15/09/2025
በኢትዮጵያ ዘንድሮ ከ5285,882 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መሀል ያለፉት 48,920፣ የወደቁት ደግሞ 536,962 ሆነዋል። በሌላ አገላለፅ 91.6% ተማሪዎች ወድቀው 8.4% ብቻ አልፈዋል ነው።
ይህ የትምህርት ስርዐቱን የሚመሩት አካላት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት የወደቀ ነው የሚለውን ለማሳየት ብቻ በማለም እያደረጉት የመጣ አደገኛ ልምምድ ነው:: ልምምዱ የተማሪዎችን እያደገ የሚሄድ ልጅነታቸውን; የሐገሪቱ የትምህርት መሠረተ ልማት ያሳደረባቸውን ውስንነት ታሳቢ ሳያደርግ የሚገታ; ወለጆችን ጥረት የማይመለከት እንዲሁም ከአመታት በሇላ ሐገሪቱን የሚቀበል enlighted ትውልድ የማያስቀር አደገኛ ልምምድ መሆኑን ለመመልከትና ለመገምገም አይፈልጉም:: በመሆኑም የትምህርት ስርዓቱ የግል ፍላጎትን ብቻ እንጂ ሰፊ ዓላማ ባላቸው አመራሮች እየተመራ አለመሆኑን እነዚህ ልምምዶች እያስመለከቱን ይገኛሉ:: በትምህርት መሠረተ ልማቱ ላይ እዚህ ግባ የሚባል investment ሳይደረግ ውጤቱን መገምገም ጥፋት ብቻ እንጂ ዓላማው ግልፅ አይሆንም::
የትምህርት ሚንስቴር በተከታታይ ዓመታት ልያሳዬን እየሞከረ ያለው ትውልድ ለማብቃት የተወጣውን የራሱን ሀላፊነት ሳይሆን''' ትውልዱ ላይ ታይቷል'' ያለውን ጉድለት ብቻ እየሆነ መጥቷል::
የመማር ማስተማር ግብዓቶች እጥረት ማለትም በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች የመማሪያ መፃህፍት፣ ላብራቶሪዎች እና ቤተ-መጻሕፍት እጥረት አለ። ታዲያስ ተማሪዎች ያለ በቂ ግብዓት እንዴት ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ?
ከመሰረተ ልማት አንፃር ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ምቹ ናቸው ወይ? በክፍል ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር መጨናነቅ፣ የንፅህና መጠበቂያ ስፍራዎች እጥረት እና ሌሎች መሰረተ ልማታዊ ችግሮች በውጤቱ ላይ የራሳቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፋቸው አይቀርም። ለዚህም ነው አሁን ''አለፉ" ከተባሉትም ያለፉት ከሺህ በላይ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ሳያሳልፉ በተሻለ አፈፃፀም የግል ትምህርት ቤቶችና የመንግስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልያሳልፉ የቻሉት::
በእውነቱ ትምህርቱን የሚመሩ ግለሰቦች በትውልዱ ላይ ከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት እያስከተሉ ከመሆናቸውም ባለፌ እያስከተሉት ያለው ማህበራዊ ቀውስ ቀላል አይደለም:: ይህ ውድቀት በተማሪዎችና በቤተሰቦቻቸው መካከል ከፍተኛ ውጥረት ይፈጥራል። ወላጆች ለልጆቻቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ስጋት ሊገባቸው ይችላል።
በመሆኑም ይህ የፈተና ውጤት ከመንግስት እና ከትምህርት አመራሮች ትልቅ ኃላፊነትን ይጠይቃል። ተማሪዎቹ በብዛት የወደቁት ለምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ በግልፅና በሙያዊ መንገድ መመለስ አለበት።
መንግስት የችግሩን መንስኤ እና ዘላቂ መፍትሄ መቀየስ ያስፈልጋል። ይህ ማለት በትምህርት መሰረተ ልማትና ጥራት ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ማድረግ ማለት ነው። በተለይም የተማሪ ምዘና በፈተና ብቻ ከመታጠር ይልቅ ተለዋዋጭነት ያለው የትምህርት ስርዓት መከተል ያስፈልጋል:: ፈተናው ብቻ የተማሪዎችን ዕውቀት መመዘኛ መሆን የለበትም። የትምህርት ስርዓቱ የተማሪዎችን የችሎታና የፍላጎት ልዩነት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት። ምክንያቱም
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በየዓመቱ ወድቀው የትምህርት ምህዳሩን ለቀው መውጣታቸው የራሱ የሆነ የሀገር የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄን ያስነሳል።
ይህ ውጤት የትምህርት ስርዓቱን የውድቀት ማሳያ ብቻ ሳይሆን፣ በሐገር መፃዕ ዕድል ላይ የተቃጣ ትልቅ አደጋ እንደሆነ ማሰብ ይገባል። አለበለዚያ፣ በአመታት በኋላ ሀገርን የሚመራ ብሩህ ትውልድ የማጣት አደጋ ያንዣብብብናል።