉ በጀግንነት የወለደን ልጆቹ ትግሉ በድል እንዲጠናቀቅ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየታገልን ነውና እምባችሁ ሊታበስ ልባችሁ ሊበረታ ይገባል። በስሙ በተደረገው ዘ*መቻ የተሳተፋችሁትን እጅግ እያመሠግንን፤ በቀጣይም ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ በሚቀጥለው "ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ሁለገብ ዘመቻ" እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።

2. ለአማራ ፋኖ በጎንደር አመራሮች እና
የፋኖ ሠራዊት አባላት:-
ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ የሁሉም አማራ እና ሀገር ወዳድ ተስፋ ቢሆንም እናንተ ሁላችሁም በቅርብ እና በአካል የምታውቁት ወንድማችሁ ነውና ሀዘናችሁ መራር እና የበረታ እንደሆነ እንገነዘባለን:: ስለምታደርጉልን ማጽናናት እና ድጋፍም የከበረ ምስጋና እናቀርባለን ። ዛሬ ተሰባስበን እና ጠንክረን ከጎናችሁ ቆመናል እና ደስ ሊላችሁ ይገባል። በምታዙን በምትሰጡ ግዳጅ ሁሉ ዝግጁ ነን!!!

3. ለሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ
የቅርብ ሰዎች እና የስጋ ቤተሰቦች:-
በእውነት ስለእናንተ ምን ይባላል፤ ከአንድ ቤተሰብ የተከፈለ አማራን የመታደግ ዋጋ፤ ለራስ ያልተኖረ ህይወት ነውና ሁላችንም ልጆቻችሁ ቤተሰቦቻችሁ እና የልጆቹ ወንድሞች እንደሆንን ይልቁንም የቆመለትን አላማ ለማስቀጠል የቆምን መሆናችን በማሠብ ከሀዘናችሁ ትጽናኑ ዘንድ ቤተሰባዊ ምክራችን እናቀርባለን።

4. "ለጎንደር ዕዝ" መስራች አባት አርበኞች እና ወገኖች:-
እኛ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ልጆች አባታችን በሚያከብራችሁ ልክ እናከብራችኋላን በሚያውቃችሁ ልክ እና መጠን እናውቃችኋላን። ጦርነት በተከፈተበት የአማራ ሕዝብ ስንል ሁሉን መገፋቱን ትተን ዛሬም ስለ አንድነት ጥሪያችን ይድረሳችሁ። የአባታችን አቋም እና ምኞት ለሆነው ወጥ የጋራ ተቋም ይኖረን ዘንድ በጀግንነት ውድ ህይወታቸውን በሰጡን በሁሉም አማራውያን ደም እንለምናችኋለን!

5. ለሚዲያ ሰዎች እና የሚዲያ ባለቤቶች በሙሉ:-
በሚዲያው ዓለም ያለባችሁን ጫናና እና ተጽዕኖ ተቋቋምማችሁ ይልቁንም መረጃ ለማግኘት አዳጋች በሆነበት በዚህ ጊዜ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ እና ተጋድሎ ሙያዊ ስነምግባር ጠብቃችሁ እና ገልለተኛ ሆናችሁ ለህዝብ የምታደርሱትን አካላት እናመሰግናለን። ነገር ግን አጀንዳ ማራመጃ ሆናችሁ በሚሰፈረው ንዋይ መጠን ከስነ ምግባር ውጭ በጀግናው አባታችን ላይ ዘመቻ የከፈታችሁትን እና የተሳዳቢዎችን ልሳን የሆናችሁትን ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት እየሰራችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ በይቅርታ ትመለሱ ዘንድ የመጨረሻ ጥሪ ማቅረብ እንወዳለን። ይህ ባይሆን ግን ከጠላት ለይተን የማናያችሁ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል።

በመጨረሻም መላው የአማራ ሕዝብ እና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ድጋፋችሁን ለፋኖ የህልውና ትግል አጠናክራችሁ ትቀጥሉ ዘንድ ጥሪያችን በድጋሜ ይድረሳችሁ።
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በተባበረ የአማራ ሕዝብ ሁለገብ እርብርብ ድል ያደርጋል!
=====
የአማራ ፋኖ በጎንደር አካል የሆነው
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር:-
√•1~ክፍለ ጦር መሪ
*ጌታ ሰው በሬ
=ም/ል
*ተመስገን ውባንተ
√•2~ዘመቻ መሪ
*ለምለሙ ታፈሰ
*ተመስገን ጓዴ
*ም/ል የቆየ አበጀ
√•3~አስተዳደር
*እያሱ አባተ
*ም/ል
√•4~ሕዝብ ግንኙነት
*ብዙአየው ወንድም ነው
*ም/ል ቴድሮስ አለም
√•5~አደረጃጀት
*ፀዳሉ ሙላት (መምህሬ)
*ም/ል አማኑኤል ዋሴ
√•6~ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ
*መብራቱ ባለው
=ም/ል
*ታድሎ ደሳለኝ
√•7~ጤና መኮነን
*ዳንኤል ጌጡ

√•8~ቀጠናዊ ትስስር
*
√•9~ወታደራዊ እቅድ እና እስትራቴጂ መምሪያ
አያሌው ደራሽ
= ም/ል
√•10~ወታደራዊ ምልመላ እና ስልጠና
* ግርማ ብሩ
*ጥሩየ ሙጬ
√•11~መረጃ
* ሀ. ፀ.
*ብ. ም.
√•12~ማህበራዊ ዘርፍ
*አባይነው ጌታ
*
√•13~ሎጅስቲክ ሀላፊ
*ሰለሞን አደመ
*ፋሲል ሲሳይ
*ባንቲ ምህረቱ
√•14~ጽህፈት ቤት ሀላፊ
*ጥላሁን (ቄሴ)
√•15~ፖለቲካዊ መምሪያ ሀላፊ
*ሀቅ ፀጋየ
=ም/ል ሀብታሙ ቢያዝን
==================
የአማራ ፋኖ በጎንደር!!!!

የአማራ ፋኖ በጎንደር በግፍ አገዛዙ ጦርነት ለተከፈተበት የአማራ ሕዝብ ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ጥሪ አቅርቧል። ሁላችንም የየድርሻችንን እንወጣ!April 13 to April 27 2024!
10/04/2024

የአማራ ፋኖ በጎንደር በግፍ አገዛዙ ጦርነት ለተከፈተበት የአማራ ሕዝብ ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ጥሪ አቅርቧል። ሁላችንም የየድርሻችንን እንወጣ!
April 13 to April 27 2024!

19/03/2024

የአማራ ፋኖ በጎንደር
በፋኖ እያሱ የተሰጠ ማብራሪያ

17/03/2024

Ethiopia ፦ "ትግላችን ሁለንተናዊ ነው፣ ወደጦርነት የገባነው ተገደን ነው"

16/03/2024

የአማራ ፋኖ በጎንደር የምስረታ ጋዜጣዊ መግለጫ
Amhara Fano in Gondar Inauguration Press Release

14/03/2024

Ethiopia፦ ሰበር! የጎንደር ፋኖ ዕዝ ተመሰረተ፣ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ተሰጠኢትዮጵያ #ቀይባሕር #ኤርትራ #ዐብይአህመድ #ወልቃይት #አማራ #ፋኖ Ethiopia፦ ለህወሓት በአውሮፕላን የገባው መሳሪ.....

Address

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Fano in Gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share