Ethio Celebrity Fan's

  • Home
  • Ethio Celebrity Fan's

Ethio Celebrity Fan's life is short😏 so make the most of it !!🤣❤️

👉ከንፁህ ና ጠንካራ ክር በእጅ የተሰራ ኮፍያ፣ ስካርብ፣ ኒካህ ና  ምንጣፍ በተመጣጣኝ ዋጋ በፈለጉት ከለር ና ዲዛይን  ከማንኛውም ልብስ ጋር የሚሄዱ ግርማ መገሱን የሚያለብሱ  በአጭር ጊዜ ...
15/11/2021

👉ከንፁህ ና ጠንካራ ክር በእጅ የተሰራ ኮፍያ፣ ስካርብ፣ ኒካህ ና ምንጣፍ በተመጣጣኝ ዋጋ በፈለጉት ከለር ና ዲዛይን ከማንኛውም ልብስ ጋር የሚሄዱ ግርማ መገሱን የሚያለብሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ

ይዘዙን ባሉበት ቦታ እናደርሳልለን

ለበለጠ መረጃ 👇

ስ.ቁ 0946670603

22/10/2021
አ.አ ጎላ ሠፈር ዮሴፍ ሞተር ቤት ፊትለፊት መንደር የምትኖር እፁብ አየለ ትባላለች የ15 ዓመት ወጣት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነች በጭንቅላት ቲቢ እና በጭንቅላት እጢ መሠቃየት ከጀመረች 6 ወሯ ...
15/06/2021

አ.አ ጎላ ሠፈር ዮሴፍ ሞተር ቤት ፊትለፊት መንደር የምትኖር እፁብ አየለ ትባላለች የ15 ዓመት ወጣት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነች በጭንቅላት ቲቢ እና በጭንቅላት እጢ መሠቃየት ከጀመረች 6 ወሯ ነው ቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል ከተኛች 4 ወሯ አትናገርም አትሠማም ራሷን ከሳተች 2ወሯ ነው

በአሁን ሰዓት ላይ ኤሲ ውስጥ ነው ያለችው ቤተሠብ ወላጅ እናቷ እዛው እየዋለች እያደረች የምታስታምም ስትሆን አሁን ግን መድሀኒት መግዣ መንቀሳቀሻ ቀለብ ቀሪ ቤተሠብ ማስተዳደር አልቻልኩም ልጄን በህይወት አትርፍሉኝ የተሻለ ሕክምና የተሻለ መድሀኒት እንድታገኝ በሀሳብም በገንዘብም እርዳታችሁ በፈጣሪ ስም አይለየኝ ትላለች ወላጅ እናቷ እያለቀሠች።

094 021 5213(ንብረት በሬቻ)
1000030804398 ( ንብረት በሬቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ምንጭ ቶለሳ ኢቢሳ

27/04/2021

👉መገፋት መልካም ነው የዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ አነቃቂ ንግግር👌 #ሼር

video credit arts tv world👇
https://www.youtube.com/channel/UCSnwxtpNr-2QupM0qi11Y6Q

26/04/2021

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ና ሰለሞን አለሙ የዛሬ 5 ዓመት በሰይፉ ሾው ያደረጉት ቆይታ!

ለአርቲስቱ ቤተሰቦችና አድናቂዎች መፅናናትን እንመኛለን😭😭

በ 2021 MTV አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት ላይ በአድማጮች ምርጫ ዘርፍ (Listener choice) ኢትዮጵያን ወክሎ ዳጊዲ ተመርጧል። እናም ውድድሩን ለማሸነፍ የኛ ድጋፍ ያስፈልገዋል።እስኪ ሁ...
25/01/2021

በ 2021 MTV አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት ላይ በአድማጮች ምርጫ ዘርፍ (Listener choice) ኢትዮጵያን ወክሎ ዳጊዲ ተመርጧል። እናም ውድድሩን ለማሸነፍ የኛ ድጋፍ ያስፈልገዋል።እስኪ ሁላችንም እዚህ👇link ላይ እየገባን እንምረጠው 👇👇

https://www.mtvmama.com/info/aljvas/vote

በሀዘን ላይ የመረረ ሀዘን ወደ ውስጥ ማልቀሴ በቃኝ .....አሁንስ እጮሃለሁ......ወደ አንድነት እንመጣለን ብለን ተስፋ ስንሰንቅ ......ምነው የአማራ በግፍ መቀጠፍ አልበቃ አለ ? ምነ...
24/12/2020

በሀዘን ላይ የመረረ ሀዘን
ወደ ውስጥ ማልቀሴ በቃኝ .....አሁንስ እጮሃለሁ......

ወደ አንድነት እንመጣለን ብለን ተስፋ ስንሰንቅ ......

ምነው የአማራ በግፍ መቀጠፍ አልበቃ አለ ?
ምነው የአማራ ሞት ሰቆቃ አልበቃ አለ ?
ምነው በየአቅጣጫው የአማራ ጨፍጫፊ በዛ ?
ምነው የአማራን ደም በየሜዳው ማፍሰሱን አላባራ አሉ ?
ምነው የአማራ የዘር ጭፍጨፋ ልክ አጣ ?
ምነው አማራን የወጋው ሰንኮፍ መርዙ አልነቀል አለ ?
ኧረ ያማል .....ሰቆቃው ያማል .....በዛ ....በአማራው ህዝብ ላይ በየአቅጣጫው የሚፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ማቆሚያ ጠፋለትሳ?
ጠዋት ማታ ከቤተሰቡ፣ ከመሬቱና ከከብቶቹ ጋር እየታገለ ኑሮን ለማሸነፍ የሚታትርን
የዋህ ገበሬ እየተሹለከለኩ የአረመኔነት ጫፍን በማሳየት መጨፍጭፍ ምን የሚሉት ጀግንነት ነው ? የጭካኔ ጥግ ማሳያ ነው ወይስ የፈሪነትን ልክ ?
ኧረ ይበቃል....ይበቃል ....
ኧኧይ አሁንስ በዛ......
ኧኧይ አሁንስ ልክ አጣ ......ጀግነቱና ቆራጥነቱ ሳያንሰው ....
የአማራ ህዝብ የመንግስትን ህግና መመሪያ ስለሚያከብር በየቦታው በአልባሌዎችና አላማ ቢሶች በግፍ መጨፍጭፍ አለበትን ?
መንግስት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የንፁሀን አማራን ደም
ዳግም ከመፍሰስ እንዲታደግ ብሎም የደም ምስ ያላቸውን አስጨፍጫፊና ጨፍጫፊዎች በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ እኔም እጮሃለሁ ።
እኔ እጮሃለሁ ...ሀዘኑ የተማችሁም አብረን እንጩህ

ሼር በማድረግ ተባበሩ አስቸኳይ_የእርዳታ_ጥሪ !ለሁሉም ሰው ለሆነ ሁሉ...እናት ልጇ ደርሶላት በመጦሪያዋ  # ፈተና ተጋፍጦባታል። በድህነት ያሳደገችውንጧሪ ልጇን የኩላሊት ህመም አልጋ ላይ ...
16/10/2020

ሼር በማድረግ ተባበሩ

አስቸኳይ_የእርዳታ_ጥሪ !

ለሁሉም ሰው ለሆነ ሁሉ...
እናት ልጇ ደርሶላት በመጦሪያዋ # ፈተና ተጋፍጦባታል። በድህነት ያሳደገችውን
ጧሪ ልጇን የኩላሊት ህመም አልጋ ላይ አውሎባታል።
ወጣቱ # ግዛቸው_ትኩ ይባላል። በሰሜን ወሎ ወልድያ ከተማ ተወልዶ ያደገ ልጅ ነው። በቅርቡም ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን
ተቀብሏል።

አባቱ በህይወት ባይኖሩም፣ እናቱ የምትችለውን ሁሉ ዋጋ ከፍላ ልጇን ከሰው እኩል አድርጋ የዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አስጨርሳዋለች። እናቱን ለማገዝ ስራ ሳይንቅ ሳይመርጥ ያገኘውን ሰርቶ ቤተሰቦቹንና እናቱን ለመደገፍ የወሰነው ወጣት ግዛቸው፣ በማህበር ተደራጅቶ ኮብል ስቶን የማንጠፍ ስራ ጀምሮ ነበር። እስከ ቅርብ ጊዜ ሁሉም ነገር ሰላም ነበር። በድንገት የተፈጠረው ነገር ግን የሁላችንንም ቅስም ሰብሮታል።

ግዛቸው በድንገት አሞት ለህክምና በሆደበት ወቅት፣ ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት
ማቆማቸውን እና በአስቸኳይ ዲያሊስስ እንዲጀምርና፣ በቅርቡም ውጭ ሀገር ሂዶ ንቅለ-ተከላ ማድረግ እንዳለበት በሃኪሞች ተረጋገጠ። በአሁኑ ወቅት የግዛቸውን ህይወት የመታደጉ ስራ ዲያሊስስ በማድረግ ተጀምሯል። ነገር ግን ይሄ ጊዜያዊ መፍትሄ ብቻ ነው። ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም
ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ከሀኪሞች ተረድተናል። ይሄን ለማድረግ ደግሞ ወጣቱም ሆነ ቤተሰቦቹ አቅም የላቸውም። የሁላችንንም እርዳታ ይፈልጋሉ።

ዛሬም ስለ # እናት እና ገና ብዙ መኖር ስላልጀመረው ወጣት ግዛቸው ስንል እጃችን ልንዘረጋላቸው ይገባል።
የዚህን ብርቱ ወጣት ህይወት ለመታደግ፣ የምትችሉትን ለማገዝ እንዲመችም በሶስት ባንኮች አካውንት ተከፍቶለታል። ከታች ያሉ አካውንቶችን ተጠቅመን ለህሊናችን ሰላም፣ ለነፍሳችንም በጎ ስንቅ እናኖር ዘንድ እለምናችኋለሁ።
# ዳሽን_ባንክ ➙ 5222 196 435 011
# የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ➙1000 345 116 145
# አዋሽ_ባንክ ➙ 01 320 834 382 901
በውጭ ሀገር የምትኖሩ ወንድምና እህቶችም በ gofundme የምትደግፉበትን
መንገድ ተመቻችቷል

ወንድማችን የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቶለታል ማገዝ የምትችሉ በማገዝ ማግዝ የማትችሉ ሼር በማድረግ ተባበሩ

https://gf.me/u/y273bw
https://www.gofundme.com/f/fund-raising-for-gizachew-tikus-kidney-transplant?utm_source=customer&utm_medium=copy_link_all&utm_campaign=p_cp+share-sheet

እንኳን ደስ አለህ ሙሌድምጻዊ ሙሉአለም ታከለ ከእህቶቹ ጋር
15/09/2020

እንኳን ደስ አለህ ሙሌ
ድምጻዊ ሙሉአለም ታከለ ከእህቶቹ ጋር

😍😍
31/08/2020

😍😍

Ruth Araya - ሩት አርአያ
30/08/2020

Ruth Araya - ሩት አርአያ

ለ ሂወት አስፈላጊ ከሆኑት መካከል አንደኛው ጥሩ ጓደኛ ነዉ ይባል የለ ጥሩ ጓደኛ መስታወት ነዉ .
29/08/2020

ለ ሂወት አስፈላጊ ከሆኑት መካከል አንደኛው ጥሩ ጓደኛ ነዉ ይባል የለ ጥሩ ጓደኛ መስታወት ነዉ .

✅✴   ✴✅ ይነበብ በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገል...
29/08/2020

✅✴ ✴✅ ይነበብ

በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል። ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው? ሲሉት።
ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው።

በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ።
ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?”

ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው። ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል።

ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት።

ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው።

በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስለተሰበረ ሳይወስዱት ቀሩ።

ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?”

ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” አላቸው ይባላል፡፡

🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵

🚺🚹

✅ ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን።

✅ ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን። የገበሬው አመለካከት እጅግ የሚደንቅ ነው።

ምርጥ መጣጥፎች
#ሟርርርር

እናትነት ክብር ነው😍
29/08/2020

እናትነት ክብር ነው😍

😍😍😍 .tibebu
28/08/2020

😍😍😍 .tibebu

መልካም ልደት አርቲስት ሄለን በድሉ🎂🎂🎂ከአርቲስት ሄለን በድሉ ጋር ልደታችሁን የምታከብሩ ሁሉ መልካም ልደት ብያለሁ
28/08/2020

መልካም ልደት አርቲስት ሄለን በድሉ🎂🎂🎂

ከአርቲስት ሄለን በድሉ ጋር ልደታችሁን የምታከብሩ ሁሉ መልካም ልደት ብያለሁ

👉አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።እንኳን ደስ አለሽ🙏🙏
27/08/2020

👉አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።
እንኳን ደስ አለሽ🙏🙏

ፍቅር ሰላም አንድነት ለሁሉም ሰው!
27/08/2020

ፍቅር ሰላም አንድነት ለሁሉም ሰው!

ብናገር ማን ያምነኛል ሁሉም ይፈርድብኛል ብልጥ ሁኚ ተገዢ ይሉኛል ሴት ልጅ ብልሀተኛ ናት ባልሽን በብልሀት ያዢው ይሉኛል.......ሴት ልጅ ልብ የላትም? አትሰበርም? አታዝንም? ተስፋ አትቆ...
29/06/2020

ብናገር ማን ያምነኛል ሁሉም ይፈርድብኛል ብልጥ ሁኚ ተገዢ ይሉኛል ሴት ልጅ ብልሀተኛ ናት ባልሽን በብልሀት ያዢው ይሉኛል.......ሴት ልጅ ልብ የላትም? አትሰበርም? አታዝንም? ተስፋ አትቆርጥም? መኖር አትጠላም? ተስፋዋ ሲነጠቅ ህልሟ ቅዠት ሲሆን ራሷን አትጠላም? ሴት ልጅ ማነው ሚስት ብቻ ያደረጋት ሴት ልጅ ሀገር የሀገር መጠሪያ እናት ናት ሴት ሳትከበር ሀገር አትኖርም፡፡


Boni's scary makeup

👉"አልጀዚራ ተቀጥሬ ብሰራም ባገኘሁት ዕድል ሁሉ የሀገሬን ጥቅም ለማስጠበቅ ምንም አያግደኝም"ዩስራ ሲራጅ
17/06/2020

👉"አልጀዚራ ተቀጥሬ ብሰራም ባገኘሁት ዕድል ሁሉ የሀገሬን ጥቅም ለማስጠበቅ ምንም አያግደኝም"
ዩስራ ሲራጅ

👉ዴክሳሜታሰን መድሃኒት የፅኑ ህሙማን ለማከመን ጥቅም ላይ መዋሉን በበጎ መልኩ እንደሚመለከተው የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።የዴክሳሜታሰን መድሃኒትን የመጀመሪያ ዙር ውጤት የኮቪድ 19 ፅኑ ...
17/06/2020

👉ዴክሳሜታሰን መድሃኒት የፅኑ ህሙማን ለማከመን ጥቅም ላይ መዋሉን በበጎ መልኩ እንደሚመለከተው የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዴክሳሜታሰን መድሃኒትን የመጀመሪያ ዙር ውጤት የኮቪድ 19 ፅኑ ህሙማን ህይወት ለመታደግ እንደሚስችል ድርጅቱ ገልጿል።

ድርጅቱ መድሃኒቱ በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱትን ታማሚዎች የመሞት እድልን የሚቀንስ መሆኑን የብሪታንያ ተመራማሪዎች ያወጡትን ውጤት እንደሚገራም አስታውቀዋል።

ይህ መድሃኒት በፅኑ ህመም ላይ የሚገኙ የኮቪድ 19 ተያዦችን ለማከም እንደሚውል ያስታወቀው ድርጀቱ ህመሙ ላልጠከረባቸው ሰዎች ግን አይመከርም ብሏል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱትን ታማሚዎች የመሞት እድል ለመቀነስ የሚያስችል የመጀመሪያው መድሃኒት መሆኑን ገልፀዋል።

የዴክሳሜታሰን መድሃኒት ከፈረንጆቹ 1960 ጀምሮ ለተለያዩ ህክምናዎች ጥቅም ላይ ሲውል እንደነበረ ነው የአለም ጤና ድርጅት ያስታወቀው።

የአለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያውን የጥናቱን ውጤት እንደደረሰው በመግለፅ በቀጣይ ቀናትም ከመድሃኒቱ ጋር ተያይዞ ሙሉ ትንተና እንደሚያደርግ ነው የገለፀው።
መድሃኒቱን ለኮቪድ 19 መቼ እና እንዴት ጥቅም ላይ መዋል እንደሚገባም በቀጣይ አሳውቃለሁ ብሏል።

ከሚሊኒየም ማገገሚያ ማዕከል ከኮሮና ያገገሙ ሰዎች በፎቶ
16/06/2020

ከሚሊኒየም ማገገሚያ ማዕከል ከኮሮና ያገገሙ ሰዎች በፎቶ

ተስፋን ይሰጣል🙏👉ዴክሳሜታሰን መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት እንደሚታደግ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁበአነስተኛ ዋጋ በስፋት የሚገኘው “ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድ...
16/06/2020

ተስፋን ይሰጣል🙏

👉ዴክሳሜታሰን መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት እንደሚታደግ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ

በአነስተኛ ዋጋ በስፋት የሚገኘው “ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታገድ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ።

እንደተመራማሪዎቹ ገለፃ በመድሃኒቱ በአነስተኛ ዶዝ በሚሰጠው የስቴሮይድ ህክምና የኮሮና ቫይረስን በመዋጋት ሂደት ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣ ነው።

መድሃኒቱ በተለይም በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱትን ታማሚዎች የመሞት እድልን የሚቀንስ መሆኑንም አስታውቀዋል።

👉ዛሬ 118 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋልበኢትዮጵያ ተጨማሪ 109  ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ በበሽታው የተጨማሪ 1  ሰው ሕይወት አለፈባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5102...
16/06/2020

👉ዛሬ 118 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ በበሽታው የተጨማሪ 1 ሰው ሕይወት አለፈ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5102 የላቦራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3630 ደርሷል።

"ልጄን በቀለሟ  የሚያገል ህግን እልደግፍም" አንጀሊና ****     እውቅ አሜሪካዊት የሲኒማ ተዋኒት፣ዳይሬክተር እና የስብአዊ አገልግሎት አምባሳደር አንጀሊና ጁሊይ ለእርሷ እና መሰል  ነጮ...
16/06/2020

"ልጄን በቀለሟ የሚያገል ህግን እልደግፍም" አንጀሊና
****
እውቅ አሜሪካዊት የሲኒማ ተዋኒት፣ዳይሬክተር እና የስብአዊ አገልግሎት አምባሳደር አንጀሊና ጁሊይ ለእርሷ እና መሰል ነጮች ብቻ የቆመ፣በተቃራኒው የእርሷን ትውልደ ኢትዬጵያዊት ሴት ልጅን ሆነ ሌሎችን በቆዳቸው ቀለም መጥቆር ብቻ የማያከብር ህግን እንደማትደግፍ ተናገረች።

የአርባ አምስት አመቷ የኦስካር ተሸላሚዋ ፣አንጀሊና ሃርፐር ባዛር ዩኬ ከተባለ መጽሔት ጋር ባለፈው አርብ እለት ባደረገችው ቃል ልምልልስ"ለእኔ ጥብቃ ያሚያደርግ ፣ ነገር ግን ለሴት ልጄ(ዘሃራ) ፣ለሌሎች ወንዶች እና ሴቶች በቆዳቸው ቀለም መጥቆር ብቻ የሚያገል ስርዓትን(ሲስተም)አልታገሰውም" በማለት ዘረኝነት ከስድስት ወሯ ጀምሮ ያሳደገቻት የትውልደ ኢትዮጵያዉቷ፣ ዘሀራን እጣ ፈንታን ጭምር ሊያጠቃ እንደሚችል አቋሟን ገልጻለች ።

ለዘረኝነት ሰለባዎች እና ተጠቂዎች ከንፈር ከማምጠጥ እና ሀዘንን ከመግለጽ ባሻገር ፣ፖሊሲዎች እና ህጎች መቀየር እንዳለባቸው የተናገረችው አንጀሊና በአሜሪካው ሚኒሶታ ግዛት በጥቁር አሜሪካዊው ፣ጆርጅ ፍሎይድ ላይ ባለፈው ግንቦት 25,2020 እኤአ በነጭ ዘረኞ ፖሊሶች በግፍ መግደል ያስቆጣት መሆኑን የገለጸች ሲሆን "በአሜሪካ የተጀመረው የተጠያቂነት እንቅስቃሴ ጥሩ ጅማሮ ነው፣እንቅስቃሴው በማህበረሰቡ ውስጥ፣በትምህርት ቤት እና በፖለቲካው ውስጥ ሊሰርጽ ይገባል"ስትል አቋሟን ገልጻለች።

የጥቁሮች መብት ያገባናል/ብላክ ላይፍ ማተርስ/ የሚለው አለማቀፋዊ እንቅስቃሴ አውቆ የተኛው የአለም ህዝብን የቀስቀሰ ታላቅ ለውጥ መሆኑን የጠቆመችው አንጀሊና"በገዛ አገራቸው እንደ ባይተዋር የተቆጠሩ ጥቁር አሜሪካኖች ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል፣ተቋማቱም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋቸዋል" ስትል ጥሪ አቅርባለች።

ከቀድሞው ባላቤቷ ከታዋቂው የሲኒማ ተዋኒው ብራድ ፔቲት ከወለዷቸው ሶስት ልጆች በተጨማሪ የአስራ አምስት አመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዘሃራን ጨምሮ ስድስት ልጆች አፍርተዋል።

 #ጣና ከመታመም አልፎ እየሞተ ነው ‼ ድማፃችንን በማሰማት መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እናድርግ    ጣና ጠፍቶ እኛ መኖር አንችልም ✊
15/06/2020

#ጣና ከመታመም አልፎ እየሞተ ነው ‼

ድማፃችንን በማሰማት መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እናድርግ

ጣና ጠፍቶ እኛ መኖር አንችልም ✊

+ 50 = 545ተመሠገን ፈጣሪ!!!ዛሬ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 50 ሠዎች ከቫይረሱ አገግመዉ በሠላም በደሥታ ከቤተሰቦቻቸዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር ተቀላቅለዋልበድምሩም እሥካሁን 545 ሠዎች አገግመዋልእ...
14/06/2020

+ 50 = 545

ተመሠገን ፈጣሪ!!!

ዛሬ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 50 ሠዎች ከቫይረሱ አገግመዉ በሠላም በደሥታ ከቤተሰቦቻቸዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር ተቀላቅለዋል

በድምሩም እሥካሁን 545 ሠዎች አገግመዋል

እንኳን 50 ሠዉ ይቅርና 1 ሠዉ እንኳን ከዚህ ወጥመድ አምልጦ ከቤተሠቡ ጋር ሲቀላቀል ያሥደሥታል

እሥቲ ይልመድባችሁ ፈጣሪን እናመሥግነዉ
እግዚአብሔር ይመሥገን በሉ!!!!

ዛሬ የአለም ደም ለጋሾች ቀን ነው! የኮሮና ወረርሽን በሃገራችን መከሰቱን ተከትሎ የደም ክምችት እጥረት ተከስቷል። ደም በመለገስ ህይወትን ማዳን ትልቅ ስጦታ ነው። በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የደ...
14/06/2020

ዛሬ የአለም ደም ለጋሾች ቀን ነው!

የኮሮና ወረርሽን በሃገራችን መከሰቱን ተከትሎ የደም ክምችት እጥረት ተከስቷል። ደም በመለገስ ህይወትን ማዳን ትልቅ ስጦታ ነው። በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የደም ባንክ ሄደው ደም ይለግሱ።

249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ተመለሱ**************************249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ዛሬ ተመልሰዋል።እነዚህ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ...
13/06/2020

249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ተመለሱ

**************************

249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ዛሬ ተመልሰዋል።

እነዚህ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዛሬ የመጡትን ጨምሮ እስካሁን በችግር ምክንያት በመጠለያ የነበሩ 748 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Via - EBC

👉ጥበብ ከመሸማቀቅና ከመታቀብ የተላቀቀችው በአብይ ሥርዓት ነውዶ/ር አብይን እንድቃወም የሚጋብዘኝ ምንም በቂ ምክንያት አላገኝም።በየትኛውም ጊዜ አለመረጋጋቶች ነበሩ ይኖራሉም።ነገር ግን ከሌላ...
09/06/2020

👉ጥበብ ከመሸማቀቅና ከመታቀብ የተላቀቀችው በአብይ ሥርዓት ነው

ዶ/ር አብይን እንድቃወም የሚጋብዘኝ ምንም በቂ ምክንያት አላገኝም።በየትኛውም ጊዜ አለመረጋጋቶች ነበሩ ይኖራሉም።ነገር ግን ከሌላ ጊዜ አንጻር ይህ በጣም የተረጋጋ ጊዜ ነው።በተለይ ለእኛ የእሱ መምጣት አዲስ ምዕራፍ ነው።ጥበብ ከመሸማቀቅና ከመታቀብ የተላቀቀችሁም በዚሁ ሥርዓት ነው። ፖለቲካ ነው ብለን የምንቆርጠው ፓርት ሥራዎቻችን ውስጥ ቀርተዋል። ይህ ለእኔ ትልቅ ለውጥ ነው።

አርቲስት ሠለሞን ቦጋለ

👉ጥንቃቄ አይለየንዛሬ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸውበዛሬው እለት 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወ...
07/06/2020

👉ጥንቃቄ አይለየን

ዛሬ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በዛሬው እለት 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል

63 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል በአጠቃላይ ያጉሙ ቁጥር 344 ደርሷል

👉ትውልድን በተግባር መቅረፅ እንዲህ ነው❤️
06/06/2020

👉ትውልድን በተግባር መቅረፅ እንዲህ ነው❤️

100 ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4950 የላብራቶሪ ምርመራ 100 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ እነሱም :-* 3ቱ ሰዎች የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው* 35 ሰዎች...
28/05/2020

100 ሰዎች

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4950 የላብራቶሪ ምርመራ

100 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

እነሱም :-

* 3ቱ ሰዎች የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

* 35 ሰዎች በሽታው ከያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

* 62 ቱ ሰዎች የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በሽታው ከያዘው ሰው ጋር ንከኪ የሌላቸው

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር

831 ደርሷል፡፡

* 53 ወንዶች
* 47 ሴቶች ናቸው

* 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ
* 1 ሰው ከትግራይ ክልል
* 2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል
* 3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

ቤሩት 🇱🇧🇱🇧🇱🇧ታዋቂው የአሜሪካኑ Yahoo News ስለ ቤሩት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ና ትልቅ ጉዳይ ሀገሮች እንዲሰጡ ሀገሮች ህዝቦቻቸውን በጊዜው ወደ ሀገራቸው እንዲያስወጡ አለበለዚያ ግን ት...
25/05/2020

ቤሩት 🇱🇧🇱🇧🇱🇧

ታዋቂው የአሜሪካኑ Yahoo News ስለ ቤሩት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ና ትልቅ ጉዳይ ሀገሮች እንዲሰጡ

ሀገሮች ህዝቦቻቸውን በጊዜው ወደ ሀገራቸው እንዲያስወጡ አለበለዚያ ግን ትልቅ ችግር ይከሰታል ሲል ዘግቧል

አክለው አሁን ባለው ደረጀ ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች በጭንቀት በሽታ እየተሰቃዩ እና ችግር በጊዜው ካልተወገደ አሰከፊ ችግር ሊደርስ ይችላል ብሏል

ኢትዮጵያ ያሉ የመንግስት ሚዲያዎች እስካሁን ስለ ቤሩት ላሉት ኢትዮጵያውያን ምንም ያሉት ነገር የለም እየሱም እያዳመጡ ምንም አየነት ዘገባም አልሰረሙ

ቃና ቲቪ ብቻ ነው እስካሁን ቤሩት ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን ዘገባ የሰራው

ሼር አድርጉላቸው ከአሜሪካ የአሜሪካው Yahoo News እንኳን ስለ ቤሩት ዘገባ ሰርቷል በሏቸው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Celebrity Fan's posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Celebrity Fan's:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share