Ethio Information Center

  • Home
  • Ethio Information Center

Ethio Information Center Together we can!

06/08/2023

መካላከያን የነካ የለውም በረካ!!!!

05/08/2023

"ጦርነት መፍትኄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ!"

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ።

***

ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሃገራችን አንዳንድ አከባቢዎችና በተለይም በአማራ ክልል

ከዕለት ወደ ዕለት ተባብሶ የቀጠለውን የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታ በአንከሮ እየተከታተለው ይገኛል።

በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ካደረሰብን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገና በቅጡ እንኳ ባላገገምንበት በዚህ ወቅት፣ ዳግም ወደ ሌላ መጠነ ሰፊ የእርስ በርስ ግጭት መግባት በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰው ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ ልቡናዊ ጉዳት በእጅጉ የሚያሳስብ ነው።

ጦርነት ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብኣዊ እልቂትን እና ቁሳዊ ውድመትን ከማስከተል በቀር፣ ለችግሮቻችን መፍትኄ እንደማያስገኝ ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው። ይልቁንም በሀገር ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት የሀገር አንድነት ፀንቶ የቆመባቸውን የእሴት እምዶች በማፍረስ የሕዝባችንን አንድነት የሚንድ በመኾኑ፣ ሁሉም አካላት ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡና ወደ ውይይት መምጣት የሚቻልበትን መላ እንዲያፈላልጉ ምክር ቤታችን በአንክሮ ለማሳሰብ ይወዳል።

ስለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ እጅግ አውዳሚና አክሳሪ ከኾነው ጦርነት የችግር መፍትኄን ከመጠበቅ ይልቅ፣ በአስቸኳይ ወደ ውይይት እንዲመጡ ጠቅላይ ምክር ቤታችን ይህን የሰላም ጥሪያችንን እያቀረብን ይህ እንዲሳካ ምከር ቤታችን አስፈላጊውን ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

አዲስ አበባ

ሐምሌ 29 ቀን 2015

05/08/2023
05/08/2023

ጃዊሳ !

05/08/2023

አቶ ክርስቲያን ታደለ በፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

| የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ አርብ ምሽት፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለ #ቢቢሲ አረጋገጡ።

አርብ ምሽት 3፡30 አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ በርካታ ፖሊሶች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ተወካይ የሆኑት አቶ ክርስቲያንን አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው “በኃይል አፍነው” መውሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት “በአጥር ዘለው በመግባት” ወደ ቤታቸው መግባታቸውን እና አቶ ክርስቲያንን እና አንዳንድ ነገሮችን ይዘው መውሰዳቸውን የአቶ ክርስቲያን ባለቤት እናት ወ/ሮ ዛብሽወርቅ ካሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በወቅቱ አቶ ክርስቲያንም “እኔ ሕጋዊ ሰው ነኝ፣ ለምንድን ነው የምትፈልጉኝ? ብሎ ሲያናግራቸው ከፖሊሶቹ መካከል አንደኛው በቦክስ ደበደበው” በማለት በቦታው የነበሩት እኚሁ የቅርብ ቤተሰብ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሌላኛዋ የፖሊስ ባልደረባ ደግሞ ወደ ቤት ውስጥ ዘልቃ በመግባት “የቤተሰቡን ፓስፖርት አንድ ላይ ሰብስባ ወስዳለች” ብለዋል።

የፖሊስ አባላቱ ከሁለቱ በስተቀር ሌሎቹ የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ መሆናቸውን የተናገሩት የአቶ ክርስቲያን ቤተሰቦች፣ “ሁኔታውን ለማስረዳት ብንሞክርም መሣሪያ ደቅነው አስጠነቀቁን” ብለዋል።

ዛሬ [ቅዳሜ] ጠዋት 2፡30 አካባቢ ደግሞ ሌሎች ፖሊሶች አቶ ክርስቲያንን ይዘው ወደ ቤት በመመለስ ፍተሻ ማድረጋቸውንም ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።

“የዛሬዎቹ ፖሊሶች ሥነ ሥርዓት አላቸው” ያሉት ቤተሰቦቹ፣ ጎረቤት እና የአቶ ክርስቲያን ቤተሰቦች በተገኙበት ፍተሻ አካሂደው እና አስፈርመው ከአቶ ክርስቲያን ጋር ተመልሰው መሄዳቸውን ተናግረዋል።

አቶ ክርስቲያ ታደለ በተመረጡበት የአማራ ክልል ውስጥ ባለፉት ቀናት በተባባሰው የፀጥታ ችግር ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተደነገገበት ሲሆን፣ የክልሉን ፀጥታ ለማስከበር እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ የፌደራል መንግሥቱ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

አቶ ክርስቲያን በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ሲውሉ በምክር ቤት አባልነታቸው ያለመከሰስ መብታቸው ስለመነሳቱ እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ስለመያያዙ የታወቀ ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 29/2015 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ከትናንት አርብ ጀምሮ “ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ስምሪት የሚሰጡ፣ በተለያየ መንገድ ችግሩን የሚያባብሱ ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ማድረግ ተጀምሯል” ያሉ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈጻሚ አካል የሚወሰዱ እርምጃዎችን በቀጣይ ቀናት እንደሚያሳውቅም ገልጸዋል።

አቶ ክርስቲያን በአማራ ክልል ያለው ቀውስ በተባባሰበት ጊዜ ከሁለት ቀናት በፊት “የዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራ እና የንፁሃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስባለሁ” በማለት ሌሎች አካላትም ድርጊቱን እንዲያወግዙ ጠይቀው ነበር።

በቅርቡ በተደረጉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባዔዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ከሥልጣን ይልቀቁ” በሚል በመሞገት እና ገዢውን ፓርቲ የብልጽግና አስተዳደርንም ሲተቹ ይደመጣሉ። በማኅበራዊ ሚዲያም ላይ እንዲሁም መንግሥትን የሚተቹ ጽሁፎች ይጽፋሉ።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ የምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክትር ካሳ ተሻገር እኩለ ሌሊት ላይ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ “ፓሊሶች ነን የሚሉ በሌሊት መጥተው ክፈት እየተባልኩ ነው!!” የሚል መልዕክት አስፍረው ነበር።

ቀጥሎ ስለተፈጠረው ነገር ለማወቅ ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የዶክተር ካሳን ባለቤት ለማናገር በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። ለግለሰቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እሳቸውም መታሰራቸውን ቢገልጹም ቢቢሲ ማረጋገጥ አልቻለም።

BBC

05/08/2023

ህብረተሰቡ ከህግና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያሏት ሀገር ነች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶች እያጋጠሙ መሆኑን የተመለከተ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

በከተማችን አንዳንድ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች የሀገሪቷን ህግ በሚጥስና ከማህበረሰቡ ወግ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ መኖሩን መረጃዎች እያመለከቱ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቀዋል፡፡

ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ፖሊስ በሚደርሰው መረጃ በመመስረት በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድ እያስታወቀ በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር የሚጠረጠሩ ሆቴል ቤቶች እና ሬስቶራንቶች የሀገርቷን ህግ አክብረው የመስራት ግዴታ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማኝኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ በተጨማሪም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

05/08/2023

የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት የህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ከአርቲስት እስከ አክቲቪስት እና ጋዜጠኛ... የመከላክያ ልብስ በመልበስ ዘመቻው ደግፎ ነበር::

ዛሬ በአማራ ክልል ጥጋብ ወጥሯቸው የስልጣን ጥማት ይዟቸው ከእውነተኛው ታጋይዮች (ፋኖ) በተለየ መልኩ የፋኖን ስም ይዘው ሊያውም በከተማ ውስጥ ለህዝቡ ሳያስቡ ሽምቅ ውጊያን የከፈቱ ጽንፈኞች ላይ መከላክያ የህግ ማስከበር ዘመቻውን ሲያከናውን ኡኡታቸውን እያቀለጡት ነው::

ለነሱ ህግ ማስከበር ማለት በትግራይ (ወያኔ) በኦሮሚያ (ሸኔ) ላይ ሲሆን ትክክል በአማራ (ፋኖ) ትክክል አይደለም እያሉን መከላክያ ተማረከ ሸሸ በማለት ፕሮፓጋንዳ ከመለፈፍ አልፈው መከላክያን እየኮነኑ ነው:: እነዚህ የአዞ እንባ ያላቸውን ቁራዎች አስመሳዮችን ውስጣቸው ያለውን የውሸት ኢትዮጵያዊ ነን ባዮችን እጸየፋለሁ እንዲህ አይነት ሾተላይ የሆነ ኢትዮጵያዊነት በአፍንጫዬ ይውጣ!!!! ውስጣችሁ ያለው ጥላቻችሁን አሁን በግልጽ እየተመለከትን ነው በግሌ እኔ በሚገባ እየተገነዘብኩኝ ነው:: ሾተላዮች!!!

05/08/2023

ዶክተሩ በድንገት ተደውሎለት ለአስቸኳይ የቀዶ ህክምና በጥድፊያ ወደ ሆስፒታሉ እየገባ ነው።

በተቻለው አቅም የስልክ ጥሪውን በአግባቡ አስተናግዷል። የህክምና ልብሱን በአስቸኳይ ቀይሮ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እያመራ ሳለ ኮሪደሩ ላይ የዶክተሩን መምጣት እየተንጎራደደ ይጠብቀው የነበረውን ሰው አገኘው።

"እንዴት ለመምጣት ይህን ያህል ግዜ ይፈጅብሀል? የልጄ ህይወት ልትጠፋ አደጋ ላይ እንዳለች አይታይህም? ህሊና የለህም?" ብሎ ዶክተሩ ላይ ጮኸበት።

ዶክተሩም በትንሹ ፈገግ አለና ,,,,
"አዝናለሁ ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም። የስልኩን ጥሪ ከተቀበልኩ በሗላ በቻልኩት ፍጥነት እዚህ ለመድረስ ጥሬያለሁ አሁን አንተም ብትረጋጋ እኔም ስራዬን ብሰራ መልካም ነው" ብሎ ሊያረጋጋው ሞከረ።

ሰውየው ግን ,,,
"ተረጋጋ ነው ያልከው? ያንተ ልጅ ቢሆንስ አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ሆኖ ትረጋጋ ነበር? ልጅህ ቢሞት ምን ታደርግ ነበር?" አለ አባት በቁጣ።

ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ መለሰለት
"የአምላክ ፈቃድ ይሁን። ዶክተር ህይወት ሊያራዝም ሊያጠፋም ሊተካም አይችልም ግን የቻልነውን ያህል እንጥራለን። እንደ አምላክ ፍቃድ ልጅህም ይድንልሀል አንተ ብቻ ተረጋጋ" አለው አሁንም ፈገግ እያለ።

ሰውየውም ,,,
" ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው" እያለ አጉረመረመ። ቀዶ ጥገናውም የተወሰነ ሰዓታትን ወስዶ በሰላም ተጠናቀቀ ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ወጣ።

ለአባትየውም ,,,,
"ፈጣሪ ይመስገን ልጅህ ተርፏል።" ብሎት የአባትየውን መልስ ሳይጠብቅ "ማንኛውም ጥያቄ ካለህ ሌሎች ረዳት ዶክተሮችን መጠየቅ ትችላህ።" ብሎት ዶክተሩ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ።

የልጁም አባት "ለምንድነው ዶክተሩ እንደዚህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው? ምናለ አሁን አንድ ደቂቃ ስለ ልጄ ሁኔታ ብጠይቀው?" ሲል ተናገረ።

ይህን የሰማችው ነርስ እንባ በጉንጮቿ እየጎረፈ ,,,,
"ትላንት ነበር የዶክተሩ ልጅ በመኪና አደጋ የሞተው። ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት የልጁ ቀብር ላይ ነበር አሁን ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ የራሱን ልጅ ደግሞ የቀብር ስርዓት ሊጨርስ በሩጫ ሄደ።" አለችው።

አባት ከሰዓታት በፊት ዶክተሩ ያሳየውን ፈገግታ እያሰበ ተንሰቀሰቀ። የፀፀት ለቅሶ፤አንድ ሰው ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሳታውቅ ለመፍረድ አትቸኩል።

"ቀድሞ መፍረድ ለህሊና ፀፀት ይዳርጋል"
⛲⛲ምንጭ አንድ ለመንገድ

05/08/2023

አሜሪካ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ብሊንከን በዚሁ ውቅት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ስጋት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የእርዳታ እህል በፍትሃዊ መንገድ በሚቀርብበት መንገድ ላይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር መክረዋል።
በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶችንም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል ተብሏል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

05/08/2023

ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ከሕዝብ አብራክ የተገኘ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጋሻ ነው

ጥቂት መረን የለቀቁ የመንደር አጉራ-ዘለሎች፤ ኢትዮጵያን ከብተና እና ሕዝቧን ከአደገኛ እልቂት የታደገውን፤ ጀግናውን፣ ትንታጉንና አይበገሬውን፤ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ አለኝታና መከታውን፤ የምስራቅ አፍሪካ ኃያል ክንዱን፤ በእነርሱ ሸውራራ መነፅር ያሳነሱት እየመሰላቸው፤ በየማህበራዊ ሚዲያው "አራምባና ቆቦ" የውሸት ትርክት ሲዘበዝቡ መመልከት ያስገርማል፤ ያስቃልም። የኢትዮጵያዊያን የቁርጥ ቀን ልጆችን ስም በማጠልሸት አሊያም ወደ እርሱ በመተኮስ የሚገኝ ድልም ሆነ ነፃነት ከቶም አይኖርም።

በባዶ ወታደራዊ ቁመና መከላከያ ሠራዊታችንን በተግባር ሳይሆን በፌስቡክ ቅብጥርጥሮሽ ለመገዳደር መሞከር "ላም አለኝ በሰማይ" ዓይነት የሞኝ ተረት ከመሆን አይዘልም‼️እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በዚህ አስገራሚና አስቂኝ መንገድ የሚገኝ ነፃነትም ሆነ ድል ሊኖር እንደማይችል በሰከነ መንፈስ መረዳት ብልህነት ይመስለኛል‼️

በአማራ ክልል እየተመለከትን ያለነውና "በፋኖ" ስም እየተፈፀመ ያለው የቀን ቅዠት፤ የትም የማያደርስና ሽቅብ የመሽናት ያህል ነውረኛ ድርጊት ከመሆን ያለፈ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ማንኛውም ሕሊና ያለው ሰው፤ ከትናንቱ የእነ ህወሓት ሕዝብ አስጨራሽ የመከነ መንገድ መማር ያለበት ይመስለኛል። ህወሓትም ሆነ ሸኔ ሕዝባቸውን ስለ ጦርነት ሲሰብኩ ቢከርሙም፤ ለሕዝባቸው ሞት፣ የሠላምና የልማት እጦት እንዲሁም ስቃይና ሰቆቃ ከመደገስ ውጭ ያስገኙለት አንዳችም ነገር የለም። ሕዝባቸው በእነርሱ ቀረርቶ፣ ፉከራና ሽለላ ያገኘው ነፃነትም ሆነ ድል አልነበረም፤ አሁንም የለም‼️

በአማራ ክልል የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙት፣ "ቆመህ ጠብቀኝ" እና ጓንዴ መሳሪያዎችን ይዘው በባዶ ሜዳ ላይ በየፈፋው የሚሸልሉትና የሚፎክሩት እንዲሁም ለሕዝብና ለሀገር ሲል የሚሰዋውን መከላከያ ሠራዊታችንን የሚተነኩሱት፤ ሕዝቡን የማይወክሉ ጥቂት የሥልጣን ጥመኞች መሆናቸውን በአደባባይ እየነገሩን ነው። እነዚህ አካላት የአማራን ሕዝብ እንደ መደበቂያ ምሽግ የሚጠቀሙና "ግባችን የሥርዓት ለውጥ ነው" በሚል ነፍጥ አንግበው፣ ሥልጣንን በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ሳይሆን በኃይል ለመያዝ የቋመጡ የጎበዝ አለቃዎች መሆናቸውን በይፋ እየተናገሩ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከምርጫ ውጭ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግ ሩጫ መቅረቱን እነዚህ ሰዎች አልሰሙም አሊያም እያወቁ "ጆሮ ዳባ ልበስ" ያሉ አላዋቂ ሳሚዎች ናቸው። ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ደግሞ፤ ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ፀረ-ሠላም ኃይሎች የመጠበቅ ሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ የተሰጠው አካል ነው። እናም ሚዛናዊው፣ ሠላም ወዳዱና አርቆ አሳቢው የአማራ ሕዝብ፤ በእነዚህ "ሥልጣን ወይም ሞት" ባይ የመንደር አውደልዳዮች፤ ሠላሙ እንዲናጋ፣ ልማቱ እንዲደናቀፍና ማህበራዊ መስተጋብሩ እንዲስተጓጎል ፈፅሞ መፍቀድ የለበትም። ስለሆነም የመንደር ወጠጤዎችን አደብ ማስገዛት ይኖርበታል። ለዚህም ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ከሚያከናውነው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባር ጎን በመሰለፍ የሠላሙ ጠባቂ መሆን ይኖርበታል‼️

ሠላም ለኢትዮጵያ፤ ሠላም ለሕዝቧ‼️

05/08/2023

የዓይናችን ብሌን በሆነው መከላከያ ሠራዊታችን ፈፅሞ አንደራደርም‼

"የአበራሽን ጠባሳ ያየ፣ በእሳት አይጫወትም‼"
አይበገሬው መከላከያ ሠራዊታችን የኢትዮጵያ ካዝማ እና ማገር ነው። አለኝታችን፣ ብሔራዊ ኩራታችን እንዲሁም ለእኛ ሠላምና ደህንነት ሲል ሌት ተቀን በቁርና በሐሩር እየማሰነ ዳግም የማትገኝ ሕይወቱን የሚሰዋ ብርቅዬ ክንዳችን ነው። ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችንን የነካ የመላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጠላት ነው‼የዓይናችን ብሌን በሆነው ሠራዊታችን ለአፍታም ቢሆን አንደራደርም‼ተሳስቶም እንኳን ቢሆን፤ ሳተናው መከላከያ ሠራዊታችንን የነካ፤ በአንድ ነገር ርግጠኛ መሆን ይችላል። ይኸውም ግብዓተ-መሬቱን በብርሐን ፍጥነት እያፋጠነ መሆኑን ነው‼

"የአበራሽን ጠባሳ ያየ፣ በእሳት አይጫወትም" እንደሚባለው፤ ከትናንት ያልተማሩ ፅንፈኞች፣ የመንደር ወጠጤዎች፣ ዘራፊዎችና ሕገ-ወጦች ሠራዊታችንን ቀና ብለው የሚያዩበት አቅምም ሆነ የሞራል ልዕልና የላቸውም። የምስራቅ አፍሪካ ኩራት የሆነው ሠራዊታችን በዘረኞች ልክ የተሰፋ አይደለም። እጅግ በጣም ይሰፋባቸዋል‼️ሠራዊታችን ውስጥ ዘረኝነት ውግዝ ነው‼️በነበልባሎቹ ጀግኖቻችን ልብ ውስጥ የገዘፉት ኢትዮጵያና ሁሉም ሕዝቦቿ ናቸው። ወገንተኝነታቸውም ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ብቻ እና ብቻ ነው‼️የዘረኝነት ተውሳክ የተጣባቸው ፅንፈኞችና ዘራፊዎች እንዲሁም በሕዝብ ደም የሚቆምሩ ሲራራ ቆማሪዎች፤ የዓይናችን ብሌን በሆኑት ጀግኖቻችን ከመጡ፤ አወዳደቃቸው የከፋ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ከጥቂት ሆድ-አደሮች በስተቀር፤ በዓይኑ ብሌንና የክፉ ቀን ደራሹ በሆነው ሠራዊቱ የሚደራደር ኢትዮጵያዊ ስለሌለ ነው‼

ክብር ለሠራዊታችን፤ ክብር ለሁልጊዜ ጀግኖቻችን‼️

05/08/2023
04/08/2023

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው?

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የዚህን አዋጅ አላማ ለማሳካት አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፦

1) የአደባባይ ስብሰባና ሰልፍ ማድረግ፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን የመከልከል፣

2) የሰዓት እላፊ የማወጅ፤ ለተወሰነ ጊዜ አንድ መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋም መጓጓዣ ዘዴ እንዲዘጋ እና እንዲቋረጥ ለማዘዝ፣

3) ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቁ ለማዘዝ፣

4) የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስን ለመከልከል፣

5) በሀገረ መንግስቱ እና በህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችን እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመጣስ እና አፈፃፀሙን የማደናቀፍ ወንጀልን መፈፀሙ፣ መሞከሩ ወይም ለመፈፀም በዝግጅት ላይ መሆኑ የተጠረጠረ ማናቸውንም ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትአዛዝ በቁጥጥር ስር በማድረግ ለማቆየት፣

6) ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ወይም ሊፈፀምባቸው እንደሚችል የተጠረጠሩ እቃዎችን ለመያዝ ሲባል
ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በየትኛዉም ጊዜ ማናቸውንም ስፍራ እና መጓጓዣ ለመበርበር፣

7) መንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማቶች ጥበቃ ሁኔታን ለመወሰን፣

8} ማናቸውም ከዚህ አዋጅ አላማ በተፃረረ መልኩ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የተጠረጠሩ የመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ሌሎች አካላት አንዲዘጕ፣እንዲቋረጡ፣ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ወይም እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብ ለማዘዝ፣

9) ማንኛዉም አገልግሎት መስጫ ተቋም እንዳይዘጋ እና ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማዘዝ፣

10) ማንኛዉም የህዝብ ትራንስፖርት መስጫ ተሸከርካሪዎች እና ማጓጓዣ እቃዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ለማዘዝ፣

11) የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እና መዋቅሮችን መልሶ ማቋቋም፣ ማደራጀት ወይም የአስተዳደር እና የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ እና ሌሎች እርምጃዎችን የመውሰድ፣

12) የህዝብን ሰላም፣ የሃገር ደህንነትን አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን የመዉሰድ፣ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ እና ትእዛዝ የመስጠት ስልጣን አለዉ፡፡

የተከለከሉ ተግባራት እና ግዴታዎች

1) ማንኛውም ሰው ይህንን አዋጅ፣ በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር አና የማክበር ግዴታ አለበት።

2) የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ ነው።

3) በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።

4) ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረ የተከለከለ ነው።

5) ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

6) ማንኛውንም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው።

7) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

04/08/2023

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የጸና ይሆናል - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የጸና እንደሚሆን የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ።

የፍትሕ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ዓ.ም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ የክልሉን የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እያወከ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም የማይቻል የጸጥታ መደፍረስ እንዳጋጠመው መግለጹን አስታውሰዋል።

የጸጥታ መደፍረስ ተግባሩም በክልሉ ነዋሪ ጫና የፈጠረ መሆኑን በመግለጽ በህገ-መንግስቱ መነሻነት ለፌደራል መንግስቱ አስፈላጊውን የህግ ማስከበር ስራ እንዲያከናውን ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።

በዚሁ መነሻነትም በፌደራል የጸጥታ ተቋማት እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተገምግሞ አሳማኝ መሆኑን ከግምት በማስገባት የህዝብ ሰላምና ጸጥታ በመጠበቅ ህግና ስርዓትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱን አዋጁ መደንገጉንም ነው የተናገሩት።

አዋጁም የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ዓ.ም ተብሎ የሚጠራ መሆኑን አስረድተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በዋናነት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር ውስጥ መሆኑ በግልጽ መመላከቱንም አስረድተዋል።

ነገር ግን አዋጁ በክልሉ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለን የጸጥታ ችግር የሚያባብስ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለማስቆም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተፈፃሚነት እንደሚኖረውም አመላክተዋል።

ለአዋጁ ተፈፃሚነትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ እንደተቋቋመም ነው ያነሱት።

ጠቅላይ መምሪያውም በኢፌዴሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል የሚመራ ሆኖ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

የዕዙን አባላት፣ መዋቅርና አደረጃጀት በሚመለከትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን መሆኑንም በአዋጁ እንደተገለጸ አንስተዋል።

ጠቅላይ መምሪያ ዕዝም የሰዓት እላፊን የማወጅ፣ ለተወሰነ ጊዜ አንድን መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋም መጓጓዣ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ የማዘዝ ስልጣን ተሰጥቶታል ብለዋል።

በሀገረ መንግስቱና በህገመንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የመጣስና አፈፃጸሙን የማደናቀፍ ወንጀል መፈጸሙ፣ መሞከሩ ወይም ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የጠረጠራቸውን ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር የማዋል ስልጣን እንደተሰጠውም ነው የገለጹት።

ወንጀል ሊፈጸምባቸው የሚችሉ የሚጠረጠሩ እቃዎችንና መሳሪያዎችን ለመያዝ ሌሎች ማስረጃዎችን ለማግኘት ማስረጃዎችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየትኛውም ጊዜ ማንኛውንም ስፍራ የመጓጓዣ ተሽከርካሪዎችንና ሌሎች ተቋማትን እንዲሁም መኖሪያ ቤቶችን ለመበርበር ስልጣን ተሰጥቶታልም ነው ያሉት።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስጥ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብና መመሪያ የማውጣት ተፈፃሚ የማድረግ ስልጣን እንደተሰጠው ተናግረዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልል ተፈፃሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ዓ.ም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የጸና ይሆናል ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዋጁ አስፈላጊነቱን አብቅቷል ብሎ በሚያምንበት ጊዜ የአዋጁን ተፈፃሚነት ከስድስት ወራት በፊት እንዲቋረጥ ሊያደርገው እንደሚችልም አንስተዋል።

04/08/2023

የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ

04/08/2023
04/08/2023

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፥ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡

መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለው ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡

የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፥ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል።

በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ህገመንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ የተቃጣ አደጋን በመደበኛ የህግ ስርዓት ለመቆጣጠር ባልተቻለ ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ህገመንግስታዊ ስርዓትን ከአደጋ የመከላከል ስልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 93 (1) ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህገመንግስቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ስላለበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ፡፡

ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን የሚያካሂዱ እንዲሆኑ ለማስቻል የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቀስ እንዲችል፥ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ፣ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ስርዓትን ተግባራዊ እንዲያደርግ እና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንዲሆን አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

04/08/2023
04/08/2023
04/08/2023
04/08/2023

Here is the truth about how the cluster office distribution was made.

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል(Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo and etc) ለክላስተር ለተመረጡ ከተሞች የተቋማት ስርጭት መስፈርት :
#. የመስፈርቱ አይነት ክብደት በመቶኛ( %)
#. የህዝብ ብዛት ----------------( 47%)
#. ከተማው የገቢ አቅም ---------( 15%)
#. ከተማው የመሸከም አቅም -----( 17%)
#. የከተማው የማልማት አቅም-------( 13%)
#. የከተማው ፈርጅ-------------------( 8%)
በደቡብ ኢትዮጵያ የክልል የር/መስተዳድር መቀመጫ ምርጫ መስፈርት:
1.የህዝብ ብዛት (40%)
2.ማዕከላዊነት (41%)
3.ከተማው የመሸከም አቅም (6%)
4.ከተማው የገቢ አቅም ( 7%)
5.የከተማው የማልማት አቅም (6%)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል (Hadiya, Kembata, Gurage, Silxe and Halaba region)
የር/መስተዳድር መቀመጫ ምርጫ መስፈርት፡
1.የህዝብ ብዛት ( 58%)
2.ማዕከላዊነት (26%)
3.የከተማው የመሸከም አቅም (16%)ሲሆን

የማዕከላት ምርጫና የተቋማት ስርጭት በውውይይት/Consensus/ ነው የተካሔደው፡፡

Our cluster Bureau division was not based on any criteria, it is based on only consensus..

04/08/2023

*******ለታርክ ማስታወሻ ይሆናል*******
✓ደቡብ አቅጣጫ ነው እየተባለ ስተች የቆየው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሕዳር 29/1987 ዓ/ም በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊ ሕገ መንግሥት እውቅና ያገኝው በ30 ዓመቱ መክሰሙን የክልሉ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ገለፁ።
የአደረጃጀት ጥያቄዎች በዲሞክራስያዊ መንገድ ምላሽ ያገኝ ዘንድ ትልቅ ድርሻ ለነበራቸው ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የደቡብ ክልል መንግስት እና ሌሎችም በሂደቱ የተሳፉ አካላትን አፈ ጉባኤዋ አመስግነዋል።

✓ዛሬ 28/11/2015 ዓ/ም የከሰመው ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አራት ክልሎችን ወልዶ ነው የከሰመው። ሁለቱ አንድ ዓመት ዕድሜ ያስቆጠሩ ስሆን አዲሶቹ ሁለት ክልሎች መሰረታ ሂዴት ላይ ናቸው።

ምንጭ:- ዎላይታ ዎጌታ ኤፍ ኤም ሬዲዮ 96.6

04/08/2023

በሰው ማገት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ ተያዘ

| በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ በሰው ማገት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ መያዙን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር ፈንታሁን አስፋው እንዳስታወቁት ማሬ መኳንንት የተባለው ግለሰብ እሥራኤላዊ ዜግነት ያቸውን በግምት የ80 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑትን አቶ ውዱ አደባባይ የተባሉትን ግለሰብ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሻሁራ ከተማ ወደ ፍንጅት ቀበሌ ጫካ ውስጥ በመውሰድ አግተው 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ድርድር ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው ከአለፋ ወረዳ የፖሊስ አባላትና ከዞኑ የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በተቀናጀ ኦፕሬሽን የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነውን ማሬ መኳንንት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን 2 ግብረ አበሮቹ ለጊዜው ማምለጣቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኦፕሬሽኑ የተሳካ እንዲሆን ለተባበሩ የህበረተሰብ ክፍሎችና የፖሊስ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበው ህበረተሰቡ ከእንዲህ አይነቱ ወንጀል ራሱን ማራቅ እንዳለበት አሳስበዋል ሲል አለፋ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል ፡፡

The Beautiful City Asella !! ,   !!
04/08/2023

The Beautiful City Asella !!
,
!!

We Greet You With Peace From Gondar Amhara Ethiopia 🇪🇹The People of Amhara Are The Most Civilized and Highly Educated Na...
04/08/2023

We Greet You With Peace From Gondar Amhara Ethiopia 🇪🇹
The People of Amhara Are The Most Civilized and Highly Educated Nation
God Bless Ethiopia and Its People😍

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Information Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share