Ra'iisaa M

Ra'iisaa M Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ra'iisaa M, Digital creator, .

31/10/2023
31/10/2023

የመደመር ትውልድን የፈጠረው አብዮት አይደለም፡፡ ጥቂት ግለሰቦች ወይም የለውጥ ተዋንያን ሃሳብና ፍላጎታቸውን በጉልበት ጭነውበት የተፈጠረም አይደለም፡፡

በጊዜ ሂደት ትውልዱ ክፉና ደጉን ተመልክቶ ፣የሚጠቅመውን መንገድ ለመምረጥ በሚያደርገው መውተርተር ውስጥ የወለደው የጋራ ጠባይና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡

ይኼ በህዝብ ገፊነትና በብዙሃኑ ልሂቃን ትብብር በታሪክ ሂደት የተፈጠረ የህብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ፍፁም ነው አንልም፤ ብዙዎችን ወደ ሚያግባባና ይኼ ነው ተብሎ ወደ ተበየነ ግብ ለመጓዝ የሚያስችለውን ትክክለኛ አቅጣጫ ገና በመፈለግ ላይ መሆኑም አይካድም፡፡

እንደቀደሙት ለውጦች ያለፈውን በዜሮ አባዝቶና አማራጭ ምዕራፎችን ዘግቶ እንደ አዲስ ከመጀመር ልይቅ ቀስ በቀስ ሪፎርም እያደረጉ መጓዝን የመረጠ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ዙሪያውን ወንዞች ተደርድረው እንደሚያጠጡትና የዘሩበትን እንደሚያበቅል ለም መሬት ተደርጎ ሊታሰብ ይችላል፡፡

በአግባቡ ከተያዘ መሬቱ ለብሩህ መነሻ የሚሆን ትልቅ የለውጥ ስንቅ ነው፡፡
የመደመር ትውልድ ገጽ 265

24/10/2023

Tokkummaan Sab-daneessummaa Obbolummaa Irratti Ijaarame Utubaa Ijaarsa Biyyaati
------
Itoophiyaan biyya hirmaannaafi tokkummaa saboota, sab-lammootaafi uummattootaan ijaaramte, hirmaannaa isaaniitiinis birmadummaafi bilisummaan ishee kabajamee har'a geessedha.

Akkasumas biyya saboota, sablammootaafi uummattoota afaan, aadaa, amantiifi seenaa qaban of keessatti hammattee kan jirtu; garaagarummaan kunis akka madda miidhaginaatti ilaalamuun hariiroo sabootaa cimsuun tokkummaa biyyaa jabeessee tursiisedha.

Heddumminni carraafi miidhagina malee madda rakkoo miti. Dhimmi ijoon akkaataa heddummina kana sirna federaalizimii sabdaneessa diriirsuun hariiroo cimaa, wal qixxummaa, jaalalaafi obbolummaa jabeessuun Itoophiyaa hundaan ijaaramtu, hunda fakkaattu, hundaaf taatu ijaaruudha.

Kanaafuu, tokkummaa sab-daneessaa obbolummaa sabootaa irratti ijaarame daran cimsuufi misooma jalqabame hirmaannaa waloo sabootaa sablammootaafi uummattootaan itti fufsiisuun badhaadhina hundagaleessa dhugoomsuun dhimma xiyyeeffannoo olaanaan hojjetamaa jirudha.

Facebook: https://www.facebook.com/oromiabc
Telegram: https://t.me/Oromiacommunicationaffairsbureau
Twitter: twitter.com/OromiaBureau
YouTube: https://www.youtube.com/results?search_query=Oromia+Communication+Bureau
TikTok: tiktok.com/
Website: https://www.oromiacommunication.gov.et/
kallachaOromia: https://m.facebook.com

24/10/2023

ፖለቲካዊ ስርዐቶች የሐሳብ ውጤቶች ናቸው።የፖለቲካ ፓራዳይም የፖለቲካ ቡድኖችና ግለሰቦች "የተሻለው የፖለቲካ ሥርዐት እንዴት ሊፈጠር ይችላል?"የሚለውን ጥያቄ የሚመፅሱበት አጠቃላይ የእይታ ማዕቀፍ ነው።

ይህ ማዕቀፍ የተሻለ ስርዐትን ለመፍጠር ፖለቲካ እንዴት ይመራል? በፖለቲካ ውስጥ እንዴት መንቀሳቀስ አለብን? ችግሮችን እንዴት እናልፋቸዋለን? የሚሉ ጉዳዮችን የሚወስን አጠቃላይ ማዕቀፍ ነው።በዚህ ማዕቀፍ ስርዐቶች ይፈጠራሉ ወይም ይከስማሉ፣ይጠነክራሉ ወይም ይሰበራሉ።

እነዚህ ስርአዐቶችም በሁለት ዓይነት የለውጥ ሂደቶች የተወጠሩ ናቸው።የመጀመሪያው "የፖለቲካ መደርጀት ነው"።የፖለቲካ መደርጀት በፖለቲካ ስርዐት ውስጥ የሚከሰት አዎንታዊ ለውጥ ነው። ሁለተኛው "የፖለቲካ መፋለስ ሲሆን መነሻው ከውስጥም ይሁን ከከባቢው፣ስርዐቱ ድጋፍን መገንባት ሲያቅተው፣የራሱን ሂደት መቆጣጠር ሳይችልና፣አንድነቱን ማስጠበቅ ሲሳነው፣የሚፈጠር ነው።

ስርዐቱ የቆመበትና የሚመራበት የሐሳብ ማዕቀፍ ውስጣዊ እና ውጫዊ ለውጦችን ተቋቁሞ፣ድጋፍን ማመንጨት ሲያቅተው፣በስርአቱ ውስጥ መፋለስን ይፈጥራል።

የፖለቲካ ፓራዳይም ጥንካሬውና ዘላቂነቱ የሚወሰነው፣ፈተናዎችን ተቋቁሞ የፖለቲካ ስርአትን ወደ መደርጀት በመውሰዱ ነው።አንድ የፖለቲካ ፓራዳይም ለስርአቱ ጥንካሬውን ለማምጣት፣በስርአቱ ለሚፈጠሩ ተፅእኖዎች በቂ ምላሽ መሰወጠትና መቋቋም የሚችል መሆን አለበት።መቋቋም ለሚመጣ ተፅዕኖ ምላሽ መስጠትን አመላካች ነው።

እነዚህ ተፅዕኖዎች ውስጣዊም ውጫዊም መነሻ ሊኖራቸው ይችላል።ከስርአቱ ውስጥን ይነሱ፣ከስርዐቱ ውጪ፣ከባቢ የፖለቲካ ስርአቱ መደርጀት ወይም መፋለስ የሚመሰረተው፣አሉታዊ ለውጦችን ለመቋቋም ባለው ዐቅም ላይ ነው።

የመደመር ትውልድ ገፅ 18-19

24/10/2023

የሀገር ግንባታ የዘመናትና የማያልቅ የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ነው።ሀገር የትውልዶች ትስስር ውጤት ናት።የትውልድ ቅብብሎሽ ሲባል፣በትውልዶች መካከል በሚኖር ጠንካራ ተግባቦት የሚፈጠር፣የጠንካራ እሴት መወራረስ ነው።

በዚህ አይነት መንገድ መልካም ያልሆኑ እሴቶች እየታረሙ፣ጠንካራ ሀገራዊ እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ፣ዘመኑን እየዋጁ ሲሄዱ፣ሀገር እየተጠናከረ ይመጣል።

ትውልዶች የሚያልፉበት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ የተለያየ ከመሆኑ የተነሳ፣በትውልዶች መካከል የሚኖር ልዩነት አይቀሬ ነው።

አልፎ አልፎም ልዩነቱ ወደ ተቃርኖና የለየለት ጠላትነት ሊለወጥ ይችላል።በትውልዶች መካከል ያለውን ልዩነት ተረድቶ ለማስማማትና ለማቻቻል አለመሞከር በትውልዶች መካከል የትስስር ክፍተት ይፈጥራል።

ይህ የትውልድ ትስስር ክፍተት እየሰፋ ሲሄድ በሀገር ጥንካሬ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል።በቀደመውና በተተኪው ትውልድ መካከል ያለው የዕሴትና የባህሪ ልዩነት እጅግ የሰፋ ሲሆን ፣በማህበረሰብ መካከል የጥቅም ገወጭት በመፍጠር አፍራሽ ሀገራዊ ሁኔታ ይፈጥራል።

አንዱ የአንዱን ሁኔታ የሚገነዘብ ሳይሆን፣ተተኪው የቀደመውን አምርሮ የሚጠላ፣የቀደመው ተተኪውን የሚያብጠለጥ በመሆኑ፣ባለው ላይ የመገንባት ሳይሆን የማፍረስ ባህል እንዲፈጠር ያደርጋል።

የመደመር ትውልድ ገፅ 23

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ra'iisaa M posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share