Rooba isa

Rooba isa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Rooba isa, Digital creator, .

07/11/2023

ልዩነቶቻንን ተሻግረን ዐቅማችንን ለማካበትና ከብቸኝነት ጉድለት ለመውጣት የጋራ ግብ ማስቀመጥ እና ከብቸኝነት ጉድለት ለመውጣት ተነሳሽነት ማሳየት አስፈላጊዎች ናቸው፡፡

“ የጋራ ግብ” የመደመር አንዱ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ስንል መደመር ልዩነትን ተሻግሮ ለጋራ ዓላማና ጥቅም መሰለፍን ስለሚመርጥ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ልዩነት ውስጥ የጋራ ግብን መሠረት አድርጎ መተባበርና ውጤት ማምጣት ይቻላል ብሎ ታሳቢ ያደርጋል፡፡ የዓድዋ ድል እውን የሆነው በውስጣችን የነበረውን ልዩነት የተሻገረ የጋራ ግብ ስለያዝንና ለዚያ ስለተሰለፍን ነው፡፡

በትብብርና በፉክክር መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ አንዱን ትተን በአንዱ ላይ ብቻ ካተኮርን የጋራ ግብን ማረጋገጥና የጋራ ህልውናን ማስቀጠል አይቻልም፡፡

ለምሳሌ በሀገራችን በቡና ዘርፍ የተለያዩ የግል ባለሀብቶች እርስ በእርሳቸው ፉክክር ሲያደርጉ የተሻለ ጥራት ያለው ቡና ወደ ገበያ እንዲቀርብ በር ይከፍታሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አጠቃላይ ዘርፉ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ከመፍታት አንጻር ትብብር ያስፈልጋል፡፡

ቡና አብቃይ አርሶ አደሮችን በጋራ መደገፍ፣ ዘመናዊ የቡና ማከማቻ በጋራ መገንባት እንዲሁም ሀገርን በሚወክል በአንድ የንግድ ምልክት ምርቶቻቸውን በዓለም ገበያ ለመሸጥ ቡና በአእምሯዊ ንብረትነት እንዲመዘገብ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡

በቡና ምርትና ሽያጭ ሂደት ውስጥ ያሉ ተዋንያን ተባብረው በጋራ በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ቢሰሩ የዘርፉ አጠቃላይ እድገት እመርታዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፣ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ያሳድጋሉ፡፡

የጋራ ግብ የጋራ ህልውናንና የጋራ ድልን ያቀዳጃል፡፡ ለጋራ ግብ መሰለፍ ጤናማ የሆነና ሚዛኑ የተጠበቀ ትብብርና በፉክክር እንዲኖርና ኃይላችንን መሰብሰብ እንድንችል የሚያደርግ ነው፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rooba isa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share