ፍቅር ያሸንፋል fikr yashenfal

  • Home
  • ፍቅር ያሸንፋል fikr yashenfal

ፍቅር  ያሸንፋል  fikr yashenfal ልዩ ልዬ አስተማሪ ታሪኮችና አስገራሚ ጥቅሶች
ወቅታዉ ጉዳይ

22/12/2023

Check out shag(ሻግ)@101's video.

19/11/2023
28/10/2023

" አለሽ ድብቅ ውበት "
ነይ እስኪ አለሜ ፍቅር አያረጅም
አይኖቼም ቢደክሙ ላንቺ ግን አላንስም
አው የኔ ፍቅር ትዝ ይልሻል ያኔ
እንዳሁኑ ሳይሆን አቅፌሽ ከጎኔ
ዞማ የመሠለው ዘንፋላው ፀጉርሽ
ንፋስ ሲበትነው ደግሞ ሲያስቸግርሽ
ወደኋላ ላስር ሳነሳው ከፊትሽ
ስንሄድ በዛች መንገድ ሰውሁሉ ሲያይሽ
ጥቅጥቅ ባለው ጫካ በሚያምር ተፈጥሮ
ሰዓት ሳይዛነፍ ጠብቀን ቀጠሮ
በሚያምረው ሽንሽንሽ እኔም በቦላሌ
አብረን ያሳለፍነው ወጣት ሆነን ጮሌ
ከታፋሽ ተኝቼ ቁልቁል እያየሽኝ
የሚያምሩት አይኖችሽ ፍቅር ሲመግቡኝ
ስሜን አቆላምጠሽ ደጋግመሽ ስጠሪኝ
በእንጆሪ ከንፈርሽ ከንፈሬን ስትስሚኝ
ነብሴን ከሰማያት ሀሴትን ልትሰጫት
ገነት አስገብተሽ ደግሞ ስትመልሻት
ፍክት ያለው ገፅሽ እንደ ፀሐይ በርቶ
ፈንጨት ያለው ጥርስሽ ከጨረቃ ፈክቶ
ዛሬም ይታየኛል ያንቺ ወጣትነት
ልክ እንደትላንቱ አለሽ ድብቅ ውበት።
♥♥♥
ትዝታ
እንዳይመስል
ለኔ ግን
ህልሜ ነሽ♥♥♥

Copy from sami king fb
09/10/2023

Copy from sami king fb

በጣም አስተማሪና አስገራሚ ታሪክ ከወደድከው ለጓደኛ  ሼር  ማድረግ እንዳትረሳ .. 😂 ..😥አንድ ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ወደሚጠብቀው አዳራሽ አመራና በጭብጨባ ከተቀበሉት በኃላ ወደ መድረክ እን...
02/10/2023

በጣም አስተማሪና አስገራሚ ታሪክ ከወደድከው ለጓደኛ ሼር ማድረግ እንዳትረሳ .. 😂

..😥

አንድ ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ወደሚጠብቀው አዳራሽ አመራና በጭብጨባ ከተቀበሉት በኃላ ወደ መድረክ እንዲወጣ ተጋበዘ
በመጀመርያ የሚያምር ቀልድ ነገራቸው አዳራሹ በፉጨት ተቀወጠ በሳቅ ደመቀ።

ከዚያም ያንኑ ቀልድ ደገመላቸው ግማሾቹ ሳቁ ግማሾቹ ደግሞ ግራ ተጋቡ🙄

#ለሶስተኛ ጊዜ አሁንም ቀልዱን ደገመው።በዚህ ሰዓት ግን አንድም የሚስቅ ሰው አልነበረም። ያኔ ቻርሊ በጣም ደስ አለው ከዛም ኢሄን ተናገረ.....

(በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ እንደማትስቁ ሁላ ስለምን በአንድ ነገር ደጋግማችሁ ታለቅሳላችሁ?????????

"ህይወትኮ እጅግ ውብ ናት" ዛሬ በህይወት ካላችሁ ነጋችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ። በትናንት ውስጥ ስላጣችሁት ነገር አታስቡ ዛሬን ብቻ በህይወት በመኖራችሁ ፈጣሪን አመስግኑ።

ዛሬ ውስጥ ጠንካራ ከሆናችሁ ነጋችሁ የተዋበ ይሆናል። ነጋችሁ የሚጥም ይሆናል አሁንም አሁንም አሁንም በሂወት መኖራችሁን ብቻ እያያችሁ "አልሃምዱሊላህ " ፈጣሪን አመስግኑ!

ከተሰጣን ስጦታዎች ሁሉ ህይወታችን ይበልጣልና፤ በህይወት ካላችሁ ደሞ በነጋችሁ ላይ ለውጥ መፍጠር ትችላላችሁ።

መልካም ምሽት 🥰

24/04/2023

💖 ነፍስ ስታፈቅር💕
ክፍል 12
‹‹ታዲያ ለምን አታገቢውም….. አታፈቅሪውም ወይ?›› ብለው ሲጠይቋት ሁል ጊዜ መልሷ በውዝግብ የተሞላ ነው፡፡ታፈቅረዋለች ..ግን ደግሞ እሱን የምታፈቅርበት መጠን ላይ እርግጠኝነት አይሰማትም፡፡ፍቅሩ አዕምሮ ዋ ላይ ብቻ ያለ ይመስላታል፡፡‹‹ልቤ ላይ አይሰማኝም፡፡››ትላለች
ቆንጆነቱ፤ብስልና የተሞረድ ንግግሩ፡አለባበሱና ዝነጣው፡በሰዎች ያለው ተወዳጅነት እና ተቀባይነት፤ለሰው የሚያሳየው እንክብካቤና ቸርነት ወዘተ ለፍፅምነት የቀረበ ሰው መስሎ እዲሰማት ያደርጋል፡፡ግን እነዚህ ሁሉ ምዘናዎች ከጭንቅላቷ ተርፈው ወደልቧ ሲንጠባጠቡ አይሰማትም..ለዛ ነው ደፍራ ልታገባው እስከአሁን ያልወሰነችው…እና ታዲያ መጨረሻው ምንድነው ? ከተባለ…እሷም የናፈቀት መጨረሻውን ለማወቅ ነው ፡፡
///.ከደቂቃዎች ቡኃላ ስልክ እያወራና በድንጋጤ እየተርበተበተ ሆቴሉን ለቆ ወደእሷ መጣ፡፡
‹‹መጣው….››
‹‹መጣው አልኩሽ እኮ…ዶክተሩ ጋር ደውይለት››
‹‹..መድሀኒቱን ስጪው››
‹‹ደግሞ ከስሩ እንዳትነቀሳቀሺ..››ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹ምነው?››ግራ ገብቷት ጠየቀችው ሲፈን
‹‹አይ አባዬ ኮማ ውስጥ ገባ ብላ ሰራተኛዋ ደውላልኝ ነው፡፡››
‹‹ምን ሆኑ? አሞቸው ነበር?፡፡››
‹‹አዎ ሰሞኑን ጥሩ አልነበረም..ለማንኛውም አልሸኘውሽም ቸው…››
አብረን ካላደርን የሚለው ጭቀጭቅ ሙሉ በሙሉ ተረስቶ በሌላ ድንጋጤ ተተክቶ መገኘቱ የአጋጣሚው ነገር ሲፈን አስገረማት፡፡
ሄኖክ›› ደውልልሻለው፡፡›› ብሎ ጉንጬን ሳመና ወደመኪናው ሮጦ ገባ…እሷም ከጎኑ ወደቆመችው የራሷ መኪና ገባች፡፡
‹‹በዚህ ሁኔታ እንዴት ዝም ብዬ ወደቤቴ እሄዳለው..?››፡፡ተወዛ
ገበች፡፡ሳታስበው.. ከኃላው ተከተለችው፡፡ቢያንስ አይናቸውን አይቼ ብመለስ ይሻላል፡፡በሰላሙ ቀን የማታውቀውን ቤታቸውን በዚህ ሁኔታ ለዛውም በምሽት…ገረማት፡፡ብዙ ቀን ‹‹እቤቴ ልውሰድሽን ከአባትና ከእህቴ ጋር ላስተዋውቅሽ ብሏት ነበር..››እሷ ግን ከቤተሰቡ ጋር እንዲህ በቀላሉ ለመቀላቀል ልቧ ስላልፈቀደ የተለያየ ሰበብ እየፈጠረች ጥያቄውን ስትገፋ ነበር የኖረችው….ዛሬ ግን በዚህ ምሽት ይሄው….
ግን እንዳሰበችው እቤታቸው እንዲህ በቀላሉ የሚደረስብት ሆኖ አላገኘውትም እሱ ይነዳል እሷ ከኃላ ትከተለዋለች፡፡እንዳላያት እርግጠኘ ነች ፡፡ቢያያት ኖሮ መኪናውን አቁሞ የሆነ ነገር ይላት ነበር ፡፡ላፍቶ ሲደረሱ አራት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ይገርማል በአየር ላይም ቢሆን ፍቅር ፍቅር መጫወት ከጀመሩ አንድ አመት አልፎቸዋል፡፡አንድ ቀን ግን እቤትህ የት ሰፈር ነው ብላ ጠይቃው አታውቅም ፡፡ግቤው ደርሶ የመኪናውን ጡርንባ አስጩሆ ዘበኛው ሲከፍትለትና ወደውስጥ ሲገባ እሷም ተከትላው ገባች ..አቁሞ ከመኪናው ሲወርድ እሷም በተመሳሳይ ከመኪናዋ ስትወርድ ሲያያያት በጣም ነው የደነገጠው
‹‹እንዴት?››
‹‹እንዴት ምን?››
‹‹እንዴት መጣሽ..ማለቴ ለምን?›
‹‹የሰማውትን ሰምቼ መሄድ አላስቻለኝም፡፡››
እሷን በዚህ ሰዓትና በዚህ የጭንቅ ጊዜው ጊቢው ውስጥ ስላያት በጣም ተደስቷል…ቅድም እዛ ሆቴል ሲጨቃጨቁ ተስፋ የመቁረጥ እና ያለመፈለግ ስሜት ውስጡን እያኮማተረው ነበር..አሁን ግን የተስፋ ብርሀን በውስጡ ሲፈነጠቅ ተሰማው…‹‹.አዎ ግንኙነታችን የማስበውን ያህል ተስፋ አስቆራጭ አይደለም…እንዳለችው ጊዜ ብቻ ነው የሚፈልገው….ጊዜውን ደግሞ እሰጣታለው፡፡››ሲል ወሰነ
‹‹እሺ ነይ እንግባ..አለና ተያይዘን ወደውስጥ ገቡ፡፡››
///
አባትዬው መኝታቤት ተከታለን ገቡ
ቀይ… የፂማቸው ርዝመት ከእሷ ፀጉር የማይተናነስ…ግን ደግሞ ሙሉ ነጭ ፀጉራቸው ግማሽ መላጣ ግመሽ ጎፈሬ የሆኑ ጥልቅ እና ስምጥ የሆኑ ተቁለጭላ

💖ክፍል 11💕  ❤አዎ ሴት መንከባከብ እና በፍቅር ማቅለጥ ይችልበታል፡፡ግን ይህ ችሎታ ው በአሰበው መጠን ሲፈን ላይ እየሰራለት አይደለም፡፡በዚህ ምክንያት በችሎታው ላይ ያለው በራስ መተማመን...
09/04/2023

💖ክፍል 11💕

አዎ ሴት መንከባከብ እና በፍቅር ማቅለጥ ይችልበታል፡፡ግን ይህ ችሎታ ው በአሰበው መጠን ሲፈን ላይ እየሰራለት አይደለም፡፡በዚህ ምክንያት በችሎታው ላይ ያለው በራስ መተማመን እየተሸራረፈበት ነው፡፡
///
እንደተለመደው የመግቢያ ሰላምታ ተቀያይረው ተረጋግተው ተቀመጡ ፤እራት መጣ ተበላ፤ መጠጥ ጠጡ ፤የተወሰነ ደነሱ እና ወደተለመደው ጭቅጭቃቸው ገቡ፡፡
‹‹እሺ አይበቃንም?››አለችው፡፡
‹‹አረ ገና እኮ ሶስት ሰአት አልሆነም፡፡››
‹‹ቢሆንም እንሂድ››
ለምቦጩን ጣለ ..‹‹ከሚስቅ ይልቅ ሲያኮርፍ ወበቱ ይጎላል፡፡››ይህን ያለችው በውስጧ ነው፡፡
‹‹ባዶ ቤት ለመግባት ይሄ ሁሉ ሩጫ ምንድነው?፡፡››
‹‹ቦዶ ቤትም ቢሆን ያው እቤት አይደል መገባት አለበት..በዛ ላይ ነገ ስራ ገቢ ነኝ፡፡››አለችው፡፡
‹‹እስኪ ዛሬ ነፍሴን አስደስቻት..፡፡ዘና እንበል ፡ተጨማሪ እንጠጣ ፤እንደንስ፤ እዚሁ አልጋ እንያዝ….›ልክ እንደህፃን ልጅ ባለ ጉጉት በመለማመጥ ጠየቃት፡፡
‹‹አልጋ?››አደነጋገጧ ልክ የወንድ አካል አካሏን ነክቷት እንደማያውቅ ልጅአገረድ ነው የሆነችው፡፡
‹‹ምን ችግር አለው …?ከእኔ ጋር መተኛት ካልፈለግሽ ሁለት አልጋ እይዛለው፡፡››
እሱ አልገባውም እንጂ እሷ ወደቤቷ በፍጥነት መመለስ የፈለገችው እቤቷ ናፍቋት ወይም የሚጠብቃት ሰው ኖሮ ሳይሆን አልጋዋ ላይ ብቻዋን ተጋድማ ለማሰብ ነው፡፡ልቧ ላይ አርፎ እየተንገዋለለ ስለለው እብድ ለማሰላሰል….ምን አልባትም እንቅልፍ ከወሰዳት ትናንት እንዳለመችው አይነት ጣፋጭ ህልም ለማለም…በህልሟ ልታቅፈው..በህልሞ ልትስመው …በህልሞ……….
‹‹መልሺልኝ እንጂ ምነው ፈዘሽ?››
‹‹ኡፍ እንግዲህ ወደተለመደ ጭቅጭቅህ ልትገባ ነው፡፡ለዚህ እኮ ነው እንገናኘ ስትለኝ የማቅማማው፡፡ሁሉን ነገር ተነጋግረን ስምምነት ላይ የደረስን መሰሎኝ፡፡ካንተጋር መተኛት የወሰንኩ ቀን እኔ ራሴ ነግርሀለው፡፡››
‹‹መቼ…?››
‹‹ካንተ ጠንካራ ፍቅር እንደያዘኝ እርግጠኛ የሆንኩ ቀን ..አንተም ከአንጀትህ እንዳፈቀርክኝ ስሜቱ ልቤ ድረስ ዘልቆ የተሰማኝ ቀን፡፡››
‹‹የእኔን ፍቅር እንኳን ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ በእርግጠኝነት ታውቂዋለሽ ….የራስሽን ፍቅር ተጠራጠሪ››እውነቱን ነበር..እሱ በሚረዳው መጠን በመጨረሻ መጠን ወይንም እስከጥግ በሚባል ደረጃ ይወዳታል፡፡አዎ ማፍቀር ብቻ ሳይሆን እሺ ባለችው ቅፅበት ወዲያውኑ ሊያገባት በጉጉት እየጠበቀ ነው፡፡ለእሱ ሲፈንን ማግባት ማለት የፍቅር ጉዳይ ብቻ አይደለም፤የክብር ጉዳይም ጭምር ነው፡የኃይል ጉዳይም ጭምር ነው፡፡
እርግጥ ሄኖክ ስኬታማ የተባለ የቢዝነስ ሰው ነው፡፡የራሱ የሆነ የተደላደለ ሀብትና ንብረት አለው፡፡ከሲፈን ጋር ሲነፃፃር ግን ግማሹንም አይሆንም፡፡በዛ ላይ የሁለቱ ካማፓኒ የጋብቻውን ጥምረት ተከትሎ አንድ ላይ ሲዋሀድ ሁለቱም በተናጥል ካላቸው ልምድ ጋር ሲደመር ምን ያህል ግዙፍ ካምፓኒ እንደሚሆን ዘወትር እያሰበ ምራቁን የሚወጥበት የእየእለት ህልሙ ነው፡፡
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩ.. በራሴ እርግጠኛ አይደለውም፡፡››
‹‹መቼ ነው እርግጠኛ የምትሆኚው?፡፡››
‹‹እኔ አንጃ››
‹‹የእኔ ጊዜስ አያሳዝንሽም?፡፡››
‹‹እንግዲህ ጠብቀኝ ብዬህ አላውቅም..እራስህ ነህ እጠብቅሻለው ያልከኝ….ጥበቃው በቃኝ ባልክ ቀን የሚያበቃ ነው የሚሆነው፡፡››
‹‹ወይ ሄኖክ መጨረሻህ እንዲህ ይሁን…..?በይ ተነሽ እንሂድ ››ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ….ሂሳብ ዘግቶ እስኪመጣ ተነጥላው በመውጣት በረንዳ ላይ እየጠበቀችው ነበር፡፡
ሄኖክ በእሷ ቢበሳጭ አይፈረድበትም ፡፡ከተዋወቁ እና አብረው መሆን ከጀመሩ አመት አልፎቸዋል፡፡በዚህ የጊዜ ርዝመት ውስጥ ከከንፈር መሳሳም

ነፍስ ስታፈቅር😘🔥ክፍል 10ቁጭ አለና መፅሀፉን ገልጦ ማንበብ ጀመረ….መፅሀፉ ደግሞ‹ The HistoryOf Mankind >የሚል ርዕስ ያለው በእንግሊዘኛ የተጻፈ የውጭ መፅሀፍ ነው…‹‹አይ የ...
07/04/2023

ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 10

ቁጭ አለና መፅሀፉን ገልጦ ማንበብ ጀመረ….መፅሀፉ ደግሞ‹ The History
Of Mankind >የሚል ርዕስ ያለው በእንግሊዘኛ የተጻፈ የውጭ መፅሀፍ ነው…‹‹አይ የእብድ ነገር አሁን ሲያደርጉ አይቶ ነው አይደል..?››ስትል በውስጧ
አማችውና ወደ ምግብ ማብሰሏ ገባች፡፡
‹‹ስምህ ግን ማነው?››መልስ የለም
‹‹እናትህ ደህና ናቸው?››አንደቀረቀረ ነው፡፡
ተወችው….እሷም በዝምታ ምግቡን ለማብሰል 15 ደቂቃ ያህል ፈጀባት…እዛው
ፊትለፈቱ ቀላል ያለች ጠረጵዛ አስጠጋችና ምግቡን አቅርባ እሷም ምትቀመጥበትን ጠረጵዛ ከፊት ለፊቱ አስቀመጠችና‹‹ መታጠቢያ ቤት ሄደህ እጀህን ታጠብ›› ብትለው ምን እንደሚመልስላት እርግጠኛ ስላልሆነች እዛው በተቀመጠበት የእጅ ውሀ ይዛለት ጎንስ ብላ ‹‹ምግቡ ደርሶል እጅህን ታጠብና እንብላ››አለችው… እንዲህ አጎንብሳ አንድ እብድ ሳስታጥብ እቤተሰቦቾ ወይም የመስራቤቴ ሰራተኞቾ ቢያዮት ትንግርት ነበር የሚሆንባቸው፡፡ እሱ የእሷን ማጎንበስ ከቁብ ሳይቆጥረው‹‹አይ ይቅርብኝ አልታጠብም›አላትና
ያንን የከዋክብት ሽራፊ መሰሉ ሰማያዊ አይኖቹነ አንከባለለባት..በዛ ቅፅበት
ልቧን እንደመቅለጥ ስትል ታወቃት፡፡
‹‹ለምን?››እሷ በሚለማመጥ ድምፅ
‹‹መፅሀፍ ለማንብብ እጄን ለምን እታጠባለው?›
‹‹ለማንበብ አይደለም ምግቡ አይታይህም ..መክስ እንብላና ከዛ ታነባለህ››
‹‹ወይ!! ረበሺኝ…ደህና ሁኚ ..መፅሀፍን ወስጄዋለው›› አለና ከመቀመጫውን
ተነስቶ ኪችኑን ለቆ.. ሳሎኑን ለቆ ግቢውን ለቆ ሄደ …እሷ ባለችበት ድንዝዛ
ቀረች፡፡ተዘራን ጮኸ በመጥራት ያዝልኝ ሳይበላ እንዳይሄድ አትለው ነገር እንዴት
ብላ በዚህ መጠን እራሷን ታዋርድ….
‹‹እውነት ይሄ ልጅ ለመፅሀፉ ምን እንደሚል ገብቶትና መስጦት ነው…ወይስ
የንክ ነገር ሆኖበት ነው .››በውስጧ የሚወራጩ የጥያቄዎች ብዛት የምግብ
ፍላጎቶን ዘጋባት..ወደተዘራ ሄድች ያለመደባትን ወሬ ለመቃረም፡፡
‹ተዘራ›
‹አቤት እትይ›
‹‹ሄደ››
‹‹ማ?››
‹‹ልጁ ነዋ?››
‹‹እብዱን ማለትሽ ነው?››
‹‹አዎ ሄደ…››
‹‹ የሰጠሸውን መፅሀፍ ይዞ ሄዷል…ሰጥተሸው ነው አይደል?፡፡››በመጠራጠር
መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ..ለምን አንደፈለገው አላውቅም ስጪኝ አለ ሰጠውት››
‹‹እንዴ ሊያነበው ነዋ?››በንግግሯ በመገረም መለሰላት
‹‹አማርኛ እኮ አይደለም ጠጠር ያለ የእንግሊዘኛ መፅሀፍ ነው?››
‹‹አይ እትዬ ስለዚህ እብድ ምንም አታውቂም አይደል….?ሰፈሩ ውስጥ ሁሉ እኮ የማንበብ ብዛት እዳሳበደው ነው የሚወረው….እርግጥ አንዳንዶቹ ፍቅር ነው
ያሳበደው ይላሉ..አብዛኞቹ ግን ማንበብ እንዳሳበደው ነው የሚናገሩት .እትዬ
ብታይው እኮ እንግሊዘኛውን ሲያንበለብለው ፈረንጅ ያሰንቃል፡፡››
‹‹የተማረ ነው እንዴ?››
‹‹ፈረንጆቹ ሀገር ፍሮፌሰር ነበር አሉ ..ያው ንክ ሲሆን አምጥተው ጣሉት እንጂ››
‹‹ይሄን ሁሉ የምታወራው ግን እውነት ነው?››ሲፈን ብዥ እያለባት በጥርጣሬ
ጠየቀችው፡፡
‹‹እትዬ አታስዋሺኝ እውነት መሆኑን እንዴት ብዬ ላውቅ እችላለው?፡፡ በሰፈሩ
ሲወራ የሰማውትን ነው፡የእንግሊዘኛውን ማነብነብን ግን እኔ ምሰክር እሆናለው…
ሁለት ሶስት ቀናትን በጆሮ ሰምቼያለው፡፡አንድ ቀን እንደውም ከአንድ ፈረንጅ ጋር
አንድ ሰዓት ነው አደባባይ ላይ ቆመው በፈረንጅ አፍ ሲከራከሩ ሲጨቃጨቁ
እንደሞኝ ተገትሬ ሳዳምጣቸው ነበር››
‹‹ስለምንድነበር የሚያወሩት?›››
‹አይ እትዬ የፈረንጅ አፍ ነው እያልኩሽ ..ምኑን አውቄው ግዕዝ ቢሆንማ..?››
ዝም ብላው ወደውስጥ ተመለሳ ገባች …አንድ ሰዓት ከፍቅረኛዋ ከሄኖክ ጋር
የእራት ግብዣ ቀጠሮ አለባት፡፡ በተረባበሸ ስሜት

😘ነፍስ ስታፈቅር😘🔥ክፍል 9‹‹ሲፈን ጉድሽ ፈላ….የምን ካምፓኒ ማስተዳደር …የምን የምቾት ኑሮ.. እንደሽፍታ ከሽፈቶች ጋር የዋሻ ኑዋሪና የአምስት ሽፍቶች ሚስት ልትሆኚ ነው››ስትል በሚቃትት...
26/03/2023

😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 9
‹‹ሲፈን ጉድሽ ፈላ….የምን ካምፓኒ ማስተዳደር …የምን የምቾት ኑሮ.. እንደሽፍታ ከሽፈቶች ጋር የዋሻ ኑዋሪና የአምስት ሽፍቶች ሚስት ልትሆኚ ነው››ስትል በሚቃትት ድምጽ ለራሷ አንሾካሾከች …እዚህ ቤተሰቦቾ ሆኑ የትኛውም የመንግስት አካል አስሶ ሊደርስላት የማይችልበት ከምድርግ ግርጌ የሆነ ስፍራ ላይ ለዘላለም ልትኖር፡፡
አንድ የምታውቀው ብቸኛ ነገር ቢኖር ከዛች ቀን ጀምሮ ቢሮም ቁጭ ብላ ሆነ ከሰራ
ወደቤቶ ገብታ ስትተኛ ምስሉ በአዕምሮዎ ፊት ለፊት ስፍራ ላይ በግዙፍ
እንደተለጠፈ መቅረቱን ነው፡፡
ቆይ ያውና ….››አለች፡፡.ከፊት ለፊቴ አንገቱን ደፍቶ በዝግታ እየተራመደ
አየችው….ደረሰችበትና መኪናዎን አቆመች….አንገተቷን በመስኮት አሰገገችና
‹‹እ…እንዴት ነህ?፡፡››አለችው ….ስሙን እንኳን አታውቅም አኮ ….አይገርም፡፡
በግማሽ ቀና ብሎ አያትና መልሶ አቀረቀረ፡፡
‹‹አንተን እኮ ነው….አላወቅከኝም?››
እርምጃውን ገታ አደረገና መልሶ እያያት‹‹..አንቺን አላወቅኩሽም ነፍስሽን ግን..››
‹‹ነፍሴን ምን?››
‹‹ነፍስሽን አስታወስኮት..ባለስድስት ክንፎ አይደለሽ?››
‹‹አዎ ተመስገን. አውቆኛል ማለት ነው…አዎ የተገናኝ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ሲለየኝ እንደዛ ነበር ያለኘ ፡፡››ስትል በደስታ ፈነጠዘች፡፡
‹‹ትክክል ነህ ግበና ወደቤት እንሂድ››
‹‹የት ቤት ?›
‹‹እኔ ቤት››
‹‹ቤት አለሽ…?ቤት ግን ምን ይሰራልሻል?፡በዚህ ምድር በድንጋይ ቁልል እና
በመስተወት ድርድር ቤት በማነፅ ሽራፊ ጊዜያቸውን የሚያባክኑ ቀሽሞች ተራ
እራስሽን ለምን ታሰልፊያለሽ?››
‹‹ምን አልክ?›እውነቷን ነው ምን እንዳለ አልገባትም፡፡
‹‹ቤትሽ ምን እሰራለው?››ያለውን መደገም ትቶ ሌለ ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹መክሰስ እንበላለን፡፡››
‹‹መክሰስ….››እንደማቅማማት ካለ ቡኃላ ተስማምቶ ገቢና ገበ….ከቤቷ
ከ2መቶ ሜትር የበለጠ መንገድ ስላልቀራቸው ቶሎ ደረሱ ….በራፉ
ተፍከቶላቸው ወደውስጥ ገብተው ሞተሩን አጥፍታ ተያይዘው ሲወርድ ተዘራ
የተለመደ አግራሞቱንና ንጭንጩን ቀጠለ…
‹‹እንዴ እትዬ !!!ዛሬ ደግሞ ምን ፈለገ…?ኃላ ይሄ ልጅ ..!!››ከአንጀቱ
ሊያስጠነቅቃት ሞከረ፡፡
‹ተዛራ..›እሷ ደግሞ በተቃራኒው በቁጣዋ አስበረገገችው፡፡
‹‹እሺ እትዬ ላንቺ ብዬ ነው ፡፡››እየተነጫነጨ ለመኪና መግቢያ የከፈተውን
የውጭ በራፍ መዝጋት ጀመረ እነሱም ተያይዘው ገብ ፡፡
‹‹ቁጭ በል ልብስ ቀይሬ መጣው፡፡››
ዝም ብሏት ሄደና ሶፋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹ቴሊቪዠን ልክፈትልህ››
‹‹ቴሌቪዝን አልወድም››መለሰላት፡፡
‹‹ለምን? ››ገርሞት ጠየቅችው
‹‹ጫጫታ ብቻ ነው›
‹‹እሺ በቃ መጣው›› ብላው ወደፎቅ ወጣች..ለብሷን ቀይራ ለመመለስ ከ5
ደቂቃ በላይ አልወሰደባትም፡፡
ስትመለስ ከተቀመጠበት ተነሰቶ ሳሎን የሚገኘው የመጽሀፍ መደርደሪ ላይ
ያሉትን መፅሀፍቶች እያገላበጠ ነበር፡፡
‹‹ኪችን መክስ ልሰራ ነው .አብረሀኝ ትመጣለሀ ወይስ እዚሁ ትጠብቀኛለህ?››
‹‹ዝም ብሎ እጁ ላይ ያሉትን መጽሀፎች ወደመደርደሪያው መልሶ አንዱን
መፅሀፍ ብቻ ይዞ ወደእሷ ኄደ…በመገረም ውስጥ ሆና ቀድማው ወደ ኪችን
ሄድች ተከተላት… .ስትገባ ከኃላዋ ተከትሎት ገባና በራፉ አካባቢ ተገተረ..ክፍል
ውስጥ ካሉ ወንበሮች አንደኛውን አመቻችታ አስቀመጠችለትና
‹‹ ቁጭ በል…አሪፍ መክሰስ አሁን በፍጥነት ነው የማደርሰው›› አለችው

👇ይቀጥላል... 👇

💖ነፍስ ስታፍቅር😘🔥ክፍል 8‹‹ይሄው የፈራሁት ደረሰ››‹‹ምንድነው ?የምን ግንድ ነው?›› ሄኖክም ተርበተበተ‹ሸፍቶች መሰሉኝ››‹‹ምነው በቀረብኝ….እኔ እኮ የአባቴን የትውልድ ሀገር ጎብኝተን...
26/03/2023

💖ነፍስ ስታፍቅር😘

🔥ክፍል 8
‹‹ይሄው የፈራሁት ደረሰ››
‹‹ምንድነው ?የምን ግንድ ነው?›› ሄኖክም ተርበተበተ
‹ሸፍቶች መሰሉኝ››
‹‹ምነው በቀረብኝ….እኔ እኮ የአባቴን የትውልድ ሀገር ጎብኝተን እንምጣ ስትይኝ መች እደዚህ ሲኦል ውስጥ ይዘሽኝ እደምትገቢ ገመትኩ››
‹‹አላስገደድኩህም እኮ..ተስገብግበህ የመጣሀው በፍቃድህ ነው፡፡››
‹‹ልብሽን ባገኝ ብዬ ነዋ.እንድንጋባ እሺ ብትይኝ ባዬ ››
‹‹ለማንኛውም አሁን ከፊታችን ያለው ችግር ላይ እናተኩር….››የመኪናውን ፍጥነት እየቀነሰች…3ሜትር ያህል ሲቀራት አቆመች፡፡ሰዓቱ ወደአንድ ሰዓት አካባቢ የተቃረበ በመሆኑ አካባቢው ደብዝዞል፡፡ግራና ቀኝ የመንገዱን ጠርዝ ሲመለከቱ በግራ በኩል ሶስት በቀኝ በኩለ ደግሞ ሁለት ፀጉራቸው ሸሩባ የተሰሩ አስፈሪi ሽፍቶች መሳሪያቸውን ወደእነሱ አቀባብለው በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡
‹‹ወይኔ ገና ለገና እሺ ብለሽኝ አንቺን አገባለው በሚል ምኞት እዚህ መጥቼ በገዛ ደደብነቴ ሲኦል ልግባ፡፡››
‹‹ኸረ እስኪ አትንቦቅቦቅ፡፡››
ከሽፍቶቹ አንዱ ወደእነሱ ተጠጋና በጋቢናው መስታወት አጨንቁሮ ከተመለከተቡኃላ፡፡ ‹‹እጃችሁን ግንባራችሁ ላይ አድርጋችው ሁለታችሁም በዝግታ ውረዱ›› የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ ፡፡ወረዱ፡፡
‹‹ምንህ ነች ?ሚስትህ ነች?፡፡››ጠየቀ ሽፍታው፡፡ ሲፈን ፍቅረኛዬ ነች ብሎ ይመልሳል ብላ ነበር የጠበቀችው ሄኖክ ግን ‹‹አይ ምኔም አይደለች ..ማለት ጓደኛዬ ብቻ ነች›› በግልምጫ አንስታ አፈረጠችው፡፡
‹‹መኪና መንዳት ትችላለህ?››
‹‹አዎ እች..ላለ..ው፡፡››
‹‹ግባ››
‹‹የት?››
‹‹ መኪና ውስጥ፡፡›› በወረደበት ተመልሶ ሊገባ ሲል፡፡
‹‹አይ በሹፌሩ በኩል ግባ››
‹‹እሺ ››እየተሸቆጠቆጠ እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ሽፍታው ለጓደኞቹ እንጨቱን እንዲያነሱለት ትዕዛዝ ሰጠ….
‹‹በል አንተ ነፃ ነህ ተረጋግተህ እየነዳ ቀጥል..እሷ ግን ከእኛ ጋር ትሄዳለች፡፡››
‹‹እሺ…አመሰግናው፡በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው፡፡››
‹‹አንተ ትንሽ እንኳን ክብር የለህም …ጭራሽ አመሰግለው››ከፍራቻዋ እየታገለች አንቧረቀችበት ‹‹እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ .. ?በማላቀው ሀገር ይዝሽኝ መጥሽ..አይዞሽ እንግዲህ ››
‹‹በል ቀጥል››ሽፍታው በመስታወት አሻግሮ ሊነርተው የመሳሪያውነ ሰደፍ ሲያስተካክል
‹‹እሺ.. ጌታዬ ››በማለት መኪናዋ አስጓራና አይኗ እያየ ጥሏት ተፈተለከ፡፡
ሽፍታውን ክንዷን ጨምድዶ ጓደኞቹን ከኃላው አስከትሎ ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ ይዟት ገባ ፡፡ጫካው በድቅድቅ ጨለማ ቢዋጥም ከሽፍቶቹ እጅ ላይ በሚነሳ የባትሪ ብርሀን እየታገዙ ጥሻውን እየገለጡ በእሾህ ሰውነቷ እየተወጋ አስደንጋጭና አስፈሪ በሆነ የአውሬ ድምፅ ታጅበው ለአንድ ሰዓት ያህል ከተጎዙ ቡኃላ በደን በተከበበ ተራራ ጫፍ ላይ ካለ አንድ ዋሻ ውስጥ ይዘዋት ገቡ፡፡
ዋሻው ልክ እደእቤት ነው ፡፡መሬት የተነጠፈ ፍራሽ …ማብሰያ እቃዎች፤ በማዳበሪያ የተደረደረ እህል… በእጅ ከግንድ ተጠርቦ የተሰራ አግዳሚ መቀመጫ በዋሻው የሚገኙ ዕቃዎች ውስጥ ዋናዎቹ ናቸው….
መቀመጫው ጫፍ ላይ ተቀመጠች፡፡
ሽፍቶቹ የዋሻው የውጭ በራፉ ግራና ቀኝ ባለ ጠፍጣ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ይመካከራሉ..ከንቀታቸው የተነሳ እሷ ትስማ አትስማ ከቁብም አልቆጠራትም፡፡
‹‹እና ምንድነው የምናደርጋት፡፡››
‹‹ያው እንደተለመደው አድራሻዋን እንጠይቃትና .. ለቤተሰቦቾ ደውለን ብር እንጠይቅባታለን፡፡ ግን ይህቺኛዋ እንደከዚህ ቀደሞቹ አይደለችም፡፡አዎ ትክክል ነህ፡፡ ብዙ ሚሊዬን ብር የምታስገኝ የቱጃር ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ..አታየውም እንዴ ጉንጮን ተንጠልጥሎ እኮ የሚወድቅ ነው የሚመስለው…..የፊቷ ጥ

💕ነፍስ ስታፍቅር💕🔥ክፍል 7///* ፍቅርየህይወት ጣዕም መዓዛን-አመንጭቶ ያተናልበናርዶስ ሽቶ አውዶ-በደስታ ልብን ያሰክራልደግሞም ትንሽ ስቃይ አለው…ያስጨንቃል ያስተክዛልፍቅር ሲይዝ እንደዛ ...
24/03/2023

💕ነፍስ ስታፍቅር💕

🔥ክፍል 7
///
* ፍቅር
የህይወት ጣዕም መዓዛን-አመንጭቶ ያተናል
በናርዶስ ሽቶ አውዶ-በደስታ ልብን ያሰክራል
ደግሞም ትንሽ ስቃይ አለው…ያስጨንቃል ያስተክዛል
ፍቅር ሲይዝ እንደዛ ነው…ሁሉ ነገር ግራ ያጋባል
…………..ያስፈግጋል…….
……………ያስፈዝዛል……..
///
‹‹በብርሀን አምድ ያሸበረቀች እና ስድስት ክንፍ ያላት ነች..ደግሞ ነጭ የሀር ልብስ እየተጎናፀፈች በነጭ የፍቅር ፈረስ የመጋለብ ልምድ ያለት የተቀደሰች
ነፍስ አለችሽ››ብሎ ከእሷ ምንም መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን አዞረና በራፉን ከፍቶ ወጥቶ ሄደ፡፡እሷ ደንዝዛለች፡፡ የተናገራቸው ቃላትን ገጣጥማ መልሳ ማስታወስ አልቻለችም.ግን ወደውስጧ ዘልቀው ገብታው ልቧን ወግተውታል…፡፡
‹‹እትዬ…አረ እትዬ‹‹ሳሎን በራፍ ላይ ግራ በመጋባት የቆመው የተዘራ ድምጽ ነው ከድንዛዜዋ ያባነናት፡፡፡
‹‹አቤት ምን ያስጮህሀል?››
‹‹ አልሰማሺኝማ ..ልጁን ላስወጣው መሄድ ፈልጋለው እያለ ነው፡፡›
‹ቅድም አትገባም ስትለው ነበር ..አሁን ደግሞ አትወጣም ብለህ አገትከው?››ተበሰጫጨችበት፡፡እውነታው ግን ተዘራ ምንም ያጠፋው ነገር ኖሮ
ሳይሆን ባልገመተችው ሁኔታ በዚህ ታአምራዊ በሆነ አጋጣሚ ስሜቷ ድብልቅልቅ ስላለባት ነበር፡፡
‹‹ታዲያ ምን አድርጎ እንደወጣ በምን አውቃለው…?ሰላም ነው ልልቀቀው?፡›
‹‹አዎ ሰላም ነው ተዘራ.. አንተም ውጣልኝ እሱም ወደቤቱ ይሄድበት በራፋን ክፈትለት፡፡››
‹‹ተመስገን እትዬ… ሰላም ከሆነ ጥሩ.››ወጥቶ ሄደ እሷም ሶፋዋ ላይ ወደኃላ ተዘረረች ፡፡
ሰማያዊ ቀለም በተቀባች ላንድኩሩዘር መኪና በእሷ ሹፌርነት እየተጓዙ ነው፡፡ከጎኗ ሄኖክ ቁጭ ብሏል፡፡በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ከአዲስ አበባ ከ400 ኪ.ሜትር ገደማ ርቀው ይገኛሉ፡፡ወደ ቦንጋ እየተጓዙ ነው፡፡ጥቅጥቅ ባለው ደን ውስጥ ሰነጥቆ በሚያልፈው ፒስታ መንገድ ላይ በሰዓት 80 ኪሎ ሜትር እየነዳች ነው፡፡ከፒስታው መንገድ እየተሸረፈ የሚነሳው አቧራ ሰማዩን ሞልቶ እየተበተነ መልሶ ከኃላ መኪናዋ ሲከተላት ሆነ ብሎ እነሱን የሚያሳድድ የጥቁር መንፈስ ትንፋሽ ይመስል፡፡ የሀገር መሪን አቀባበል እንደሚያደርጉ መንጋ ህዝብ በዚህ ዱር ውስጥ መንጋ ዝንጀሮዎች የግራና ቀኝ የመንገዱን ጠርዝ ሞልተውታል፡፡ፀሀይ በሰማይ ጠቀስ ዛፎች መካከል እየተሸለኮለከች ወደማደሪያዋ ስትሸሽ ይተያል ፡፡
‹‹ውዴ ከተማ ሳንጠጋ መሸብን እኮ፡፡››ፍቅረኛዋ ሄኖክ ነው ፍራቻ ባረበበት እና በተጨነቀ ስሜት ሀሳቡን የሰነዘረው፡፡
‹‹ምን ላድርግ ታዲያ አነሳሳችን ነው፡፡መቼስ ይሄ ኤክስፕረስ መንገድ አይደል ከዚህ በላይ በሆነ ፍጥነት የምነዳው››የእሱ ፍራቻ ወደ እሷም እያጋባባት በመኆኑ ተበሳጭታለች፡፡
‹‹ግን መንገዱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው አይደል?››
‹‹በፈጣሪ በዚህ ዘመን በኢትዬጵያ ምድር ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ይኖራል፡፡..የእናት ማኅፀን ውስጥ ብትሆን እንኳን ስለደህነትህ በእርግጠኝነት መናገር አትችልም፡፡››
‹‹መንገድ አስቁሞ የሚተናኮለን አውሬ አለ ማለት ነው?››
‹‹አውሬ እርግጥ አለ ፤አንበሳም ፤አነርም ሌሎች ሌሎች አውሬዎች አሉ..ግን መንገድ አስቁሞ የሚተናኮለው ዋነኛው አውሬ የሰው ልጅ ነው፡፡››
‹‹የሰው ልጅ ..አልገባኝም ማሬ?››
‹ግልፅ ነው…በዚህ ምድር በጣም አስፈሪው አውሬ የሰው ልጅ መሆን አታውቅም?››
‹‹አረ ተይ እየቀለድሽ ነው?››
በዛ ቅፅበት በመንገዳቸው በ10 ሜትር ርቀት ትላልቅ የግንድ ጉርማጅ አንድ ላይ ተደራርበው መንገድን በአግድም ዘግተውት አየች፡፡
#ክፍል 8 ይቀጥላ...

💖ነፍስ ስታፈቅር💕🔥ክፍል 6‹‹እንዴ ወደየት ነው.…?››ቆም አለና ፊቱን ብቻ ወደእሷ ዞሮ ከእብድ ይልቅ የጅላጅል በሚመስል በተንቀረፈፉ ቃላት‹‹እ..ማዬ ጋር ››ሲል መለሰላት፡፡‹‹እማዬ ጋር...
22/03/2023

💖ነፍስ ስታፈቅር💕

🔥ክፍል 6
‹‹እንዴ ወደየት ነው.…?››
ቆም አለና ፊቱን ብቻ ወደእሷ ዞሮ ከእብድ ይልቅ የጅላጅል በሚመስል በተንቀረፈፉ ቃላት‹‹እ..ማዬ ጋር ››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹እማዬ ጋር .ልብስህን ልበሰና ትሄዳለህ፡፡››
‹‹እኮ ሰውነቴን ታጥቤ የለ …የምቀይረውን ልብስ እረስቼ ስለመጣውእኮ ነው..ልብሴ እማዬ ጋር ነው ያለው፡፡› ሳቋ ሊያመልጣት ነበር..እንደምንም ስሜቷን ተቆጣጥራ‹‹ቆይ ቆይ.እንደእሱ አይደለም …እኔ ንፅህ ልብስ እሰጥሀለው፡›› ‹‹ይሻላል …?›› ‹‹አዎ …ና ተከተለኘ ››አለችና እንዳይጠጋት አምስት እና ስድስት ሜትር ከእሱ ርቃ ወደላይ ወደፎቅ ለመውጣት ደረጃውን መንደርደር ጀመርች ምንም እንደልተፈጠረ .ረጋ ብሎ ..ደረቱን ነፍቶ.. ግንባሩን አኮሳትሮ.. እንትኑን እያንጀለጀለ ተከተላት.፡፡አንደኛ ፎቅ ላይ እንደደረሱ ሻወር ወደወሰደበት እንግዳ
ክፍል በእጇ እየጠቆመች ‹‹እዛ ግባና ጠብቀኝ የምትለብሰው ልብስ ይዤልህ እመጣለው›› ብላው ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ወደ መኝታ ቤቷ አመራች፡፡
ከደቂቃዎች ቡኃላ ገዝታ ከአንደ ቀን በላይ ያለበስችውን ቢጃማ ሱሪ ከነአላባሽ ጃኬቱ እንዲሁም ቲሸርት መርጣ አመጣችለት፡፡ አሁን እንዴት ነው ተጠግታ የምትሰጠው? ፡፡እሱ እንደሆነ እንደአለችው የእንግዳ ክፍል ገብቶ ተረጋግቶ አልጋ ጠርዝ ላይ ተቀምጧል፡፡ ስታቀብለው እጇን ለቀም አድርጎ ወደውስጥ ጎትቶ የተቀመጠበት አልጋ ላይ ቢዘርራትስ..ደግሞ የለበሰችው በቀላሉ የሚገለብ ስስ ቢጃማ ቀሚስ› ሀሳቡ በውስጧ ፍረቻ፤እፍረትና፤ሙቀት የመሳሰሉትን ድብልቅልቅ እና ተለዋወጭ ሰሜቶች አንዲሰማት አደረገ እንደምንም በሩን ታካ ቆመችና ፍቷን ወደውጭ አዙራ ልብስ የያዘው እጇን ወደ ውስጥ በመቀሰር..‹‹ማነህ… ይሄው ንፅህ ልብስ አምጥቼልሀለው…ልበስና ሳሎን ና››አለችው፡፡ ‹‹እሺ ››ብሎ ተቀበላት. ተንደርድራ ደረጃውን ወረደቸና ሳሎን ስትደርስ ማራቶን እንደሮጠ አትሌት ልቧ ደረቷን ሰንጥቃ ልትወጣ እስክትመስል ድረስ እያለከለከች ሶፋዋ ላይ ተዘረረች፡፡ የሆነ ህልም ውስጥ ያለች መሰላት ..ደግሞ መለስ ብላ መሳጭና ልብ አንጠለጣይ አድቪንቸር ፊልም እያየች ያለችም መስሎ እየተሰማት ነው፡፡‹‹ቆይ ምን አይነት ድፍረት ነው ከእብድ ጋር አጉል ጫወታ የምጫወተው? ነው ወይስ እኔም ከእሱ ያልተሻልኩ ያልታወቀልኝ ስውር እብድ ኖሬያለው?፡፡እንትኑ ሲንጀላጀል በአይነ ህሊናዋ መጣባትና በእፍረት አይኖቾን በእጆቾ ከደነች ደግሞ ጥርግ ተደርጎ የተላጨ ፀጉር አልባ መሆኑ የፈጠረባት ገረሜታ በራሱ አስገራሚ ነው… የእግር ኮቴ እርምጃ ስትሰማ እጇን ከአይኗ ላይ አነሳችና ተመለከተችው፡፡ እንዳለችው የሰጠችውን ቢጃማ ለብሶ በመምጣት ሳሎን መሀከል ላይ ቆሟል፡፡ ሌላ ሰው መስሏል.. ቢጃማው በልኩ የተሰፋ ነው የሚመስለው. ቁመቱን ይበልጥ እንዲመዘዝ በማድረጉ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቻ አስመስሎታል፡፡ደግሞ በፊትም ሉጫ የነበረ ፀጉሩን በጄል ይበልጥ ጥቅልል ብሎ በግንባሩ እንዲደፋ
አድርጎታል፡፡‹‹ይሄ ልጅ በአዕምሮ መናጋት አደጋ ከመጠቃቱ በፊት እኔ ነኝ ያለ ዘናጭና ሽቅርቅር እንደነበር ለመገመት የስነልቦና ባለሞያ መሆን አይጠይቅም.፡፡ስትል አሰበች፡፡
‹‹ቁጭ በል… ቁርስ አቅርቤልሀለው..ብላ››
‹‹እሺ›› ብሎ ወደጠቆመችው የምግብ ጠረጵዛ ሄደና ቁጭ አለ ‹‹ብላ እንጂ››
እሺ ብሎ ሶስቴ ጎረሰና…‹‹በቃኝ አሁን ልሂድ እማዬ ትጠብቀኛለች››አላት፡፡‹‹እንዴ ?መች በላኸው..?አልጣፈጠህም?››
‹‹ይጣፍጣል…ግን እኔ መብላት የምፈልገው የማዬን ቁርስ ነው፡፡› ‹‹ወይ ማበድ ደጉ የ30 ምናምን አመት ጎረምሳ ሰውዬ እንደ 3አመት ልጅ በየደቂቃው እማዬ እማዬ ማለቱ ያስፈግ

😘ነፍስ ስታፈቅር😘🔥ክፍል 5ሸፍኗት የቆየውን ፤ የስጋ ልብሷን አውልቃነፍሴ እርቃኗን ቀረች፤ በፍቅር አይን ስር ወድቃ///እቤቷ ያስገባችው ጥቁር እንግዳ ታጥቧ ከጨረሰ ቡኃላ የሚቀማምሰው ምግብ...
20/03/2023

😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 5
ሸፍኗት የቆየውን ፤ የስጋ ልብሷን አውልቃ
ነፍሴ እርቃኗን ቀረች፤ በፍቅር አይን ስር ወድቃ
///
እቤቷ ያስገባችው ጥቁር እንግዳ ታጥቧ ከጨረሰ ቡኃላ የሚቀማምሰው ምግብ
ፍለጋ ኪችን ገብታ መንጎዳጎድ ጀመረች….ከቁርሷ የተረፈ ምግብ ስለነበር እሱን
አሙቃ አሰናዳችና ወደሳሎን ይዛ ሄደች….፡፡የምግብ ጠረጳዛ ላይ በማስቀመጥ
ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ቻናል እየቀያየረች ቲቪ ለማየት ሞከረች ግን ትኩረቷን
የሚስብ ፕሮግራም አላገኘችም….ከፕሮግራሞቹ የጥራት ችግር ይሁን ወይሰ የእሷ ቀልብ እቤቷ ውስጥ ባለው እብድ ተብየ ልጅ መሳብ አልገባትም፡፡
በግምት 15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች ቡኃላ ከቴሌቭዝን ድምፅ ጎላ ያለ ድምፅ
ሰማችና ከተጋደመችበት በርግጋ ተነሳች፡፡ቆመች፡፡ ድምፁን ወደሰማችበት
ወደላይ ወደፎቅ መወጣጫ አይኗቾን ላከች… .
ከደረጃ ላይ ወደታች እየወረደ ነው…..ልጁ ‹‹ወይኔ በጌታ›ሰትል ድምፅ አሰማች
‹ የቀበጡ እለተ ሞት አይገኝም› ይላሉ የሀገሬ ሰዎቸ›› በውስጧ ነው ይሄን ሁሉ
የምታጉረመርመው፡፡ምክያቱም አሁን ፊት ለፊቷ ቅድም እንዳይሆን የፈራችውን
ነገር ነው ሆኖ እያየች ያለችው
…..ልጁ ፎጣውን ተከሻው ላይ ጣል አድርጎ መለመላውን እንትኑን እያንጀለጀል
እርቃኑን ወደታች እየወረደ ነው…አዎ ወደ እሷ እየመጣ…‹ወይኔ ምን ላድርግ …?
ተዘራን ልጥራው.ወይስ ታግሼ የሚሆነውን ልጠብቅ…?›…… የምታደርገው
እስኪጠፋት ተጨነቀች፡፡
ከነገ ጥዋት ጀምሮ የታዋቂው የኢትዬ ዳይመንድ ካማፓኒ ባለቤትና ስራ-
አሲኪያጅ ወጣቷ ወይዘሪት ሲፈን ይርጋ በገዛ ቤቷ ውስጥ በአንድ የሰፈር እብድ
ተደፈረች ›ተብሎ በየሚዲያውና በየፌስ ቡኩ ስሟ ሲብጠለጠል እና በገዛ
ቅብጠቷ ታሪኳ ጭላሸት ሲቀባ ታያትና ዝግንን አላት፡፡
የፈራችው ግን አልሆነም ልጁ ወደእሷ አይደለም እየሄደ ያለው ተጠምዝዞ
ወደመውጫው የሳሎን በር እያመራ ነው፡
‹‹እንትና ማን ነበር ስምህ……? ››…..እብድ ስሙ ምን ያደርግለታል…?
ለመሆኑ ስሙን ያውቀው ይሆን …?ስትል በዛች ጭንቅ ሰዓት በውስጧ አሰበችና
ፈገግ አለች፡፡
‹‹እንዴ ወደየት ነው.…?››
ቆም አለና ፊቱን ብቻ ወደእሷ ዞሮ ከእብድ ይልቅ የጅላጅል በሚመስል
በተንቀረፈፉ ቃላት‹‹እ..ማዬ ጋር ››ሲል መለሰላት፡፡

16/03/2023

💕ነፍስ ስታፈቅር💕

🔥ክፍል 2
#ፊልም ለምኔ የሚያስብል ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ....Share የምታረጉ ከሆነ ታሪኩ በየቀኑ ሳይቆራረጥ ይቀርባል።
አብረው መሆን ከጀመሩ ስድስት ወር ቢያልፋቸዉም የእሱ ነገር እስከአሁን ከጉሮሮዋ አልወረደላትም፡፡ሙሉ በሙሉ ቆርጣ አንዳትተወው ደግሞ አሳቢነቱ፤ ሁለቱን በተመለከተ ያለው እቅድ፤በቢዝነሱ አለም ያለው ብቃትና ተሰሚነት የመሳሰሉት ነገሮች ስታስብ ‹ቆይ ትንሽ እድል ስጪው› ይላታል ልቧ፤እና ይሄው እየተወዘገበች በተሰለቻቸ ስሜት አብራው ትዳክራለች፡፡
ስልኩን አነሳችው
‹‹ሄሎ ማር››ጎርናና ወንዳ ወንድ ድምፅ
‹‹ሄሎ እንዴት ነህ?››ቀዝቃዛ የደከመ መልስ
‹‹አለውልሽ የእኔ ጨረቃ….ብታይ ንፍቅ ብለሺኛል፡፡››
‹‹አረ ባክህ….ደግሞ የትነህ ..ኳኳታ ነገር ይሰማኛል፡፡››
‹‹ጂም ነኝ፡፡››
‹‹በሰንበቱ ሰው ቤተክርስቲያን ይሄዳል አንተ ጅም…..?››
‹‹ምን ላድርግ ብለሽ ነው… ሸንቀጥቀጥ ስል ምናልባት በምመኘው መጠን ትወጂኝ እደሆን ብዬ እኮ ነው እንዲሀ የምዳክረው›› በቀልድ አስመስሎ ለፍቅራቸው እውን መሆን ምን ያህል እየጣረ እንዳለ እየነገራት ነው…እሷም ገብቷታል፡፡ ‹‹ቦርጬን አጠፋለው ብለህ ልብህን አቅልጠህ እዳ እንዳታስገባኝ››
‹‹ውይ!! ምነው ማሬ ….ከአንቺ ጋር ተሞሽሬ አንቺን የመሰለች የፀሀይ ሽራፍ ትንሽዬ ንግስት ሳልወልድማ እንኳን ሞት እንቅፋትም አይነካኝም፡፡››
‹‹ያድርግልህ››
‹‹እና የዛሬ ፕሮግራምሽ አንዴት ነው?፡፡››
‹‹ያው እንደተለመደው ነዋ፡፡››
‹‹ማታ ከቤተሰቦችሽ ጋ ስትመለሺ እራት ብጋብዝሽስ?››
‹‹መመለሴን በምን አወቅክ?››
‹‹ለእኔ ስትይ ብታደርጊው ምን አለበት?››
‹‹በል ቸው…ከተመለስኩ እደውልልሀለው››
‹‹ከ11 ሰዓት ቡሃላ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለሁ፡፡››
‹‹ተስፋ አታድርግ …..አባዬ እንዳድር ከጠየቀኝ አድራለሁ፡፡››
‹‹ባንቺ ተስፋ ማድረግ የህይወቴ ዋነኛ ተግባር ነው….››
‹‹በርታ ከማለት ውጭ ምን እላለው….በል ቸው››ስልኩን ዘጋችው፡፡ ይሄ ነገር ከእለት እለት እያስጨነቃትና ምቾት እየነሳት ነው፡፡ምንድነው ወይ ማይበርድ ወይ ማይቀዘቅዝ ፍቅር…..?ዝም ብሎ ለብ ያለ፡፡››ስትል አሰበች፡፡ ፍቅር በእጮኝት ጊዜ መንበልበል አለበት ካለበለዚያማ ወደጋብቻ ሲገባ በረዶ ሊሆን ነው፡፡››ይህ የእሷ እምነት ነው፡፡ ሲፈን ወንዶችን በተመለከተ ከ16 አመቷ ጀምሮ ሀይ አንድ አመት እስኪሞላት ድረስ ከፍተኛ የሚባል ልምድ አላት፡፡ የቤተሰቾን ሀብት ፤ወጣትነቷን እና አማላይ መልኳን እየሰባቸው ዙሪያዋን የሚያዣብቡ ወንዶችን ሁሉ በየተራ እያገላበጠች አጣጥማቸዋለች፡፡ከአንዱ የአበባ ዛፍ ወደሌላው በሰከንድ ልዩነት እየተስፈነጠረች ሁሉን በመቅሰም ለማዳረስ እንደምትጥር እንደሰራተኛ ንብ ነበረች፡፡ከሀያ አንድ አመቷ ቡኃላ ግን በድንገት ወንዶች ሰለቾት፡ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ተወችና ጭምት ወንድ ነክታ የማታውቅ የድንግል ሴት ባህሪን ተላበሰች፡፡አጃቢዎቾ የነበሩ ወንዶች እስኪገርማቸው ድረስ…ወዳጅ ዘመዶቾ በለውጧ እስኪደመሙባት ድረስ..እሷም በራሷ እስክትገረም ድረስ፡፡ልክ ገና በጨቅላ እድሜዋ እንደሰላቾትና እንደተወቻቸው ቡዙ ነገሮቸ ሁሉ ከወንድ ጋርም ያላትን ፆታዊ ግንኙነት በተመመሳሳይ አቅለሸለሻት፡፡ከሶስት አመት ቡኃላ ነው ከሄኖክ ጋር በመጠኑ ለመቀራብ ለራሷ ብጣቂ እድል ለመስጠት እየጣረች ያለችው…፡፡እሱንም በሩቁ …በአይን እይታ እና በቃላት ልውውጥ ብቻ፡፡ከዛ ውጭ
አሁን በእጆ ላይ ያለው ብቸኛ ያልሰለቻት ነገር ስራዋ ነዉ ..

ይቀጥላል..

😘ነፍስ ስታፈቅር😘🔥ክፍል 4‹‹እና ምን ፈልጎ ነው ….…?እርቦት ይሆን…?›.‹‹ኸረ እትዬ… እሱ ቅንጦተኛ ነው…››.‹‹ማለት….…?››ፊቷን ከዘበኛው ወደልጁ መልሳ ‹‹አባ ምን ፈልገህ ነው…?...
16/03/2023

😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 4
‹‹እና ምን ፈልጎ ነው ….…?እርቦት ይሆን…?›.
‹‹ኸረ እትዬ… እሱ ቅንጦተኛ ነው…››.
‹‹ማለት….…?››
ፊቷን ከዘበኛው ወደልጁ መልሳ ‹‹አባ ምን ፈልገህ ነው…?››ስትል ጠየቀችው፡፡ፍረጥም ብሎ‹‹ሻወር ፈልጌ ነው….እማዬ ጋር ውሀ ስለጠፋች መታጠብ
አልቻልኩም››
የምትሰማውን ማመን አልቻለችም፡፡ምታደረግው ግራ ገባት ፡፡
‹‹እውነትህን ነው ……?ሻወር ፈልገህ ነው…?፡፡››
‹‹አዎ ካልታጠብኩ ይቀፈኛል..ያመኛልም›› አላት ልክ ሰውነቱን እያሳከከው እንዳለ በመቁነጥነጥ እና ፊቱን በማጨማደድ፡ለእሷም ባልገባት ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ስሜት በራፍን ወለል አድርጋ በመክፈት ከተገተረችበት ወደዳር ገልል ብላ‹‹ግባ እሺ››አለችው፡፡
በአንድ አፍ ወደውስት ገባ…በራፍን መልሳ ዘጋችው፡፡ሲያበሽቁት የነበሩ ልጆችም የተፈጠረው ነገር ብዙም ሳይረዱ እያስካኩ ሰፈሩን ለቀው ሄዱ፡፡
‹‹ተከተለኝ ፡፡››አለችና እየመራች ወደሳሎን ይዛው ገባች፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆንዘበኛው ተዘራም ተከትሎቸው ሳሎን ተገኘ፡፡
‹‹ተዘራ ምን ፈለክ?››ጠየቀችው፡፡
‹‹እትዬ ብቻሽን እንዳትሆኚ ነው››የተዘራ ስጋቱ ስለገባት ፈገግ አለችና ‹‹ግድ የለም ተዘራ ወደስራህ ተመለስ››አለችው፡
‹‹እትዬ የማይሆነውን …ለእበድ ጥዬሽ ወዴትም ዝር አልልም››ቆፍጠን ብሎ
መለሰላት::
‹‹ተዘራ …››እጆን በማወራጨትም …ግንባሯን በመቆጠርም አፈን ዘግቶ ሳሎኑን ለቆ እነዲወጣላት ያላትን ፍላጎቴን አሳወቀችው፡፡
‹‹እትዬ…በቃ በረንዳ ላይ ነኝ ….ትንሽ ድምፅ ከሰማው ዘልዬ ስርሽ ነኝ፡፡››አለት
ደጀንነቱን በሚገልፅ መወጣጠር ከወዲህ ወዲያ እየተወራጨ
‹‹እሺ በቃ አሁን ውጣ››የመጨረሻውን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ይሄን ሁሉ ሲጨቃጨቅ ልጁ ምንም እንዳልተፈጠረ አንዴ የቤቱን ዙሪያ ገባ …ከዛ
ደግሞ እሷን እና ተዘራን እያፈራረቀ በማየት እንደተገተረ ነው፡፡ተዘረ ከወጣ ቡኃላ
‹‹ተከተለኝ›› ብላው ቀድማ ወደ ፎቅ መወጣት ጀመረች ….እንግዳ ክፍል ይዛው ገባች….የሻወሩን በራፍ ከፍተችና በትክክል እንደሚሰራ እና ውሀም
መኖሩን ከፈተሽች ብኃላ‹‹…ያው ፎጣም ሳሙናም አለልህ… ታጥበህ ስትጨርስ ሳሎን ና..››አለችው
‹‹እሺ›› ብሎ እዛው በቆምመችበት የእሷን ክፍል ውስጥ መሆን ከምንም ሳይቆጥር ከላይ የለበሰውን ቲሸርት መዥርጦ አወለቀው….ልጥልጥ ጥቁር ሰውነቱ እንደተወቀጠ ኑግ ያብረቀርቃል…ከእንብርቱ ጀምሮ ወደተች የሚወርድ ሉጫ ፀጉር ይታያል...ደረቱም እንደዛው ግምሽ ግዛቱ በፀጉር እንደተሸፈነ ነው…
ሳትወድ በግድ ግማሽ እርቃኑን በጥንቃቄና በአድናቆት ፈዛ አየችው.የሚፈታተናት አይነት የሰውነት አደረጃጀት ነው ያለው፡በዛ ቀበጥ በነበረችበት በአስራዎቹ መጨረሻ የእብደት እድሜ ላይ በነበረችበት ጊዜዋ ላይ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ለዚህ እይታዋ የምትሰጠው ግብረ መልስ የተለየ ይሆን ነበር፡፡አሁን ግን በልቧ ብቻ አስባ ወደተግባር መሸጋግር አቁማ በአዕምሮዋ በማመዛዘን የነገሮች ትርፍና ኪሳራን በማስላት ውጤቱንም በመገመት ነገሮችን ማስኬድ በጥልቅ ልምምድ የተካነችበት በእድሜ ብስለት ያገኘችው ብቃቷ ስለሆነ ስሜቷን ለመጨቆን ብዙም አልተቸገረችም፡፡ለሌላ ተጨማሪ ደቂቃ በቆመችበት ሆና
እብድ ተብየውን ለግላጋ ወጣት ማየቷን ከቀጠለች ሱሪውንም ጭምር ፊት ለፊቷ እንደማያወልቅ እርግጠኛ መሆን ስላልቻለች የመሮጥ ያህል ዘላ
ከእንግዳ ክፍል ወጣችና ወደኪችን አመራች፡፡
#ክፍል 5 ይቀጥላል...

😘ነፍስ ስታፈቅር😘🔥ክፍል 3ካምፓኒዋን በብቃትና በትጋት የመምራቱን ስራ፡፡ አንድ የሀያ አራት አመት ፤ስኬታማ እናአማላይ ወጣት ሴት እዚህ ስሜት ላይ በዚህ እድሜዋ መገኘት አስገራሚና አስፈሪ ...
15/03/2023

😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 3
ካምፓኒዋን በብቃትና በትጋት የመምራቱን ስራ፡፡ አንድ የሀያ አራት አመት ፤ስኬታማ እና
አማላይ ወጣት ሴት እዚህ ስሜት ላይ በዚህ እድሜዋ መገኘት አስገራሚና አስፈሪ ነገር ነው፡፡
ስለሄኖክና ስለእሷ ግንኙነት አስባ ሳትጨርስ የውጭ በራፍ አካባቢ ከተለመደው
ውጭ ጭቅጭቅ ሰማችና ትኩረቷን ወደእዛው አደረገች …ዘበኛው በራፉን
አጥብቆ ይዞ ዱላውን ለመደባደብ በሚመስል ሁኔታ እየወዘወዘ ያምቧርቃል..፡፡
‹‹ሰውዬ..ወግድልኝ….በህግ እምላክ ብያለው ዞር በል..››ይህ ዘበኛ ለሲፈን
በአባቷ ቤት ውስጥ አብሮት ያደገ እንደቤተሰብ አንድ አባል የሚቆጠር እሷን
በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ለመጠበቃ አደኃላ እንደማይል የታመነበት ሰው
ነው፡፡በማታው ጥበቃ የሚያግዘው ሌላ ዘበኛ ቢኖርም ቀን ግን ግቢ
መጠበቁንም ፤የአትክልተኝነቱንም ሆነ ጠቅላላ አስፈላጊ የሆኑ ስራዎችን ከልቡ
ያለመሰልቸት ብቻውን ይሰራል፡፡
‹‹ተዘራ ምንድነው…?››በተቀመጠችበት ሆና ጠየቀች..መልስ ስላላገኘች
እያነበበች የነበረው መፅሀፍ የተቀመጠችበት ወንበር ላይ አስቀመጠችና
ወደበራፍ ሄደች..
‹‹እትዬ…አንድ እብድ በሰንበቱ ቀን እየነጀሰን ነው፡፡››ዘበኛው ነው ሁኔታውን
የሚያስረዳት
‹‹እብድ….!!ምን ፈልጎ ነው…?››ይህንን የምትጠይቀው ዘባኛውን ከፊት ለፊቷ
ዞር በማድረግ አንገቷን ወደውጭ በማስገግ ነበር፡፡
ረጅም ነው..በጣም ረጅም፡፡ ደግሞም ፈርጣም….ወደጥቁርነት ያደላ የሰውነት
ቀለም ያለው..ልጥልጥ ጥቁር ዞማና ሉጫ ፀጉር ..ልቅም ያለ
ቆንጆ..አፍንጫው የተመጠነ ሲሆን አይኖች ጎላ ጎላ ያሉና ቀለማቸው
ያልተለመደ አይነት ነው፡፡ሰማያዊ የድመት የሚመስሉ አስደነንጋጭ አይኖች፡፡
ከንፈሮቹ ደልዳላና የበሰለ ብርቱካን ክፋይ የሚመስሉ አጓጊ፤፡
አዲስ የቆዳ ሸበጥ ጫማ ተጫምቷል፡፡ ከላይ የነተበና ከወደ እጄጌው ጫፉ
መተልተል የጀመረ ሰማያዊ ሹራብ ከስር ከሰማያዊ ወደ ዳለቻ ተቀይሮ ቀለሙ
የወየበ ጅንስ ሱሪ ለብሷል…የለበሳቸው ልብሶች ያረጁ ቢሆኑም ንፅህ ናቸው፡፡
ከኃላው ተከትለውት የሚያስካኩ አራት የሚሆኑ ህፃናት አሉ፡፡
ሲፈን ጠቅላላ እሱነቱን እንደመረማሪ ፓሊስ አንድ በአንድ ከአስተዋለችው ቡኃላ
የመደንገጥ ወይም የመጠየፍ ስሜት አይደለም የተሰማት፡፡ ከዚህ በፊት
ተስምቷት የማታውቀው የሆነ የጠፋባትን የቅርቧን ሰውን በድንገት እንዳገኘ ሰው
የመንሰፍሰፍ ስሜት ነው በውስጧ የተረጨው..ፊት ለፊቷ እያየችው ያለው ልጅ
እብደ ሳይሆን ቀን የከዳው ችግረኛ እንደሆነ ገመተች፡፡‹‹አዎ እርቦት ይሆናል››
አለች….በውስጧ፡፡የተራበ ማየት የዲስ አበባ ኑዋሪ አንደመሆኗ መጠን የየአለት
ገጠመኞ ቢሆንም እንዲህ አይነት ስሜት ግን በውስጦ አጭሮባት አያውቅም፡፡
ፍፅም ፡ታዲያ ይህ ፊቷ የተገተረው ወጣት ምን የተለየ ነገር ቢኖረው ነው
ውስጧን በሰከንዶች እይታ ሊነካ አቅም ያገኘው፡፡አልገባትም፡፡
ካለችበት ሳትነቃነቅ ፊቷን ብቻ ወደውስጥ መልሳ ዘበኛውን‹‹ እርግጠኛ ነህ
እብድ ነው…?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እትዬ እርሷ እቤት ሰለማይውሉ እና ሰፈሩንም ዞር ዞር ብለው ስለማያውቁት
እንጂ እዚህ ሰፈር ከላይ እታች ሲንገላወድ የሚውል ንክ ነው..አረ እንደውም
የቤተሰቦቹ ቤት ከዚህ ብዙም እሩቅ አይደለም….››በሚያውቀው መጠን
አብራራላት፡፡
‹‹እና ምን ፈልጎ ነው ….…?እርቦት ይሆን…?›.
‹‹ኸረ እትዬ… እሱ ቅንጦተኛ ነው…››.
‹‹ማለት….…?››

#ክፍል 4 ይቀጥላል...
👉

💕ነፍስ ስታፈቅር💕❣ክፍል 1  #በዉብ ቃላቶች የተከሸነ ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ...ፍቅር ከስጋ ቢሆን ኖሮ ስጋዬን አቃጥዬ ከፍቅር ህመሜ እራሴን እፈውስ ነበርነገር ግን ፍቅሬ ...
14/03/2023

💕ነፍስ ስታፈቅር💕

❣ክፍል 1

#በዉብ ቃላቶች የተከሸነ ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ...
ፍቅር ከስጋ ቢሆን ኖሮ ስጋዬን አቃጥዬ ከፍቅር ህመሜ እራሴን እፈውስ ነበር
ነገር ግን ፍቅሬ ከነፍሴ ሆነና ልደረስበት አልቻልኩም፡፡
ካህሊል ጅብራን
///
ምድር አብዛኛውን የሚያስፈልጋትን ኃይል የምታገኘው ከሀያሏ ፀሀይ ነው፡፡በብርሀን እና በሙቀት መልክ፡፡ምድር እና በውስጧ ያሉት እንስሳትም ሆኑ እፅዋት በፀሀይ ተፅእኖ ስር ናቸው፡፡እኛ ሰዎች የምንኖርበት አካባቢ የአየር ፀባይ፤ በየስፍራው የሚበቅለው የዕፅዋት አይነት፤ እሱን ተከትሎ የምንመገበው የምግብ አይነት፤ በየአካባቢው የምንለብሰው የልብስ አይነት ፤ከዛ አልፎ አኗኗራችን እናም ግለሰባዊ ፀባያችንን ላይ የራሷን ውሳኔና ምርጫ
ታስተላልፋች…እኛ አሜን ብለን ከመቀበል ውጭ እሷን ለመገዳደር እና ተፅኖዋን
ለማስቀረት አቅም የለንም ፡፡ከዚህ በላይ ደግሞ በውበቷም መደመማችን የእየእለት አጋጣሚያችን ነው፡ጥዋት ስትወጣና በፍቅር መቀበል እናም ማታ ስትጠልቅ በተስፋ መሸኘት የዘወትር ድርጊታችን ነው፡፡እንግዴህ አሁንም የጥዋቷ ፀሀይ በመስኮት አሻግራ ግንባሯ ላይ አርፋ በፍቅር ስትዳብሳት ነበር ከእንቅልፎ የባነነችው፡፡ሲፈን፡፡ ሰዓቱ ሁለት ሰዓት አልፎል፡፡እስከዚህን ሰዓት ድረስ መተኛት የሲፈን ፀባይ አይደለም፡፡ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ከአስራ ሁለት ሰዓት ቀድማ ከእንቅልፎ ነቅታ አንድ ሰዓት ሳይሆን በፊት ቢሮዋ ወንበር ላይ ተቀምጣ በእለቱ
የምትሰራውን የስራ ፕሮግራም ማሰናዳት መጀመር በቀላሉ የምትከውነው ነገር
ነው፡እሁድ ግን የእሷና የወላጆቾ ቀን ነው፡፡ጥዋት የብቻዋ ከሰዓት ከወላጆቾ ጋር
በአንድነት የምታሳልፈው፡፡ ተነሳችና ለብሳ ያደረችውን ቢጃማ ሳትቀይር ወደ ኪችን ገባች፡እዚህ ግዙፍ ቤት ውስጥ ብቻዋን ነች እንጂ እንዲህ በለበሰችው ቢጃማ ከኃላ የሚያስተውላት ሌላ ሰው ቢኖር ምራቁን መዋጡ አየይቀሬ ነበር፡፡የሚካኤል አንጀሎ እጆች ያረፈባቸው የሚመስሉት የሰውነቷ ቅርፅ ከኢንቨስተር ነት ይልቅ ለሞዴልነት
የተፈጠረች ነበር የሚያስመስላት፡፡ያ ማለት ይህ አማላይነቷ አሁን በምትሰራው
የስራ-አስኪያጅነት ስራዋ አልጠቃማትም ማለት አይደለም፡፡ከሚገባው በላይ የሰውን ቀልብ ለመግዛትና በወንዶች በተሞላው የንግዱ አለም ላይ በሚደረጉ የቢዝነስ ድርድሮች በቀላሉ ትኩረት እንድታገኝና በድርድር ትላልቅ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የረዳት በተፈጥሮ ያገኘችው እሷም ያንን አውቃ በአግባቡና
በተመጠነ ስውር ዘዴ የምትጠቀምበት የእግዜር ስጧታዋ ነው ፡፡ እርቧታል ፡፡ተመላላሽ ሰራታኛዋ ደግሞ እሁድ አትገባም፡፡እንዲህ እንዲሆን
ያደረገችው ደግሞ እሷ እራሷ ነች፡፡እንደፈለገችው አይነት የእረፍት ቀን
ለማሳለፍ ካላት ምኟት የተነሳ፡፡በቀላሉ የሚሰናዳ ቀለል ያለ ቁርስ አሰናድታ
ከበላች ቡኃላ የሚነበብ መፅሀፍ ይዛ ወደ በረንዳ ወጣች፡፡ልዩ ፕሮግራም ካልገጠማት በስተቀር ይህ የእለተ እሁድ የዘወትር ፕሮግራሟ ነው፡፡ በግማሽ ልብ እያነበበች በግማሽ ልብ ደግሞ እያሰላሰለች ደግሞ የተወሰነ ደቂቃ በአትክልት እና በተለያዩ ቀላማት በለበሱ አበቦች የተሞውን የጊቢዋን አፀድ በፍቅር እየቃኘች አዕምሮዋን ጅምናስቲክ ሳታሰራ ሞባይል ስልኳ ጮሀ…ካስቀመጠችበት አነሳችና አየችው፡፡ሄኖክ ነው፡፡ሄኖክ በፍቅረኝነት እና በጓደኝነት መሀከል የሚዋልል ወዳጇ ነው፡፡ማለት ሙሉ በሙሉ ተቀብላ ፍቅሯ እንዳታደርገው ልቧን ቅልጥልጥ የሚያደርግ ምንም ነገር ከእሱ አላገኘችም፡፡ ይቀጥላል??... Part 2

13/03/2023

S♥ G:....
"ምን ያክል ነው ፍቅርህ?
ብለሽ ብጠይቂኝ
❤️❤️
ምን ያክል ልበልሽ?
ምኑን አውቀዋለሁ፣
እኔ አምላክ አይደለሁ፣
ብቻ ግን...
ማንም ጓደኛውን ከሚወደው በላይ፣
ማንም ፍቅረኛውን ከሚያፈቅረዉ በላይ፣
ውስጤን ገዝተከዋል ቦታ አለሽ ልቤ ላይ፡፡
😍😍😍
ብታምኝም ባታምኝም፣
እውነቱን ልንገርሽ ፍቅሬ አንቺን አልዋሽም፣
እስከ ዘላለሙ እኔ አላፈቅርሽም፣
እንደ ሞኝ አፍቃሪ
የዘላለሜ ነህሽ ብዬ አልደልልሽም፣
ምክንያቱም...
ዘላለም የሚኖር ሠው ተፈጥሮ አያውቅም፡፡
አንቺ
እኔም
ሁሉም
ማንም ቢሆን ማንም፣
ዘላለም አፍቅሮ ዘላለም አይኖሮም፡፡
ግን...
እስከ'ድሜዬ ክልል እስከ ሂወቴ ጫፍ፣
መቼም አይሰለቸኝ
አንቺን ና ፍቅርሽን አዝያችሁ ብከንፍ፡፡
አፈቅርሻለሁ 💖💖ትላንትም
ዛሬም
ነገም
አስካለው በምድር ፣ከዛም በኋላ ❤️❤️😘
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
💞
💞

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍቅር ያሸንፋል fikr yashenfal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share