Bichenatube.com

  • Home
  • Bichenatube.com

Bichenatube.com እኔ ምለዉ ለምንድነው ግን ራሱን ወክሎ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ዓይኑን የሚያጉረጠርጠዉ??

19/12/2023

ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ !!

የአማራ ህዝብ እየታገለ ያለው ለህልውናው ነው። ይህን ስንል በአማራ ህዝብ ላይ በአለም ታይቶ ማይታወቁ አሰቃቂ ግፎች ተፈጽመውበታል። ለምሳሌ ያክል፦ ከነፍስ ወከፍ እስከ ጅምላ የዶዘር ቀብር፤ ህፃናትን ከመቆራረጥ እስከ የእናት ሆድ መሰንጠቅ፤ ከእምነት ተቋማት መውደም እስከ አባቶች መቃጠል፤ ከተማሪዎች መታገት፣ ሰነድ መቃጠል፣ መደፈር፣ ከፎቅ መወርወር እስከ አሰቃቂ ግድያዎች፣ ተንቀሳቅሶ መስራት ማይቻልበት፣ ሾፌሮች የሚታገቱበት አለፍ ሲልም በአማራነታቸው የሚታረዱበት፣ በአማራነቱ በየቦታው የሚፈናቀልበት፣ የልማት ጥያቄና መማር ቅንጦት የሆነበትና እንደህዝብ መጥፋት አለበት ተብሎ ተፈርጆ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ለመጨፍጨፍ የተዘመተበት ህዝብ ነው። ስለዚህ የአማራ ህዝብ የሚታገልለት ጽኑ የሆነ አላማና ግብ አለው።

የጎጃም ዕዝ ያወጣውን ሶስተኛውን መግለጫ ዕዙ ሳይሆን ከዕዙ ውጭ የሆነ አካል ፅፎ የላከው ነው በማለት የሚዲያ ዘመቻ የከፈቱና ያስከፈቱ አካላት መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነት ያልተረዱ መሆናቸውን የተገነዘብን ሲሆነ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን የጎጃም ዕዝ በውጭም ሆነ በውስጥ የራሱ ባልሆኑ ሀይሎች የማይዘወር እና የአማራ ህዝብ ትግል በወለዳቸው፤ ከጎጃም ማህፀነ ለምለም እናቶች በተገኙ፤ በእሳት ቀለበት እየተራመዱ ትግሉን በሚመሩ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚመራ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን። በመሆኑም የተወሰኑ ውይይቶች ጥሪያችንን ከተቀበሉ የቀድሞ አደረጃጄቶች ጋር የተጀመረ ሲሆን ችግር ፈቺ የሆነ ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን እየገለጽን ዉጤታማ እንዲሆ የተለያዩ ስራዎች ተጀምረዋል። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ይህን ጨፍጫፊ ስርዓት ማስወገድ የመጀመሪያ መፍትሄ አድርጎ አገረ መንግስትን የመስራት ጥበብ ከሌላ አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር የራሱን አሻራ እንደሚያስቀምጥ ጥርጥር የለንም እያልን ዕዙ ባንዳንድ ጉዳዮች ከተወያዬ በኋላ ይህን ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ, እጃችሁን እንድትሰጡ ብሎ አሸባሪውና ጨፍጫፊው መንግስት በሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ይህ የሀይል ሚዛንን ለይቶ የማያውቅ፣ ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀትና የአማራ ፋኖ የሚታገልለትን አላማና ግብም ለወንበራቸውና ለእኩይ አላማቸው ፈፅሞ ጠር እንደሆነባቸው ያሳዬ መግለጫ ነው። በመሆኑም ከአማራ ፋኖ ጋር የገጠማችሁ እና ከሞት የተረፋችሁ በየቦታው በግዴታ ታፍሳችሁ የመጣችሁ እና በሙስናና በማጭበርበር የተዘፈቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት በድህነት የጣራ ወለል በታች ሁናችሁ እንደ ስራ እድል ቆጥራችሁና አላማው አገርን መጠበቅ ነው በሚል ቅንነት ተቀላቅላችሁ የነበርና በሴራ ውጊያ ከሞት የተረፋችሁ ውስን ሃይሎች የጨፍጫፊው መንግስት ስልጣን አስጠባቂ ከመሆን ወጥታችሁ ብሄር ሳይመርጥ ምርኮኞችን ለሚንከባከበው ፍኖ እጃችሁን እንድትሰጡ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

2ተኛ, የሀገሪቱ ከፍተኛው የጦር ባለስልጣን የሰጠው መግለጫ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ያሳየበት ንግግር ከበቂ በላይ ነው። ድሮኑን ከበቂ በላይ እንደተጠቀመበት በበቂ ሁኔታ ባልተጠበቁ የከሰሩ የመዘለባበድ ንግግሮቹ አስቀምጧል። አሸባሪው ሀይል ፋኖን በድሮን ደበደበ የሚል መግለጫም አላወጣንም ትጥቅ ይዞ እየተዋጋ ያለውን የአማራ ፋኖ አንገት ማስደፋት የሚችል አቅምም ስነልቦናም የላቸውም። ይህ ደግሞ ከክላሽኮቭ እስከ ዙ-23 ያስታጠቀን የአሸባሪው ስልጣን አስጠባቂ መሆኑ በቂ ምስክር ነው። የአማራ ፋኖ በድሮንና ከባድ መሳሪያ ህፃናትን፣ አዛውንቶቾን፣ የእምነት ተቋማት አባቶችንና ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን በአጠቃላይ ንፁሃንን እየደበደበ መሆኑን ብናሳውቅም አማራ እንደ ህዝብ መጥፋት አለበት የሚለውን እቅድ በአደባባይ ምስክርነት የሰጠበትን እና አቅም ያነሰው ይህ ቡድን ንፁሃንን መጨፍጨፉን እንደሚቀጥል በአደባባይ ምስክርነት ሰጥቷል።

ሚዲያ የሌለው ህዝብ ሰሚም ሆነ አልቃሽ እንደሌለው ጠንቅቀን እናውቃለን። በመሆኑም የትግሉ አጋር የሆናችሁ የሀገራችን ህዝቦች እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሙሉ በህዝባችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት እንዲያውቅልን ስንል እያሳሰብን ይህን አለም አቀፍ የጦር ወንጀል በማሳወቅ ከጎናች እንድትሆኑ ስል እውነትን ለሚደፍር ሚዲያዎች፣ የሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሁሉም ማህበረሰብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

3ተኛ, የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በተመለከተ የለት ጉርሳቸውን በዚህ እንቅስቃሴ ላይ ላደረጉነ ሰብል ለመሰብሰብ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑና መንገድ ላይ የቆሙ መኪኖችን ግምት ውስጥ በማስገባት ላልተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ የተፈቀደ መሆኑን እየገለጽን የጨፍጫፊው ሃይል ሸቀጣሸቀጦች ስንዴን ጨምሮ መድሃኒቶች ወደ አማራ *ክልል እንዳይገባ ትእዛዞች መሰጣታቸው ይታወቃል። ስለዚህ በተቃራኒው ከክሰል እስከ ማርና ቅቤ፣ ከስንዴ እስከ ጤፍ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየገዙ ሲሆን አላማውም ጦርነትን በማራዘም የአማራን ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፍና በኢኮኖሚው እንዲዳከም በመዋቅራዊ መንገድ ታቅዶበት እየሰሩ መሆናቸውን በባለፈው መግለጫችን ማስታወቃችን አይዘነጋም።

ስለሆነም የጨፍጫፊው ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሀይል እጁን መስጠት የሚፈልግ እጁን እስኪሰጥ እና የተራረፈው በአማራ ፋኖ እስኪደመሰስ ድረስ ምንም አይነት ጭነት ከአማራ *ክልል ወደሌላ ቦታዎች ጭኖ መውጣት የማይቻል መሆኑን እያሳሰብን ይህን አድርጎ በተገኜ ግለሰብም ሆነ ተቋም በየትኛውም የጎጃም አካባቢ በሚገኙ ለዕዙ አደረጃጀቶች ውርስ ተደርጎ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል የተተኳሽ መግዣና ለትግሉ እንዲውል ትእዛዝ የተላለፈ መሆኑን በአፅኖት እንገልፃለን።

ከእውነት ጋር የቆመ ህዝብ ያሸንፋል!!
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!
ድል ለፋኖ!!

የጎጃም ዕዝ ፋኖ!
ታህሳስ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

18/12/2023
18/12/2023

በአማራ ክልል የምትንቀሳቀሱ ሹፌሮች ግን ይህን ጦርነት በዋናነት የጀመርነው ለማን መብት እና ነፃነት ይመስላችኋል ??? እንዳውም አብራቹህን መታገል ነበረባችሁ በተለይ ከደጀን ቢቸና ሞጣ ያላቹህ የህዝብ እና የጭነት ባለንብረቶችም ጭምር ።

30/05/2023

“በደብረ ኤሊያስ ጥንታዊ ገዳም ላይ የሚካሄደው የከባድ መሣሪያ ጥቃት ባስቸኳይ ይቁም!” አሕግ

ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!

የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ የኦሮሚያ ልዩሃይል አባላትን የመከላከያ ዩኒፎርም አልብሶ በማሰማራት በአማራ ክልል በደብረ ኤሊያስ ወረዳ አርሶ አደሮች ላይ እና በደብረ ኤልያስ ገዳማትና በመነኮሳት ላይ የሚፈጽመውን ፍጅት መላው ኢትዮጵያዊና የዓለም አቀፋ ሕብረተሰብ እንዲያወግዘው በጥብቅ እናሳስባለን።

ከስድስት መቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው የደብረ ኤሊያስ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በውስጡ ካሉ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ መንፈሳዊ ንዋየ ቅዱሳን እና ታሪካዊ ቅርሶች ለከፍተኛ ጥፉት ተጋልጠዋል። በአብይ አህመድ የሚታዘዘው ጨፍጫፊው ሠራዊት በዚህ ትልቅ የሀይማኖት እና የባህል ቦታ ላይ እያደረሰው ያለው የቦምብ ጥቃት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለም ማህበረሰብንም ሊያሳስብ ይገባል።

አብይ አህመድ የመከላከያ ልብስ አልብሶ ያሰማራው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከአለም አቀፍ ድንጋጌዎች እና ከወታደራዊ ስነምግባር ውጭ በንጹሃን አርሶ አደሮች እና በገዳማዊ መነኮሳት ላይ እንደ ዙ-23 ሞርታር ዲሻቃ ያሉ ከባድ መትረየሶችን በመተኮሱ በገዳሙ እና በአካባቢው ከ7 ያላነሱ ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን ለማጣት በቅተዋል። በደብረ ኤልያስ ይህን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ስለመፈጸሙ አገዛዙ እስካሁን ይፋዊ ማብራሪያ ባይሰጥም ከአካባቢው ከደረሰን ተጨባጭ ማስረጃ ተረድተናል።

ፉሽስታዊው የብልጽግ/ኦሮሙማ አገዛዝ በደብረ ኤሊያስ የስላሴ ገዳም አብያተ ክርስቲያናት፣ መነኮሳት፣ ተማሪዎች እና በደብረ ኤልያስ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ የጦር ወንጀል እንዳይፈጽም የዓለም ማህበረሰብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን።

በተጨማሪም የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ ሆን ብሎ በታሪካዊው የደብረ ኤልያስ ገዳማት እና በወረዳው ኗሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን በከባድ መሳሪያ የታጀበ ከፍተኛ ጥቃት በማውገዝ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተቃውሟችሁን እንድታሰሙ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) ጥሪውን ያቀርብላችኋል።

ዘገባው የ Mereja TV ነው።

27/04/2023

ግርማ ደሞ ማን ነው ?

12/04/2023

ትመር እንደሆነ ምረር እንደ ቅል፣
አልመር ብሎ ነው ዱባ እሚቀቀል።

06/04/2023

መከላከያ ግን የአማራን ህዝብ ለመውጋት ሞራል ከዬት አገኘ? የትግሬ ሴቶች በውሃና በእንጀራ ውስጥ መርዝ እየጨመሩ የገደሉት መከላከያ፣የአማራ ህዝብ እርጎ እየዘረገፈ፣ሰንጋ እያረደ እንዳላበላው፣ወያኔ አፈር እያስጋጠች ስታባርረው እንጀራ እየፈተፈተ እንዳላጎረሰው፣ጀግናው ፋኖና ልዩ ሃይል ከወያኔ አፈና እንዳልታደጉት…ዛሬ "ልዩ ሃይል ፈሪ!" እያለ ይሳለቅብን!?

"ነጩ ዶክተር ካላከመኝ"ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከአንድ ነጭ ተማሪያቸው ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ህመምተኞችን እየጎበኙ ነው። አንድ በአንድ ህመምተኞቹን እያዳረሱ፣ አንድ ...
20/03/2023

"ነጩ ዶክተር ካላከመኝ"

ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከአንድ ነጭ ተማሪያቸው ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ህመምተኞችን እየጎበኙ ነው። አንድ በአንድ ህመምተኞቹን እያዳረሱ፣ አንድ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት ጋር ደረሱ።

አዛውንቱ ነጭ–አምላኩ ነበሩና " ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" ብለው ድርቅ አሉ። እንግዲህ ወጣቱ ነጭ ፕሮፌሰር አስራትን ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ በስራ ልምድ ፣ በግል ተሰጥኦ ይወዳደራል ተብሎ አይታሰብም ። ከእርሳቸው ሰፊ ልምድ፣ ስር ሆኖ ሊማር በፈቃደኝነት የመጣ ነው።

አዛውንቱ ግን በሀሳባቸው ፀኑ። ስለዚህ ፕሮፌሰር አሥራት መላ ዘየዱ። እርሳቸው ለነጩ ተማሪ እንደ ረዳት ሆነው አዛውንቱን ሊመረምሩ ( ትህትና የአዋቂዎች ንብረት ናት)

በዚህ መሰረት ነጩ ተማሪ የፕሮፌሰር አሥራትን መመሪያ እየተከተለ አዛውንቱን መረመረ። በሽታቸውም ታወቀ። ፕሮፌሰር አሥራት የፈውስ መድሃኒቱን ማዘዣው ላይ ፅፈው ለነጩ ተማሪ አስረከቡ። ተማሪው ደግሞ ለአዛውንቱ። አዛውንቱ ፣ መልአክ የመሰለ ነጭ ሰው ስላከማቸው በጣም እየተደሰቱ፣ ገና መድሃኒቱን ሳይወስዱ የመሻል ስሜት እየተሰማቸው ፣ ሆስፒታሉን ለቀው ወጡ።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ፕሮፌሰር አሥራት ያንን አዛውንት ከመንገድ ያገኟቸዋል። የተለመደ ጥያቄያቸውንም ይሰነዝራሉ ፦ " እንዴት ኖት አሁን? ጨርሶ ተሻሎት?"

አዛውንቱ ሲመልሱ ፦ "አሁን ፍፁም ጤነኛ ነኝ። ጭራሽ አሞኝ አያውቅም። ያ የተባረከ ፈረንጅ በሙሉ ነው የፈወሰኝ"

ፕሮፌሰር አሥራት በአዛውንቱ የጤንነት ሁኔታ ተደስተው፣ አሁን እውነቱን ብነግራቸው ችግር የለውም ብለው አሰቡና፦

"ይኸውሎት አባቴ፣ ፈረንጁ የኔ ተማሪ ነበር፣ ከኔ ሊማር ነው የመጣው። ያከምዎት፣ ህመምዎን ያገኘሎት ፣ መድሐኒት ያዘዘሎት እሱ አይደለም፣ እኔ ነኝ" ቢሉ፣

አዛውንቱ መልሰው፦ "ለዚያ ነዋ ህመሙ እየደጋገመ የሚነሳብኝ!"

ታሪካዊቷ የብቸና ከተማ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የፍቅር፣የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት  የብቸና ከተማ ከፊል ገፅታ
22/02/2023

ታሪካዊቷ የብቸና ከተማ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የፍቅር፣የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የብቸና ከተማ ከፊል ገፅታ

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ Computer engineering መምህር የነበረው መምህር ታደለ ባሳዝን የእርዳታ ጥሪ!------------------ፌስቡክን ለበጎ ነገር እንጠቀመው !!ይኸ ወጣ...
29/11/2022

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ Computer engineering መምህር የነበረው መምህር ታደለ ባሳዝን
የእርዳታ ጥሪ!
------------------

ፌስቡክን ለበጎ ነገር እንጠቀመው !!
ይኸ ወጣት #ታደለ ባሳዝን አየለ ይባላል። ቢቸና አካባቢ የልሜት ቀበሌ ተወላጅ ነው።

ትምህርት-
የመጀመሪያ ዲግሪ ከሃረምያ ዩንቨርስቲ በElectrical Engineering፣ ሁለተኛ ድግሪ ደግኖ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በComputer Engenering ተመርቋል።

የስራ ሕይወት
በደብር ብረሃን univrsity ለ 3 አመት ያህል አስተምሮል። ይኸው ወንድማችን አሁን ላይ በጤና መታወክ ምክንያት ውሎ አዳሩ በሚያሳዝን ሁኔታ 5ኪሎ አካባቢ ጎዳና ላይ ሆኗል።

የጥሪ መልእክት፣
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ወገኖች፣ ይህን መርጃ በማጋራት ወንድማችንን ወደ ቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን። በጎነት ለራስ ነው የማናችንም ነገ አይታወቅምና በጎ እንሁን እንረዳዳ።

ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው!

መርጃ ምንጭ Amare kassie via Getaye Dagnaw

ብቸና ታላቅ አባት አጣለች። የመጀመሪው የቶታል ማደያ በከተማችን የከፈቱት ሀጅ ጋሹ ለከተማችን ዕድገት ፈር ቀዳጅ ከሆኑት ነጋዴዎች አንዱ ናቸው። ለከተማችን ሰን ራይዝ የተባለ ፔኒሲዬን ፎቅ ...
07/11/2022

ብቸና ታላቅ አባት አጣለች። የመጀመሪው የቶታል ማደያ በከተማችን የከፈቱት ሀጅ ጋሹ ለከተማችን ዕድገት ፈር ቀዳጅ ከሆኑት ነጋዴዎች አንዱ ናቸው። ለከተማችን ሰን ራይዝ የተባለ ፔኒሲዬን ፎቅ ገንብተዋል። ከነጋዴዎች ጋር በመተባበር ብቸና ከተማ ላይ ትልቅ ዕቁብ በመክፈት በማስተዋወቅ ለነጋዴው ማህበረሰብ መለወጥ ታላቅ አስተዋፆ ያደረጉ ታላቅ አባታችን ናቸው። ነፍሳቸውን ለጀነት ፈጣሪ ያውልልን ይማር እንላለን ። አበበ ፀጋዬ ብቸና bichena ketema communication Bichenatube.com ቢቸና meme

20/10/2022

ማንኛውም ተሽከርካሪ መኪና ከጎጃም ወደ አ/አ ላልተወሰነቀን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጠን ስራ የማቆም አድማ ስለሚደረግ ያልሰማችሁ ካላችሁ እንዳትሄዱ ::ከህይወታችን የሚበልጥ የለም ደህንነታችን እስካልተረጋገጠ ድረስ የትኛውም ተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ አንዳይገባ ::

6 ጋዜጠኞች እና 5 የኃይማኖት አባቶች "የህወሃት የሽብር ቡድንን በመደገፍና የሃይማኖት ተቋማትን ለወታደራዊ ማሰልጠኛ የጦር መሳሪያ ዝውውር ማስፈጸሚያ በማድረግ በሚል ወንጀል"  ተከሰው ፍር...
29/09/2022

6 ጋዜጠኞች እና 5 የኃይማኖት አባቶች "የህወሃት የሽብር ቡድንን በመደገፍና የሃይማኖት ተቋማትን ለወታደራዊ ማሰልጠኛ የጦር መሳሪያ ዝውውር ማስፈጸሚያ በማድረግ በሚል ወንጀል" ተከሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የአማራ ሚዲያ ማእከል
መስከረም 18 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ቄስ ግርማይ ሀላነህ ተፈራ፣ቄስ ቀለብ ደረሰ መኮንን፣ ቄስ ዳዊት ምህረት ዘለቄ፣ ቄስ ኃይለሚካኤል ማለደ፣ ቄስ ዋጋ ተስፋ ጫኔ፣ ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ አብነህ (የየኔታ ቲዩብ ጋዜጠኛ)፣ ጋዜጠኛ አንዷለም እንዳሻው አለሙ (የኛ ቲቪ ጋዜጠኛ)፣ ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው( የእዮሀ ሚዲያ ጋዜጠኛ)፣ ጋዜጠኛ አንዷለም ስማቸው የሸዋ ( የአሀዱ ሬዲዮ የስፖርት ጋዜጠኛ) እና ዘመኑ አታላይ ያለው (የእኛቲቪ ካሜራ ማን ) በሽብር ፈጠራ ወንጀል ተከሰው ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የክሱ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡-

‹የህወሃት የሽብር ቡድን በመደገፍና የሃይማኖት ተቋማትን ለወታደራዊ ማሰልጠኛ የጦር መሳሪያ ዝውውር ማስፈጸሚያ በማድረግ በሃይማኖት ሽፋን በርካታ የወንጀል ድርጊት ሲሰሩበት የነበረውን ገዳም መንግስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ እያለ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሆነ ብለው መንግስት በሃይማኖት ላይ ጣልቃ ገብቷል የሀይማኖት አባቶች አስሯል በማለት በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር እና አቅጣጫ በማስቀየር በህዝብ እና በመንግስት ላይ አለመተማመንና ቅስቀሳ በማድረግ በህግ የተያዘን ጉዳይ መንግስት በራሱ መግለጽ ሲገባው በተሳሳተ መንገድ ለማስተላለፍ መንግስት ግለሰቦችን ያለአግባብ ያሰረ ለማስመሰል ከሌሎች ከወንጀሉ ተባባሪዎች ጋር በመመሳጠር መንግስት ለጊዜው ባለበት እንዲቆይ እና ምርመራ እንዲጣራ ባደረገበት ወቅት ወደቦታው በመሄድ የቅስቀሳ ስራዎችን በመስራት ላይ እያሉ በተደረገ ክትትል› በሚል ዝርዝር የክስ ውንጀላ በሽብር ፈጠራ ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እያጣራ ይገኛል ይላል የክስ ዝርዝሩ።

ከነህሴ 11 ጀምረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅኑ እና ታታሪው ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገር ታሰረ!መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ታታሪው ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገር ኦሮሚያ ክልል ለስራ በሄደበት ዛሬ ከስዓት መታሰሩ ተሰም...
29/09/2022

ቅኑ እና ታታሪው ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገር ታሰረ!

መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ታታሪው ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገር ኦሮሚያ ክልል ለስራ በሄደበት ዛሬ ከስዓት መታሰሩ ተሰምቷል።

በኦሮምያ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት እንደሚገኝም ተረጋግጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመነ ወያኔ ጋዜጠኞች ይታፈኑ ነበር። ብልፅግና ደግሞ ወያኔን ያስንቃል። በብልፅግና ዘመን ደግሞ ሙያውንም ሆነ ሙያተኞችን በማሰር በዓለም አዲስ ጥቁር ታሪክ እያስመዘገበ ይገኛል።

ሰው በገዛ ሀገሩ እንደፈለገ እንዳይቀሳቀስ እያደረጉ ይገኛል::

ፍትህ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች !!

ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw

Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24

ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

አሰሩት 😡ቅኑ ና ታታሪ ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገርበኦሮሚያ ክልል ለስራ በሄደበት ስአት በኦሮምያ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ይገኛል::ያሳዝናል ሰው በገዛ ሀገሩ እንደፈለገ እንዳይቀሳቀስ እያደረጉ...
29/09/2022

አሰሩት 😡

ቅኑ ና ታታሪ ጋዜጠኛ ዋልተንጉስ ዘሸገር

በኦሮሚያ ክልል ለስራ በሄደበት ስአት
በኦሮምያ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ይገኛል::

ያሳዝናል

ሰው በገዛ ሀገሩ እንደፈለገ እንዳይቀሳቀስ እያደረጉ ይገኛል::

ዋልቴን ፍቱት
ዋልቴን ፍቱት
ዋልቴን ፍቱት

ቢቸና ከተማ አስተዳደርየስራ ቋንቋ ለውጥ ወይስ ምንድን ነው ?bichena  ketema  ቢቸና meme Bichenatube.com Bichena Ketema Communcation
20/09/2022

ቢቸና ከተማ አስተዳደር
የስራ ቋንቋ ለውጥ ወይስ ምንድን ነው ?
bichena ketema ቢቸና meme Bichenatube.com Bichena Ketema Communcation

🔳 እነሆ ጀግና ... ሥብሃት ገብረእግዚአብሔር 🙄     ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖▣ ተጋሩው [ትግሬው] ስብሃት ገብረእግዚአብሔር በሐምሌ 1972 ዓ.ም የካቲት መፅሔት ላይ [3ኛ አመት ቁጥር 7 ...
17/09/2022

🔳 እነሆ ጀግና ... ሥብሃት ገብረእግዚአብሔር 🙄
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

▣ ተጋሩው [ትግሬው] ስብሃት ገብረእግዚአብሔር በሐምሌ 1972 ዓ.ም የካቲት መፅሔት ላይ [3ኛ አመት ቁጥር 7 - ሀምሌ 1972] ያወጣውን መጣጥፍ “እነሆ ጀግና” ብሎ በሰየመው መፅሐፍ ላይ አስፍሮታል!

▣ ጋሽ ስብሃት አማራ አይደለም! ግን ጀግናን ለማድነቅ አጥንት መቁጠር አላስፈለገውም! “እነሆ ጀግና” በሚለው ስብስቡ 10ኛ ዕትም ላይ ከገፅ 1 - 39 ስለ ጀግናው አፄ ቴዎድሮስ፤ ከገፅ 41 - 57 ስለ ጀግናው በላይ ዘለቀ፤ ከገፅ 59-86 ስለ ታከለ ታገለ ... ወዘተ ፅፏል!

▣ ጋሽ ስብሃት በገፅ 41 ላይ ስለበላይ ዘለቀ ሲፅፍ ታሪኩን የነገሩትን ሰዎችም በመዘርዘር ነው የሚጀምረው! ለዚህ ፅሑፍ በመረጃ ምንጭነት የተጠቀመው የበላይ ዘለቀ ዘመዶችንና የቅርብ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ ነው! እነሱም፦

◉ ፊታውራሪ - የበላይ ዘለቀ የአጎቱ ልጅ!
◉ ፊታውራሪ - የበላይ ዘለቀ አጎት!
◉ ፊታውራሪ - የበላይ ዋና ፀሐፊ!

▣ እንግዲህ ፅሁፉን ከላይ በስም ከተገለፁት አዛውንት ቃለ መጠይቅ ወስዶ ጋሽ ስብሃት በፅሁፍ ቋንቋ ደወረው፤ ሸምኖም በህትመት ሚዲያው ሰጠን!🙂

▣ እና ከእነዚህ አዛውንት የተሻለ የትኛው ሰው መረጃ ኖሮት ነው የሚኳትነው?!🙂 ለገለልተኝነቱስ ከማንም ጋሽ ስብሃት አይሻሉም??☹️ ያው አትድከሙ! ለማለት ያህል እንጅ እውነታውስ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” አይነት ነገር መሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም!!🙄

▣ ሞላጫነትም - ቀላዋጭነትም ሁለቱም ከንቱ ናቸው!☹️ እንዴው ለምሳሌ ብቻ ይሄን መፅሐፍ አነሳሁ እንጅ እንደ “የኢትዮጵያ ደም መላሽ” አይነት ከ1985 - 2010 ድረስ ተጠንተው የተፃፉ መፅሐፉትም አሉ!🙄

▣ ይልቁንስ መፅሐፏን ሸምቱና በውስጧ ከሰበሰበቻቸው ጀግኖች በጥቂቱም ቢሆን ተቋደሱ! በመፅሃፉ ከቨር ላይ የሚታዩት ከባድ ሚዛኖች በውስጥ ገፆች ላይ ተሰይመዋል - ጠይቋቸው!🙂

የሸዋን ባህል፣ ቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥና በዓለምአቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ አምባሳደር ሁና የተመረጠችው አርቲስት ብሌን ማሞ
10/09/2022

የሸዋን ባህል፣ ቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥና በዓለምአቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ አምባሳደር ሁና የተመረጠችው አርቲስት ብሌን ማሞ

ይድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ይድረስ ለአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፤*****አብን እሁድ ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ምልዓተ ...
06/09/2022

ይድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤
ይድረስ ለአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፤
*****
አብን እሁድ ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል። እውነታው ይኼ ሆኖ እያለ ባልተካሄደ ስብሰባ፣ ውይይት ባልተደረገበት አጀንዳና ተገቢ ፖለቲካዊ ምክክር ተደርጎ ባልተላለፈ ውሳኔ፤ ስብሰባ እንደተጠራ፣ አጀንዳ ተዘርግቶ ውይይት እንደተካሄደና ውሳኔዎች እንደተላለፉ ተደርጎ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የስነስርዓት ጥያቄዎች የሚቀርቡበበት፣ ድርጅታዊ አሰራርንና መርኅን የጣሰ እንዲሁም ከዴሞክራሲ ልምምድ ያፈነገጠ የነውር ሥራ ነው። የስንስርዓታዊ ጉዳዮች መሟላት ስብሰባው ከመካሄዱና በስብሰባው ከሚወሰነው ውሳኔ እኩል ወይንም የበለጠ አስፈላጊ በመሆኑ ባልተሟላ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባዎች አይካሄዱም።

ለውጥ ፈር በሆኑ ጥቂት የአብን ከፍተኛ አመራሮች እየተደረገ ያለው ሁኔታ ግን ለንቅናቄው አባላትና አመራሮች ብቻ ሳይሆንም ለስርዓት ግንባታም ደንታ የሌላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሰኞ ነሐሴ 30/2014 የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርገን ውሳኔዎችን አሳልፈናል ይበሉ እንጂ የሰኞ ስብሰባ ስለመኖሩ የትኛው የድርጅቱ አካል፣ መቼና በምን መንገድ ጥሪ አስተላለፈ? ጥሪውስ ለሁሉም የማዕከላዊ አባላት እኩል ተላልፎላቸው ነበር ወይ? የድጋሚ ስብሰባ ቀኑ ሲወሰን ከስብሰባ ቦታው ርቀው የሚገኙ አባላትን የመጓጓዣ ቀናት ታሳቢ ያደረገ ነበረ ወይ? ወዘተረፈ ቀላል ግን መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል ተጨባጭ ነገር ማቅረብ አይቻላቸውም።

ባለፈው እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ማኅተም ስለያዙ ብቻ የንቅናቄው የሥራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ያልመከረባቸውንና ያላፀደቃቸውን የኦዲት ሪፖርት እና የሪፎርም ጉባዔ (የደንብ ማሻሻያና የአመራር አመላለመል እንዲሁም አወቃቀርን ጨምሮ) ውይይት ተካሂዶባቸው የጸደቁ በማስመሰል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የደብዳቤ ልውውጦች ማድረጋቸውን ስለታዘብን፤ጉዳዩ የወንጀል ተጠያቂነትን ጭምር የሚያስከትል ጉዳይ ያለው ስለሆነ ይህንንም የሚመለከታቸው ተቋማት በተለይም የንቅናቄው በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች፣ አመራሮችና አባላት በልዩ ልዩ አማራጮች አሳውቀናል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔው የተወሰነበት ቃለጉባዔ ይምጣልኝ የሚል ደብዳቤ ስለፃፈ፤ የቦርዱን ጥያቄ አሰነባብቶና ቀባብቶ ምላሽ ለመስጠት በሚል ከስነስርዓት ውጭ ስብሰባ ተደርጎ፥ ውሳኔ እንደተላለፈ መግለጫ ማውጣት፤ በተደጋጋሚ ጊዜ የተፈፀመ ነውር እና የምርጫ ቦርድን በተሳሳተ ደብዳቤ የተሳሳተ ውሳኔና ግንዛቤ ላይ እንዲደርስ የሚደረግ የወንጀል ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር ነው። መሰል ስህተቶችን ነቅሰን ጉዳዩ ለሚመለከተው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተናል። ቦርዱ ተገቢውን ማጣራትና ምርመራ አድርጎ ተገቢ ውሳኔ ላይ እንደሚደርስም እምነት አለን። በተለይ ከኦዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ከንቅናቄው አመራሮች ጭምር ይመርመርልን ጥያቄ የቀረበበት በመሆኑ እና የምርጫ ቦርድም መሰል ጥርጣሬዎችና ጥያቄዎች ሲቀርቡለት የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን ልዩ ኦዲት እንዲሰራለት የመጠየቅ መብት ስላለው፤ ይኽንኑ እንዲያደርግ ደግመን ማስታወስ እንፈልጋለን።

መላው የአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ንቅናቄያችን የሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴ ለግላዊ ጥቅማቸው ሲሉ ከገዥው ፓርቲ ጋር በተጣበቁ ጥቂት ግለሰቦች መታገቱን በውል በመረዳት፤ ፓርቲው የተሟላ ሪፎርም አድርጎ መላው ሕዝባችን የሰጠውን አደራ እንዲወጣ በተገቢው ሁኔታ ብርቱ ትግል ታደርጉ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

የኛ አገር መሪዎች ግን ጤነኞች ናቸው ወይ? ጠላት ህፃናትን እንደ ማዕበል አሰልፎ ወሎን እያጥለቀለቀ ሳርቅጠሉን ሲያወድም፣ የአመራሮቻችን ምላሽ ያስቃልም ያበግናልም።"ህፃናትን ለጦርነት ላከ"...
28/08/2022

የኛ አገር መሪዎች ግን ጤነኞች ናቸው ወይ? ጠላት ህፃናትን እንደ ማዕበል አሰልፎ ወሎን እያጥለቀለቀ ሳርቅጠሉን ሲያወድም፣ የአመራሮቻችን ምላሽ ያስቃልም ያበግናልም።

"ህፃናትን ለጦርነት ላከ" እየተባለ ፕሮፓጋንዳ አይሉት ጫጫታ ይስተጋባል።መጀመሪያ እንደአመጣጡ መልስ፣እንደአመጣጡ ደምስስ።ነፃ ሁን።
ቤትህን እያቃጠለ፣እየዘረፈ፣ እየደፈረ አንተ ልጅ ነው ገለመሌ ነው ውስጥ ምን አስገባህ?
የጠላት ትንሽና ትልቅ የለውም እኩል ነው።

ለካንስ ፈጣሪ ብቻ አይደለም ህዝብ በሞላ ይወድሀል፣ ለካንስ ከሆድአደር ውጭ አንተን የሚጠላ የለም። አንተንና ጓዶችህን ያሳደደው መንጋ ሲፈረጥጥና ጥገኝነት ሲጠይቅ ያሳየህ አምላክ ምንኛ ይወድ...
28/08/2022

ለካንስ ፈጣሪ ብቻ አይደለም ህዝብ በሞላ ይወድሀል፣ ለካንስ ከሆድአደር ውጭ አንተን የሚጠላ የለም። አንተንና ጓዶችህን ያሳደደው መንጋ ሲፈረጥጥና ጥገኝነት ሲጠይቅ ያሳየህ አምላክ ምንኛ ይወድሀል!! ወዲህ ደግሞ የደምበጫ ሚሊሻወች ፋኖ ዘመነ ካሴንና ወንድሞቹን ካሰደዳችሁበት ካላመጣችሁ አንዘምትም፣ አንድ ሆቴል ላይ እንዳንጠቀም አድርጋችሁ አንድነታችንን ያጠፋችሁት እናንተው ዝመቱ ማለታቸውን ነገሩኝ።
ገና ብዙ ታያለህ መመኪያችን።

Address


132

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bichenatube.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

Amhara

የአማራ ህዝብ ትግልና ፖለቲካ በማንም ጎጠኛ፣ ህዝብን በሚከፋፍሉ፣ ሆዳም፣ ባንዳ፣ ካድሬ መመራት የለበትም።