Mesmer media

Mesmer media Balance the maladminstration.

24/11/2022

፨፨በፈጣሪ እለምናችኋለሁ ሼር_ላይክ ይደረግ፨፨

በምስራቅ ወለጋ ዞን በስቡ ስሬ ወረዳ በስሬ ከተማ የተጠለሉ ወገኖቻችን ወደተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ከሔዱት ውጭ በከተማዋ የተጠለሉ 5970 ሰዎች ይገኛሉ።

እነዚህ በስሬ ከተማ በሸራ ውስጥ ወጥረው የሚኖሩ በብርድና በጸሐይ እየተሰቃዩ የሚገኙ ሲሆን በስሬ ከተማ በሚገኘው የአኗር መስጅድ አጠር ክልል ውስጥ ሸራ ወጥረው የሚኖሩ ከወረዳው ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ያለምንም ጠያቂ ከአንድ አመት በላይ የሆናቸው ናቸው።

ስለሆነም አጠቃላይ ማህበረሰቡን፣ በስሬ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮችንና እርዳታውን ለህዝቡ በቅርበት ሊያደርሱልን የሚችሉትን በሙሉ ኢንተርቪው አድርገን ለእናንተ ይዘናል።

የስሬ መስጅድ ኢማም የሆኑት ሸህ ኡመር ሞላ በጣፋጭ አንደበታቸው ሁሉንም ተጎጂዎች ሰብስበው በቀጥታ መልዕክታቸውን አስተላልፏል።

ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ በወለጋ የሚኖሩ አጠቃላይ ማህበረሰብ አለም ያሉበትን አውቆ፤ በተቻለው አቅም በአካል ተገኝቶ፣ መንግስትም እውነቱን ተገንዝቦ፣ አቅጣጫ ለማስያዝ አጉልዞ ጥያቄ ስራውን በኢፋ በቦታው ጥርት ባለቪድዮ፣ ጥርት ባለድምጽ፣ ይዞላችሁ ቀርቧል።

ይህንን በወለጋ አከባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ብሶት፣ ረሐብ፣ ሰቆቃ፣ ሞትና መፈናቀል ከመነሻው ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ እና በቀጣይ ማንኛውም ባለድርሻ አካላት ለመፍትሄው እንድዘጋጁ የሚያደርግ ይሆናል ብለን እናምናለን‼

ስለሆነም ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ከቀያቸው ለቀው፣ ተሰደው፣ የሚበሉት፣ የሚለብሱት አጥተው፣ በየሜዳው ለሚገኙት ጥርት ባለሁኔታ ሁሉም በተገኙበት፣ የሐይማኖት መሪዎች ባሉበት፣ የሐገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ቀረፃ አድርገን፤ ማገዝ ለሚፈልጉ አካላት ግልፅ አሰራር ይዘን መጥተናል።

እንደዚህ አይነት ግልፅ ለሆነው አሰራር ፍቃደኛ ሆነው ችግሮቻቸውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንድደርስና መንግስትም ትኩረት እንድሰጥ የሚደርስባችሁን መከራና ስቃይ ተቋቁማችሁ ለቀረፃ የተባበራችሁን በሙሉ ክብረት ይስጥልን‼🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ቀረፃው በሁሉም አከባቢዎች ይቀጥላል..
ሙሉ ቪድዎውን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኛሉ።
https://t.me/my_Angergutin_77

10/11/2022

የሰላም ሚኒስትሩ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ለዜጎች “በጣም ትልቅ አደጋ እና ስጋት ፈጥረዋል” አሉ

በኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለዜጎች “በጣም ትልቅ አደጋ እና ስጋት” እየፈጠሩ ያሉት “የታጠቁ ኃይሎች” መሆናቸውን የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ። ችግሩን ለመፍታት የሰላም ሚኒስቴር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ነው። በዛሬው የፓርላማ ውሎ ጥያቄዎችን ካቀረቡ የቋሚ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሞጋ አባቡልጉ፤ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ ኢሉባቡር እና ሌሎችም አካባቢዎች የታጠቁ ኃይሎች “በስፋት እየተንቀሳቀሱ” መሆኑን አንስተዋል።

“ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያየ ነው። የሰው ህይወት እየጠፋ ነው። ንብረት እየጠፋ ነው። ከፍተኛ የሆነ ግጭት ነው ያለው። የብሔር ግጭት አለ። ሌሎችም ችግሮች እየታዩ ስለሆነ፤ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና ህዝቡ በሰላም እንዲኖር የሰላም ሚኒስቴር ድርሻ ምን ይሆናል?” ሲሉ የፓርላማ አባሉ ጥያቄ አቅርበዋል። የሰላም ሚኒስቴር ይህን ችግር ለመፍታት ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር የሚሰራቸው ስራዎችን የመስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች እንዲያስረዱ በአቶ ሞጋ ተጠይቀዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ በ“ሸኔ” እና በሀገሪቱ ነፍጥ አንግበው በሚንቀሳቀሱ ሌሎች ታጣቂዎች ምክንያት “በዜጎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች አሉ” ሲሉ የጠያቂውን ገለጻ አጠናክረዋል። ታጣቂዎቹ በምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ አካባቢዎች በዋነኛነት እንደሚንቀሳቀሱ የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ “እነኚህ አካላት ለዜጎች ደህንነት ትልቅ ስጋት ናቸው” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት አስረድተዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/8525/

28/10/2022

፨፨፨፨፨፨በአስቸኳይ ሼር ይደረግ፨፨፨፨፨፨፨
በምስራቅ ወለጋ ዞን በ #ጉቴ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ማህበረሰብ በወረዳው ከአቅሜ በላይ ነው‼ እባካችሁን እራሳችሁን አትርፉ‼ ሲል በወረዳው አስተዳደር የተላለፈውን መልእክት ተከትሎ በርካታ በወረዳው የሚገኙ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ድረሱልን ሲሉ ተማፀኑ‼

ጥቅምት 17-2015ዓ.ም። #ጉቴ ወረዳ

የጉቴ ወረዳ አስተዳደር በሰሞኑ በወረዳው ከሚንቀሳቀሱት የኦነግ ሸኔ አሸባሪ የታጠቁ ሐይሎች እና በወረዳው ካለው የመንግስት የፀጥታ አካል አንፃር
"ከአቅሜ በላይ ነው!" ውጡ ሲሉ ኗሪዎች የደረሰ አዝመራቸውን ትተው መውጣታቸውን ኗሪዎች ለአጉልዞ ጥያቄ ገለፁ።

ቦታው ከነቀምቴ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የ #ጉቴ ወረዳ ትገኛለች። ቀኑ ደግሞ ዛሬ ጥቅምት 17-2015ዓ.ም ነው። ከባለፈው አመት የተረፉ አማራዎች ነበሩ። እነሱም ዛሬ ውጡ ተባልን፥ ይለነናል! ከኗሪዎቹ አንደበት!!!

በምስራቅ ወለጋ ዞን ስር የምትገኝ ጉቴ ወረዳ ውስጥ የተወሰኑ የአማራ ተወላጆች ነበሩ፤ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ የለፉበትን ትተው እንዲወጡ ተደርገዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳደር እናታቸው ታመው ወደ አድስ አበባ በመሔዳቸው በምክትል አስተዳደሩ አቶ ኤባ ከረዩ አማካኝነት መልእክቱ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።

እንድወጡ ከተደረጉት የወረዳው ቀበሌዎች መካከል ሰፈሮቹ ስም፦
1- ሞኮፍ
2- ባንዲራ
3- ጣጤሳ ይባላሉ።
ይሄ ህዝብ የዛሬ አመት ልክ በዚህ ወር ቤት ንብረቱን ጥሎ ወጥቶ ጉቴ ወረዳ መጠለያ ውስጥ ለአስር ወር ሰፍሮ ነበር።
ከዛ ቡሃላ እየተረዳ የነበረው በዞኑ ብቻ ስለነበረ፥ ከዚህ ቡሀላ መርዳት ስለ ማንችል መጠለያውን ለቃችሁ ውጡ ተባሉ። በመጨረሻም ወደ ደብረ ብርሀን የሄደም፤ ወደዛ ገባ።
"ብንሞትም እንሙት" ብለው ካላ በጠቀስኳቸው ቦታዎች ገብተው እርሻቸውን አረሱ።
እሄው አሁን ልክ መሰብሰብያ ሰአት ላይ በወረዳው ትዛዝ ውጡ ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ወጥተዋል።
የመንግሥት ያለህ⁉ ሲሉ እየተማፀኑ ነው‼
"ኧረ ፍትህህህህህህ ለአማራ ህዝብ!!!"
😢😢😢😢😢
አጉልዞ

27/10/2022

ሰበር ዜና!

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሀሮ ሀቦ አካባቢ በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን አሰማርቶ በአማራ ገበሬዎች እና ሚሊሾች ላይ ተኩስ ከፈተ።

ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ወለጋን ጨምሮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ማንነታቸውን እንደ ወንጀል በመቁጠር የአማራ ተወላጆችን በጅምላ እየፈጀ፣ እያፈናቀለ፣ እየዘረፈ እና እያሳደደ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን በማሰማራት በሀሮ ሀቦ አካባቢ ተኩስ መክፈቱ ተሰምቷል።

የሽብር ቡድኑ የቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም የተለመደ የወረራ ጥቃቱን የጀመረው ጥቅምት 16/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ራሳቸውን፣ህጻናትንና ሴቶችን ከጭፍጨፋ ለመታደግ ጥረት እያደፈጉ ያሉ ገበሬዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በጃርቴ እና በጃርዴጋ ከተሞች መካከል በሚገኘው በሀሮ ሀቦ ቀበሌ ተኩስ ስለመኖሩ ለማወቅ ተችሏል።

በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ካሉት ከ32 ቀበሌዎች መካከል:_
ጃርዴጋ ከተማ፣
ቂልጡ ጬካ እና
ደርጌ ኮቲቻ ብቻ ናቸው በሽብር ቡድኑ ቁጥጥር ስር ያልገቡት።

ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል አሚማ ያነጋገረው አመራር መስከረም 12/2015 በኦነግ ሸኔ ወረራ ስር የነበረው የጃርቴ ከተማ ተመልሶ በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከሆነ መሰንበቱን አስታውቋል።

በጃርዴጋ በግምት በ7 ኪ/ሜትር ርቀት ባለው በሀሮ ሀቦ የተጀመረውን የወረራ ጥቃት ለመቀልበስም ከአካባቢው ሚሊሾች ጋር በመተባበር በተለይም ከርቀት ሽፋን በመስጠት ረገድ እያገዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ነገር ግን ኋላቀር መሳሪያ የያዘ ገበሬ እና ሚሊሻ ሚስቱ፣ልጆቹ እና ቤተሰቦቹ በጨካኞች እንዳይጨፈጨፉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲታገል ደመወዝ ተከፋይ ልዩ ኃይሎቹ ሚናቸው ሽፋን በመስጠት ላይ መወሰኑ አሳዛኝ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

"ውረዱ እንውረድ" ተባብለው የመጡ ይመስል የኦሮሚያ የልዩ ኃይል አባላት ከጃርቴ ወደ ጃርዴጋ ከማቅናታቸው በተወሰነ የሰዓት ልዩነት ተኩስ መጀመሩ እንደገረማቸው ነው ነዋሪዎች የተናገሩት።

አሚማ አመሻሹን ያጣራው መረጃ እንዳመለከተው በተኩሱ መሀመድ ተሾመ የተባለ አርሶ አደር እግሩ ላይ ሲቆስል በአንጻሩ ወረራ ከፈጸመው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን 3 አባላቱ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸው እና ቡድኑም እየሸሸ ስለመሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ አሚማ

26/10/2022

በኦሮሞ ነጻነት ጦር ታጣቂዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት በርካቶች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሽዋ ዞን ተገደው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በተገኙበት የታጣቂዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ።

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ ሸዋ በዞን በምትገኘው ጮቢ ወረዳ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎች እያስመረቀ ሳለ ነበር የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ የተነገረው።

ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እንደሰማው የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ሰላማዊ ዜጎች በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ አስገድዶ የምርቃት ስነ-ስርዓቱ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው።

በዚህ ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን እና የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ጨምሮ እስከ 70 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ120 ያላነሱ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ታጣቂ ቡድኑ ላይ ያነጣጠር የአየር ጥቃቶችን በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ሲፈጽም ቆይቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ትናንት በትዊተር ገጻቸው ላይ ከጥቅምት 10/2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ቢያንስ 6 የሰው አልባ አውሮፕለን ጥቃቶች ተፈጽመዋል ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሜታ ወልቂጤ እና ጮቢ ወረዳዎች የተገደሉ 'ሰላማዊ ሰዎች ከ150 በላይ ናቸው' ይላሉ።

ኦዳ ተርቢ በጮቢ ጨምሮ 150 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ይበሉ እንጂ በወረዳው የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው የታጣቂ ቡድኑ የምርቃት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ሳለ ስለመሆኑም ይሁን በእነዚህ የአየር ጥቃቶች የተገደሉ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ስለመኖራቸው ያሉት ነገር የለም።

የአየር ጥቃቶቹን በተመለከተ ቢቢሲ የጮቢ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ የአካባቢው ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ መረጃ ካለው ተጠይቆ ተፈጽመዋል የተባሉ የአየር ጥቃቶችን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጿል። አጉልዞ

17/10/2022

በጃርቴ እስር ቤት፣ ማንነት ያስከፈለው
መስዋዕትነት!

ይህ በእጅጉ የተላላጠ እና የቆሰለ የውስጥ እግር፣ በተለያዩ ጊዜያት በግፍ ታስሮ ብዙ ግፍ የደረሰበት፣ ቤተሰቦቹ እንኳ በአግባቡ ሄደው ለመጠየቅ በማይችሉበት፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአካባቢው መስተዳድር በማንነታቸው እየተለዩ ያለፍርድ የታሰሩ ወገኖች እንዳይጠየቁ ከህግ እና ከአሰራር ውጭ የሚከለክልበት፣ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚለው መንግስት ሸኔ የሚለው የሽብር ቡድንም ከበርካታ የመንግስት አካላት ጋር በመናበብ መንገድ የሚዘጋበትና ከአንደኛው ወደ ሌላኛው አካባቢ ለመንቀሳቀስ የሚሞክር የሚገደልበት፣የሚታገትበት፣ ገንዘብ የሚቀጣበትና አድራሻው የሚጠፋበት ሁኔታ በተለመደበት በሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ነዋሪ የሆነ ወንድማችን ነው።

በማንነቱ አማራ ነው፤ ያለፍትህ የታሰረውና ግፍ የተፈጸመበትም ውስጣቸው ኦነግ ሸኔ እና የቡድኑ ተልዕኮ አስፈጻሚ በሆኑ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮች ነው።

አሁንም ያለበት አካባቢ የተከበበ እና አስቸጋሪ ስለሆነ ለደህንነቱ ሲባል አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ስሙን ለጊዜው ለመጥቀስ አልፈለገም።

ይህ እስረኛ በብዛት አማራዎች ከሚኖሩበት ጃርዴጋ ከተማ የነቁ፣ግፍን የሚጠየፉ፣ ለሸኔ የማይበገሩ፣ ለምን ብለው የሚጠይቁ፣ በአማራ ላይ በተከታታይ እየተፈጸመ ያለውን የሽብር የወንጀል ድርጊት የሚያወግዙ እና እንዲቆምም የሚጠይቁ በመሆናቸው ብቻ በወረዳው ቢሮ ላይ በተቀመጠው የኦነግ ሸኔ ክንፍ በኃይል ታፍነው ወደ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርቴ ከተማ ተወስደው ከታሰሩ በርካታ ወራትን ካስቆጠሩት መካከል አንዱ ነው።

መስከረም 12/2015 በጃርቴ ከተማ አያሌ ከላይ እስከ ታች ያሉ የመንግስት አካላት በስንቅ፣ በትጥቅ እና በመረጃ የሚደግፉት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ይፋዊ የወረራ ጦርነት በመክፈት ከ100 በላይ የአማራ አባዎራዎችን ከእነ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው በድምሩ ከ500 በላይ የሚሆኑ አማራዎችን ሲጨፈጭፍ፣ ሲያርድ እና ሲያቃጥል መዋሉን ከዘር ተኮር ጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መግለጻቸው ይታወሳል።

ከዚህ የጭካኔ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በተጨማሪ የሽብር ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው በሚሰጣቸው ተልዕኮ መሰረት ቢሮ ውስጥ ባሉ አጋሮቹ ከወራት በፊት ያለፍትህ ቢያንስ ከ28 በላይ የሚሆኑ የተመረጡ አማራዎች ታስረው በሚገኙበት ፖሊስ ጣቢያ ላይ ነው።

የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላት በጃርቴ ፖሊስ ጣቢያ የእስረኞችን ክፍል በር እንደሰበሩ "እዚህ ውስጥ አማራ አለ ወይ?" የሚል ጥያቄ በማንሳት እና እርምጃ በመውሰድ ነው።

እስረኞች በአንድ ላይ "አማራ የለም" የሚል ምላሽ" የሰጡ ቢሆንም እየጠየቁ መረሸን ስለጀመሩ በዚህ እጅግ አስጨናቂ፣ በአንድ በኩል እሳት በሌላ በኩል የቡድን መሳሪያ በሚያጓራበት፣ የጥይት አረር በሚዘንብበት፣ የንጹሃን ደም እየፈሰሰ ጃርቴ በጨቀዬችበት ፈታኝ ሰዓት ላይ ከሶስት እስከ አራት የሚደርሱ የግፍ እስረኞች ቆመን ከምንታረድ፣ ከምንረሸን ወይም በእሳት ከምንቃጠል እየሸሸን እንሙት፣ እግዜአብሔርም ይረዳናል በማለት መሮጥን መረጡ።

በባዶ እግራቸው ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ከኋላቸው ከሚተኮስባቸው የጥይት አረር በፈጣሪ ፍቃድ አምልጠው ስለነበረው ጭፍጨፋ እና በእስር ላይ ስለቀሩትና ስለተረሸኑት ጓደኞቻቸው ወሬ ለመንገር በቅተዋል።

ከመካከላቸው የአንዱ እግር በዚሁ መልኩ ተላልጦ፤ ቆዳው ተገፎ እና ቆስሎ ይስተዋላል፤ህመሙ አሳዛኝና የከፋ ነው።

የህክምና ተቋምና ባለሙያ በሌለበት በሽብር ቡድኑና ከቡድኑ ጋር አብረው እየሰሩ ባሉ በኦሮሚያ ክልል የሆሮ ጉድሩ ወለጋ/የሻምቡ አመራሮችና የልዩ ኃይል አባላት ጥርስ በተነከሰበት፣ ሁለት ጊዜ ወረራ ተፈጽሞ የብዙዎች ደም ፈሶ በተቀለበሰበት፣ ሶስተኛ ዙር ወረራ በተደገሰበትና ቀን እየተቆጠረለት በሚገኘው ጃርዴጋ አሁንም ኑሮ ጨለማ ነው፤ የመውጫ እና የመግቢያ በሩ የታጠረ ነው፤ መብራት ሆንተብሎ እንዲጠፋ የተደረገበት፣ መዳን የሚችሉ ቁስለኞች በህክምና እጦት የሚሞቱበት፣ እናቶች፣ አዛውንቶችና ህጻናት በህክምና እጦት የሚሞቱበትና ውሃ ሊቀዱ እና እንጨት ሊለቅሙ ከቤታቸው ሲወጡና በቤታቸው ጓሮ ሲታዩ በጭካኔ የሚገደሉበት ጃርዴጋ አሁንም በጭንቅ ላይ ነው።

በጃርዴጋ አሁን ላይ በስፋት አማራዎች ነው የሚኖሩ።
የኦሮሞ ተወላጆችን የሽብር ቡድኑ በአጭር ጊዜ አማራዎችን ጨፍጭፈን/አጽድተን/ ትመለሳላችሁ በሚል እንዲወጡ እና ወደ ሻምቡ እንዲሄዱ ማድረጉ፣ ከ15 ሽህ በላይ ወራሪ ጦር አሰማርቶ መስከረም 12 እና 14/2015 የፈጸመው ጥቃት በመክሸፉ እንዳሰበው ወዲያውኑ እንዲወጡ ያደረጋቸውን ወገኖች ወደ ጃርዴጋ ለመመለስ አልቻለም፤ የጭፍጨፋ እቅዱ በፈጣሪ ድጋፍ በጥቂት እና ኋላቀር መሳሪያ በብዙዎች መስዋዕትነት መመከቱን ካስተዋለ በኋላ ሌላ ሶስተኛ ዙር የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ከሻምቡ ዞንና ከከተማዋ በርካታ አመራሮች ጋር መምከሩ እና ራሱ "በአጭር ጊዜ ጃርዴጋን አጽድቼ እመልሳችኋለሁ" ሲል ቃል የገባላቸውን የኦሮሞ ተወላጆችንም "አማራ አፈናቀለን በሉ" በማለት በሚዲያ እንዲዘምቱ እያደረገ ነው፣ ከፍተኛ ኃይል ከቄለም ወለጋ በሰቀላ/ኦዳቡልቅ በኩል እያስጠጋ ስለመሆኑና በከበባ ላይ ያሉ አማራዎችም የድረሱልን ጥሪ በተደጋጋሚ እያቀረቡ መሆኑን አሚማ ለማስታወስ ይወዳል።

በጃርዴጋ መስከረም 12 እና 14/2015 ከተፈጸመው የወረራ ጥቃት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጥቅምት 4/2015 ድረስ የደረሰላቸው አንድም የመንግስት ኃይል የለም::
ከአጉልዞ ጥያቄ

15/10/2022

በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርቴ ከተማ መስከረም 12/2015 የተፈጸመውን የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የተባባሪዎቹ የወረራ ጦርነትን ተከትሎ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ አማራዎች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ በጃርቴ ከተማ መስከረም 12/2015 የተፈጸመውን የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የተባባሪዎቹ የወረራ ጦርነትን ተከትሎ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ አማራዎች በግፍ መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ እስረኞች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

አሚማ ያነጋገራቸው ከአሰቃቂ የጃርቴ የእስር ቤት ግድያ እና ቃጠሎ የተረፉ ጥቂት አማራዎችና ቤተሰቦች እንደገለጹት በጃርቴ እስር ቤት መስከረም 12/2015 ከተፈጸመው የኦነግ ሸኔ እና የተባባሪዎቹ ጥቃት ሮጠው ለማምለጥ የቻሉት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

ከ28 በላይ የሚሆኑ አማራዎች በማንነታቸው ብቻ ከጃርዴጋ በመስተዳድር አካላት ትዕዛዝ በጸጥታ አካላት ድንገት እየታፈኑ ወደ ጃርቴ ተወስደው ታስረው እንደነበር አውስተዋል።

በአብዛኛው እስሩ የጠፉ ከብቶችን ሲፈልጉ የነበሩ ወንድማማቾች አቶ አለም ኢብራሂም (ይብሬ) እና ቃሲም ኢብራሂም የካቲት 5/2014 በአሸባሪው ሸኔ ጫካ ላይ ተይዘው በአሰቃቂ ሁኔታ በእሳት እየተቃጠሉ መገደላቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

በወቅቱ የአቶ ቃሲም ኢብራሂምን አስከሬን እንኳ እንዳይገኝ ማድረጋቸው የሚዘነጋ አይደለም።

እየተቃጠለ ያለ አስከሬንን ለማንሳት እና በወጉ ስርዓተ ቀብር ለመፈጸም ይቻል ዘንድ ሄዶ የሽብር ቡድኑን መታገል ቢቀር እንኳ አስከሬን አፋልጉን በሚል የሟች ቤተሰቦች ለጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ፣ ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በወረዳው ለነበረው ለፌደራል ፖሊስ የጠየቁ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም።

የሟች ቤተሰቦችም ተሰባስበው አስከሬን በእሳት የተቃጠለ የሟች አቶ አለም ኢብራሂምን አጽም ለማንሳት ባቀኑበት በበርካታ የመንግስት አካላት ጭምር በስንቅ፣በትጥቅና በመረጃ የሚደገፈው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን የቡድን መሳሪያ ጠምዶ በመተኮሱ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

በዚህ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት አስከሬን ለማንሳት ሲባል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሸኔዎችን በሀሰት ንጹሃን ገድላችኋል በሚል ቢሮ ላይ የተቀመጠው ሸኔ በእነ አቶ አለም ኢብራሂም እና ቃሲም ኢብራሂም ሞት በማዘን ለቅሶ ቤት የተቀመጡ የሟች ቤተሰቦችንና ወደ ሀዘን ቤት የሚሄዱትን መንገድ ላይ ጠብቆ በመቆዬት፣ አሉ የሚባሉ፣ የሚፈሩ እና የሚከበሩ የአማራ ልጆችን እያሳፈነ ማሰሩ ይታወሳል።

ከእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ጭምር ከታፈኑት እና ያለጠያቂ ቤተሰብ በጃርቴ እስር ላይ ከነበሩት ከ28 በላይ አማራዎች መካከልም ጥቂቶች ሮጠው አምልጠዋል።

(1) ከመስከረም 12/2015ቱ የግፍ ግድያ ሮጠው ካመለጡት መካከልም:_

1_ሰይድ አደም፣
2_መከረ አህመድ፣_የእነ አለም ኢብራሂምን አስከሬን ለማንሳት ሄደሃል በሚል ባልነበረበት በግፍ የታሰረ_በወቅቱ የጃርዴጋ የሚሊሾች አስተባባሪ ነበር።

3_ አደም አለም ከእነ ወንድሙ፣ (የሟች የአቶ አለም ኢብራሂም ልጆች ናቸው።)
4_ወጣት ያህያ አሰፋ፣ (የሟች የእነ አቶ አለም እና ቃሲም ኢብራሂም ቤተሰብ) እና
5_ሀምዛ ሰይድ የተባሉ እስረኞች ይገኙበታል።

(2) በእስር ላይ እያሉ በግፍ በጥይት፣ በእሳትና በስለት ጭምር ከተገደሉት መካከልም:_

1) ሰይድ ይሃ_ አለ የሚባል ጀግና እና ደፋር ተናጋሪ፣ ህዝብ የቆመ ተቆርቋሪ ነበር ይላሉ ምንጮች።

አማቹ አቶ ቃሲም ኢብራሂም ከእነ ወንድሙ አለም ኢብራሂም ጋር በአሰቃቂ መልኩ የተገደለበት ከመሆኑም በላይ በግፍ አይፈሬዎች ከአንድ ወር በላይ ሲሳደድ ቆይቷል።

ይህ ብቻ አይደለም። ይልቁንስ ከማል ይሃ የተባለ ወንድሙንና ሁለት የ7 እና የ10 ዓመት ሴት ልጆቹን አሰሩበት።

በተጨማሪም ልጆቹ እና መላ ቤተሰቦቹ እንኳ የመካዘን እህል አውጥተው እንዳይሸጡ እና እንዳይበሉ 300 ኩንታል እህሉ ታገደበት።

የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ እና የሆሮ ጉድሩ ዞን አመራሮች አቶ ሰይድ ይሃ እጅ ካልሰጠ ህጻናት ልጆቹንና ወንድሙን አንለቅም በማለታቸው አንዳች እንኳ ወንጀል የሌለበት ኦነግ ሸኔም ሆነ የመንግስት አካላት እንዲሁ የሚፈሩት ጀግናው ሰይድ ይሃ ስለቤተሰቦቹ ሲል እጅ ለመስጠት ተገደደ።

አቶ ሰይድ እጅ ከሰጠ በኋላ አሳሪው እና ግፈኛው መስተዳድር ምንም እንኳ ህጻን ልጆቹን ቢለቅለትም ወንድሙን ከማል ይሃን ለ15 ቀናት ያህል በግፍ አስረውበታል።

2) ኑሬ አህመድ፣_የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን የውስጥ ባንዳ ከውጭ ጠላት ጋር እየተመሳጠረ እና እየተደገፈ አማራን ብሎም አጠቃላይ ኢትዮጵያን ማጎሳቆል የለበትም በሚል በ2013 ዓ/ም በመከላከያ ሰራዊት ተመዝግቦ ስልጠና ከወሰደ በኋላ በከሚሴ በኩል በነበረው የተኩስ ልውውጥ ቆስሎ በመከላከያ በጦረታ የወጣ የተገለለ ነበር፤ ነገር ግን የቢሮ ኦነግ ሸኔዎቹ ገና ለገና ልምድ ስላለው ሊያጠቃን ይችላል በሚል ሰበበ ባሰሩበት የተገደለ ነው።

3) ወርቁ ይመር_በእድሜያቸው ትልቅ ሰው ሲሆኑ የግል ታጣቂ ሆነው በሚሊሻነት ሲሰሩ ነበር፤ በጃርዴጋ ኬላበላይ ከሚጠብቁበት ታፍነው ወደ ጃርቴ ተወስደው በታሰሩበት የተገደሉ ናቸው።

4) መሀመድ ወርቁ_ሚሊሻ ሲሆን
በእነ አለም እና ቃሲም ኢብራሂም አሰቃቂ ግድያ በማዘን ለቅሶ ላይ ለመገኘት ከሀርቡ ነጋሶ ቀበሌ ወደ ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ ሀምዛ ሰይድ ከተባለ ቤተሰባቸው ጋር ሲሄዱ መንገድ ላይ የተያዙ ናቸው።

አቶ መሀመድ ወርቁ በተመሳሳይ በጃርቴ በእስር ላይ እያለ ተገድሏል።

የሟች የአቶ አለም ኢብራሂም እና
የቃሲም ኢብራሂም ቤተሰቦችም ሀዘኑ ድርብርብ እና አሳዛኝ ሆኖባቸዋል።

የተገደሉ፣ የታሰሩ እና እየተሳደዱ የሚገኙም እነሱ ናቸው።

በሆሮ ጉድሩ ዞን እና በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮችና በሸኔዎች እየተሳደዱ ከሚገኙት የሟች አቶ አለም ኢብራሂም እና ቃሲም ኢብራሂም ቤተሰቦች መካከልም:_

1) ተመቸው ቃሲም፣
2) መሀመድ ቃሲም፣
3) ኢብራሂም ቃሲም፣
4) በለጠ አህመድ፣
5) ሞላ የስጋት፣
6) ኢብራሂም ገዜ፣
7) ሰይድ ወርቁ (የሟች መሀመድ ወርቁ ወንድም) እና ሌሎችም ይገኙበታል።

የወለጋን አማራ እውቅና ያልሰጠ ሀገራዊ ምክክር በሰው ዘር ላይ መቀልድ ማለት ነው።
14/10/2022

የወለጋን አማራ እውቅና ያልሰጠ ሀገራዊ ምክክር በሰው ዘር ላይ መቀልድ ማለት ነው።

13/10/2022

ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን አንገብጋቢ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን እንዳለበት ተገለጸ

(ዜና ፓርላማ)፤ ጥቅምት 1፣ 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስር የሰደዱ አንገብጋቢ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን እንዳለበት እና ሕዝቡም በየደረጃው ሊሳተፍበት እንደሚገባ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ባቀረበው ስትራቴጂክ ዕቅድ እና አበይት የስራ ተግባራት ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሆኖ ችግሮችን በየደረጃው ለመፍታት እንዲችል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው በውይይት መድረኩ ተነስቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሠ ጫፎ፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የሀገሪቱን ቁልፍ ችግሮች ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት በመሆኑ በፍጥነት ወደ ሥራ መግባት እናዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ፣ የጋራ ማንነት ለመገንባት እና ቅቡልነት ያለው ሀገረ-መንግስት እንዲኖር ሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ሚና እንዳለው የተከበሩ አቶ ታገሠ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑን ስትራቴጂክ ዕቅድ እና በቀጣይ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ባቀረቡበት ወቅት የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ተዋናይ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

አካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን የመንግስት ድጋፍ፣ ጠንካራ አመራርነት መስጠት፣ የውጭ ሀገራትን ጣልቃ-ገብነት መከላከል እና ሕዝባዊ ተሣትፎ እንዲኖር ማመቻቸት አይነተኛ የመፍትሄ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን ገዥው ፓርቲ ብልጽግና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ በምክክሩ ጥራትና ፍጥነት፣ አሳታፊነትና ውጤታማነት፣ እንዲሁም የኮሚሽኑና የሌሎች አካላት ሚና፣ በአካታችነትና በብቃት፣ በሀገር በቀልና በውጭ ሀገራት ድጋፍ ሰጭነት መካከል ሚዛናዊ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ይህ ሀገር ለማሻገር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ሀገራዊ ምክክር እንዳይካሄድ እንቅፋት የሚፈጥሩ ሀይሎች ካሉ ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ አስፈላጊ ከሆነም መንግስት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ እንደሆነም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ አደም ፋራህ አስገንዝበዋል፡፡

የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች፤ የዜጎችን አንኳር ችግርች በዘላቂነት ለመፍታት እምነት የተጣለበት ይህ ሀገራዊ ምክክር ስኬታማ እንዲሆን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የገጠሟትን የተወሳሰቡ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ሀገራዊ ምክክሩ አይነተኛ መሳሪያ እና አቅጣጫ ቀያሪ እንደሆነ ያመኑበት የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች፤ ሕዝቡ እንዲወያይባቸው በሚቀረጹ አጀንዳዎች ላይ በቂ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የክልሎች አስተዋፅኦ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ሀገር ለማሻገር የሚያስችሉ ሀሳቦችን በማቅረብ ረገድ በቂ ተሳትፎ የሚያደርጉ እንደሆነም ከፍተኛ አመራሮቹ በውይይት መድረኩ አንስተዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን ለሕዝቡ የሀሳብ ግልጸኝነት እና በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ሁለንተናዊ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የገለጹት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ፤ ሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ

13/10/2022

፨፨፨፨፨፨፨በአስቸኳይ ሼር_ላይክ ይደረግ፨፨፨፨፨፨
ጥቅምት 03-2015ዓ.ም። #ቱሉጋና

በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን በአቤደንጎሮ ወረዳ በቱሉጋና ከተማ በዛሬው እለት የኦሮሚያ ልዩ ሐይል የለበሱ የታጠቁ ሐይሎች በከተማዋ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሽገው፣ ዘግተው ጭነው ለመውጣት ሲሉ በህዝቡ እርብርቦሽ ለማትረፍ ተችሏል።

በቅርቡ በቱሉጋና ከተማ፣ በአንገር ጉትን ከተማና በተለያዩ አጎራባች አከባቢዎች በመንግሥት እውቅና የተሰጣቸው የመዳሎ ጀግኖች ወደቦታው ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን አንዳንድ የሸኔ ናፉቂ ሐይሎች ከፍተኛ ሽብር በመፍጠር ለወረዳና ለዞን እንደተወረሩ በማስመሰል ሪፖርት አድርገው ነበር።

በዚህም መሠረት በቱሉጋና ከተማ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ አንዳንድ ከሸኔ ጋር በግልጽ የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ማስተማር የማይችሉና ሌሎች በተለያዩ ዘርፍ የተመደቡም ተመሳሳይ ቅሬታ በማቅረባቸው ከንቲባውን ጨምሮ ሌሎችም ወደተለያዩ ቦታዎች በመሰወር ነገሩን መልኩን ለመቀየር ሞክረው ሳይሳካ ከሽፏል።

በመጨረሻም በዛሬው እለት የቱሉጋና ከተማ ኗሪዎች ወደስራ በወጡበት አሳቻ ሰዓት የኦሮሚያ ልዩ ሐይል የደንብ ልብስ በመልበስ አከባቢው ረብሻ የተነሳ በማስመሰል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሰራተኞች እና የህዝቡን ገንዘብ ጭኖ ለመውጣት ሲሞክሩ በህዝቡ እርብርቦሽ ለማስቆም ተችሏል።
የበለጠ
አጉልዞ

፨፨፨፨፨ሸዋ ሳይራብ፤ እናንተም አትራቡም!!፨፨ኢትዮጵያዊነት በተግባር!!! !ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ምአሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳርበዛሬው ቀን ከወለጋ ከሞት ተርፈው ደብረብርሃን ከተማ ቻይና ካ...
11/10/2022

፨፨፨፨፨ሸዋ ሳይራብ፤ እናንተም አትራቡም!!፨፨
ኢትዮጵያዊነት በተግባር!!!

!

ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር

በዛሬው ቀን ከወለጋ ከሞት ተርፈው ደብረብርሃን ከተማ ቻይና ካምፕ ለሚገኙ ወገኖቻችን የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን
ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል።
✅-100 እስፖንጂ ፍራሽ
✅-100 ብርድልብስ
✅- 18 ኩንታል መኮረኒ
✅-ሩዝ እና ዘይት ድጋፍ ተደርጓል።

ለተደረገው ድጋፍ የሲቪል ማህበረሰቦች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ በቦታው ተገኝተው ከልብ አመስግነዋል በተመሳሳይ የደብረብርሃን ከተማ የምግብ ዋስትና ሀላፊ አቶ ግርማ ለተደረገው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል።

ይሁን እና የተፈናቃዮች ቁጥር በደብረብርሃን ከተማ ብቻ 6 መጠለያ ጣቢያ ያለ ሲሆን እስከ 23,000 /ሀያ ሶስት ሺ / ተፈናቃዮች ያሉ ሱሆን በአጠቃላይ በሰሜን ሸዋ ዞን እስከ 80,000 /ሰማንያ ሺ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ይሄንን ችግር በማየት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ወገኖች በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ በመደገፍ ወገንተኝነታችሁን ታስመሰክሩ ዘንድ የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ያሳስባል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000377415891 "ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት" ብሎ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

ስልክ ☎️ +251116661086
0996856611

"የወሎን መልካም እሴት እናስቀጥላለን"

የ ወሎ ቤተ አምሐራ - Wello Bete Amhara የልማት እና በጎ አድራጎት ድርጅት
የዘገበው አሻራ ሚድያ ነው።
ከ አጉልዞ

11/10/2022

ላብአደር አቅራቢው…… #ወሎ

ሰያ ጋር ከጦርነቱ በፊት ስለ ወሎ ቁጭ ብለን እንደ ወንድም ተወያየን፣ አወጋን። መቼም የማልረሳቸውን በሳል ንግግሮቹን እንሆ እንዳመነዠኩ አለሁ። «ከሌሎቹ የአማራ ክልል ቀጠናዎች አንፃር የወሎ ሁኔታ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ወሎ እንደተለመደው ወዛደር አቅራቢ ሆኖ ይቀጥላል።» አለኝ። እያዘነ።

ወሎ ወዛደር እያቀረበ እንዲኖር የተደረገው ለአረብ አገር ብቻ እንዳይመስልህ። ለጎጃምና ለጎንደር አጨዳ፣ ለሽዋ ፋብሪካ፣ ለደቡብ ቡና ለቃሚ ወዘተ ሆኖ ነው።

አሁን ጦርነቱ የወሎን ህዝብ አዳክሞታል። «ወሎ ፈርጣጩ!» እያሉ በሁሉም በር ዘግተውበታል።

አንድ ገበሬ ብቻ በሺዎችን ላብአደር የሚፈልገው የጎንደር በርሃ ጭንቅ ላይ ነው።

ጦርነት ቀርቶ ልማት ካለ ግዴለም የወሎ ወጣት እንደለመደው ሄዶ ምዕራብ ጎንደርን ያቅና የእነ ሀብታሙ አያሌውን የአዛኝ ቅቤ አንጓች ቅስቀሳ እርሱት‼
@አብዱልጀሊል

የወሎ ድምፅ Voice Of Wollo
https://www.facebook.com/Voiceofwollo2019/
https://t.me/VoiceOfWollo

10/10/2022

በወለጋ የኦሮሞ ብሔረሰብ የሠላም ጥሪ መልእክት!!!

መስከረም 29-2015ዓ.ም። ስለሠላም እንስበክ!!

ይነበብ....!!!
በኢትዮጵያ ሐገራችን ሠላም ቅንጦት ከሆነ ሰነባብቷል። አብረን ተወልደን፣ አድገን፣ ቦርቀን፣ ተምረን፣ በልተን፣ ጠጥተን ከሶስት አስርት አመታት በላይ በጋራ፣ በፍቅር፣ በሠላም የኖረነውን ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን አጥተናል።

እኛ በወለጋ የምንኖር የኦሮሞ ተወላጆች በተፈጠረው ሐገራዊና ክልላዊ ቀውስ ምክንያት መማር አልቻልንም፤ ወጥተን መግባት አልቻልንም። ነግደን ማትረፍ አልቻልንም። መታከም አልቻልንም። በቃ በጥቅሉ በሰው ልጆች የመኖሪያ ክልል ውስጥ ሳይሆን፤ በሆነ በታጠረ ቦታ ውስጥ የምንገኝ ከሆንን ቆየን።

እኛ ከሰላሳ አመት በላይ በፍቅር ከኖርነው በላይ አሁን ላይ የተፈጠረው ቀውስ ስለአማራ ወንድሞቻችን መበደል፣ መጨቆን በዚህ የተወሰነ አመታት ውስጥ ለመረዳት ችለናል።

ሆኖም ግን ስለኛ መገፋት፣ መበደል፣ የጅምላ ፍረጃና ኩነና የማዎራ ማን ይሆን?! ሲሉ ለአጉልዞ ጥያቄ ይገልጻሉ!!

በሆነ አከባቢ በተፈጠረው ቀውስ ላይ ለማረጋጋት የሚሔደው ሐይል ሌላ ጥፋት ይዞ ይመለሳል!! እሳትን በእሳት በሚል የሞኝ አባባል ጥላቻን በፍቅር የሚቀይር አጣን!!

ከኦሮሞም አጥፊ አለ። ከአማራም እንደዚሁ። ታድያ ከሁሉም ያለው ጎራ ጎራ ይዞ ስንት ሚስኪን ወንድሞቻችንን አጣን። እኛም ስናጠፋ ተው! ማለት ነው የሚበጀው!! ስማቸው የአማራ የሆኑ ደግሞ አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ በዚህ አጋጣሚ ለመክበር የሰው ንብረት ይዘርፋሉ! ያቃጥላሉ! ምንም ያልታጠቁ ሰዎችን በሆያሆዬ ይገላሉ።

ከኦነግ ሸኔም እንደዚሁ ያግታሉ። ይገላሉ። ንብረት ይዘርፋሉ። ያቃጥላሉ። ንፁሃን ይገላሉ። ታድያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ነው ወደመተማመን መምጣት የምንችለው!? ሲሉ ይጠይቃሉ።

ስለሆነም እባካችሁ እኛ በወለጋ አንገር ጉትን ከተማና በዙሪያው የምንገኝ የኦሮሞ ተወላጆች አሁንም መቀጠል የምንፈልገው እንደድሮው በሠላም፣ በፍቅር፣ በደስታና በመቻቻል መኖርን በመሆኑ በአንዳንድ አከባቢዎች በተፈጠረው ቀውስ ከሁለቱም ወገን ንብረት የዘረፉ፣ በጥፋቱ አግባብነት የሌለው ነገር የፈጸሙ፣ በየከተማው ተቀምጠው የሚያባሉ፣ የተዘረፈ ንብረትን የሚቀበሉትንና ሌሎች የሚያራርቅ ተግባር የሚፈጽሙትን በጋራ ሆነን እንታገላቸውና እንደድሮ ሰላም እንኑር!!! ሲሉ ሠላማዊ የኦሮሞ ወንድሞቻችን ለአጉልዞ ጥያቄ አብራርተዋል።

እኛም ይህንን መልካም እሳቤ ተቀብለን ለሠላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት ለመስራት ቃል ገብተናል። እንወዳችኋለን!!!
"""ቅድሚያ ለሠላም ፈላጊዎች!!"

10/10/2022

ለመግደል የተሰለፈ ኃይል ፥ ግድያ ለመፈፀም "ውሃ ቀጠነ" በቂ ምክንያቱ ነው!

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት 18 አመት ያልሞላው ታዳጊ እንድሪስ ሰኢድ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገውና የሚኖረውም በቄለም ወለጋ መቻራ ከሚባል አካባቢ ነበር፡፡

ከሰሞኑ በከተማ ውስጥ ሞተር እየነዳ በሚያልፍበት ወቅት በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች ከኃላው ተከታትለው በመያዝ " ውሃ ረጭተኸን ነው ያለፍከው!" በሚል ሰበብ በአደባባይ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል!

ቤተሰቦቹም "ህግ ሊያስከብርልን የሚችለው አካልም በአደባባይ እየገደለን ፍትህን ከየት እንጠይቅ!" ሲሉ እያለቀሱ ይገኛሉ!

10/10/2022

፨፨መንግስት በአስቸኳይ ክሳቸውን ሊያቋርጥላቸውና ከእስር ሊፈታቸው ይገባል!!፨፨

መስከረም 27-2015ዓ.ም። ለህሊና እስረኞቹ ከወለጋ ህዝብ የቀረበ መልእክት፥

በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ በበጎም ይሁን፣ በመጥፎ በርካታ ክስተቶች ውስጥ መርጦ አልቃሾች ሊኖሩ ይችላሉ። በኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ክልል፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በትግራይ ወራሪ ሐይሎች ግን የተፈጸመውን ግፍ፣ መከራና ስቃይ መቃወም ግን ሰብዓዊነት ነው።

በአራት አመታት ውስጥ ከተፈጸሙት መካከል እንደው ድምፅ ኖሯቸው የተነሱ፣ የተገለጡ ቢኖሩም እንኳን ሩብ አይሆንም፤ ሲሉ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ የሚኖሩ ህዝቦች ለአጉልዞ ጥያቄ ያስረዳሉ።

መንግስት በወለጋ ለተፈጸመው ግድያ፣ እገታ፣ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ ዝርፊያ እና ድፍን የማህበረሰብ ጥላቻና መገፋት እጅጉኑ እንደሚያሳዝነው ሲገልፅ ኖሯል። ታድያ ይህንን መበደል፣ መገፋት፣ ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ አገዳደል፣ የሐይማኖት ተቋማት መውደም፣ የባንክ ዝርፊያ በሙሉ በጋዜጠኞች ይፋ ቢወጣ፣ ቢነገር አለም ቢያውቀው በምን ጥፋታቸው ነው ለእስር የሚዳረጉት?

ስለወለጋ ሰቅጣጭ ሁኔታ እንኳን ሙያዊ ግዴታ ያለባቸው ቀርቶ በፓርላማ ውስጥ ያሉት ለጭፍጨፋው ህሊና አስገድዷቸው፥ ለጭፍጨፋው መሪ ነው ያሉትን ሁሉ በፊት ለፊት የተጋፈጡም አሉ። አቅጣጫም ተጠቁሟል።

ታድያ የወለጋው ጭፍጨፋ፦
የጉራፈርዳው
የመተከል
የከማሽ
የደምቢደሎው
የጊምቢ የቶሌ ጭፍጨፋ
የሊሙ ወረዳ የአርቁምቢው ጭፍጨፋ
የኪረሙ ወረዳ የሐሮ አድስ አለም ቀበሌ ጭፍጨፋ
የአጋምሳው፣ የአሙሩው፣ የጃርቴ ጃርዴጋው ጭፍጨፋ
የነቀምቴ መንገድ ጭፍጨፋ፣ እገታ፣ ዝርፊያ
የወጤው(የመርካቶ) ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ዝርፊያ
የአኖው ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ እና እገታ
የሉጎው ጭፍጨፋ
የኡኬው ጭፍጨፋ
የሎሚጫው ወረራ
የሻምቡው፣ የአቤደንጎሮዉ እስርና እንግልት
የሲቡስሬው
የመንደር 10 (አንገር ለሊስቱ) ጭፍጨፋ
የፊጢበቆው ጭፍጨፋ፣ እገታና ወረራ
የሐሮ ገሊላው
የጊዳ አያና ወረዳ ቀበሌዎች ወረራ፣ ጭፍጨፋና ዝርፊያ
የአንገር ጉትን ከተማ አስተዳደራዊ በደል፣ እስርና ውንብና
የአርጆው ጭፍጨፋ
** የሶጌው ጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ እገታና ዝርፊያ ወዘተረፈ......
በሙሉ በሙያዊ ግዴታ ባላቸው ቢነሳ፣ ቢወሳ፣ ቢነገር፣ መንግስት ይህንን ችግር እንድቀርፍ ቢነገረው ምንድነው ጥፋቱ!?
ወይስ የተፈጸመ የለም!? ሁሉም ውሸት ናቸው ወይ???
ታድያ በዚህ ጥግ በደረሰ ጽንፈኝነት ህይወታቸውን ያጡ ሁሉ ማን በደላቸውን፣ እምባቸውን ያብስ!?

ስለሆነም እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ ከክልሉ ውጭ ተወልደን ያደግን፣ በመኖር ላይ የምንገኝ በሙሉ የመንግስትን አስተዳደራዊ መዋቅር ለመፍጠር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ለሊት ተሰልፈን፤ የመረጠ ህዝቦች ነበርን!!
ችግሮችን ሁሉ በሞታችን፣ በእገታ፣ በመፈናቀል፣ በዝርፊያ እና በውንብድና ውስጥ ካለው የኦነግ ሸኔ ከበባ ውስጥ ሆነን ለችግሮቹ ሁሉ ድምፅ በመሆን ከጎናችን የነበሩትን ሁሉ በአሻችሁ ሰዓት አስራችሁ የሚቀረፍ ችግር ባይኖርም በመንግስት ላይ እምነታችን ግን ይጠፋል።

ደግሞም የወለጋ ህዝብ በመንግሥት ላይ እምነት ቢያጣ፣ ቢያኮርፍ፣ ቢተች፣ ቢቃወም፣ አደባባይ ቢወጣ ያንስበት ይሆናል እንጅ የሚበዛ አይሆንምና፥ እባካችሁ በችግሮቻችን ሁሉ ከጎናችን ለሆኑት በሙሉ ድምፃችን ተዘግቷል፣ የምናማክረው የለንምና እባካችሁ ፍቷቸው!!!

08/10/2022

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር):
ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚገድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የሃንዳውት፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ እራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ እንዳለው ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ እራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ እንጂ። አንተ'ኮ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"እራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ እንደ ቴኳንዶ ያሉ ራስን መከላከያ ሥልጠና፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ቆሻሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ኣ? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። እራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"እራስን በሱስ በመጉዳትና እራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"

(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

07/10/2022

የአማራ ዜጎች ከወለጋ የሰው ማረጃ ቄራ በሰላም እንዲወጡ የብልጽግና ፌዴራልና፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልላዊ መንግሥቶች ግዴታና ተጠያቂነት አለባቸው
========በፂዮን ዘማርያም===========
‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው!!!›› በወለጋ፣ በመተከል፣ በቤኒሻንጉል የሚኖሩ አማሮች በህይወት የመኖር መብታቸው ተጥሶል፡፡ የህወኃት ኢህአዴግ የዘር ቨይረስ ወደ ኦነግ ብልፅግና የዘር አባ ሠንጋ ቨይረስ ከተላለፈ ቆይቶል፡፡ አራጆቹ!!!
በወለጋ የሰው ቄራ እርድ በጥበቃ ስር ያሉና ያለፍርድ የታገቱ ሰዎች መብት ስብዓዊ ክብራቸውን በማይጠብቁ ሁኔታዎችበኦህዴድ ብልፅግና መንግሥትና በኦነግ ሸኔ ያለፍርድ ለሰው ቄራ የደም መሥዋትነት እንዲቀርቡ የሚያደርጉ አንደኛ ነተጠያቂዎች የፌዴራል መንግሥቱን የሚመሩት ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት መሪ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉሉ መሪ አሻድሊ ሃሰንና የአማራው ክልል መሪ ይልቃል ከፍያለ ዋነኛ ተጠያቂነትን አቶ አንድአርራቸው ጽጌ ሲያስተባብሉ ታይተዋል፡፡ የእርሶ ልጆች በወለጋ ቄራ ውስጥ ቢሆሩ መጀመሪያ ከዚህ የእርድ ክልል ጣቢያ አስወጡን ብሎ የሚለምነውን ደሃ የአማራ ህዝብ ከመታደግ ሌላ ምን አለ፡፡ አሁንም ህዝቡ ነፃ የማርያም መንገድ ተከፍቶለት ከወለጋ ኦሮሚያና ከመተከል ቤኒሻንጉል ክልል መውጣት ነው የሚፈልገውና መፍትሔው ይሄ ብቻ ነውና ለዶክተር አብይ አህመድ እንዲወጣ ቢለምኑለት እንጠይቅዎታለን፡፡ ይሄ የሰው ደም ፈሶ አይቀርምና አንድ ቀን እንደሚያስጠይቅ ሊመክሩቸው ይገባል፡፡ ከዚህ በኃላ ስንት ዓመት ይኖራሉና በወለጋ የሰው ቄራ እርድ የመጀመሪያ ተጠያቂዎችን አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ፣ አሻድሊ ሃሰንና ይልቃል ከፍያለ መሆናቸውን ማድበስበስ የትም አያደርስዎትም እንላለን፡፡ በ1966ቱ አብዩት በግፍና ባልሰሩት ተግባር ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ካቢኔቸው በርሃብ ለረገፈው ህዝብ ተጠያቂ ሆነው መረሸናቸው የእርሷ የተማሪ ቤት ትዝታ መሆኑን የዘነጉት ይመስላሉ፡፡ ዛሬም ‹‹የአማራን ጥቃት ለማስቆም አንድ መፍትሔ አለኝ››……………(1) በአሉት ዲስኩርዎ ወለጋ ሂዱና ታስረው የጮህልዋትን ህዝቡ የሚልዎትን ብትሰሙ ሃቀኝንዎትን ያሳያሉ፡፡ ያለበለዛ በኢትዮጵያ የፍርድ ቀን ይመጣል!!! አንድ ቀን ይህን የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ለመደባበስ በመሞከርዎና፣ ህዝብን በማሳሳት የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ሊህቁ/ ምሁራን ናቸው ብለው ማሳበብ አንድ ቀን ያስጠይቃል እንላለን፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተቀረጸው ህገ- መንግሥት ምን ይላል፡-
 ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡››አንቀጽ 14
 ‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› አንቀጽ 15
 ‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 16

በዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ሸኔ የተገደሉ አማራዎች ከሰባት ሽህ ቁጥር በላይ አሻቅቦል፣የቆሰሉ ሰዎች በሽህ ይቆጠራሉ፣ የተዘረፉ የቁም ከብቶች ሁለት መቶ ሽህ በላይ ይገመታል፣ የተቃጠሉ ቤቶች ብዙ ሽህ ይቆጠራል፣ 68 (ስልሳ ስምንት) ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ 46 (አርባ ስድስት) መስጊዶች ተቃጥለዋል፣ 84 (ሰማንያ አራት) ወፍጮ ቤቶች 163 (መቶ ስልሳ ሦስት) ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ ብዙ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ 756 (ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል የትምህርት ማስረጃዎች ተቃጥለዋል፡፡325 (ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሽህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 5227(አምስት ሽህ ሁለት መቶ ሃያ ሰባት) አስተማሪዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል፡፡ በወለጋ 500 (አምስት መቶ) ሽህ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች 647 ንፁሃን አማሮችን መግደላቸው ተገልፆል፡፡ 1252 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 85 (ሰማንያ አምስት) ሽህ ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 26.7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዩን ብር የሚገመት ንብረት ወድሞል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በጦርነቱ 11.6 (አስራአንድ ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፆል፡፡ ከዚህ ውስጥ 9.3 (ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ በሰሜኑ ጦርነት በእርሻ ዘርፍ እንዳያመርቱ የተገደዱ ገበሬዎች ናቸው፡፡ 2.3 (ሁለት ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆኑ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ የነፍስ አድን ድጋፍ ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ ወዘተ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ የአማራ ህዝብ በተለይ በወለጋ ኦሮሚያና በመተከል ቤኒሻንጉል ክልሎች ያሉት ህዝብ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፎል ምንም የቀረን ነገር የለምና ከነዚህ የሰዎች እርድ ቄራዎቸ ስቃይና መከራ ተላቀን ወደፈለግንበት በሰላም እንድንሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምፅ ተነስቶ ነፍሳችንን እንዲያድን በህፃናቶች፣ በእናቶችና በአረጋዊያኑ ስም እንጠይቃለን፡፡ አቶ አንዳርጋቸውም የህዝቡን ጥያቄ በኢሳት አማካኝነት ቦታው ድረስ በመሄድ ማረጋገጥ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ይቻልዎታልና ጊዜውን ተጠቀሙበት እንላለን፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
06/10/2022

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹
03/10/2022

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

I am abdullah umer strugler for those of kidnapped voice.

( በአሙሩ ወረዳ ከምትኖር አንድት ሚስኪን የኦሮሞ ተወላጅ መልእክት)" #ከቻላችሁ ህፃናት እና አረጋውያንን ባስቸኳይ አውጧቸው፤ጃል ፈቀዳ እና ጃል መሮ እና የወረዳው የብልፅግና አመራሮች ዝግ...
02/10/2022

( በአሙሩ ወረዳ ከምትኖር አንድት ሚስኪን የኦሮሞ ተወላጅ መልእክት)

" #ከቻላችሁ ህፃናት እና አረጋውያንን ባስቸኳይ አውጧቸው፤ጃል ፈቀዳ እና ጃል መሮ እና የወረዳው የብልፅግና አመራሮች ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል...."

#ከአሙር ወረዳ ተነስተው ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ የሚገኙ አማሮችን ለመጨፍጨፍ #ጃል ፈቀዳ እና ጃል መሮ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ወስነዋል።

በመሆኑም ከቻላችሁ ቢያንስ ህፃናት እና አረጋውያንን በማውጣት አድኗቸው ስትል በአሙር ወረዳ የምትገኝ እና መረጃውን የሰማች አንዲት ቅን የኦሮሞ ተወላጅ መልዕክት ልካለች።

የጃል ፈቀዳ እና የጃል መሮ የጋራ ጦር እንደ ዲሽቃ፣ብሬን፣ስናይፐር እና የመሳሰሉ ከባድ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከክልሉ መንግስት በወረዳው የብልፅግና አመራሮች በኩል እንዲታጠቁ ተደርጓል።
ተተኳሽ ጥይቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎትም በበቂ ሁኔታ እንደቀረበላቸው መረጃ ሰጭወቻችን አጋልጠዋል።
#ጃል ፈቀዳ የምዕራብ ወለጋ የኦነግ ሠራዊት መሪ እና ጃል መሮ የምስራቅ ወለጋ የኦነግ ሠራዊት መሪ ከትናንት በስቲያ በሬ አርደው ዕርቅ ፈፅመዋል።
በወለጋ አንድ፣ አንድ አካባቢዎች የቀሩ አማሮችን ለመጨፍጨፍ የግል ፀባቸውን ፈትተው ስምምነት መፍጠራቸውን ነው መረጃ ሰጫችን የገለፀልን።
ጃል ፈቀደ እና ጃል መሮ ከዚህ ቀደም ፀብ ነበሩ።ይሁን ዕንጅ አሁን ላይ በጋራ ጉዳይ በጋራ ዓላማ ለመሰለፍ የቀደመ ችግራቸውን ፈትተው አንድ ሆነዋል ተብሏል።
እነዚህ ኃይሎች ሆሮ ጉድሩ ዞን አሙር ወረዳ የሚገኙ አማሮችን አፀድትው አካባቢውን ከተቆጣጠሩ ሳምንታት አልፈዋል።ብሏል መረጃ ሰጫችን።
እነዚህ ጨፍጫፊ የኦነግ ኃይሎች አሁን ላይ የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን #አሙሩ ወረዳ ተቀምጠው ነው ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ በመግባት በአካባቢው ተጠልለው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮችን ለመጨፍጨፍ ውሳኔ ላይ የደረሱት።ተብሏል።

በአካባቢው የኔት ወርክ አገልግሎት በኦሮምያ መንግስት ከተቋረጠ ወራት አልፈዋል።ቢያንስ እየተደዋወልን መረጃ በመለዋወጥ ህይዎት ለማትረፍ እንኳን አልቻልንም።በተጨማሪም ንፁሃን አማሮች ወደ ቡሬ፣ጎጃም እንዳይሸሹ እንኳን መንገድ ከተዘጋ ብዙ ጊዚያችን ነው ብለዋል።

በስተመጨረሻ በአካባቢው ሊታደገን የሚችል የፀጥታ ኃይል የለም።የክልሉ ልዮ ኃይሎችም ከሚለብሱት ሚሊተሪ ቀለም ባሻገር የተለየ ዓለማ የላቸውም፤እራሳችንን ተደራጅተን ልንከላከል ስንሞክር እንኳን ከኋላ የሚገድሉን እነሱ ናቸው።በመሆኑም ባስቸኳይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሊደርሱልን ይገባል።ካልሆነ ዛሬም ጥሪ እያቀረብን ልናልቅ ነው።ብለዋል።
መንገድ፣ኔትወርክ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ተከፈተውልን ቢያንስ ህይዎታችንን እናትርፍ ሲሉ ተማፅነዋል።
© Wogderes Tenaw ወግደረስ ጤናው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesmer media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share