Meseret Abebe

  • Home
  • Meseret Abebe

Meseret Abebe Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Meseret Abebe, Digital creator, .

07/06/2024
03/06/2024
19/05/2024
18/05/2024
03/04/2024
03/04/2024
03/04/2024

ከተማችን ላይ የድህነት ደሴት ሊኖረን አይገባም፤ ተቀናጅተን ሰርተን በጋራ እንለወጣለን!

ልማት የአካባቢ ማደግ ፣ መዋብና መለወጥ ብቻ አይደለም ፤ ልማት የህዝባችን የኑሮ ደረጃ መሻሻል እንዲሁም የተፈጥሮ ሚዛንን አስጠብቆ የመጓዝ ጕዳይ ጭምር ነው።

የዘመሙ ቤቶች ካልታደሱ ፣ ለሰው መተላለፊያ ጭምር የሌላቸው ሰፈሮች መንገድ ካልተሰራላቸው ፣ መብራት ፣ ውሀ እና መሰል መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ ማድረግ እና እንዳይቆራረጡ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ካልተዘረጉ ፣ ተገቢውን የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት መስጠት ካልተቻለ ፣ እሳትና መሰል ድንገተኛ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከልና ፈጥኖ መቆጣጠር ካልተቻለ ልማት ትርጉሙን ያጣል።

የቤታችንን የሰፈራችንን እና የአካባቢያችንን ገፅታ ካልቀየርን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አበባ ሳይሆን ወደ ጉስቁልና ነው የምትመለሰው።

ፓርቲያችን ብልፅግና አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ አቅጣጫ አስቀምጦ ህዝባችንን እያስተባበረ መረባረብ ከጀመረ ሰነባብቷል።

ልማታችን የሚረጋገጠው በህዝባችን ርብርብ ነው ፤ የሚሰራው ልማት ለዚህ ትውልድ ብቻም ሳይሆን ለመጪው ትውልድ ጭምር ነው።

ያለፈው ትውልድ የደም እና የአጥንት መስዋዕትነት ከፍሎ ሉዓላዊነቷ የተከበረ አገር አውርሶናል። ይሁን እንጅ የድህነት አዙሪት ሲንከባለል ከእኛ ትውልድ ላይ ደርሷል። ላብአችንን ጠብ አድርገን ሰርተን ድህነትን ድል በማድረግ ለልጆቻችን ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ማውረስ ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው።

የሁሉም ኢትዮጵያውያን ቤት፣ የአፍሪካውያን ድምቀት ፣ የዓለም የዲፕሎምቲክ ስበት የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ በየጊዜው የተለያዩ የልማት ስራዎችን ብታስተናግድም ጉዞዋ በሚጠበቅባት ልክ ሳይሆን አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል።

ፓርቲያችን ብልፅግና አዲስ አበባ እሷን በማይመጥናት ገፅታ ውስጥ የኖረችባቸውን ዘመናት በሚያካክስ መላኩ የተቀናጀ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

መሀል ላይ የሚገኙ የከተማችን አካባቢዎች የቅርብ ሩቅ እየሆኑ የልማት ዕድሎች ሲያልፏቸው ቆይተዋል።

ከፊል ልማት የለም። ሁሉንም የከተማችንን አካባቢ ካላለማን ፣ ሁሉንም የከተማዋ ነዋሪ አቅም በፈቀደ መጠን ፍትሀዊ የልማቱ ተቋዳሽ ካላደረግን አይደለም የምንፈልገው ብልፅግና ላይ ልንደርስ ይቅርና ከድህነት አረንቋ ውስጥ መውጣት አንችልም ።

ከተማችን ላይ የድህነት ደሴት ሊኖረን አይገባም በሚል የልማት ነጥብጣቦችን የመገጣጠም ስራአችንን መሀል ከተማ ላይ ጀምረናል፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን ተደጋግፈን ተባብረን በመስራት በጋራ እንለወጣለን።

ያለፈውን ትውልድ ሲንከባለል የመጣ ዕዳ ጭምር በመሆኑ የምንከፍለው በስራዎቻችን ላይ ለነዋሪዎቻችን ምቾት የማይሰጡ ችግሮች ቢያጋጥሙ እንኳን ለአጭር ጊዜ ብቻ መሆኑን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በቅርቡ አረጋግጠዋል። የከተማ አስተዳደራችንም 7 / 24 የመስራት ባህልን በማዳበር በቅርቡ በጀመረው የኮሪደር ልማት ተግባር በትራንስፖርቱ የተጉላሉትን ለመካስ ፣ ተገቢው ካሳ እና ምትክ ቤት እየተሰጣቸው ለልማቱ የተነሱ ዜጎችም በውሳኔአቸው ዳግም የሚደሰቱበትን የልማት ውጥን እውን ለማድረግ በማይዋዥቅ ጠንካራ አቋም ላይ ይገኛል።

ህዝባችንም ከፍተኛ የሆነ የመለወጥና የመልማት ፍላጎት አለው :: ለመጪው ትውልድ እንደ ስሟ ያበበች አዲስ አበባንና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማውረስ እንደከተማም እንደ አገርም በድህነት ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፍተናል። ህዝባችንን ይዘን በአርበኝነት ድል እንደምንወጣውም እርግጠኞች ነን።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meseret Abebe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share