Baadiyyaa Iddoo Omiishaa Hayyoota

  • Home
  • Baadiyyaa Iddoo Omiishaa Hayyoota

Baadiyyaa Iddoo Omiishaa Hayyoota Hararge Lafaa Hayyoota

10/12/2023

Hordoftoota


Nu filattanii waan nu hordoftaniif galatoomaa!

Biiroo Kominikeeshinii Oromiyaa

10/12/2023
10/12/2023

Malaammaltummaa Aduu Qabsoo Uummataatiin Gogsina!

04/12/2023
07/11/2023
01/11/2023
01/11/2023
01/11/2023
01/11/2023

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ኅብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው።

የፓርቲያችን ኅብረ ብሔራዊነት በሁሉን አቀፍነት፣ በብዝኃ ልሳንነት እና በአሳታፊነት ሊገለጽ ይገባል ብሎ ፓርቲያችን ያምናል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ብዝኃነትን እንደጸጋ የሚመለከት ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና የሚሰጥና ካላቸው የታሪክ ትሥሥር፣ ተመሳሳይ አሁናዊ ሁኔታ፣ የጋራ ጥቅም እና ተስፋ በመነሣት ጠንካራ ኅብረትና ትብብር ሊኖራቸው ይገባል የሚል ዕሴት ነው።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ማንነታችን እርስ በርሱ የተጋመደ፣ የተሠናሰለ እና የተዋሐደ መሆኑን አመላካች ነው። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዕጣ ፈንታችን እጅጉን የተቆራኘ መሆኑን በመገንዘብ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን መቆም፣ አብረን መሥራት፣ መደጋገፍ እና መተጋገዝ እንደሚገባን የሚያስገነዝብ አመለካከት ነው።

ኅብረ ብሔራዊ፣ አንድነት ታሪካዊና ነባራዊ በደሎች ከማድበስበስ ይልቅ ታርመው እንዲሄዱ፣ ይህም ለቁርሾ ሳይሆን ወዳጅነትን ለማጠናከር እንዲውል የሚያደርግ አካሄድ ነው።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የሚከፋፍሉ እና የሚያጣሉ ትርክቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሣሥሩንን እውነታዎች በማጉላት፣ ከትናንት ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር እህታዊ/ወንድማዊ ኅብረትን በብሔሮች መካከል ማጠናከርን ይመርጣል።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ብዙ ሆነን አንድ፣ አንድ ሆነንም ብዙ የምንሆንበት፣ ለጋራ ግብና ዓላማ የምንደመርበት ቀመር ነው። በብዝኃነታችን ደምቀን፣ በአንድነታችን በርትተን ወደፊት የምንራመድበት የውበትና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው።

01/11/2023

“የብልፅግና ዋና መርህ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ነው። ይህ መርህ እርስ በእርሳችን አንድንተሳሰብ እንድንደጋገፍ ይረዳል።እንደ ሀገር የሚገጥሙንን ችግሮች ልናልፋቸው የምንችለው በዚህ እሳቤ ስንመራ እና የአንዳችን ቁስል የአንዳችን ህመም መሆኑን ስንገነዘብ ብቻ ነው!”

አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት

01/11/2023

መልካም እሴቶችን ማጎልበት የብልጽግና ፓርቲ ልዩ መገለጫ ነው!

በብልጽግና የሚመራው መንግስት የህብረተሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች በመለየት አብሮነትን ሊያጎለብት በሚችል መልኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ የህዝብን አቅም በማስተባበር የላቀ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።

ፓርቲው ከለውጡ በኋላ አብሮነትን ፣ መተሳሰብን ፣ እርስ በርስ መረዳዳትን ማዕከል በማድረግ ሰው ተኮር ተግባራትን በማስቀደም በርካታ ሰውኛ ኩነቶችን አከናውኗል፤ እያከናወነም ይገኛል።

በተለይ የአቅመ ደካማዎች ቤት እድሳትና ግንባታ ስራዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስራዎች ናቸው።

በዚህ በጎ ተግባር ለኑሮ የማይመቹ የተጎሳቀሉ ደሳሳ ጎጆዎች ተቃንተው ታድሰዋል፤ በክረምት ዝናቡ ፣ በበጋው ፀሀዩ ሲፈራረቅባቸው የነበሩ ቤተሰቦችም የእፎይታ ህይወትን ጀምረዋል።

ጎዳና ላይ የነበሩ አሰታዋሽ ያጡ አቅመ ደካማ ዜጎቻችን ትላልቅ ህንፃዎች ተገንብተው የቤት ዕድለኞች እንዲሆኑ ተደርጓል።

ተባብረን፣ ተጋግዘን፣ ተደማምጠን ፣ መተሳሰብንና አብሮነትን ከፍ በማድረግ ከሰራን ብልጽግናችን ከደጃፋችን ነው።

እርስ በርስ የመረዳዳት ፣ የመደጋገፍ ፣ አብሮ ማደግና መበልጸግ መልካም እሴቶችን ማጎልበት የብልጽግና ፓርቲ ልዩ መገለጫ ነው።

01/11/2023

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Baadiyyaa Iddoo Omiishaa Hayyoota posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share