Rior ahmed

Rior ahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Rior ahmed, Digital creator, .

16/06/2024
16/06/2024
01/06/2024

"ሀረር ከተማን ዘመናዊ ከተማ ( Smart City ) የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" -አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ሲስተምና መሰረተ ልማቶች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርአት የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሀረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም አፕሊኬሽን (መተግበሪያ) እና የቋንቋ መተርጉሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የCCTV መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሀረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራእይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርአት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሀረር ዘመናዊ ከተማ( smart city) ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከተማዋን በስትራቴጂ ልማት እቅድ በመምራት ከተማውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስማርት ሲቲ ለማሳደግ ወሳኝ ብለዋል።

ሀረርን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ይህም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሳልጥ፤ የከተማ መሠረተ ልማትን የሚያስፋፋ፤ ወጪን እና የሀብት ብክነትን የሚቀንስና የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው በሚከናወኑ ስራዎችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነትና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

01/06/2024

የሐረር ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረር ከተማን ዘመናዊ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች እና መሰረተ ልማቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርዓት÷ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና ለንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሐረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም መተግበሪያ እና የቋንቋ መተርጎሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የደህንነት ካሜራ መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህንነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሐረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርዓት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሐረርን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት እንደሆኑ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

01/06/2024

"ሀረር ከተማን ዘመናዊ ከተማ ( Smart City ) የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" -አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ሲስተምና መሰረተ ልማቶች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርአት የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሀረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም አፕሊኬሽን (መተግበሪያ) እና የቋንቋ መተርጉሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የCCTV መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሀረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራእይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርአት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሀረር ዘመናዊ ከተማ( smart city) ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከተማዋን በስትራቴጂ ልማት እቅድ በመምራት ከተማውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስማርት ሲቲ ለማሳደግ ወሳኝ ብለዋል።

ሀረርን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ይህም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሳልጥ፤ የከተማ መሠረተ ልማትን የሚያስፋፋ፤ ወጪን እና የሀብት ብክነትን የሚቀንስና የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው በሚከናወኑ ስራዎችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነትና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

13/05/2024

#የኢትዮጵያ #ጠቅላይ #ሚኒስትር #ክቡር #ዶ/ር

13/05/2024
13/05/2024
13/05/2024
12/05/2024
12/05/2024

ለ #ጽዱኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር የምናሰባስብበት ልዩ የዲጂታል ቴሌቶንን ተቀላቅለናል።

የዚህ አኩሪ ታሪክ ባለድርሻ እንሁን!

12/05/2024

ሐረሪ ሑስኒቤ 26ታኝ አለም ሑቁፍ ሐረር ሞይ ዚነጀሓ ሐለትቤ መግደርሌ የትፊርኪዛል ጠብቲ ዪትሜሐርቤ ዛልነት ተገለጣ።

ተኼታይ ወህሪቤ ዱጉስ ዚታ ሐላትቤ ሐረር አሲማቤ ዪትገደርዛል 26ታኝ አለም ሑቁፍ ሐረር ሞይ ዚነጀሓ ሓለትቤ መግደርሌ የትፊርኪዛል ጠብቲ ዪትሜሐርቤ ዛልነት ሐረሪ ሑስኒ ሑኩማ ኮሙዩኒኬሽን ሓጃች መ/ጋር ገለጣ።

ሑስኒዞ ሑኩማ ኮሙዩኒኬሽን ሓጃች መ/ጋር መስኡል ጌስሲ ሔኖክ ሙሉነህ 26ታኝ አለም ሑቁፍ ሐረር ሞዩው ዪነክዛልቤ ዚሰጦ መግለጥቲቤ አለም ሑቁፍ ሐረር ሞይ ዪ ቤቀድ ዚትሊያዩ አለም ባዳችቤ ዪትገደሪቤ ቀላህ ዛያነት አቀነኡ።

ተኼታይ ወሕሪቤ ሐረር አሲማቤ ዪትገደርዛል 26ታኝ አለም ሑቁፍ ሐረር ሞይ ዚነጀሓ ዪኹኒኩት ሑስኒዞ ሑኩማ ላቂ ኤመሮታችቤ ዪትኤቀድዛል ሐቢዶኛቹው መኤሰስቤ ኪም ዲላጋ መቦአዞው ገለጡማ አኽኸእ ወቅቲቤም ጠብቲ ዲላጋች ዪትሜሐርቤ ዛልነት አሴነኑ።

ሞይዞ ሐረር አሲማቤ መትገደርዞ ቃጪቤ ዪነብሩዛሉ ሐረሪያቹው ዋ ሐረር ወልዳች ታሪኻችዚዩው፣ አዳችዚዩ ዋ ቀድራችዚዩው አክከዞቤ ዩቁኩት ጊርጋራ ሞሸዞቤ ዲባያ ባድዚዩ ዋ ሸእቢዚዩ በህ ዛለዩ ተቃጠሮት ዋ ዳይነቱው ዚቅ ያሹኩት የትፊርካል ባዩ።

ዪቤ ዲባያም ቃጪ ባድቤ ዪነብሩዛሉ ሐረሪያች ዋ ሐረሪ ወልዳች መሐለቅዚዩ ዋ ኢቆትዚዩው መትኣወንቤ ሑስኒዞቤ ዳይነት ኔሮት ኩሽኩሽቲ ለአይቤ ተሳአዶትዚዩው ዚቅ ያሹኩት ጊርጋራ ያሻል ባዩ።

ሞይዞ ሐረር ኣሲማቤ መትገደርዞ ኦር ሒጃጆቱው መቼኸልሌ፤ ኢንቨስትመንት ሌጦት ዋ ዘያሪነት ኩሽኩሽቲ ዪጡኚኩት ሞሸሌ ኦር ነሲብ ዪኸልቂዛልነት አቀነኡ።

ሑስኒዞ ሑኩማም 26ታኝ አለም ሑቁፍ ሐረሪ ሞይ ዚነጀሓ ዪኹኒኩት ቁጭነትቤ ዪደልጊቤ ሐል ባል።

ኢስበልበላት አለምቤ ዪትረኸብዛሉ ሐረሪያች ዋ ሐረሪ ወልዳቹም ዚወዚራች መላቅ ዶክተር አብይ አህመድ ሺኢሽታኝ ጂልሌ ሑሉፍ ዛሾ ኪላሖቱው መትቄበልቤ ዋ ሙች ሓለታቹው መትናፈእቤ ሞይዞ ለአይቤ መትረኸብሌ አኽኸእቤ ጠብ ዪሊኩት ኪላሖት አቀረቡ።

12/05/2024

Guyyaa Idile Addunyaa 26ffaa Harar naannichatti geggeeffamu milkaa'inaan kabajuuf qophiin godhamaa akka jiru ibsame.

Guyyaa Idile Addunyaa 26ffaa Harar naannichatti geggeeffamu milkaa'inaan kabajuuf qophiin godhamaa akka jiru Waajjirri dhimmoota Kominikeeshinii Mootummaa Naannoo Hararii beeksise.

Itti Gaafatamaan Waajjira Dhimmoota Kominikeeshinii Mootummaa Naannichaa obbo Heenook Muluneh ibsa kannaniin guyyaa idil addunyaa 26ffaa Harar kanaan dura biyyoota addunyaa adda addaa keessatti kabajamaa akka ture ibsaniiru.

Guyyaan idil Addunyaa 26ffaan Harar baranaa ji'a dhufu magaalaa Hararitti kabajamu milkaa'inaan kabajuuf mootummaan naannichaa koreewwan sadarkaa adda addaa hoggantoota olaanoon hogganaman hundeessuun gara hojiitti akka gale ibsaniiru.

Ayyaanni kun magaalaa Hararitti kabajamuun isaa ummata Hararii fi dhalattoonni naannichaa biyya ambaa jiraatan seenaa, aadaa fi duudhaa isaanii akka baraniif qofa osoo hin taane, walitti dhufeenyaa fi hariiroo biyyaa fi ummata isaanii waliin qaban cimsuufiis ni gargaara jedhaniiru.

Kana malees, Ummata Hararii fi dhalattoonni Hararii biyya alaa jiraatan qabeenya isaanii beekumsa qaban walitti gurmeessuun hojiilee misooma naannichaa keessatti hirmaannaa isaanii akka cimsaniifiis ni gargaara jedhaniiru.

Ayyaanni kun maqaa gaarii naannichaa beeksisuu fi ijaaruuf, invastimantii baballisuu fi sochii turizimii naannichaa guddisuuf haala mijjaawaa kan uumu ta’uu addeessaniiru.

Mootummaan naannichaa sagantaa guyyaa idil addunyaa 26ffaa Harar karaa bifa milkaa'aa ta'een akka kabajamuuf xiyyeeffannaan hojjachaa jira jedhan.

Ummata Hararii fi dhalattoonni naannichaa biyyoota ambaa adda addaa keessa jiraatan haala mijjaawaa fi waamicha dhaloota 3ffaa Kabajamoo Ministira Muummee Dr.Abiyyi Ahmad dhiheessan fudhachuun ayyaanicha irratti hirmaachuuf akka of qopheessan waamicha dhiheessaniru.

Address

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rior ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share