Mamush Ayana jasho

  • Home
  • Mamush Ayana jasho

Mamush Ayana jasho Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mamush Ayana jasho, Digital creator, .

14/12/2023

በሸገር ከተማ መኖሪያ ቤቶችን ሰብረው ገብተዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ በሙስና ወንጀል በምርመራ የታሸጉ መኖሪያ ቤቶችን ሰብረው ገብተዋል የተባሉ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ነው።

የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ምድብ ዐቃቤ ሕግ ዘጠኝ መዝገቦችን በማደራጀት ገላሞ ዋቤ ሀጂን ጨምሮ አጠቃላይ 13 ግለሰቦች ላይ ክስ መስርቷል።

በክስ ዝርዝሩ ላይ በሸገር ከተማ በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ሀጫሉ መንደር እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ከተሰሩ መኖሪያ ቤቶች መካከል በሙስና ወንጀል ድርጊት ለምርመራ የታሸጉ 13 ቤቶችን ተከሳሾቹ ሰብረው መግባታቸው ተጠቅሶ የወንጀል ህግ አንቀጽ 439 ሀ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በዚህ መልኩ በዘጠኝ መዝገቦች በዐቃቤ ሕግ ተደራጅተው የቀረቡ ክሶችን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በክሱ ላይ የግራ ቀኝ ክርክር ለማድረግ ለታኅሣስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከዚሁ መኖሪያ ቤትን ከሶማሌ ክልል ተፈናቃይ ነን በማለት በማጭበርበር በተፈናቃዮች ስም ያለአግባብ በመውሰድ የድጎማ ገንዘብ በመቀበል ጭምር በተፈጸመ የሙስና ድርጊት ከ8 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉና በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ 50 ግለሰቦች ላይ የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ 3 የሙስና ወንጀል ክሶችን አቅርቦ በክልሉ ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሂደት ላይ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል።

በታሪክ አዱኛ



ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ ተወላጆች በቦሮ ሽናሻ መስቀል በዓል (በጋሪ ዎሮ በዓል) አከባበር ዘላቂነት እና ቀጣይነት ዙሪያ ውይይት አደረጉ ፤🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹(ታህሳስ 04/04/2016ዓ...
14/12/2023

ቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ ተወላጆች በቦሮ ሽናሻ መስቀል በዓል (በጋሪ ዎሮ በዓል) አከባበር ዘላቂነት እና ቀጣይነት ዙሪያ ውይይት አደረጉ ፤
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

(ታህሳስ 04/04/2016ዓ/ም) በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ ተወላጆች በቦሮ ሽናሻ መስቀል በዓል (በጋሪ-ዎሮ በዓል) አከባበር በተመለከተ በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ አደራሽ ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጋሪ ዎሮ በዓል አብይ ኮሜቴ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መልካሙ ጃራ ሲሆኑ የውይይት መድረኩ የተከፈተው በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃ ሰነ_ስርዓት በመከወን ነው ።

የውይይቱ ዋና አላማ የቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው የጋሪ ዎሮ በዓል አከባበር በተመለከተ እሴቱን አስጠብቆ በዘላቂነት ለትውልድ ማሰተላለፍ እንዴት እንደሚቻል የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተደረገ ውይይት ነው ።

በዚህም መሰረት የ2016ዓ/ም የጋሪ ዎሮ በዓል አከባበር በተመለከተ አጭር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በረዳት ፕሮፌሰር ሰሜነ በድሞ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጋሪ ዎሮ በዓል በዘላቂነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሽጋገር በሚያስችል መልኩ እሴቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል የብሔሩ አንጋፋ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች ርብርብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በውይይቱ ለመግለጽ ተችሏል።

በቀረበው ሪፖርት መነሻ በማድረግ ሀሳብ እና አስታየት ከቤቱ እንዲሰጥበት እና የጋራ ግንዛቤ ፈጥሮ ለመሄድ ያመች ዘንድ የውይይት መድረኩን የመሩት የመተከል ዞን ምትክል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ግዛቱ ባልዳ ሆራ እና የመተከል ዞን ገ/ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የጋሪ ዎሮ በዓል አብይ ኮሜቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መልካሙ ጃራ ናቸው።

በመጨረሻም የቦሮ ሽናሻ መስቀል በዓል (የጋሪ ዎሮ በዓል) አከባበር በተመለከተ እሴቱን አስጠብቆ እንዲቆይና ለትውልድ ለማሰተላለፍ ይመች ዘንድ በቋሚነት ይህን በዓል የሚያስተባብሩ አብይ ኮሜቴዎች በቋሚነት የተመረጡ ሲሆን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ የተቋጨው በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃ ፕሮግራም ነው ።

የተፃፈውን በማንበብ ብቻ እዉቀት አይሆንም  ሊነበብ የሚችል ፎቶግራፍ መልእክታቸው ለማወቅ ለእዉቀት ይጠቅማል ፎቶግራፍን ማንበብ እንልመድ!!
10/12/2023

የተፃፈውን በማንበብ ብቻ እዉቀት አይሆንም ሊነበብ የሚችል ፎቶግራፍ መልእክታቸው ለማወቅ ለእዉቀት ይጠቅማል

ፎቶግራፍን ማንበብ እንልመድ!!

10/12/2023
  🇪🇹🇪🇹❤️🇪🇹🇪🇹እንሰራለን ለህዝባችን እንወያያለን ስለሰላማችን እንመካከራለን ስለልማታችን መደመር መንገዳችን  መዳረሻው ብልፅግናችን ነው እናመሰግናለን መሪዎቻችን 💖💖ስለተገኛችሁ በጥሪያች...
30/11/2023


🇪🇹🇪🇹❤️🇪🇹🇪🇹

እንሰራለን ለህዝባችን
እንወያያለን ስለሰላማችን
እንመካከራለን ስለልማታችን
መደመር መንገዳችን
መዳረሻው ብልፅግናችን ነው

እናመሰግናለን መሪዎቻችን 💖💖
ስለተገኛችሁ በጥሪያችን 💖💖

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ቀን በዓል በክልል ደረጃ በግልገል በለስ ከተማ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።(ህዳር፣1...
29/11/2023

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በክልል ደረጃ በግልገል በለስ ከተማ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።

(ህዳር፣19/2016 ዓ.ም)18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በክልል ደረጃ በግልገል በለስ ከተማ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት በፓናል ውይይት እየተከበረ ይገኛል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳና ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ዓለምነሽ ይባስ፣የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ጌታሁን አብዲሳ እና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

"ብዝሃነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት"

26/11/2023
26/11/2023

እሾህ እየዘሩ እህል አይታለምም

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mamush Ayana jasho posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share