EBC sport news

  • Home
  • EBC sport news

EBC sport news Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from EBC sport news, Film/Television studio, .
(2)

25/09/2023
31/01/2023

!!!

1. የምትኖርበት ቤት ማንነትህን አይወክልም!

አሁን ያለህበት ቤት ወደፊት የምትኖርበትን ስፍራ እስክታዘጋጅ መቆያህ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትኖርበት ቤት ማንነትህን እንዲተረጉመው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

2. የምትሰራበት ስፍራ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምትሰራው ስራ ጨዋና የስራ ሰው የመሆንህ ማሳያና ለወደፊት ማዳበር ለምትፈልገው ነገር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትሰራው ስራህ የማንነትህ መለኪያ እንዲሆን ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

3. የምታገኘው ደሞዝ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምታገኘው የገቢ መጠን ራእህን በመከታተል ላይ ሳለህ ለጊዜው ያለህን ፍላጎት ማሟያና ቀዳዳ መድፈኛ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ደሞዝህ የማንነትህን ደረጃ እንዲመድብ ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

4. የትምህርት ደረጃህ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን በጭንቅላትህ ውስጥ ያለው እውቀት ወደፊት ማወቅ ለምትፈልገው ነገር መነሻ፣ እንዲሁም ጥበብን ጨምረህበት የወቅቱን ሁኔታህን መግፊያ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የትምህርት ደረጃህ ሰው የመሆንህን ዋጋ እንዲጨምረውና እንዲቀንሰው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

5. ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ነገር ማንነትህን አይወክልም!

ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ሃሳብ በመላ ምት ላይ የተመሰረተ፣ ከራሳቸው ምልከታ፣ ውስንነትና ልምምዳቸው ጋር የተዛመደ፣ ማመን የሚፈልጉትን ነገር እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ማንነትህን እንዲተረጉሙት ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

ከላይ የዘረዘርኳቸውን እውነታዎች በሚገባ ስትገነዘብ በዙሪያህ ካሉ ሁኔታዎች ባሻገር ዘልቀህ የመሄድ አቅም ይሰጥሃል፡፡ ይህንን ሃሳብ በመታጠቅ ቀና ብለህ ራእይን ተመልከት፣ እቅድን አውጣ፣ ባለህ አቅም የመጀመሪያዋን እርምጃ ተራመድ፣ ግራና ቀኝ ሳትል በርትተህ መንገድህን ቀጥል . . . ትደርሳለህ !!!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።በእግር ኳሱ ዓለም ትልቅ ስም ያለው ብራዚላዊው ታሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቹ ባጋጠመው ህመም ...
29/12/2022

ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በእግር ኳሱ ዓለም ትልቅ ስም ያለው ብራዚላዊው ታሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቹ ባጋጠመው ህመም ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም ህይወቱን ማዳን አልተቻለም።

ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር ሶስት / 3 የዓለም ዋንጫዎችን ማሸናፍ የቻለው ፔሌ በሰማንያ ሁለት ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EBC sport news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share