30/07/2024
ማሳሰቢያ
ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ስርጭት ላይ የሚገኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ይመለከታል፤
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀፅ 30 መሰረት ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ የብሮድካስት ፈቃድ ሳያገኝ የብሮድካስት አገልግሎት ማሰራጫ መንገዶችን ተጠቅሞ በብሮድካስት አገልግሎት ስራ ላይ መሰማራት የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
በዚሁ መሰረት በአሁኑ ወቅት 43 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3/ለ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ከባለሥልጣኑ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ፈቃድ አውጥተው በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ
1. ኦሲኤን (OCN Tv)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima Tv)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን ( Presence Tv ) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful Tv )
የተሰኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከባለሥልጣኑ ህጋዊ ፈቃድ ሳያወጡ በስርጭት ላይ መሆናቸውን ባደረግነው የክትትል ስራ ማረጋገጥ ችለናል፡፡
በመሆኑም ከላይ ስማችሁ የተጠቀሰ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፈቃድ እንድታወጡ እያሳሰብን ይህን በማታደርጉት ላይ ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም
በመገናኛ ብዙኃን ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁመገናኛብዙኃንለማህበረሰባዊንቃት
#የጥላቻንግግርናሐሰተኛመረጃንበጋራእንከላከል
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን:-
ድረ ገጽ
www.ema.gov.et
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority/
ትዊተር
https://twitter.com/ethmediaauth?lang=en
ሊንክዲን
https://www.linkedin.com/.../ethiopian-media.../...
ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/channel/UC43CTskC37Jr5BkcGKbMghw
ቴሌግራም
https://t.me/EthMediaAuth
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMMSPt78Y/