13/01/2024
በዓላት እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዲስ አበበ የፖሊቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን ለመወጣት በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
በዩኔስኮ በመመዝገቡ ከኢትዮጵያውያን አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነው የጥምቀት በዓል እንደ ሌሎች አገራዊ በዓላት ሁሉ ወንድማማችነትና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቋል።
ከበዓሉ እሴት የሚፃረሩ ከማንኛውንም እንቅስቃሴዎች በመታቀብ በዓሉ የታለመለትን ሀይማኖታዊ ባህላዊ እንዲሁም የአገርን መልካም ገፅታ የማጉላት ግብ እንዲመታ የተለመደውን አብሮነትን ማንፀባረቅ እንደሚገባም ተገልጿል።
ከፊታችን ጥር 10/2016ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር መንግስት ፀጥታን የማስከበር ሃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ህዝባችንም ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱንና መከባበሩን አስጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እንዲወጣ ምክር ቤቱ ከመልካም ምኞት ጋር መልዕክቱን አስተላልፏል።