Biftuu Barii

Biftuu Barii Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Biftuu Barii, Digital creator, .

30/10/2023

አዲሱን ትውልድ መረዳት!!

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የመደመር ትውልድ ከቀደሙ ትውልዶች የተለየ እንደሚሆን እሙን ነው፡፡ የመደመር ዘመኗ ኢትዮጵያ ኀብረ ብሔራዊ አንድነት ያለባት፤ የወንድማማችነት እሴት የፀናባት፣ የሲቪክ ባህል የጎለበተባትና ቀጣናዊ ትሥሥር የጠነከረባት ትሆናለች፡፡

ኀብረ ብሔራዊ አንድነቷ እውነተኛ ፌደራሊዝምን ተግባሪ፤ ብዝኃ ማንነትን አቃፊና ብዝኃ ልሳንን አስተናጋጅ ይሆናል፡፡ ሌላውን እንደራሱ የሚመለከት፤ ብሔሩንና ሀገራዊ ብሔረተኝነትን ያስታረቀ፤ የትናንቱን በጎ ነገር ይዞ የትናንቱን ሥህተት የሚያርም፤ትናንትን ከዛሬና ከነገ የስማማ፤በእነዚህ ጉዳዮች የልሂቃንን ስምምነት በማምጣት፤ ሀገራዊ መግባባትና ዕርቅን የሚያሰፍን ትውልድ ይፈጠርባታል፡፡

በስምምነትና በመግባባት የጋራና አስታራቂ ሕጎችን በመፍጠር የሚገነቡ ተቋማት፤ሰላሟንና ብልጽግናዋን ያረጋግጡላታል፡፡

የጎረቤቶቿን ሰላምና ዕድገት እንደ ራስዋ የምትመለከት፤ በጋራ ለማደግ ያለመ አካሄድን የምትከተል፤በንግድና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለመተሳሰር የምትሻ፤ ቀጣናዊና አህጉራዊ ግንኙነቶቿን በመደመር መርሕ የምትመራ ሀገር ትሆናለች፡፡

የመደመር ትውልድ ገጽ 155

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biftuu Barii posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share