Sabrina Kalid

  • Home
  • Sabrina Kalid

Sabrina Kalid “በእቶኑ እሳት ውስጥ"Dhaloonni kitaaba kana dubbisuu hedduu fayyadama.ይኽንን መፅሃፍ የሚያነብ ትውልድ ብዙ ይጠቀማል።

11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
10/06/2024

በሐረር ከተማ ጎዳና ተዳዳሪነትን ለማስቀረት እየተሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ሰኔ 3/2016 (አዲስ ዋልታ) በሀረር ከተማ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ችግር ለመፍታት በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ የተጀመሩ ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ለመደገፍ፣ የጉዳት ተጋላጭነታቸውን ለመከላከልና ቁጥጥር ለማድረግ ከተቋቋመው ግብረ ኃይል ጋር ተወያይተዋል።

በመድረኩም ግብረ ኃይሉ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት መገምገማቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በሐረር ከተማ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።

ይህም ዜጎቹ የወንጀል መንስኤና የትራፊክ አደጋ ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና የዜጎችን ጉዳትና ተጋላጭነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመናን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ማህበረሰብም እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ እንዲያጎለብት ግንዛቤ የማስፋት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አመላክተዋል።

አስፈጻሚ ተቋማትም የወጣው ደንብ በአግባብ አውቀው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

10/06/2024
10/06/2024

በሐረር ከተማ ጎዳና ተዳዳሪነትን እና የጎዳና ላይ ልመናን ለማስቀረት በቅንጅት ይሰራል- አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀረር ከተማ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ችግር ለመፍታት በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ የተጀመሩ ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎችን ለመደገፍ፣ የጉዳት ተጋላጭነታቸውን ለመከላከልና ቁጥጥር ለማድረግ ከተቋቋመው ግብረሃይል ጋር ተወያይተዋል።

በመድረኩም ግብረሃይሉ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት ተገምግሟል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በሐረር ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።

ይህም ዜጎቹ የወንጀል መንስኤና የትራፊክ አደጋ ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና የዜጎችን ጉዳትና ተጋላጭነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተቋማዊ አሰራርና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ መልኩ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመናን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ማህበረሰብም እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ እንዲያጎለብት ግንዛቤ የማስፋት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አመላክተዋል።

አስፈጻሚ ተቋማትም የወጣው ደንብ በአግባብ አውቀው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍም አቅም የሌላቸው ዜጎችን የመደገፍና ማብቃት ስራን መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ማህበረሰብም የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

10/06/2024

የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ

በሀረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጭ ዲጂታል ሰዓትን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች እና ቀሳቁሶች ይዞ መገኘት የተከለከለ መሆኑንም ቢሮው አብራርቷል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዘከሪያእ አብዱልአዚዝ የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በአግባቡ ለመስጠት ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ሞዴል ፈተና መሰጠቱን እንዲሁም ፈተናው ታትሞ ዝግጁ መደረጉን ጠቅሰዋል።

የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ክልል አቀፍ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በተለይም ተማሪዎችን ካለፈው ተሞክሮ በመነሳት በስነልቦና ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ ለፈተናው የሚረዱ ቅድመ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሰኔ ወር በሚሰጠው ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተናም 5675 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም ቢሮው ከመምህራን ማህበር፣ ከጤና ቢሮ፣ ከፖሊስ እና ከጸጥታ ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጭ ሌላ መገልገያ ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንም ነው ምክትል ቢሮ ኃላፊው የገለጹት፡፡

በተለይም ዲጂታል ሰዓትን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችንና ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት የተከለከለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት ማንኛውም አይነት የጤና ችግር ቢያጋጥማቸው የህክምና እርዳታ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች በ19ኙም የፈተና ጣቢያዎች መመደባቸውን ጠቁመው ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናውን እንዲሰሩ አሳስበዋል።

10/06/2024

የመደመር እሳቤ ኃይል በማስባሰብ መርህ ያምናል። አብሮ የማደግ እሴትም እንዲዳብር ይሠራል!

ብቸኝነት ጉድለት መሆኑንና ጉድለትም እንደሚያስከትል መደመር ይረዳል። ጉድለትን ሟሟያ ኃይል የማሰባሰብና በጋራ ለማደግም አማራጭ ነዉ ።መደመር ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ማጠናከሪያ ሰንሰለት ሲሆን የብዝሃነትን ተፈጥሯዊነት መረዳት፣ መቀበልና ማክበር ደግሞ የመደመር እሳቤ ተቻችሎ የመኖር አንዱ መገለጫ ነዉ።

የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ... ልዩነቶች ተፈጥሯዊ ፀጋዎች፣ ህብረ ቀለማዊ ዉበቶች በመሆናቸዉ ከፉክክርና ከመገፋፋት ይልቅ ለትብብር ቅድሚያ በመሥጠት ለሀገር ግንባታዉ ሂደት መደላድል በጋራ መሠለፍ ጠቃሚ ነዉ።

ከፉክክር ይልቅ ትብብርን ማፅናት ለጋራ ብልጽግናዉ ጉዞ መሳካት መሠረት ነዉ። 'የኔንና እኔን ብቻ ' ከሚል ቁንፅል እይታ ተሻግሮ የ ' እኛናት' ን እሳቤ ማጠናከር ኢትዮጵያ ከተጋረጡባት ቀዉሶች እንድትወጣ ድርሻን ማበርከት ይችላል፡፡

ልዩነቶችን ያከበረ እሳቤ መፍጠር ፣ እሳቤዉንም የጋራ በማድረግ ትልቋ ኢትዮጵያ በሚመጥናት የትልቅነት ደረጃ ላይ እንድትደርስ የዜግነትና የሞራል ኃላፊነታችንን እንወጣ።የጠላቶቻችን የጥፋት አጀንዳ በቀላሉ ሊመክን የሚችለዉ በመደመር እሳቤ ዉስጥ ሆነን ትግላችንን ሰናጠናክር ነዉ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sabrina Kalid posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share