Wabii Dhalootaa

  • Home
  • Wabii Dhalootaa

Wabii Dhalootaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wabii Dhalootaa, Digital creator, .

     /Jimaa
09/02/2024




/Jimaa

Walqixxummaa dinagdee
08/02/2024

Walqixxummaa dinagdee

18/12/2023
14/12/2023

በኮንትሮባንድ የገቡ ቴሌቪዥኖች እና ሌሎች ዕቃዎች ተያዙ

ታኅሣሥ 3/2016 (አዲስ ዋልታ) በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 35 እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በተሽከርካሪ ተጭነው ሲጓጓዙ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 03278 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ ተጭነው ሲጓጓዙ የተያዙት ትናንት ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሻነት ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተከናወነ የማረጋገጥ ስራ 35 ቴሌቪዥኖች፣ 70 የተለያዩ ሞባይል ስልኮች፣ የሞባይል ስልክ አክሰሰሪዎች እንዲሁም ጣቃ ጨርቆች እና ሌሎች ዕቃዎች ተጭነው ተገኝተዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል::

የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያቀጭጭ እና ህጋዊ የንግድ ስርዓቱን የሚጎዳ በመሆኑ የፀጥታ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ይህንን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል በሚያከናውኑት ተግባር ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

09/12/2023

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማትን አሸነፈች

ሕዳር 29/2016 (አዲስ ዋልታ) አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ መሆኗን የዓለም የአትሌቲክስ አስታውቋል፡፡

አትሌት ለተሰንበት በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ10 ሺሕ ሜትር ውድድር መጠናቀቅ በኋላ የመውደቅ አደጋ አጋጥሟት የነበረችውን ሆላንዳዊቷን ሲፈን ሀሰን ያጽናናችበት ሁኔታ የሽልማቱ አሸናፊ አድርጓታል።

09/12/2023

ከአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

ሕዳር 29/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከተዋቀረ ጀምሮ በርካታ ሀገራዊ እና ከተማዊ ጉዳዮች ማለትም ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

ከፓርቲዎችና ከከተማ ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየፈታ መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማንኛውም ቡድንም ሆነ ግለሰብ ለሚመለከተው ለመንግሥት አካል አሳውቆ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግስታዊ መብት መሆኑን እንረዳለን።

የሚመለከተው የመንግሥት አካል ይህን ሕገ መንግስታዊ መብት ዜጎች ለመጠቀም ሕጋዊውን መንገድ ተከትለው በሚጠይቁበት ወቅት ሁሉ ተቀብሎ የማስተናገድ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነት እንዳለበት ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶቻቸውን በተለይም የአደባባይ ሰልፎችን ለመጠቀም በሚያስቡበት ወቅት ሁሉ ሀገራዊ እና ከተማዊ የፀጥታ ሁኔታውን በመገምገም የሚደረጉ ሰልፎች ከፀጥታ አንፃር ሊያመጡ የሚችሉትን ጉዳቶች የመመዘን እና ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት የመተንበይ ብሎም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የመስራት ኃላፊነት እንዳለባቸው መረዳት ይኖርባቸዋል ብለን እናምናለን።

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል:-

(1). ሀገራችን እና ከተማችን ያለችበትን ሁኔታ ያላገናዘበ በሌሎች ለሁከት እና ለብጥብጥ መነሻ የሚሆን ሰልፍ መጠራቱ አናምንም። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥያቄዎችን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ይቻላል። በመሆኑም የተጠራው ሰልፍ አግባብነት የሌለው እና ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑን ምክር ቤቱ ያምናል።

(2). የከተማችን ነዋሪዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የጋራ ምክር ቤቱ ተሳታፊ አለመሆኑን እና ወቅቱን ያልጠበቀ ጥሪ እንዲሁም ማሕበረሰብን ለእንግልት እና ለተጨማሪ ጫና የሚዳርግ ነው ብሎ ምክር ቤቱ ይረዳል።

(3). የመንግስት የፀጥታ አካላትም ሆኑ የከተማ መስተዳድሩ ፀጥታን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ሕግ ለማስከበር ሲባል ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎች በሕግ አሰራር መሠረት ጉዳያቸው ተጣርቶ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያገኙ እንጠይቃለን።

4. የከተማችን ነዋሪዎች የራሱን እና የአከባቢውን ሰላም ከፀጥታ አካላት ጋረ በመሆን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ህዳር 29/2016 ዓ.ም

09/12/2023
Amala Namoota Shira Xaxxootaa                          👇 👉1. Ofii Mul'achuuf Si dhoksu.👉2. Ofii Mi'aahuuf Si Hadheessu.👉...
05/12/2023

Amala Namoota Shira Xaxxootaa
👇
👉1. Ofii Mul'achuuf Si dhoksu.
👉2. Ofii Mi'aahuuf Si Hadheessu.
👉3. Amanamoo Of Fakkeessuuf
Amanamummaa Kee Mormu.
👉4. Cimina Kee Dhoksanii
dadhabina Kee qofa Odeessu.
👉5. Yeroo Si Bira jiran Si jajanii,
Duuba Kee immoo Si Hamatu.
👉6. Sababa Tokko Malee Si jibbu.
👉7. Hammeenya Kee qofa Ol
Kaasani Odeessu.
👉8. Akka Nama Waan Hunda
Beekuutti Of Tilmaamuun, Ana
Malee jedhu.
👉9. Waan Gaarii Hojjatan Hunda Beekamtii Argachuuf qofa Hojjatu.

31/10/2023

መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ፤ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው- አብርሃም በላይ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ፤ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷መከላከያ ሃገር ነው፤ መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ፣ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው ብለዋል ::

መከላከያ ሲነካ፣ መከላከያ ሲደፈር ሃገር ተደፈረች! የምንለውም ለዚህ ነው ያሉት አብርሃም በላይ(ዶ/ር) የሃገር መከላከያ ሰራዊት ብሔሩም፣ ዘሩም፣ ሃይማኖቱም ሆነ እምነቱ ኢትዮጵያ እና ህዝቦችዋ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል::

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ከዘር፣ ከመንደርና ከጎጥ የአስተሳሰብ ወጀብ ሳይበግራቸው፣ ሃገርና ህዝባቸውን አስቀድመው ፣በአቋማቸው ፀንተው በመታገል ዓርአያ ለሆኑ ጀግኖች መከላከያ ዕውቅና ሰጥቷል ብለዋል::

ይህ ዕውቅና አገር የሰጠችው እውቅና መሆኑን ገልፀው እውቅና ለተሰጣቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

"ረዥም ማሰብና ማየት ብሎም ለአላማ መፅናት ውጤቱ እንዲህ ያለ ላይ መድረስ ነውና ለህዝባችንና ለሀገራችን ልዕልና ሁላችንም እንትጋ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wabii Dhalootaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share