Imala Badhaadhinaa

  • Home
  • Imala Badhaadhinaa

Imala Badhaadhinaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Imala Badhaadhinaa, Digital creator, .

05/11/2023

ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ለሀገረ መንግስት ግንባታዉ ከፍተኛ ፋይዳ ኣለዉ።

ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነት እየተጠናከረ ሊሄድ የሚችለው ደግሞ የብሔር ማንነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀው ሲጓዙ ነዉ።

የብሔር፣የቋንቋ፣የባህል፣የሃይማኖት፣የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ..ብዝሃነት በገነባት ኢትዮጵያ ሚዛናዊነትን ያረጋገጠ ፣ከፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ተግባር የተጠበቀ የፖለቲካ እሳቤን ባህል ማድረግ ኢትዮጵያን ለማፅናት መሠረት ነዉ።

ፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ድርጊት ሚዛናዊነትን በማዛባት፣አካታችነትን በማሳሳት ወደ አግላይነት ያሸጋግራል ።

አግላይነት ወደ ጠቅላይነት በማምራት ብዝሃነትን ለመቀበል፣ለማክበር እና ለማስተናገድ ተግዳሮት ይሆናል።በዚህም መነሻ ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባቱን ዕድል ይፈትነዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የብሔር ማንነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀዉ እንዲራመዱ በማድረግ በሂደቱም ጠንካራ አገረ መንግስት መገንባትን መሠረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል ።

ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትመች፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ያበበባት አገር እንድትሆን ብልጽግና ተግቶ ይሠራል ።

ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህ ሁሉንም ብዝሃነቶች የማስተናገድ የመሀል የፖለቲካ አስተሳሰብና ተግባር ነዉ።

ፅንፈኝነት ኢትዮጵያን ከማዳከም ያለፈ ዉጤት እንደማያስገኝ ከዚህ በፊት የፈተኑንን ችግሮች ዞር ብሎ በማየት መገንዘብ እንችላለን። የዘርፈ ብዙ ፀጋዎች ሀገር ኢትዮጵያ ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህን እና ሙሉዕ እይታን በማጠናከር የለዉጥ ጉዞዋን እንድታፋጥን የዜግነት አደራ አለብንና የየበኩላችንን እናበርክት ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Imala Badhaadhinaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share