ከዚህም ከዛም/kezihm kezam

  • Home
  • ከዚህም ከዛም/kezihm kezam

ከዚህም ከዛም/kezihm kezam Sharing of technolgy, news and related issue

19/01/2024
09/08/2023

ዜና እረፍት🕯🕯

አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።ከዚህ ውስጥ አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል። ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው የቴሌቪዥን ድራማዎች ሲሆኑ፥ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን

በጎንደር ከተማ በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና ብዙዎች መጎዳታቸው እንዲሁም ሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የኦክሲጂን እጥረት እንዳጋጠመው ተገለጸ!በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በ...
09/08/2023

በጎንደር ከተማ በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና ብዙዎች መጎዳታቸው እንዲሁም ሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የኦክሲጂን እጥረት እንዳጋጠመው ተገለጸ!

በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ የደም፣ ኦክስጂን እና የተወሰኑ መድኃኒቶች እጥረት ማጋጠሙን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ግጭት እና የተኩስ ልውውጥ ከገጠማቸው የአማራ ክልል ከተሞች መካከል የጎንደር ከተማ አንዷ ስትሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተማዋ እና በዙሪያዋ ባለፉት ቀናት በነበረው ግጭት አብዛኞቹ ሰላማዊ የሆኑ ወደ 20 የሚደርሱ ሰዎች እንደሞቱ እና ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጎንደር ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ወደ ጎንደር ሆስፒታል በጥይት ተመትተው ከመጡ ሰዎች መካከል የ16 ዓመት ታዳጊ እንደሚገኝበት እና ተጎድተው ከመጡት መካከል በእድሜ ትልቅ የሆኑት ደግሞ የ50 ዓመት ሴት መሆናቸውን አንድ ዶክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ በኋላ የሞቱ ሰዎች አብዛኛዎቹ “ሰላማዊ ሰዎች እና ተዋጊዎች” መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎቹ ጠቅሰው፣ እስካሁን ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ የመጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አለመኖራቸውን ተናግረዋል።በግጭቱ የተነሳ በከተማዋ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በመስተጓጎላቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገኙ ህሙማን እጅግ አስፈላጊ የሆኑት የደም፣ የኦክስጂንእና የመድኃኒት አቅርቦቶች እጥረት ማጋጠሙን የጎንደር ሆስፒታል ምንጮች ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሆስፒታሉ ባጋጠመው የኦክስጂን እጥረት ምክንያት ምንም ዓይነት ቀዶ ሕክምና ማከናወን አለመቻሉን የሆስፒታሉ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።የቢቢሲ ምንጮች ጨምረውም ለቀናት በከተማዋ ባጋጠመው አለመረጋጋት የተነሳ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለመኖሩ በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የሚቀርብ ምግብ እጥረት ማጋጠሙንም ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንዳሉት በከተማዋ ለሦስት ቀናት በዘለቀው ግጭት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ለማድረስ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩ የተጎዱ ሰዎች በቃሬዛ መምጣታቸውን አመልክተዋል።

Via፣ BBC
T.me/ethio_mereja

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከዚህም ከዛም/kezihm kezam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share