Eman Salih

Eman Salih Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eman Salih, Digital creator, .

24/04/2024
24/04/2024
24/04/2024
24/04/2024

ሐረርን ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረርን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎች ተስማሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በከተማው የሚስተዋለውን የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ ለማልማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር ተፈራርመዋል።

ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ሐረርን ለነዋሪውና ለጎብኚው ምቹና ተስማሚ የማድረግ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል፡፡

በፕላስቲክ ተጽዕኖ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከልና በዘርፉም የሥራ ዕድል ለመፍጠር ጥረት መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱም በክልሉ ያለውን ውስን መሬት ከቆሻሻ በማዳን በአግባቡ ለልማት መጠቀም ያስችላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አሰፋ ቶልቻ ኩባንያው የሚያከናውነው ሥራ ደረቅ ቆሻሻ የሆነውን ፕላስቲክ ወደ ሀብት የሚቀይር መሆኑን አመላክተው÷ ይህም ሥነ-ምኅዳርን በመጠበቅና የሥራ ዕድል በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚነትን ያጎለብታል ብለዋል።

የኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ቅዱስ ፍስሃ በበኩላቸው÷ ኩባንያው የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን በመፍጨት ጡብ፣ ብሎኬት፣ ኮለንና ሌሎች ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን እንደሚያመርት ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የአካባቢንና የከተሞችን ውበት በማስጠበቅ ለዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

24/04/2024
24/04/2024
24/04/2024
24/04/2024

በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሰራል - አቶ ጌቱ ወዬሳ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ፡፡

የክልሉን ሰላምና ፀጥታን ለማጎልበት እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሂዳል።

በውይይቱ ላይ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት በክልሉ የሚገኘው አንፃራዊ ሰላም ከማስቀጠል አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢውን ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ያደረገውን አስተዋጽዖ አድንቀው ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እያከናወነው የሚገኘውን ተግባር እንዲያጎለብትም ጠይቀዋል።

በቀጣይም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሰራል። ሀገር ታፍራና ተከብራ እንድትቀጥል የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሆኑም በአንድነትና በመተባበር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በማጠናከር የሀገሪቱን ሉአላዊነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በመተባበር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በማጠናከር የሀገሪቱ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ በትጋት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ ላይም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓም sz

23/04/2024

New harari music cover mashup Alewi Zoe Mami Hashim Omera New Harari Music

ለሀገር ክብርና ለዜጎች ሰላም የሚዋደቁ ጀግኖች
23/04/2024

ለሀገር ክብርና ለዜጎች ሰላም የሚዋደቁ ጀግኖች


23/04/2024

“Harariitti gama miidiyaafi komunikeeshiniitiin hojiiwwan bu’aa qabeessa hojjetamaa turaniiru”
- Obbo Heenook Mulunaa
*******************
Gaazexaa Bariisaa

Naannoo Hararitti ji’oottan sagan darban keessatti gama miidiyaafi komunikeeshiniitiin hojiileen bu’a qabeessa ta’an hojjetamuu Waajjirri Komunikeeshinii Mootummaa naannichaa beeksise.

Hogganaan Waajjira Dhimmoota Komunikeeshinii mootummaa naannichaa Obbo Heenook Mulunaa hojiilee ji'oota sagal dabran keessatti hojjataman ilaalchisee ibsa kennaniiru.

Naannichatti gama miidiyaafi kominikeeshiniitiin ji’oottan sagal darbanitti hojiilee gaariin hojjetamuu ibsaniiru.

Odeeffannoowwan hawaasa biraan gahuu bira darbee ajandawwan diiguumsaa fashaleessuun hojiileen boonsaan hojjetamuu himaniiru.

Qabeenya turiizimii naannichaa beeksisuufi faayidaa nageenya, obbolummaa, waliin jireenya, aadaan waldanda’uu akka dagaagee ittifufu gochuu keessatti karaa miidiyaalee addaddaatiin hojiileen bu'aa qabeessa tahan hojjetamaa turuu dubbatan.

Kana malees, hojiilee misoomaafi bulchiinsa gaarii naannichatti hojjetamaa turan karaa miidiyaalee naannoofi biyyaalessaatti fayyadamuun odeeffannoo ummata biraan gahuun akka danda'ame himaniiru.

Keessattuu hojiilee miidiyaafi komunikeeshinii sirnaan hogganuun tajaajila odeeffannoo ammayyaawaa yeroon gaafatu diriirsuun hojiin milkaa'ina qabu akka hojjetame dubbataniiru.

Obbo Heenook ittidabaluun karaa mul’ata gaarii naannichaa ijaaruun hariiroo gaariin ummataafi mootummaa gidduutti akka jiraatuuf riqicha ta’uun hojiin odeeffannoo ummata biraan gahuu hojjatamaa ture jedhaniiru.

Keessattuu dhimmoota haala yeroo naannoofi biyyaalessaa keessatti hirmaannaa hawaasaa cimsuuf xiyyeeffannoon kennamee hojjatamuufi hubannoo waloo uumuu keessatti dameen komunikeeshinii gaheesaa akka bahatu gochuuf tattaaffiin guddaan godhamaa turuu ibsaniiru.

Ji'oota bara bajataa hafan keessattiis kaayyoo dhaabbatichaa gahumsaan milkeessuufi fedhii odeeffannoo hawaasaa guutuuf ciminaan kan hojjatan tahuu ibsaniiru. Kominikeeshinii naannichaatu gabaase.

23/04/2024

የመደመር ዴሞክራሲ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ነው!!

መሪ ሰነዳችን የሆነው የመደመር መጽሀፍ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመትከልና ለማጽናት በሚደረገው ጥረት ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከል በሀገራችን የወንድማማችነት እሴትና የሲቪክ ባህል ደካማ መሆናቸውን እንደ ትላልቅ ሳንካዎች ይጠቅሳቸዋል።

ኢትዮጵያዊያን ከመጣንበት የብሄረ-መንግስት ምስረታና ሀገረ-መንግስት ግንባታው ውስብስብነት የተነሳ ከተናጠል ቡድናዊ እውነቶቻችን ተሻግረን የወል እውነት መገንባት ስላልቻልን ከተወለድንበት ብሄርና ጎጥ፣ የምንከተለውን ሀይማኖትና እምነት፣ ከምናራምደው የፖለቲካ አመለካከት የተነሳ እርስ በርሳችን ስንገፋፋ፣ ስንናቆር፣ ብሎም ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት አዙሪት ዉስጥ ስንማቅቅ የኖርንበት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ይሄው ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ደካማ የወንድማማችነት እሴት የህዝበኝነት (Populism) ሰለባ የሆኑ የፖለቲካ ሀይሎች እንዲፈጠሩ ስለሚያደርግ እሱም ዞሮ ዞሮ ዴሞክራሲን ያደናቅፋል፡፡ የሲቪክ ባህል ደካማነትም ለዴሞክራሲያችን መቀጨጭ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቶአል፡፡

ከዚህ ባህል ደካማነት የተነሳ ዜጎች የኔብለዉ ከሚያምኑት ነጠላ ቡድናዊ አጃንዳዎች (የብሄር፣ የሀይማኖት ወዘተ) ተሻግረዉ ሀገራዊ አሰባሳቢ አጀንዳዎች ላይ አነጣጥረው መደገፍ፣ መቃወምና መምረጥ አልቻሉም፡፡ የመደመር ዴሞክራሲ አነዚህን የዴሞክራሲ ጋሬጣዎችን ምንነት፣ ምንጮቻቸውንና የአደናቃፊነት ደረጃቸውን በወጉ ለይቶ እየሰራባቸው ይገኛል፡፡

የመደመር ዴሞክራሲ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ነው፡፡ የመደመር ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያዊ የዴሞራሲ እጦት ኢትዮጵያዊ መፍትሄ የሚያፈላልግ ነው፡፡ ግቡም የማኅበረሰብና የሲቪክ መብቶችንና ጥቅሞች ወጥነትና ዘላቂነት ባለው አግባብ ማረጋገጥ ነው፡፡

ከሁሉ በላይ ደግሞ ወንድማማችነት፣ ነፃነትና እኩልነት ቁልፍ የዴሞክራሲ ባህል እሴቶች (ምሰሶዎች) ስለሆኑ በቤተሰብ፣ ማህበረሰብ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎችና መሰል ተቋማት ደረጃ ማበብ እንዲችሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ወጥነትና ዘላቂነት ባለው አግባብ እንዲወጡ መደረግ አለበት።

23/04/2024

በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉ ተገለፀ

AMN - ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም

በሀረሪ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ በተቋሙ ባለፍት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በኮሙዩኒኬሽን እና በሚዲያው ዘርፍ አመርቂ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እንዲተዋወቁ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጠናከር በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የተጠናከረ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማህበራዊ ሚዲያና በአካባቢው ሚገኙ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎች በመጠቀም ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።

በተለይም የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራን በአግባቡ መምራትና ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉን ተናግረዋል።

አቶ ሔኖክ አክለውም የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችም ሲከናወኑ መቆየቱን አክለው ገልፀዋል።

በተለይም በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲያጎለብት ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶት ስለመሰራቱ አንስተው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም የጋራ መግባባት ከመፍጠር አንጻር የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት መደረጉን አስረድተዋል።

በያዝነው የበጀት አመት ቀሪ ወራትም ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ በብቃት ለመወጣትና የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኔኬሽን መረጃ ያሳያል።



ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eman Salih posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share