Oromia Tourism

  • Home
  • Oromia Tourism

Oromia Tourism Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Oromia Tourism, Digital creator, .

20/01/2024

"የ ጥምቀት ከተራ ሀይማኖታዊ በዓል የሰላም ፣የመተሳሰብ ፣ የመተባበር ፣ የመደጋገፍ፤ የእንግዳ ተቀባይነታችን እሴት የሚጎላበት እና በህብር ደምቀን ለአለም የምንታይበት እንቁ ሀብታችን ነው"፡፡

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅ/ቤት ኃላፊ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 የጥምቀት ከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የጥምቀት ከተራ በዓል በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በድምቀት የሚከበር፤ በዩኒስኮ በመንፈሳዊና በማይዳሰስ ቅርስነት ከመመዝገቡ ጋር ተያይዞ በርካታ ቱሪስቶች ወደ ሀገራችን በመምጣት የሚታደሙበት ድንቅ ሐይማኖታዊ በዓል ነው ፡፡ እንደ ከተራና ጥምቀት ያሉ ሀይማኖታዊ በዓላት ሀገራችን ለበርካታ አመታት ጠብቃ ያቆየቻቸዉ የሰላም ፣የመተሳሰብ ፣ የመተባበር ፣ የመደጋገፍ እንዲሁም እንግዳ ተቀባይነት ባህላችን እና ህብር ውበታችን ጎልተዉ የሚታወዩባቸዉ እንቁ ሀብታችን ናቸዉ፡፡

ሀይማታዊ እና ሀዝባዊ በዓላት የኢትዮጵያዊያን ቱባ ባህል እና አይነተ ብዙ ትሁፊት የሚንፀባረቅበት ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የዉጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ሀገራችን በመትመም የሚታደሙበት በመላዉ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የበዓሉ ታዳሚዎች በባህል አልባሳቶቻቸው ደምቀዉ እና አሸብርቀዉ የሚታደሙበት እና ህብረብሄራዊ በሆነ ገፅታ የሚከበር በዓል መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ፡፡ እነዚህን ዉብ እና ድንቅ የሆኑ በዓላትን ፣ ታሪካዊ ሁነቶችን፣ ቱሁፊቶችን ጠብቆ ለቀጠይ ትዉልድ ማስተላለፍ ግድ ይለናል ፡፡

በተጨማሪም የጥምቀት በዓል ባህላዊ እሴቶቻችንን የምንለዋወጥበት ጠብቀን ያቆየናቸዉን አስደናዊ ትሁፊቶች የምንጋራበት ፣ በመቻቻል ሁሉም ከሁሉም ጋር የሚጋራዉ ታላቅ በዓል በመሆኑ አንድነታችን አና አብሮነታችን እንደ አለት የሚጠነክርበት ክስተት ነዉ፡፡የበዓሉ ድምቀት እና ሀይማኖታዊ ትሁፊቱን ለማሳነስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎች እራሳችንንና አካባቢያችንን በመጠበቅ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም በዓሉን በመፈቃቀርና በመተሳሰብ በፍፁም አንድነት እና ወንድማማችነት በተሞላበት ሁኔታ እንድናከብር ከወዲሁ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በድጋሚ እንኳን ለ2016 የጥምቀት ከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
አቶ ፍቃዱ ተሰማ

የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅ/ቤት ኃላፊ
መልካም በዓል!!!

20/01/2024
20/01/2024

ከሲሪላንካው ፕሬዝዳንት ራኒል ዊከርሜሲንጌ ጋር ባደረግነው የሁለትዮሽ ውይይት የንግድ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን ለማላቅ ያለንን ዝግጁነት አረጋግጠናል።

Marii garlamee Pirezdaantii Sirii Laankaa, Raaniil Wikremesingeh waliin teenyeen walittidhufeenya daldalaa keenya cimsuufi dhimmoota gar-daneessa ta'an irratti walta'insa keenya cimsuuf qophaa'ina qabnu waliif mirkaneessineerra.

In our bilateral meeting with President Ranil Wickremesinghe of Sri Lanka we affirmed our readiness to enhance commercial ties and collaborate on multilateral issues.

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oromia Tourism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share