Mihret Abebe

Mihret Abebe Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mihret Abebe, Digital creator, .

16/06/2024
16/06/2024

ለዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን 18 ቀናት ይቀሩታል።
*************

16/06/2024
16/06/2024
16/06/2024
16/06/2024
16/06/2024
16/06/2024
16/06/2024

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ገባ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2016(ኢዜአ)፦በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገብቷል።

የልኡክ ቡድኑ ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ የገባው በብሪክስ ሃገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው።

ከሰኔ 9 እስከ 12/2016 በሚካሔደውና ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ፎረም ላይ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ በብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ይሳተፋሉ።

የልኡክ ቡድኑ ከፎረሙ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል ሃገራት ከሆኑ አቻ የፓርቲ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚካሔድም ኢዜአ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

15/06/2024
15/06/2024

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት እንኳን 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያለ መልዕክቱን ያስተላልፋል
****
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እርስ በእርሱ መደጋገፍ እና መቻቻል፣ መተባበርና አብሮነት በማጠናከር ሊሆን ይገባል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብር የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

በተያያዘም ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት በማጎልበት እንዲሁም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት ድጋፉን እንዲያጠናክር የክልሉ መንግስት በዚህ አጋጣሚ ይጠይቃል።

የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ለኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

መልካም በዓል!

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
ሐረር

15/06/2024

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአረፋን በዓል አቅመ ደካሞችን በመደገፍና በማሰብ እንዲያከብር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አሳሰቡ
***************
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የ1445 ዓ.ሒ. የዒድ አል-አድኃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር ካለው ላይ ለአቅመ-ደካማ ወገኖቹ እንዲያካፍል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አሳሰቡ።

ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ይህን ያሳሰቡት የዒድ አል-አድኃ በዓልን ምክንያት በማድረግ አስቀድሞ በተቀረፀ መልዕክታቸው ነው።

የአረፋ ቀን አሏህ (ሱ.ወ.) ፀጋውን የለገሳቸው ሙስሊሞች የዑዱሂያ እርድ የሚያከናውኑበት መሆኑን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፤ እነዚህ ሙስሊሞች ከሚያርዱት እርድ ለተቸገሩ ወገኖቻቸው፣ በተለይም ለአቅመ ደካማና በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግሮች ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ማካፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

"እጅግ በጣም አዛኝና ሩኅሩኅ የኾነው ጌታችን አሏህ (ሱ.ወ.) ይቅር ባይነትን ይወዳል" ያሉት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፤ "ተበድሎ ይቅር ያለን ሰው አሏህ (ሱ.ወ.) የሠራውን ጥፋት ይቅር የሚለው በመኾኑ፣ ሁላችንም ይቅር ልንባባል ይገባል" ብለዋል።

የዘንድሮውን ዒድ አል-አድኃ (አረፋ) ለየት የሚያደርገው የሀገራችን የኢትዮጵያ ልጆች ሀገራዊ ምክክር እያደረጉ የሚገኙበት ወቅት ላይ በመሆኑ ነው ብለው፤ ሀገራዊ ምክክሩ ለጋራ ሀገራችን ሰላማዊነት ጠቃሚ መኾኑን በመረዳት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በያለበት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕግ ባለሙያዎችን፣ ዓሊሞችን፣ ምሑራንን፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና ለሀገር የሚያስቡ ሰዎችን በማሰባሰብ፣ የሙስሊሙን ጥያቄዎች በማደራጀት ለሚመለከተው አካል መላኩን ሸይኽ ሐጂ ተናግረዋል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት መሆኑን የተናገሩት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፤ ሁሉም የሰላም ዘብ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈው፣ ለሀገራችንና ለመላው ዓለም ሙስሊሞች በዓሉ የደስታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

08 / 10 / 2016

15/06/2024

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት እንኳን 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያለ መልዕክቱን ያስተላልፋል

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እርስ በእርሱ መደጋገፍ እና መቻቻል፣ መተባበርና አብሮነት በማጠናከር ሊሆን ይገባል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብር የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

በተያያዘም ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት በማጎልበት እንዲሁም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት ድጋፉን እንዲያጠናክር የክልሉ መንግስት በዚህ አጋጣሚ ይጠይቃል።

የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ለኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

መልካም በዓል!

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
ሐረር

15/06/2024

በሀረሪ ክልል 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከበአሉ ጋር ተያይዞ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ገናናው ጥበቡ በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት የበአሉን አከባበር የተመለከተ የፀጥታ እቅድ ወቶ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

በአሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የሰው ኃይል ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ከኮሙዩኒቲ ፖሊሲንግ አደረጃጃቶች እና ከሰላም አምባሳደሮች ጋር በጋራ ተቀናጅቶ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለው ባስተላለፉት መልዕክትም ሕዝበ ሙስሊሙና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ለወንጀልና ለደህንነት አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለአካባቢው ፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉም የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mihret Abebe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share