Ethio victory time's media ኢትዮ ቪክተሪ ታይምስ ሚዲያ

  • Home
  • Ethio victory time's media ኢትዮ ቪክተሪ ታይምስ ሚዲያ

Ethio victory time's media ኢትዮ ቪክተሪ ታይምስ ሚዲያ የትኛው የመረጃ ምንጭ ለህዝቡ ለማድረስ ዝግጁ የሆነ ፔጅ ነው

  የአዲሱ ማ/ኢ ክልል ም/ቤት አባላት በሙሉ "የማዕከለዊ ኢትዮጵይ ክልል "በሰላም "በኢኮኖሚ "በዲሞክራሲያዊ እና በወንድማማችነት ለመቀጠል የምስራቅ ጉራጌ ዞን "በሞሽን" ለመፅደቅ የቀረበው...
18/08/2023

የአዲሱ ማ/ኢ ክልል ም/ቤት አባላት በሙሉ

"የማዕከለዊ ኢትዮጵይ ክልል "በሰላም "በኢኮኖሚ "በዲሞክራሲያዊ እና በወንድማማችነት ለመቀጠል የምስራቅ ጉራጌ ዞን "በሞሽን" ለመፅደቅ የቀረበው ምክረ ሀሳብ፣ ከተለያዩ ዞን የመጣችሁ የክልል ም/ቤት አባላት በሙሉ "አቶ እርስቱ ዛሬ በም/ቤቱ በሰጠው አጀንዳ የማስቀየርና የማደናገሪያ ሀሳብ "ምስራቅ ጉራጌ ዞን "በሞሽን" ፀድቆ እንዳይመሰረት መሆኑ በመረዳት

"የምስራቅ ጉራጌ ዞን "በሞሽን" እንዲፀድቅ ሁሉም የም/ቤቱ አባላት ሳትደናገሩ አንድተደግፉ ስንልን "እኛ የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች በትህትና እንጠይቃለን !!!

 #ዛሬ በቀን  #10/2015 ዓ-ም ሀዋሳ @=>> ዛሬ የምስራቅ ጉራጌ ተወላጆች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ሀወሳ ድምፃቸውን ለማሰማት አቅንተዋል     የተለያዩ የግልና የመንግስ...
15/08/2023

#ዛሬ በቀን #10/2015 ዓ-ም ሀዋሳ

@=>> ዛሬ የምስራቅ ጉራጌ ተወላጆች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ሀወሳ ድምፃቸውን ለማሰማት አቅንተዋል

የተለያዩ የግልና የመንግስት ሚዲያዎች ቦታው ላይ ይገኛሉ

=> የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች በዞን የመደራጀት ጥያቄ ሠላማዊ እና ህገ_መንግስታዊ ነው።

=> እኛ የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች በዞን የመደራጀት ጥያቄ ለ30 ዓመታት ስንጠይቅ የነበረ ጥያቄ
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የክልል አደረጃጀት ጋር እንዲመለስልን እንጠይቃለን ::

የምስራቁ ጉራጌ ህዝብ የ"ዞን" ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል‼️❤️💪❤️💪❤️💪 👉 ልክ የዛሬ ዓመት ነሐሴ 7 እና 8 በ7ቱም ምክር ቤቶቻችን ክላስተርን (ከሀድያ፣ ከስልጤ...
13/08/2023

የምስራቁ ጉራጌ ህዝብ የ"ዞን" ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል‼️
❤️💪❤️💪❤️💪

👉 ልክ የዛሬ ዓመት ነሐሴ 7 እና 8 በ7ቱም ምክር ቤቶቻችን ክላስተርን (ከሀድያ፣ ከስልጤ፣ ከከምባታ ጠንባሮ እና ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከየም ልዩ ወረዳ በጋራ ክልል እንድንመሰርት) እና የምስራቁ ጉራጌ ህዝብ "ዞን እንሁን" ጥያቄ ያፀደቀበት ጊዜ ነበር። የዚህን ህዝብ ውለታው መርሳት ተገቢ አይደለም። የተገባው ቃል ተግባራዊ ይደረግ‼️

👉 የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ፍትህን አገኛለሁ፣ ከአፈናና ጭቆና ነፃ እወጣለሁ፣ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን በእኩልነት፣ በነፃነት እኖራለሁ በማለት ለ30 ዓመታት ታግሏል፤ መስዋዕትነት ከፍሏል። በሚካሄደው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ከሁሉ በፊት የአደረጃጀት ጥያቄ ምላሽ ይሰጥ! የምስራቁ ጉራጌ ህዝብ የዞን እንሁን ጥያቄ በሞሽን (በውሳኔ ሃሳብ) ይፅደቅልን‼️

👉 የሚዘጋጀው ህገ መንግስት ከግለሰቦች ተፅዕኖ የፀዳ፣ ህዝቦችን ነፃነታቸው የሚያጎናፅፍ፣ ህዝቦች የፈቀዱት፣ በህዝቦች ይሁንታ የተቸረው ሊሆን ይገባል።
የህዝቦችን ድምፅ በማፈን ሀገሪቷ እንዳትረጋጋና በየአቅጣጫው ቀውሱ እንዲባባስ ቤንዚል የሚያርከፈክፉ ጥቂት የምዕራብ ጉራጌ ከፍተኛ አመራሮች መንግስት አደብ ሊያሲዛቸው ይገባል‼️

❤️ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ❤️

28/07/2023

"ሰላም ከሁሉም ነገር ይቀድማል "የሰላምን ዋጋ በገንዘብ አይተመንም !!!

ከ4 አመታት በፊት በፖለቲከኞች ሴራ እና በእነሱ የተደራጀ ጥቂት ሰላም ጠል የፅፈኛ ቡድን "በመስቃን ህዝብ ላይ ታቅዶ እና በተቀናጀ መልኩ ወረራና ግድያ ተፈፀመ "ከእንሴኖ ከተማ ተጀምሮ በምስራቅ መስቃን ወረዳ ቀበሌዎች ቀጥሎ "በማረቆ ወረዳ የሚኖሩ የመስቃን ህዝቦች ላይ ጨምሮ አሰቃቂ "ግድያዎች በርካታ "መፈናቀሎችና ችግሮች መድረሱ ይታወሳል ።

ግጭቱ እየተባባሰ በመሄዱ መንግስት ቀጠናው በኮማንድ ፖስት ስር እዲሆን ቢደረግም "ግጭቱ ለማረጋጋት አልተቻለም ነበር "እያለ እያለ "በሁለቱም ህዝቦች በርካታ የሰው ሂወት ተቀጠፈ "ሆኖም የመስቃን እና የማረቆ ህዝብ ግጭቱ እንደማይፈልጉት ይታወቃ ነበር ።
"ሁለቱም ህዝቦች ለዘመናት "ተዋልዶ "ተጋምዶ "ተከባብሮ የኖረ በገበያዎች የሚገናኝ እና በበርካታ ማህበራዊ ጉዳዪች የተሳሰረ እንደመሆኑ "የተፈጠረው ግጭት የጥቂት ፖለቲከኞች እና ሰላም ጠል ፅንፈኞች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በተከበረው "የሰው ሂወት ላይ ቁማር ሲጫወቱ እንደነበር "ከሽምግልናው ውጤት ቡኋላ የነበረው የሁለቱም ህዝብ የሰላም ጥማት ማሳያ ነው !!!

በዚህ ግጭት የተረፈው "ሮጠው ያልጠገቡ "ህፃናት "ወጣቶች "ሽማግሌዎች እና የበርካታ ንፁሀን ሞት፣ "ከሞት የተረፉ ግለሰቦች አካል ጎዳተኛ ሆነው እንዲኖሩ "የበርካቶች ቤትና ንብረቶች ወድመዋል/ጠፍተዋል "በርካቶች ተፈናቅለው ጎዳና እንዲወጡ እና ከ3 ዓመት በላይ ተፈናቃዮች ውጪ ላይ እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል "ነጋዴው "ባለሀብቱ ከስሮ እንደገና ሰርቶ ለማግኘት ሞራን እስኪያጣ ድረስ የስነ-ልቦና ችግር ደርሶበታል "በርካታ ህዝብ በፍ/ቤት ቀጠሮ ብቻ በእስር ለአመታት እንዲሰቃይ ሆኗል "ቀጣው ለአመታት እንቅስቃሴ የሚባል ነገር ቀርቶ ማህበረሰቡ በሰቀቀን እና በስጋት እንዲኖር ተፈርዶበታል ።

"አየህ ወገኔ እነዚህ እና ተዘርዝርው ከማያልቁ ችግሮች በቀር የተገኘ አንድም ጥቅም የለም፣ ምናልባት ፖለቲካኞች እና ፅፈኞች "ከግል ጥቅማቸው በቀር ።

"ከዚህ ሁሉ ቡኋላ በመጨረሻም ተለያይቶ የማይለያየው የመስቃን እና የማረቆ ህዝብ በባህላዊ ሽምግልና ስርዓት ጉዳ ታስሮ ሰላም ተፈጠረ "የቀድሞ ማህበራዊ ግንኙነቶች ቀጠሉ "ቀጠናው እንደ ቀድሞው የሰላም ቀጠና ሆነ !!!

"ወገኔ ሆይ ከበርካታ ልፋትና ጥረት ቡኋላ የተገኘውን ሰላም እንደገና ለማጥፋት የሚጥሩት ጥቂት ሰላም ጠል ፖለቲከኞች ለግል ጥቅማቸው ሲባል ዳግም በቀጠናው ግጭት እንዲፈጥሩ አትፈቀድ፣ በግጭት የሚገኝ ጉዳት እንጂ አንድም ጥቅም እንደሌለ "በሰላም ማጣት በርካታ ችግሮችን በተግባር ያየን ህዝብ የሚነገር አይደለም "በአካባቢያችን የደረሰውን ግጭትና ጦርነት ውጤት ካላስተማረን የሰሜኑን ግጭት ቡኋላ የተፈጠረው ማየት በቂነው ።

"ሰላም በአንዱ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚመጣ ባይሆንም "ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል "የሰላምን ዋጋ ትርጉም እንዲሁም "ስለ ሰላም ብቻ እየሰበከ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ !!!

Tofik Awol Bedriya ነኝ ከምርጧ ከተማ "ቡታጅራ

50 ብር ጉቦ የሰጣቸው ትራፊክ ፖሊሶች 50 ብር ካልጨመርክ በማለት ሾፌር ገደሉ!  በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ፖሊስ አባላት የጠየቁትን የሃምሳ ብር ጉቦ አልሰጠም ያሉትን አን...
25/07/2023

50 ብር ጉቦ የሰጣቸው ትራፊክ ፖሊሶች 50 ብር ካልጨመርክ በማለት ሾፌር ገደሉ!


በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ፖሊስ አባላት የጠየቁትን የሃምሳ ብር ጉቦ አልሰጠም ያሉትን አንድ አሽከርካሪ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የሟች ቤተሰቦች እና የሥራ ባልደረቦች ገለጹ ፡፡ ባለፈው ዓርብ በትራፊክ ፖሊስ አባላቱ በጥይት ተገደለ የተባለውና ትናንት እሁድ የተቀበረው የ33 ዓመቱ ሳሙኤል መረተ ነዋሪነቱ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

ጓደኞቹ እንደሚሉት ሳሙኤል ከረጅም ጊዜ አንስተቶ የአሽከርካሪነት ሥራውን ሲያከናውን የቆየው ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በተዘረጋው መስመር ላይ ነበር ፡፡

ሳሙኤል በመስመሩ በሰበብ አስባቡ ካልቀጣንህ የሚሉትን የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለማባበል ዝርዝር የሃምሳ ብር ኖቶችን በእጃቸው እያስጨበጠ ማለፍ የሁልጊዜ ተግባሩ እንደነበር ጓደኞቹ ይናገራሉ ፡፡ይህ የሃምሳ ብር ጣጣ ታዲያ “ አንሷል ጨምር አልጨምርም “ በሚል ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር የገባበት እሰጥ አገባ ለህይወቱ መጥፋት ምክንያት መሆኑን ነው በሥፍራው ነበርን ያሉ ለዶቼ ቬለ DW የገለጹት ፡፡

የሳሙኤል ረዳት ሆኜ ሥሠራ ነበር የሚለው አንዱዓለም ሁሴን መንገደኞችን አሳፍረው ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በመጓዝ ላይ እንዳሉ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ሲደርሱ ሦስት ትራፊኮች እንዳስቆሟቸው ይናገራል ፡፡ ሟች ሳሙኤል የመውጫ ወረቀት እና ሃምሳ ብር ሲሰጥ ከትራፊኮቹ አንዱ ሀምሳውን ቀይረህ መቶ አድርግ ሲለው መስማቱን የጠቀሰው አንዱዓለም “ ሟቹም አሁን የለኝም አልተዘጋጀሁም ሲለው ትራፊኩም አለበለዚያ የተሸከርካሪውን ሠሌዳ እፈታለሁ በማለት ሟችን በቦክስ መታው ፡፡

ይሄኔ በንዴት ተሽከርካሪውን አስነስተን ወደፊት መሄድ ስንጀምር ተከትለው መተኮስ ጀመሩ ፡፡ ጥቂት እንደተጓዝን ተሸከርካሪውን በማቆም እኔም ሆንኩ ሌሎች መንገደኞች ደንግጠን ወረደን መሮጥ ጀመርን ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እሱን በጥይት መትተው ጣሉት “ ብሏል፡፡

ከትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ጋር አለመግባባቱ የተነሳው በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈጸመው ግን በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ሱተን ዙሪያ ቀበሌ ድረስ ተከታትለው በመምጣት አንደሆነ የተናገሩት የሟች ሳሙኤል አባት አቶ መረተ ለማ ” ይህን ለማን አቤት ልበል ? “ ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ DW በጉዳዩ ላይ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የተሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፈይሳ ደበላን ጠይቋል ፡፡ አዛዡ ግን ወንጀሉ የተፈጸመው እሳቸው ከሚመሩበት የተሬ ወረዳ አልፎ ጉራጌ ዞን ውስጥ መሆኑን በመጥቀስ “ በዚህ ላይ እኔ የምላችሁ ነገር የለም ፡፡ ባይሆን የደቡብ ክልል ፖሊስን ጠይቁ “ ብለዋል ፡፡

የወንጀሉ አድራሾች በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ናቸው የሚሉት የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ በበኩላቸው አሁን ላይ ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠሩ ሦስት የትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል ፡፡ “ የተከሰተው ነገር አሳዛኝ ነው “ ያሉት ኮማንደር ጠጄ “ የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ወዲያው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ጥሩ ነገር ነው፡፡ አሁን ምርመራውን ከኦሮሚያ ክልል የሥራ ሃላፊዎች ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን ፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመው በጉራጌ ዞን ውስጥ በመሆኑ ምርመራውን ወደ ዞኑ ለማዛወር በሂደት ላይ ነው ያለነው “ ብለዋል፡፡

መረጃው የዶቼ ቬለ ነው።

ጉራጌ በሁለት የዞን መዋቀር ተደራጅቶ የህዝቦቻችን የልማት እኩልነት የተጠቃሚ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና መልካም የአስተዳደር ስራዓት ለመዘርጋት እንዲሁም የህዝቦቻችን ሰላምን ለማስፈን በማዕከ...
02/06/2023

ጉራጌ በሁለት የዞን መዋቀር ተደራጅቶ የህዝቦቻችን የልማት እኩልነት የተጠቃሚ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና መልካም የአስተዳደር ስራዓት ለመዘርጋት እንዲሁም የህዝቦቻችን ሰላምን ለማስፈን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ይመሰረታል‼ሃቁ ይሄ ነው👌
ፍንክች የለም ቃል ቃል ነው👌

የአማራ ብልፅግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በትውልድ ቦታ ሰሜን ሸዋ መሀል ሜዳ በህገ ወጡ በፋኖ ታጣቂዎች በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ አልፏል። ነፍስህን ይማረው
27/04/2023

የአማራ ብልፅግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በትውልድ ቦታ ሰሜን ሸዋ መሀል ሜዳ በህገ ወጡ በፋኖ ታጣቂዎች በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ አልፏል።

ነፍስህን ይማረው

⭕በአኃዳዊ እና በአምባገነን እንዲሁም በካድሬ አመራሮች የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ የሆነው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቀር ለመደፍጠጥ መሞከር ህዝብ መናቅ ነውና ትልቅ ...
06/04/2023

⭕በአኃዳዊ እና በአምባገነን እንዲሁም በካድሬ አመራሮች የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ የሆነው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቀር ለመደፍጠጥ መሞከር ህዝብ መናቅ ነውና ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል🚫‼

⭕ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተጠየቀው የዞን መዋቀር ያለአንዳች ማመንታ የህዝቡን ጥያቄ በህጋዊ መንገድ መመለስ ስልጡንነት ሆኖ እያለ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ መንገድ ነው‼

⭕የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አከባቢውን ለማልማት ብሎም ቋንቋው ባህሉ ታሪኩን ለትውልዱ እንዳያሸጋግር 30 ዓመት በሙሉ እንቅፋት የሆነበት በአኃዳዊና በአምባገነኑ ስራዓት የሚያራምደው የሰባት ቤት የምዕራብ ጉራጌ ፅንፈኛ አመራሮች ናቸው👇

⭕ለዚህም ችግር ፍቱ መድኃኒት የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች በሰላማዊ መንገድ የጠየቁት እራስ በራስ የማስተዳደር የአደረጃጀት የመዋቀር ጥያቄ ሲመለስ ብቻና ብቻ ነው‼

⭕ቡዙ ዘመናት እየተጮቆነ ያለው የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ከዚህ በኃላ ያንን የአምባገነንን ስራዓት በድጋሚ ልተግብርብክ ማለት ህዝቡን ሰላማዊ ኑሮ እንዳይኖር ቀጠናውን ሰላሙን እንዲያጣ አላስፈላጊ ወደ ሆነው እንደ ፅንፈኞች እና እንደ አማፅያኖቹ ሰባት ቤት ጉራጌ ይጀምር ማለት ነው‼

⭕ይህም ተግባር ደግሞ ህዝቡ ህልውናው ለማስጠበቅ ሳይፈልገውም በግድ ለማድረግ አያቅተውም ሆኖም ግን ፍፁም ሰላማዊ የሆነውን የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ የጠየቀው ህገ መንግስታዊ መብቱ በህጋዊ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲመለስለት ይሻል‼

ምስራቅ ጉራጌ ዞን ያለአንዳች ኩሽታ በሰላማዊ መንገድ ይመሰረታል✅✅

⭕የትውልዱ መፃዒ እድል የሚወስነው ወጣቱ አርዴው ነው‼⭕ነፃነት በነፃ አይገኝም ለዚህም ደግሞ ቡዙ መሰዋትነት መከፈል ይኖርብናል‼⭕የህዝቡን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግሉ ኪሱ ለማደለብ የሚ...
26/03/2023

⭕የትውልዱ መፃዒ እድል የሚወስነው ወጣቱ አርዴው ነው‼

⭕ነፃነት በነፃ አይገኝም ለዚህም ደግሞ ቡዙ መሰዋትነት መከፈል ይኖርብናል‼

⭕የህዝቡን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግሉ ኪሱ ለማደለብ የሚሯሯጥ ካድሬ አመራር ካለ የማስወገዱ ስራ መስራት ይጠበቅብናል‼

⭕የህዝቡን መብት እና የትውልዱን ተስፋ እና ብረኃን እንዲጨልም ሌት እና ምሽት ህዝቡን ለመሸጥ ቀብዳ የሚቀበል በእኛው ጉያችን ውስጥ ያደረግነው ነስሩ ጀማል ላይ የማያዳግም ቅፅበታዊ እርምጃ በመውሰድ ትግላችን አኃዱ ብለን መጀመር ይኖርብናል‼

⭕የተገዢነት እሳቤ የአጎብዳጅነት መንፈስ ያለበትን የህዝቡን እድል ለማጨለም በሚታትር ባንዳና ካድሬ አመራር ካለ እሱንም ወደዛኛው ዓለም የማሰናበት ስራ መስራት ይጠበቅብናል‼

⭕የተነጠከው መብትክ ነው መብት ለማስከበር ደግሞ በግ ሆነን መጠበቅ የለብንም ሁሉም በየፊናው በመናበብ ትግላችን ማጠናከር የግድ ይለናል‼

⭕ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይመሰረት የምንም አንድነት የሚባል ተረት ተረት እና እንቆቅልሽ የለም‼

⭕ምስራቅ ጉራጌ ዞን መመስረት የህዝባችን ዋናኛው ጉዳያችን ሆኖ ነፃነት አግኝተን የትውልዳችን መፃዒ እድል የሚወሰንበት ብቸኛው መንገድ ነው‼

⭕ምስራቅ ጉራጌ ዞን ያለማንም ከልካይ ይመሰረታል💪

የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ለጉራጌ ክልል ካልተሰጠ መንግስትን በሃይል ለመናድ የሚሰለፍ ህዝብ አይደለም። የምዕራብ የቸሃ ቤተ ጉራጌ ምሁራን እና ባለሃብቶች በ11ኛውም...
24/03/2023

የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ለጉራጌ ክልል ካልተሰጠ መንግስትን በሃይል ለመናድ የሚሰለፍ ህዝብ አይደለም። የምዕራብ የቸሃ ቤተ ጉራጌ ምሁራን እና ባለሃብቶች በ11ኛውም ሰአት ቢሆን መንግስትና ህዝብ እንዳይጣላ በማሰብ ምስራቅ ጉራጌ በዞን የመደራጀት መብት መከበር እንዳለበት በማመን በምዕራብ ጉራጌ እሊቶች የሚመራ የሽብር ተግባር ወደ ጎን በመተው ምስራቅ ጉራጌ ዞን መመስረት እንዳለበት አምነዋል።

⭕ህገ መንግስታዊ መብትክ ከመጠይቅ ወደ ኃላ አትበል‼⭕በምዕራብ ጉራጌ አመራሮች እና ኢሊቶች የተደገሰልክ ድግስ መልካም አይደል ህዝብክ እና ትውልድክ የሚጨርስ የዘመናት እቅዶች ወጥቶልክ በመዝ...
20/03/2023

⭕ህገ መንግስታዊ መብትክ ከመጠይቅ ወደ ኃላ አትበል‼

⭕በምዕራብ ጉራጌ አመራሮች እና ኢሊቶች የተደገሰልክ ድግስ መልካም አይደል ህዝብክ እና ትውልድክ የሚጨርስ የዘመናት እቅዶች ወጥቶልክ በመዝገብ ተመዝግቦልኃል‼

⭕ጊዜህንና ሰዓት ተጠቀምበት‼

⭕ነፃነትክ ለማግኘት የምስራቅ ጉራጌ ዞን መመስረት ዋናኛ ጉዳይ አድርግ‼

⭕ታገግለክ አታግል‼

⭕የባንዳና የካድሬ ገፀ ባህሪይ ከሚጫወት ሌምቦ ራቅ ‼

የምዕራብ ጉራጌ "ኢ" መደበኛ ቡድን በመስራቁ ጉራጌ ህዝብ ላይ ባለፉት 30 አመታት ያደረሱት እኩይ ተግባር ዳግም ላለማስቀጠል የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ዞን መስርቶ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በሰላ...
16/03/2023

የምዕራብ ጉራጌ "ኢ" መደበኛ ቡድን በመስራቁ ጉራጌ ህዝብ ላይ ባለፉት 30 አመታት ያደረሱት እኩይ ተግባር ዳግም ላለማስቀጠል የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ዞን መስርቶ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በሰላም እና በልማት ይበለፅጋል።

የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ሰላማዊ የልማት አርበኛሰላማዊ ህዝብ እንጂ እንደ ምዕራብ ጉራጌ እሊት የጥፋት ሃይሎች ተንኮል ተቀብሎ ከመንግስት ጋር የሚጋጭ ከሽብርተኛ ቡድን የሚሰለፍ ህዝብ አይደለም።...
13/03/2023

የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ ሰላማዊ የልማት አርበኛሰላማዊ ህዝብ እንጂ እንደ ምዕራብ ጉራጌ እሊት የጥፋት ሃይሎች ተንኮል ተቀብሎ ከመንግስት ጋር የሚጋጭ ከሽብርተኛ ቡድን የሚሰለፍ ህዝብ አይደለም።
የምዕራብ ተንኮል ጠንሳሽ የሽብር ቡድን አላማ ይከሽፋል

መንግስት ይህን በሙሉ ጉራጌ ስም በፓርቲ ስም የተጠነሰሰ የም/ብ ጉራጌ የሽብር ቡድን ሴራ የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ እንደማይወክልና አስቸኳይ ሊያጤነው ይገባል።
13/03/2023

መንግስት ይህን በሙሉ ጉራጌ ስም በፓርቲ ስም የተጠነሰሰ የም/ብ ጉራጌ የሽብር ቡድን ሴራ የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ እንደማይወክልና አስቸኳይ ሊያጤነው ይገባል።

ጎጎት የሚባል የፅንፈኛው የካድሬ ፖርቲ የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ አይወክልም🚫🚫❌❌👉የጎጎት ፓርቲ ዓላማው የህዝቦችን የመኖር ዋስትናቸው የሚያኮላሽ እምነት እና ማንት የሚያከስም ሽብርተኝነትን የሚ...
12/03/2023

ጎጎት የሚባል የፅንፈኛው የካድሬ ፖርቲ የምስራቅ ጉራጌ ህዝብ አይወክልም🚫🚫❌❌
👉የጎጎት ፓርቲ ዓላማው የህዝቦችን የመኖር ዋስትናቸው የሚያኮላሽ እምነት እና ማንት የሚያከስም ሽብርተኝነትን የሚረጭ እና የሚያስፋፋ የዜጎችን ሰላም የሚንድ የፅንፈኛ ፓርቲ ነው::

12/03/2023

1 እዣ 2 ቸሀ 3ጌቶ 4 ጉመር 5 ሙህር 6 እነሞር 7 አበሽጌ 8 እንደገኝ ማነው ጉራጌ ያልሆነው ለምን 7 ቤት ተባለ ለምን ስምንት ቤት አልተባለም ???
መልስ እፈልጋለው

🔴የምዕራብ ጉራጌ ክልል በእንሁን ትርክት ናፋቂነት ከጎጥ ጎሰኝነት ከሚተቻቹ ከ7 ቤት ጉራጌ ፅንፈኛ አመራሮች በሚመሩት ያልተገባ የፖሎቲካ ትምክተኝነትት መላው ጉራጌ ከህገ መንግስት እና ከብል...
08/03/2023

🔴የምዕራብ ጉራጌ ክልል በእንሁን ትርክት ናፋቂነት ከጎጥ ጎሰኝነት ከሚተቻቹ ከ7 ቤት ጉራጌ ፅንፈኛ አመራሮች በሚመሩት ያልተገባ የፖሎቲካ ትምክተኝነትት መላው ጉራጌ ከህገ መንግስት እና ከብልፅግና ፖርቲ ራዕይ እና ተልዕኮ እንዲላተም ተደርጎ በስመ ጉራጌ የሚነገድ እና የሚሸረብ የፖሎቲካ ሴራ የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች አይወክልም::

👉ምስራቅ ጉራጌ ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ይመሰረታል::ሃቁ ይሄ ነው👌ሰዓቱ⏰የእኛ ነው‼so use ur time properly.

06/03/2023

👉የመዋቀር አደረጃጀት ጥያቄ በጉራጌ ስም ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ጉራጌ ሰፊ እንደመሆኑ መጠን ምስራቅ ጉራጌ ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ይመሰረታል‼no more gurage zone administration

የሰባት ቤት የምዕራብ ጉራጌ የፅንፈኞች ሴራ የውሸት ትርክት በስመ ጉራጌ የሚነግዱት የክልል እንሁን ጥያቄ የመላው ጉራጌ ሳይሆን የከፊሉ የሰባት ቤት የምዕራብ ጉራጌ የፅንፈኞች ፍላጎት በመሆኑ...
06/03/2023

የሰባት ቤት የምዕራብ ጉራጌ የፅንፈኞች ሴራ የውሸት ትርክት በስመ ጉራጌ የሚነግዱት የክልል እንሁን ጥያቄ የመላው ጉራጌ ሳይሆን የከፊሉ የሰባት ቤት የምዕራብ ጉራጌ የፅንፈኞች ፍላጎት በመሆኑ የምስራቅ ጉራጌ ህዝቦች የማይወክል ነው:: ሃቁ ይሄ ነው👌

የጉራጌ ስነ ልቦና የሌላቸው የምዕራብ ጉራጌ የህልም ክልል አቀንቃኞች መስቃን እና ሶዶ ለማቃቃር የሚሞክሩ  ፀረ ጉራጌ  የምዕራብ እሊቶች አፀፋው ቢያከብዱ እንጂ ራዕያቸው ፈፅሞ አይሳካም።
06/03/2023

የጉራጌ ስነ ልቦና የሌላቸው የምዕራብ ጉራጌ የህልም ክልል አቀንቃኞች መስቃን እና ሶዶ ለማቃቃር የሚሞክሩ ፀረ ጉራጌ የምዕራብ እሊቶች አፀፋው ቢያከብዱ እንጂ ራዕያቸው ፈፅሞ አይሳካም።

@የህልም ክልል አቀንቃኝ ሰባት ቤቶቹ ሁልጊዜ የጫጫታ ጋጋታ ለሁልግዜ ላጫ ጋሩማ እንደዚህ አደረገን?""ላጫ ጋሩማ እንዲ አደረገን ብላቹ ምርር የምትሉት እንደ መሐመድ ጀማልና አምባሳደር ምስጋ...
04/03/2023

@የህልም ክልል አቀንቃኝ ሰባት ቤቶቹ ሁልጊዜ የጫጫታ ጋጋታ ለሁልግዜ ላጫ ጋሩማ እንደዚህ አደረገን?

""ላጫ ጋሩማ እንዲ አደረገን ብላቹ ምርር የምትሉት እንደ መሐመድ ጀማልና አምባሳደር ምስጋኑና መኩሪያ ሁለት ቦታ ስላልረገጠ ነው ወይስ ቸሃ ስለሆነ ይሆን??

ምድረ መንደርተኞች!!

"""የነመሐመድ ጀማልና ምስጋኖ አርጋ ተላላኪው አክቲቪስት ተስፋ ንዳም ሆነ ታረቀኝ ደግፌ ላጫ ጋሩማን የተሳደባቹት ያህል ለምን የነ መሐመድ ጀማል የነ ምስጋኖና ሞክሪያ ሀይሌን ስም አትጠሩም አትሳደቡም

""""አሁንም ቢሆን እንደበፊቱ መሐመድ ጀማልና ምስጋኖ እንደሚመሯቹ የማናውቅ አይምሰላቹ ይብላኝ ገዳዩን አቅፎ ለሚዞረውና ለሚቀልበው ብልፅግና ውስጥ ያለ የጥፋት ተባባሪው ርስቱ ይርዳ በዝለለው ለማለፍም ይሞክራሉ

እኛም የህልም ክልል አቀንቃኞቹ በተገቢው እናጋልጣለን ።

የምዕራብ ጉራጌ እሊቶች ወረዳ እና ቀበሌን የሚከፋፍሉ ፀረ ሰላም የጥፋት ሃይሎች የሚጠይቁት የክልል ልሁን ጥያቄ ምስራቅ ጉራጌን ፈፅሞ አይወክልም። በአጎራባች ዞኖችና ህዝቦች ዘላቂ ሰላም ለማ...
04/03/2023

የምዕራብ ጉራጌ እሊቶች ወረዳ እና ቀበሌን የሚከፋፍሉ ፀረ ሰላም የጥፋት ሃይሎች የሚጠይቁት የክልል ልሁን ጥያቄ ምስራቅ ጉራጌን ፈፅሞ አይወክልም።
በአጎራባች ዞኖችና ህዝቦች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ምስራቅ ጉራጌ ዞን ይመሰረታል።

ይህ ፍቅርአለም ከበደ የተባለ ፅንፈኛ ከምዕራብ ጉራጌ የህልም ክልል አቀንቃኞች ረብጣ ገንዘብ በመቀበል የሶዶ ክስታኔ ህዝብን ሀይማኖታዊ ግጭት ውስጥ እንዲገባ እና በመንግስት ላይ አመፅ እንዲ...
03/03/2023

ይህ ፍቅርአለም ከበደ የተባለ ፅንፈኛ ከምዕራብ ጉራጌ የህልም ክልል አቀንቃኞች ረብጣ ገንዘብ በመቀበል የሶዶ ክስታኔ ህዝብን ሀይማኖታዊ ግጭት ውስጥ እንዲገባ እና በመንግስት ላይ አመፅ እንዲቀሰቅስ ከአብን ፓርቲ ተልኮ ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፣ ስለሆነም መንግስት ይህ ፅንፈኛ ግለሰብ ባስቸኳይ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ይገባል።

09/02/2023

ይህ ሁላ ድንፋታ መንግስትን ገልብጦ ኃይማኖታዊ መንግስት ለማቋቋም መሆኑን ህዝብ እና መንግስትም ነቅቶዋል አይሳካምም❌❌❌❌

09/02/2023
በሞላ በሞላ ክፍት ቦታ ለናንተም ተይዞዋል
13/01/2023

በሞላ በሞላ ክፍት ቦታ ለናንተም ተይዞዋል

እድግ በል√√√መርቁት እስቲ
13/01/2023

እድግ በል√√√መርቁት እስቲ

13/01/2023

~ታዳጊው ብላቴናው የስድት አመቱ የአየር ኃይል ኮማንዶነት ራዕይ ያለው ኢትዮጵያዊው

06/01/2023

ኢትዮጵያዬ ውድድ ነው የማረግሽ እናንተስ?

~ኢትዮጵያዊነት  #በወለኔ ብሄረሰብ የባህል ልብስ ድምቅምቅ ብላለች!!!
09/12/2022

~ኢትዮጵያዊነት #በወለኔ ብሄረሰብ የባህል ልብስ ድምቅምቅ ብላለች!!!

¶ የፈራሹ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ አቶ ርዕስቱ ይርዳው እና የትውልድ አከባቢው ተወላጆችን¶ በክላስተር አደረጃጀት ጽ/ቤት ውስጥ ከ25ቱ አስፈፃሚዎች ውስጥ 5 የጉራጌን ክልል አስፈፃሚዎች ሰ...
21/11/2022

¶ የፈራሹ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ አቶ ርዕስቱ ይርዳው እና የትውልድ አከባቢው ተወላጆችን

¶ በክላስተር አደረጃጀት
ጽ/ቤት ውስጥ ከ25ቱ አስፈፃሚዎች ውስጥ 5 የጉራጌን ክልል አስፈፃሚዎች ሰግስጎ በማስገባት እየሰራው ያለውን ሽረባ

¶ የፌድራሉ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጪ የህዝብ እና የመንግስትን አደራ ወደ ጎን በመተው ከአዘጋጀው የትውልድ አከባቢው ልጆች ጋር

የምስራቅ ጉራጌ ዞን አደረጃጀት ጥያቄን እና የክላስተሩን መቀመጫ ወደ ጉብሬ ለመውሰድ እና ለማዳፈን ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል!

#ስለሆነም ይሄንን ግልፅ እኩይ ተግባር የደቡብ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በአቶ #እርስቱ _ #ይርዳውና በብልፅግና ጭብል የለበሱ አጋዥ ሹማምንቶች የሚሸረበው ተንኮል የፌድራሉ #መንግስት የሚደግፈውን የምስራቅ ጉራጌ ዞን አደረጃጀት ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ያስተካክል ዘንድ ጥቆማችንን አጥብቀን እናስተላልፋለን።

~የኢሬቻ በዓል ከመስቀል አደባባይ
01/10/2022

~የኢሬቻ በዓል ከመስቀል አደባባይ

የኢሬቻ በዓል ድባብ~ከአዲስ አበባ
30/09/2022

የኢሬቻ በዓል ድባብ~ከአዲስ አበባ

ሰላም~peace for all
30/09/2022

ሰላም~peace for all

05/05/2021

""" አለሁኝ እኔስ ለሃገሬ "" በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጀግናው አርበኛ የሃገር መከላከያ ስራዊት የድምፃዊ ቢልልኝ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ተለቆዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio victory time's media ኢትዮ ቪክተሪ ታይምስ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share