የንስር ዐይን

  • Home
  • የንስር ዐይን

የንስር ዐይን ▹ ፍትሕን እና ሐቅን ፍለጋ!
▹ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ማድረግ! የኢትዮጵያ ትንሳዔን ማብሰር።

🤔  !➹ እኔ በዚህ 74 እድሜዬ ...ለዚህ ወጣት ትዉልድ  !
23/10/2024

🤔 !

➹ እኔ በዚህ 74 እድሜዬ ...ለዚህ ወጣት ትዉልድ !

 !!!??? ፤ ማንም ከእውነት ያመለጠ ቢመስለዉም የገዛ ህሊናዉ ዘወትር ሌት ከቀን ሲያሳድደዉ ይኖራል። ስለሆነም የኣሪ ዞን እና የጂንካ ከተማ መምህራንን አክብሯቸዉ። #ስለ.... ሕገ መንግ...
15/02/2024

!!!???

፤ ማንም ከእውነት ያመለጠ ቢመስለዉም የገዛ ህሊናዉ ዘወትር ሌት ከቀን ሲያሳድደዉ ይኖራል። ስለሆነም የኣሪ ዞን እና የጂንካ ከተማ መምህራንን አክብሯቸዉ።

#ስለ.... ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች እና ሴኩላሪዝሙ ምን ይላል፦

መምህሩ እና የትምህርት ተቋማቶች ከሃይማኖት፣ ከባህላዊ እና ማድረግ በቀጥታ የሴኩላሪዝም መርሆን ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

#መምህሩ ለትምህርት እና ለሃገር እድገት ወሳኝ የሆነው የሰው ሃብት ልማት የሚካሄድበት ተቋም በመሆኑ የአንዱ ወይም የሌላው ፖለቲካዊ ርዕዮት ወይም ሃይማኖት የሚስፋፋበት እንዲሁም በልማት ሽፋን ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የማስፋፋትና ውድድር የሚካሄድበት ሊሆን አይገባም፡፡

የሁሉም ዜጎች ከፖለቲካዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ ተጽዕኖ ነጻ እና ገለልተኛ በመሆን የሁሉም ሃይማኖትና እምነት ተከታዮች ዕውቀት የሚገበዩበት ማዕከል በመሆኑ ይህንን አገልገሎት ዕኩል ለማቅረብ ከፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ሃይማኖታዊ ተፅዕኖ
ነጻ መሆን አለባቸዉ፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አከባበር አንቀጽ 18 የተቀመጡት ወሳኝ እና ካለምንም ማስተጓጐል መከበር ያለባቸው መብቶች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ሴኩላሪዝምን በመንግሥትና በሕዝብ የትምህርት ተቋማት በጽናት የማረጋገጥ ጉዳይ ሕገ መንግስታችንን የማክበርና የማስከበር ጉዳይ ነው፡፡ በተያያዥነትም የዜጎቻችንን የተሟላ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የማረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ለሕግ የበላይነት የመገዛትና ለሁሉም ብዝሃነቶች ነፃነትና እኩልነት የመቆም ግዴታን የመወጣት ጉዳይም ነው፡፡ ከመዋዕለ-ህፃናት እስከ ከፍተኛ ደረጃ
የሚገኙት የመንግስትና የግል የትምህርት የተቋማት ዜጎችን ከመጥፎ ስነ-ምግባር በመጠበቅ በገንቢ
የስነ-ዜጋ ዕሴት የሚታነፁባቸው ገለልተኛና ተጠባቂ ተቋማት መሆን ይገባቸዋል፡፡

ሴኩላሪዝምን በትምህርት ተቋማት የማረጋገጥ ጉዳይ ደግሞ በተለየ መንገድ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ የትምህርት ተቋማት ብቁና በስብዕናው ሙሉ የሆነ አገር ተረካቢ ዜጋን የማፍራት ኃላፊነት የወሰዱ ተቋማት ናቸው፡፡ እነዚሁ ተቋማት የአገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብሎም የብልጽግና ጉዟችን ስኬት የሚወስኑ ተቋማት ናቸው፡፡ በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የታነፁ ዜጎች የሚወጡባቸው ተቋማት ናቸው፡፡ በጥናትና ምርምር፤ በፈጠራና ስርፀት የተካኑ ተቋማት ናቸው፡፡

የመማር ማስተማር ተግባራቸው ከየትኛውም ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ ተፅዕኖ እና ቁጥጥር በፀዳ መንገድ መፈጸም ያለበትና ሁሉም የትምህርት
አደረጃጀትና #የመምህሩ ማህበረሰብ ሙሉ ጊዜው ለዚሁ ዓላማ ብቻ እንዲያውሉ ይጠበቃሉ፡፡ ይላል።

የትምህርት ተቋማት የተገለፁትን አገራዊ ግቦች ሊያሳኩ የሚችሉት የተቀበልዋቸው ተማሪዎች፣
መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን የሚመራዉ የብልጽግና መንግስት አስፈጻሚዎች በተሟላ መንገድ ማክበር እና ማስከበር ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

በመሆኑም መምህራኑ እና የትምህርት ተቋማቶቻችን በስርዓቱ አስፈጻሚዎች ከመልካም አስተዳደር ንፍገት እና የፀረ-ሴኩላር ዝንባሌዎችንና ተግባራትን የሚስፋፉባቸው ከሆኑ የትምህርት ጥራት መጓደል ብቻ ሳይሆን የአገርና የሕዝብን ጥቅም የማያስጠብቁ ተቋማት መሆናቸው የማይቀር ነው፡፡

የመምህሩን ሞራል ማጉደፉና ማሸማቀቁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአገርና የሕዝብን ህልውና የመጠበቅና ስራ የመፍጠር ችሎታ የሌላቸው፣ የአገር ተረካቢነት ሚናን በአግባቡ ሊወጡ የማይችሉ ዜጐች የሚበራከቱበትን ዕድል የሚያሰፉ ተቋማት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ልህቀት፣ የጥናት የምርምርና የፈጠራ ስራዎች ልህቀትና
የማኅበራዊ አገልግሎቶች ልህቀት ማዕከላት እንዲሆኑ የሚጠበቅና መንግሥት እና ሕዝብ ከፍተኛ ገንዘብና የሰው ሃብት እያፈሰሰ የሚገኝ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ጤናማ ያልሆኑና የሴኩላሪዝምን መርህ የሚቃረኑ ገፊ እና አሸማቃቂ አስተዳደራዊ ዝንባሌዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጂንካ እና በአዲሱ ዞን አስተዳደር ዉስጥ ጥሰቶች እየታዩና እየተበራከቱ የመጡበት ሁኔታ ታይቷል፡፡

መምህሩ እና ትምህርት በልማት ሽፋን ከፖለቲካዊ ርዕዮት ማስፈጸሚያ እና ተፅዕኖ ነጻ መሆን እንደሚገባቸዉ ብሎም መምህሩና የትምህርት ተቋማት በማንኛውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶችና ከባህላዊ ተፅዕኖዎች ነጻ መሆን አለባቸዉ የሚል ድንጋጌ በአንቀፅ 90(2) ሰፍሯል፡፡

ስለሆነም መምህራኑን በልማት ሽፋን በዚህ የኑሮ ጡዘት ዉስጥ ሁሉን ችሎ ያለ አንዳች አመታዊ ተጨማሪ ጥቅማጥቅም ብዙ ጥያቄዎቹን ተቋቁሞ የሚኖርበትን ቀፎዉን አትንኩበት...?!

50% እጂጉን ይከብዳቸዋል እና ያመኑበትን 20% ብቻ ተፈጻሚ በማድረግ ጤናማ የሆነ አስተዳደራዊ እና አብሮ በመከባበር የመኖር ባህልን ምርጫችሁ አድርጉ።

...!
.....¿

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! የነፍጠኛው ልጅ, ሞጣኝ ቀራኒዮ
01/11/2023

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! የነፍጠኛው ልጅ, ሞጣኝ ቀራኒዮ

 ... #ሱማሊያ... ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር ወደብ ለማግኘት ያቀረበችላትን የድርድር ጥያቄ ውድቅ ማድረጓን መረዳቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ቀይ ባሕር ላይ የ...
18/10/2023

...

#ሱማሊያ... ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር ወደብ ለማግኘት ያቀረበችላትን የድርድር ጥያቄ ውድቅ ማድረጓን መረዳቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ቀይ ባሕር ላይ የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ እንደኾነ ባለፈው ሳምንት ተናግረው ነበር።

ኤርትራ፣ የኢትዮጵያን ስም ባትጠቅስም በቅርቡ በባሕር በር ዙሪያ የተነሳው ትርክት "ከመጠን ያለፈ" እና "ግራ የሚያጋባ ነው" በማለት ሰኞ'ለት ማጣጣሏ ይታወሳል።

; Somalia Rebuffs Ethiopia’s Bid to Gain Direct Access to Red Sea Port

Simon Marks, Bloomberg News
Google.com October 17, 2023

(Bloomberg) -- Somalia rejected an appeal from Ethiopia to enter into negotiations with a view to granting it access to a Red Sea port.

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed last week warned that his country’s lack of access to a harbor is a potential source of future conflict and called for efforts to address the issue in order to safeguard regional stability. Ethiopia lost its direct access to the sea in 1993 when Eritrea gained independence after a three-decade war.

While Somalia is “highly committed” to enhancing peace, security, trade and integration, it isn’t interested in providing access to a strategic asset such as a port, State Minister of Foreign Affairs Ali Omar said in a text message. “Somalia’s sovereignty and territorial integrity — land, sea and air — as enshrined in our constitution, is sacrosanct and not open for discussion.”

In a televised lecture on Oct. 13, Abiy said Ethiopia had “natural rights” to directly access the Red Sea, and if it was denied this “there will be no fairness and justice and if there is no fairness and justice, it’s a matter of time, we will fight.” He suggested his government could grant shares in its Grand Ethiopian Renaissance Dam in return for similar stakes in ports in neighboring countries

Read More: Ethiopia Says Lack of Port Access Can Fuel Future Conflict

Eritrea described the prime minister’s comments as “excessive” and said “the affair has perplexed all concerned observers.”

Alexis Mohamed, senior adviser to Djiboutian President Ismail Omar Guelleh, said Abiy’s position was a longstanding one albeit now delivered in a much more forward manner.

“Djibouti will wait for Ethiopia to propose a peaceful means to access the Red Sea, while recognising that Djibouti has always been open to have good relations with neighboring countries and notably Ethiopia,” he said by phone. He noted Djibouti’s openness to already provide access to Ethiopia’s navy.

 ....       🤔
15/10/2023

....
🤔

💀   🚨የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ በሽታ 300 ሰዎች ሞተዋል ሲል ትናንት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በሐምሌ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ብዛት 13 ሺህ 118 እንደነበር የጠቀ...
08/10/2023

💀 🚨

የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ በሽታ 300 ሰዎች ሞተዋል ሲል ትናንት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በሐምሌ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ብዛት 13 ሺህ 118 እንደነበር የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ባኹኑ ወቅት ግን ቁጥሩ ወደ 24 ሺህ 197 ማሸቀቡን ድርጅቱ ገልጧል። በሽታውን በቁጥጥር ስር ማዋል በተቻለባቸው አንዳንድ ወረዳዎች እንደገና እያገረሸ መኾኑንም ድርጅቱ ጠቅሷል። በአገሪቱ የኮሌራ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች የተከሰተው ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ ሲኾን፣ እስካኹን በ10 ክልሎች በ113 ወረዳዎች ተሠራጭቷል።

 #
08/09/2023

#

 !!!!
27/08/2023

!!!!

 #ኢትዮጵያ
18/08/2023

#ኢትዮጵያ

🕸  #አምሓራ!!!!
16/08/2023

🕸 #አምሓራ!!!!

"የአምሓራ ዋና ጠላቱ ሆዳም አምሓራ ነው"((ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከተናገሩት))📌 ሆዳም አምሓራ ደሞ ከዚህ በኋላ ሆዳም ሆኖ መኖር አይችልም !!
09/08/2023

"የአምሓራ ዋና ጠላቱ ሆዳም አምሓራ ነው"

((ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከተናገሩት))

📌 ሆዳም አምሓራ ደሞ ከዚህ በኋላ ሆዳም ሆኖ መኖር አይችልም !!

"የአምሓራ ተራሮች፣ የኦነጋዊያን መቀበሪያ ይሆናሉ...!!!"📌  !!!!
06/08/2023

"የአምሓራ ተራሮች፣ የኦነጋዊያን መቀበሪያ ይሆናሉ...!!!"

📌 !!!!

 #የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ!?የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል...
04/08/2023

#የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ!?

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፥ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡

በመሆኑም የታጠቁ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለው ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

" በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ " ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።

በዚህ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

#በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆኑ:-

በአማራ ክልል የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆነዋል።

#ዝርዝሩ በምስሉ ላይ ቀርቧል!

አንጋፋው የ " አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ " በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ!!የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚ...
04/08/2023

አንጋፋው የ " አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ " በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ!!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

 !!በፋብሪካ የተቀነባበሩና የታሸጉ፣ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ወደ ሃገራችን በብዛት በመግባት ላይ ይገኛሉ ፣ እነዚህን ምግቦችና መጠጦች አዘውትሮ በመውሰድ  የሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች እ...
04/08/2023

!!

በፋብሪካ የተቀነባበሩና የታሸጉ፣ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ወደ ሃገራችን በብዛት በመግባት ላይ ይገኛሉ ፣ እነዚህን ምግቦችና መጠጦች አዘውትሮ በመውሰድ የሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች እየጨመሩ ነው።

በፋብሪካ የተቀነባበሩ ከፍተኛ ጨው፣ ስኳር፣ የሚረጋ ዘይትና የቅባት ይዘት ያላቸው ሃይል ሰጪ መጠጦችንና ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

* ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት፣
* ካንሰር፣
* ልብ ህመም፣
* ስትሮክ፣
* ዓይነት 2 የስኳር ህመም ያጋልጣሉ።

የእነዚህ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችና መጠጦች ሰፊ አቅርቦት ወይም በገበያ ላይ እንደ ልብ መገኘትና ልቅ ማስታወቂያ በብዛት እንዲሸመቱ አድርጓቸዋል።

#ስለዚህ ለጤንነትዎ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

 ፣ 1.9 ሚሊዮን ብር ለበጎ አድራጎት ተቋማት ለገሰ::አርቲስት አብርሃም ወልዴ፣ ለሰርጉ ወጪ በሚል በጎፈንድሚ እና በተለያየ መንገድ ከሰበሰበው ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ውስጥ 1....
04/08/2023

፣ 1.9 ሚሊዮን ብር ለበጎ አድራጎት ተቋማት ለገሰ::

አርቲስት አብርሃም ወልዴ፣ ለሰርጉ ወጪ በሚል በጎፈንድሚ እና በተለያየ መንገድ ከሰበሰበው ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ውስጥ 1.9 ሚሊዮን ብር በደቡብ ጉራጌ፣ በሰሜን ሸዋ ፍቼ ከተማ፣ በሰቆጣና በደብረብርሃን ለሚገኙ አራት የበጎ አድራጎት ተቋማት ለገሰ።

ገንዘቡ የተበረከተው ለጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለፍቅር የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ማህበር፣ በደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮችና በሰቆጣ 3 ወረዳዎች ለሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ነው፡፡

አርቲስት አብርሃም ወልዴና ባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል፤ ለጋበር በጎ አድራጎት 250 ሺ ብር፣ ለፍቅር የተቀናጀ የበጎ አድራጎት ማህበር 250 ሺ ብር፣ ለደብረብርሃን ተፈናቃዮች 400 ሺ ብር እንዲሁም በአበርገሌ በሳግብጂና በሰቆጣ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር፤ በድምሩ 1.9 ማሊዮን ብር ለግሰዋል፡፡

ሙሽሮቹ ከዚህ ቀደም ከዚሁ ለሰርግ ስጦታ ከወዳጅ ዘመድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ 300 ሺ ብር ለሜቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል መለገሳቸው ይታወቃል።

አርቲስት አብርሃምና ባለቤቱ ማክዳ ለሰርጋቸው ከሰበሰቡት 2 ሚሊዮን 266 ሺህ 205 ብር ከ56 ሳንቲም ውስጥ በጎፈንድሚ የተሰበሰበው 31 ሺ 935 .20 ዶላር ሲሆን፤ ቀሪው ገንዘብ በብር የተሰበሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡

ዛሬ ቀትር 7 ሰዓት ተኩል ላይ የገንዘብ ድጋፉን በደሳለኝ ሆቴል በተካሄደ ሥነስርዓት ላይ የተረከቡት የየተቋማቱ ተወካዮች፣ አርቲስት አብርሃምንና ባለቤቱን ወ/ሮ ማክዳን አመስግነው፣ ጥንዶቹ ትዳራቸው ፍሬያማ እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

 !:በህይወት የሂደት ዑደት ዉስጥ የቅርብ ጓደኞችህን መለየት፣ በዝግታ፣ ቀስ በቀስ ከጓደኞችህ መነጠል የእድገትህ ምልክቶች ዉስጥ አንዱ መገለጫ ነው።አብሮህ ማደግ የሚፈልግ ጓደኛ ብቻውን ጥለ...
02/08/2023

!

:

በህይወት የሂደት ዑደት ዉስጥ የቅርብ ጓደኞችህን መለየት፣ በዝግታ፣ ቀስ በቀስ ከጓደኞችህ መነጠል የእድገትህ ምልክቶች ዉስጥ አንዱ መገለጫ ነው።

አብሮህ ማደግ የሚፈልግ ጓደኛ ብቻውን ጥለኸው ብትሔድ እንኳን ይከተልሃል፤ ብትነጠለውም ፈልጎ ያገኝሃል።

ጓደኝነት እድገትን አይጠላም፤ ጓደኝነት ለብቻ ከመበልፀግ ይልቅ አብሮ መበልፀግን፣ አብሮ ማደግን አብሮ መቀየርን ይመርጣል።

በእርግጥም የልብ ወዳጅ፣ የልብ ጓደኛ ካለህ በፍፁም የእድገትህ ማነቆ ሳይሆን፣ እራስህን በቀየርክ ቁጥር እየገፋህ የሚሔድ ሳይሆን ለእድገትህ ድጋፍ፣ ለለውጥህም ዋነኛ አበርታች የሚሆንህ ነው።

ጓደኝነት ዋጋውን ላልተረዳ የአንድ ሰሞን መቀራረብ ብቻ ሊመስል ይችላል፤ ለሳቅ ለጫወታና ለመዝናናት ብቻ የሚጠቅም ይመስለዋል። ዋጋው ግን እስከ ህይወት ዘመን የልብ ወዳጅነት ሊቀጥል የሚችል ነው።

አገኘህ ብሎ የሚሸሽህ፣ አደክ ብሎ የሚያገልህ፣ ተለወጥክ ብሎ በጀረባ የሚያማህ ጓደኛ መጀመሪያውኑም ጓደኛህ አልነበረም።

አንዳንዴ በጓደኝነት ገፅታ የጠላትን ገፀባህሪ የሚጫወቱ አስመሳይና እራስ ወዳድ ሰዎች ይኖራሉ። እራሱን ወዶ የወዳጁን ውድቀት የሚመኝ የለምና ለዚህ የልብ ወዳጅህና ጓደኛህ መልካሙን አፀፋ መልስለት።



በመደጋገፍ ውስጥ የላቀው ስኬት የመጣል፤ ረጅሙን ርቀት መጓዝ ይቻላል።

ልብ ለልብ በመነጋገር ከባዱን አቀበትም መውጣት፣ አዳጋቹን ቁልቁለትም መውረድ ይቻላል።

ለየትኛውም ጓደኛህ ንፋስ ሲበዛ ተራግፈው እንደሚወድቁ የዛፍ ቅጠሎች አትሁንበት፤ ከቻልክ ቅርንጫፎቹን ሁንለት፣ ካልሆነም በንፋሱ ማየል ከማይነጠሉት ለምለም እንደ አንዱ ቅጠሎቹ ሁንለት።

#አዎ! ህይወት ብዙ ሰዎችን ታስተዋውቅሃለች። ከነዚህም ውስጥ የልብ ጓደኛ መተኪያ የሌለው ስጦታው ነው።

የልብ ጓደኛ ማንነትህን ለመቀበል፣ ምርጫህን ለማክበር፣ በአዎንታዊ ለውጥህ፣ በእድገትህ ለመደሰት በፍፁም አይቸገርም።

አደክ ብሎ ከጀርባ ሊያማህ አይችልም፤ ምርጫህን ስላከበርክ ከተቀሩት ጓደኞቹ ጋር ስምህን አያጠፋም።

ስታድግና ስትሻሻል የሚለዩህ ጓደኞች ቀድሞውኑ ጓደኞችህ ስለመሆናቸው እርግጠኛ መሆን አትችልም።

እውነተኛ ጓደኝነት ለብቻ ከማደግ በተሻለ ህብረትን፣ አንድነትንና መደጋገፍን ይመርጣልና አንተም ለጓደኝነት ምርጫ ይህን መመዘኛ ተጠቀም።

ጓደኝነትህን አክብር፣ ትልቅ ቦታም ስጠው፣ በግዳጅ ሳይሆን በፍላጎትና በመፈቃቃድ ላይ እንዲመሰረት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ ባህሪ እንዲኖረው አድርግ።

፤ እርሱም ይረዳህ ዘንድ መንገዱን ክፈትለት፤ ወዳጅነታችሁን የልብ፣ እድገታችሁንም የጋራ አድርጉት።

!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የንስር ዐይን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share