15/03/2023
"ማዕድን የመበልጸጊያ ዘርፍ ነው!" አቶ ኃይሌ አበበ
~~~~
የማዕድን ሀብቱ አንዱ የመበልጸጊያ ዘርፍ ነው። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፕሮጀክት የሆነውና በቀን 130ሺ ኩንታል የማምረት አቅም ያለው የለሚ እንሳሮ ስሚንቶ ፋብሪካ በሚቀጥለው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ምርት ማምረት ይጀምራል፡፡
በክልላችን በአምስት ዘርፎች የሚካተቱ 40 የማዕድን አይነቶች ተገኝተዋል፡፡ የነበረው ሥርዓት አማራ ክልል ያለውን የማዕድን ሀብት በግልጽ እንዲታወቅ አለመፈለጉ፣ ዘርፉን ለማልማት የአደረጃጀት፣ የቴክኖሎጂ እና የክህሎት ችግሮች የነበሩት ነው፡፡
የክልላችን የማዕድን ዘርፉ አዲስ እና እምቅ ሃብት ባለቤት ነው፡፡ በክልሉ ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ክምችት አለ። በተሰራው የስነ ምድር ጥናት መሠረት ክልሉ 14 በመቶ የማዕድን የክምችት ባለቤት መሆኑ ተረጋግጧል።
ያለውን የማዕድን ክምችት ማልማት ከተቻለ ኢትዮጵያ 7መቶ 50 ሚሊዬን ዶላር ወጪ አድርጋ ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባውን የድንጋይ ከሰልን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ይችላል፡፡
ዘርፉ የትኩረት ማዕከል አድርጎ ከሚሰራባቸው መካከል አንደኛው የስራ ዕድል ፈጠራ ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ ለ23 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። በዚህ ዓመት ብቻ በማዕድን ልማት ዘርፍ 56 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር በእቅድ ይዘን እየሰራን እንገኛለን።
አቶ ኃይሌ አበበ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕድን ቢሮ ኃላፊ