03/07/2024
ሰኔ 26 - 2016 ዓ.ም
ሊቢያና ቱኒዚያ የሚዋሰኑበት ድንበር ዳግም ተከፍቷል፡፡
የሊቢያው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት መካከል ከሶስት ወራት በላይ ተዘግቶ የቆየው የመተላለፊያ ድንበር ሙሉ በሙሉ መከፈቱን ነው የገለጸው፡፡
ከዚህ ቀደም ቀጣናው የተሻለ አንፃራዊ ሰላም አግኝቷል በሚል በከፊል ማቋረጫው የተከፈተ ቢሆንም ዳግም ባጋጠመው የጸጥታ ስጋት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ድንበር መዘጋቱም ይታወቃል፡፡
ዘገባው፡-የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡
በትእግስቱ በቀለ
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን