Amhara Press

Amhara Press Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Press, Media/News Company, .

Do you choose to play games on weekends?
26/01/2024

Do you choose to play games on weekends?

Add games on weekends, double the happiness
26/01/2024

Add games on weekends, double the happiness

Spend the weekend with the game
26/01/2024

Spend the weekend with the game

04/01/2024
አስቻለው ፈጠነ በአዲስ አልበም እየመጣ ነውበእናትዋ ጎንደር እና በካሲናው ጎጃም የምናውቀው ተወዳጁ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" የተሰኜው አልበሙን ጥር 3/2016 ዓ/ም ለአድናቂዎቹ ሊያደርስ ...
04/01/2024

አስቻለው ፈጠነ በአዲስ አልበም እየመጣ ነው

በእናትዋ ጎንደር እና በካሲናው ጎጃም የምናውቀው ተወዳጁ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" የተሰኜው አልበሙን ጥር 3/2016 ዓ/ም ለአድናቂዎቹ ሊያደርስ መሆኑን አርቲሥቱ ተናገረ።

General Mohamed Hamdan DagaloBahir Dar, December 28 ( AMECO) - Sudan’s RSF Leader General Mohamed Hamdan Dagalo Arrives ...
29/12/2023

General Mohamed Hamdan Dagalo

Bahir Dar, December 28 ( AMECO) - Sudan’s RSF Leader General Mohamed Hamdan Dagalo Arrives in Addis Ababa.

The leader of Sudan's Paramilitary Rapid Support Forces (RSF) General Mohamed Hamdan Dagalo, arrived in Addis Ababa today.

Deputy Prime Minister and Foreign Minister, Demeke Mekonnen welcomed the General at Bole International Airport.

Source: ENA

🎄🎄Merry Christmas my people 🎄🎄
25/12/2023

🎄🎄Merry Christmas my people 🎄🎄

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ : "ዝማምነሽ ታወር" ሕንጻ ሥጦታ ተበረከተለት   | ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው "ዝማምነሽ ታወር" ሕንጻ ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ ...
22/12/2023

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ : "ዝማምነሽ ታወር" ሕንጻ ሥጦታ ተበረከተለት

| ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው "ዝማምነሽ ታወር" ሕንጻ ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በሥጦታ ተበረከተለት።

ዩኒቨርስቲው የ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ሲያከብር ሕዝቡ ተቋሙን ለመደገፍ ትብበር ሊያደርግ እንደሚገባ ያስተላለፈውን መልዕክት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፋቸውን እያበረከቱለት ነው። ከደጋፊዎቹ መካከል ደግሞ ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ እና ቤተሰቦቻቸው ቀዳሚዎቹ ናቸው።

በባሕር ዳር ከተማ ተወልደው ያደጉት ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን እና ከእናታቸው ወይዘሮ ዝማምነሽ ወልደየሱስ በውርስ ያገኙትን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተውን ዙማምነሽ ታወር ለባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በስጦታ አበርክተዋል ፡፡

ስጦታውን ለመስጠት ያነሳሳቸውም ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመደገፍ መኾኑን የወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

ስጦታውን የተረከቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ዩኒቨርስቲው ትልቅ ኀላፊነት እንዳለበት በመገንዘብ ነው ብለዋል። ማኅበረሰቡ ያለውን ሃብት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት በማካፈል ተቋማት ሠፊ አገልግሎት እንዲሰጡ መደገፍ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ለሃገርና ለወገን ተጠቃሚነት በሚደረገው የልማት ስራ ከወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰብ ትምህርት በመውሰድ ሁሉም ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ ጠቅሰዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስጦታ የተበረከተለት ዝማምነሽ ታወር በባሕር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ አካባቢ አወርስ ካፌ/አወርስ ገስት ሀውስ እንዲሁም የተለዩ መሰል የቢዝነስ ማዕከልነት በማገልገል ላይ የሚገኘው ህንጻ ነው፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015ዓ/ም በደማቅ ሥነ-ስርዓት ያከበረውን የ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በባሕር ዳር ከተማ በሕብረተሰብ ተሳትፎ ሊሰሩ የሚችሉ 7 ፕሮጀክቶችን ለህዝብ ማስተዋወቁ ይታወሳል፡፡

ዛንዛኒንን ነው የምጠራልህ ፡ ሲባል የማይፈራ ህጻን የለም ።.....የዚህ ልጅ እናት ፡ ይህንን ህጻን የገኘችው ፡ ከአመታት የልጅ ናፍቆት በኋላ ነው ። ከሱ በፊት አምስት ልጅ ወልዳ በሞት ...
21/12/2023

ዛንዛኒንን ነው የምጠራልህ ፡ ሲባል የማይፈራ ህጻን የለም ።.....
የዚህ ልጅ እናት ፡ ይህንን ህጻን የገኘችው ፡ ከአመታት የልጅ ናፍቆት በኋላ ነው ። ከሱ በፊት አምስት ልጅ ወልዳ በሞት አጥታቸዋለች ። እና በመጨረሻ ግን አንድ ልጅ ወለደች ።
ዛንዛኒ ስልት ስም አወጣችለት ። ሆኖም የወለደችው ልጅ ፡ ከሌላው ሰውነቱ አንጻር ሲታይ የጭንቅላቱ መጠን አነስተኛ ነበር ።
ይህም ገፅታው የተለየ አይነት መልክ ይሰጠው ጀመር ።.....
ይህም ገፅታው በመንደሩ ሰወች እንዲያገሉት ምክንያት ሆነበት ። በመንደሩ ውስጥ ህጻናት ሲጫወቱ አይቶ አብሮ ለመጫወት ሲጠጋ ፡ የያዙትን መጫወቻ ጥለው ይሮጣሉ ። ወላጆች ልጆቻቸው ሲያጠፉ ፡ ዛንዛኒን ነው የምጠራልህ በማለት ልጆቻቸውን ያስፈራሩበት ጀመር ።
ይህ የማግለል ነገር በዚህ አላበቃም ። የመንደሩ ሰወች ሲያዩት ጦጣው እያሉ ይሰድቡት ፡ ጀመር ።
ብቸኛ ፍቅር የምትሰጠው ፡ እናቱ ነበረች ። ዛንዛሚ ኤሊ ፡ በእድሜ እያደገ መጥቶ ፡ ትምህርት ቤት የሚገባበት ጊዜ ደረሰ ።
እናቱ ይዛው በአካባቢው ወደሚገኘው ት/ቤት ይዛው ሄደች ።
ሆኖም የመገለሉ ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ነበርና ፡ ወደትምህርት ቤት ለመሄድ ሲሞክር ፡ ተማሪዎች ከጦጣ ጋርማ አንማርም እያሉ ሰላም ነሱት ።...
ይህ የማግለልና የጥላቻ ሁኔታ ፡ እየባሰ ሲነጣም ፡ ሁሉን ነገር ተወላቸውና ፡ ጫካ ገባና ፡ ውሎው እዛ ሆነ ። ዛፍ ለዛፍ እየተንጠላጠለ ዱር ውሎ ይገባል ።......
እናትና ልጅ ፡ በዚህ ሁኔታ ፡ የመንደሩ ሰው አግልሏቸው ፡ ለአመታት ኖሩ ። ሆኖም ግን ታሪክ ሊለወጥ ግድ ሆነና ፡ ይህንን የዛንዛኒን ሁኔታ የሰማ አንድ የአፍሪማክስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወደ መንደራቸው መጥቶ ፡ የደረሰባቸውን መገለልና ፡ የድህነት ህይወታቸውን በተመለከተ ፡ አንድ ሰፊ ዶክመንተሪ ተሰርቶ በቴሌቪዥን ተላለፈ ።

ይህ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሚሊዮኖች ተመለከቱት ። ከቀናት በኋላም ዛንዛኒ ኤሊንና እናቱን ለመርዳት የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፈተ ።......
በአውሮፓ አሜሪካና አፍሪካ የሚገኙ ፡ ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሁሉ ፡ ለዚህ ቤተሰብ ደግነታቸውን አሳይተው ብዙ ገንዘብ ተሰበሰበ ።.......
ህይወታቸው ተቀየረ ። ዘመናዊ ቤት ተገነባላቸው ። ለእናትየው የስራ እድል ተከፈተላት ።
ያ ፡ ጦጣው እየተባለ ጫካ የሚውለው ዛንዛኒ ኤሊ ፡ ለአመታት አብራው ያረጀችውን አሮጌ ልብስ ጣለ ። በደርዘን የሚቆጠሩ ዘመናዊ ልብሶችና ጫማዎች እየቀያየረ የሚለብስ ፡ ዘናጭ ሰው ሆነ ።
ትምህርት ቤት ገባ ። አስጠኚ ተቀጠረለት ። ትምህርት ቤት የሚሄደው በሹፌር ነው ። አሁን ያ የድሮው ማግለል የለም ።
የመንደሩ ልጆች ፡ ብስክሌት እንዲያስነዳቸው የሚከቡት ። ከሱ ጋር ለመጫወት በልጆች የሚከበብ ሰው ሆኗል .
ይህን በተመለከተ እናትየው ስትናገር ፡ ፈጣሪ አንድ ቀን ታሪካችንን እንደሚለውጠው አምን ነበር ብላለች ።......
ደጋግና ፡ መልካም አሳቢ ሰወች እስካሉ ድረስ ተባብረው የማይቀይሩት ነገር የለም ።

©በዋሲሁን ተስፋዬ 👆

ባህር ዳር ከነማ ክለብ አፍሪካንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) መስከረም 6/2016 ዓ.ምበካፍ ኮንፌዴሬሽ ካፕ ኢትዮጵያን የወከለው ባህር ዳር ከነማ ...
17/09/2023

ባህር ዳር ከነማ ክለብ አፍሪካንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) መስከረም 6/2016 ዓ.ም

በካፍ ኮንፌዴሬሽ ካፕ ኢትዮጵያን የወከለው ባህር ዳር ከነማ የቱኒዝያውን ክለብ አፍሪካንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው 2ኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹን ሁለት የድል ግቦች አጥቂው ሀብታሙ ታደሰ በ58ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው ባህር ዳር ከነማዎች ኳስን መስርተው ለመጫወት ጥረት ያደረጉ ሲሆን ያገኟቸውን አጋጣሚዎችም ወደግብ በመቀየር አሸንፈው ለመውጣት ችለዋል፡፡

ክለብ አፍሪካን በአንጻሩ በረጃጅምና በቆሙ ኳሶች ግብ ለማግባት ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት የጣና ሞገዶቹ በማጥቃቱና በመከላከሉ ጥሩ ሆነው ባመሹበት ጨዋታ ወደ ምድብ ድልድሉ ለማለፍ ዘጠና ደቂቃ ብቻ ይቀራቸዋል፡፡

ከካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቅ ውድድር በሆነው መድረክ ቀሪውን የዘጠና ደቂቃ ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ወይም አቻ አሊያም አንድ ለባዶ መሸነፍ 16ቱ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባት ያስችላቸዋል፡፡

የጣና ሞገዶቹ በመድረኩ የመጀመሪያ ተሳትፏቸው ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

በሙሉቀን ጌትነት

✅ 20-year professional career Lidya Tafesee hangs up her whistle today following a fantastic stint as a referee. Enjoy y...
27/06/2023

✅ 20-year professional career

Lidya Tafesee hangs up her whistle today following a fantastic stint as a referee. Enjoy your retirement, Lidya 👏👋




𝐓𝐡𝐞 𝐭𝐫𝐨𝐯𝐞 𝐨𝐟 𝐊𝐢𝐛𝐫𝐚𝐧 𝐆𝐚𝐛𝐫𝐢𝐞𝐥!Kibran Gabriel Monastery, located just a 20-minute boat ride from Bahirdar, is one of Ethiop...
26/06/2023

𝐓𝐡𝐞 𝐭𝐫𝐨𝐯𝐞 𝐨𝐟 𝐊𝐢𝐛𝐫𝐚𝐧 𝐆𝐚𝐛𝐫𝐢𝐞𝐥!

Kibran Gabriel Monastery, located just a 20-minute boat ride from Bahirdar, is one of Ethiopia's most remarkable religious sites.

The picturesque monastery is believed to have been founded in the 14th century and is home to a treasure trove of ancient books preserved for centuries.

The museum at Kibran Gebriel Monastery is said to hold hundreds of rare manuscripts, some of which date back to the early Christian era.

We the people
24/06/2023

We the people

የአማራ ስም አመጣጥየአማራ ስም ሥርወ-ቃሉ የተለያዩ ምንጮች አሉት። የብሄር ብሄረሰቦች ስም (ቋንቋው እና ተናጋሪዎቹ) አማራ የሚለው ስያሜ በጣና ሀይቅ ዙሪያ በሰማያዊ አባይ መፋለቂያ ላይ ከ...
24/06/2023

የአማራ ስም አመጣጥ
የአማራ ስም ሥርወ-ቃሉ የተለያዩ ምንጮች አሉት። የብሄር ብሄረሰቦች ስም (ቋንቋው እና ተናጋሪዎቹ) አማራ የሚለው ስያሜ በጣና ሀይቅ ዙሪያ በሰማያዊ አባይ መፋለቂያ ላይ ከሚገኘው የመካከለኛው ዘመን የአማራ ግዛት የመጣ እና አሁን ካለው የኢትዮጵያ የአማራ ክልል በመጠኑም ቢሆን ትልቅ ቦታን ያካተተ ነው ተብሏል።
ሌሎች ሰዎች ወደ አማሪ ("አስደሳች፣ ቆንጆ፣ ሞገስ") ወይም መሃሬ ("ጸጋ ያለው") ያደርጉታል። ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ጌታቸው መኮንን ሀሰን ከጥንት የመን ሂሚያራይትስ ጋር በተገናኘ የጎሳ ስም ይጠቅሳል። ሌሎች ደግሞ እንደ ዶናልድ ሌቪን ባሉ ሊቃውንት እንደ ህዝብ ሥርወ-ቃል ውድቅ ቢደረግም ከግእዝ ዓም ('am፣ "ሰዎች") እና ከሐራ (h.ara፣ "ነጻ" ወይም "ወታደር") የተገኘ ነው ይላሉ።

ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ ተልዕኮ በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ...
24/06/2023

ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ ተልዕኮ በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ

ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ በሚል ርዕስ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ እና የመካከለኛ አመራሮች የውይይት መድረክ ተጠናቋል።

የውይይት መድረኩ በነበረው ቆይታ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች፣ በወቅታዊ የሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ብልጽግና በመጣበት የለውጥ ሂደት ውስጥ በርካታ ስኬቶችንና ድሎች ማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ በመሆኑ ይህንኑ ተረድቶ ለተሻለ አገራዊ ለውጥ መትጋት ያስፈልጋልም ተብሏል።

ፓርቲው የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ኢኮኖሚውን ከፍጹም ውድቀት ለመታደግ በርካታ ማሻሻያዎችንና እርምጃዎች መውሰዱንና ማህበራዊ ትስስርንና የዜጎች ክብርን የማከም እንዲሁም በጋራ ጥቅም መርህ የተመራ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን እየሰራ ያለ መሆኑ በመድረኩ ቀርቧል።

ብልጽግና በየጊዜው የሚገጥሙትን ፈተናዎች በመሻገር የውስጥ አንድነታችን እንዲጎለብት በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ተብሏል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ለዘላቂ ሰላም ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለህዝቡ ደህንነት አገራዊ ለውጡን ዳር ለማድረስ መትጋት እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተነስቷል።

•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•

Amhara Prosperity Party /APP/

 ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ክብራቸውን አያስነኩም፣ የሰው ክብር አይነኩም፣ ለክብር ይዘምታሉ፣ለሀገር ይሞታሉ፣ ለወገን መከታ ይሆናሉ። ተክፍቶ ማደር፣ በነፃነት መደራደር...
05/05/2023



ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ክብራቸውን አያስነኩም፣ የሰው ክብር አይነኩም፣ ለክብር ይዘምታሉ፣ለሀገር ይሞታሉ፣ ለወገን መከታ ይሆናሉ። ተክፍቶ ማደር፣ በነፃነት መደራደር አይሆንላቸውም። ነፃነት ሲደፈር፣ ሀገር ሲወረር፣ ሕዝብ በጠላት ሲወጠር፣ ጠመንጃቸውን ወልውለው፣ ካርታቸውን ሞልተው፣ ካዝናቸውን አንዠርገው፣ ሳንጃቸውን ስለው ሀገር ተደፈረች ወደተባለበት ሥፍራ ይተማሉ። የተስፋውን ምልክት የማይሸነፈውን፣ በግርማው ጠላት የሚያስጨንቀውን፣ ኃያልነቱ የማይቻለውን፣ ሚስጥሩ የማይመረመረውን፣ ክብሩ ለዘላለም ከፍ ያለውን፣ ፈጣሪ ያከበረውን፣ አብዝቶ የወደደውን ፣ በኃይሉ የጠበቀውን ለምስክር፣ ለክብር፣ ለፍቅር ያስቀመጠውን ሠንደቅ ከፊት አስቀድመው ይጓዛሉ።

አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሠንደቅ ከፊት ቀድሞ፣ ማን ሊገኝ ቆሞ፣ ጠላት ገና በአሻገር ሲያየው ይሸበራል፣ ይደነብራል፣ ወኔው ይክደዋል፣ ጉልበቱ ይደክማል። ኮርቶ መኖር፣ አሸንፎ ማደር፣ በጀግንነት መከበር፣ በኅብረት መዘመር መለያቸው ነው። ለክብርና ለሀገር ሲሉ ዱር ቤታቸው፣ ዋሻ ማደሪያቸው፣ ደርቅ ኮቸሮ ምግባቸው ሆኖ ይኖራሉ።

ሀገር ስትወረር፣ ክብር ሲደፈር፣ ቆሞ ማዬት አይቻላቸውም። ዝም ማለት አይሆንላቸውም። ቁጣቸው ይገነፍላል፣ ሳንጃቸው ይሳላል፣ አፈሙዛቸው ይወለወላል። ሀገር የደፈረውን ክብር የነካውን አሳምረው ይቀጡታል፣ ክንዳቸውን ያሳዩታል።

አባት ያወረሰው፣ ጀግና የሚወርሰው፣ ቆራጥ የሚለብሰው፣ ፈሪ የማይደርሰው፣ ለዘላለም የሚታጠቁት፣ ካጠለቁ የማያወልቁት ደምና ማንነት ነው ፋኖነት። ፋኖነት አሸናፊነት፣ አይበገሬነት፣ ለሀገር ኗሪነት፣ እምቢ ለነፃነት፣ እምቢ ለሉዓላዊነት ማለት ነው። የአማራ ፋኖ በዘመናት ቅብብሎሽ ሀገር ስትደፈር፣ ግዛቷ ሲወረር እምብኝ እያለ እየተነሳ ደምና አጥንት እየገበረ፣ በጀግኖች ጎራ ውሎ እያደረ ጠላትን መትቷል፣ ራሱ ኮርቶ ሀገር አኩርቷል።

በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን የመጣው ሁሉ ለእርሱ ጠላቱ ነው፣ የሚከፍለው ደምና አጥንት ለነፃነት፣ ለሉዓላዊነት፣ ለኢትዮጵያዊነት ነው። የአባቱን ስም የወረሰው፣ ያባቱን ጋሻ ያነሳው ፋኖ ስሙን ሊዘክር፣ ታሪኩን ሊመሰክር፣ ሀገር ሊያስከብር በረሃ ገብቷል። ጠላቱን ሳይቀጣ፣ ከበረሃው አይወጣም።

ፋኖ ቃሉን ጠብቆ፣ ሡሪውን አጥብቆ ጠላትን መውቃት ይችልበታል። ቃሉን አይሽርም፣ ክንዱን አያዝልም፣ እንደተከበረ እንደ አከበረ ይኖራል እንጂ።

የትግራይ ወራሪ ሀገር ሊያፈርስ፣ ቀዬ ሊያረክስ በመጣበት ሁሉ ፋኖው እያደነ እየወቃው ነው። በማይጠብሪ ግንባር የተሠማራው ፋኖ በዱር በገደል እየተከታተለ ወራሪውን ኃይል እየደመሰሰው ነው። እነ አጅሮችን በግንባር አግኝቻቸዋለሁ። ጦር እየመሩ ሀገር ሊያስከብሩ ዘምተው። ጣላት ሳይደመሰስ ከበረሃ ላይመለሱ ምለው።

በግንባር ያገኘናቸው የፋኖ ሻለቃ መሪ ስጦታው ዳኘው (ባሻ) ፋኖ በየትኛውም ውጊያ ላይ አለበት፣ በውጊያ ተቋዳሽ ነው ብለውናል። ጎንደርን እንዲቆጣጠር የተላከውን የአሸባሪ ቡድን ጨርሰን የቀረውን ለመደምሰስ በመገስገስ ላይ ነን፣ ፋኖ ተሰማራ ሲባል ጠላት ይሸበራል፣ የአሸባሪው ቡድን የፋኖን ስም ሲሰማ ገና ይሮጣል ነው ያሉን ባሻ። > ነውም ብለውናል።

ፋኖ የአማራ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያን ነው፣ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ፅናት የሚዋደቅ መሆኑንም ባሻ ተናግረዋል። > ነው ያሉን።

ትግራይ አንድ የኢትዮጵያ አካል የሆነች በሃይማኖት፣ በሰውነት አንድ አካል አንድ አምሳል ነን፣ ትግላችን ሀገራችን ሊያፈርሱ ከተነሱና ሀገራችን ለውጭ ወራሪ አሳልፈው ሊሰጡ ከሚጥሩት ጋር ነውም ብለውናል። የፋኖው ትግል መላ ኢትዮጵያውያንን ነፃ ለማውጣት ስለመሆኑም ነው የነገሩን። ወራሪው ኃይል ቄስና መነኩሴ ሳይቀር የሚገድል፣ ሀብትና ንብረት የሚዘርፍ የሚያወድም ነው፣ ለምንም ለማንም የማይጠቅሙ ስለሆኑ እስከመጨረሻው እንታገላቸዋለንም ብለዋል።

ሲሉም ይገልፁታል። የአማራ ሕዝብ የጀግንነት ታሪክ ይሠራል እንጂ የተዋረደ ታሪክ አይሰራም ነው ያሉት ባሻ ። ለኢትዮጵያ እርኩስ መንፈስ የሆነውን ኃይል ከገባበት ገብቶ ያስወጠዋል፣ ጠላት በሽሽት ገድል እየገባ፣ ውኃ እየበላው ነው ሲሉም የጠላትን ሩጫ ባሻ ነግረውናል።

የፋኖ የብርጌድ አዛዥ ዮሃንስ ንጉሡ ፋኖ ሀገርና ሕዝብ የሚጠበቅበት አባቶቻችን ያወረሱን ጥንታዊ ተቋም ነው ብለዋል። ውድ ዋጋ እየከፈለ ትልልቅ ድሎችን እያመጣ እየተጓዘ ነው፣ በዘመናዊ አደረጃጀት ተደራጅቶ ሰፊ ቁጥር ያለው ሠራዊት ይዞ በድል እየገሰገሰ ነው ብለውናል። ፋኖ ድል በድል እየሆነ እየማረከ፣ እያንበረከከ፣ እየደመሰሰ መሆኑንም ተናግረዋል። ጠላት አሉኝ የሚላቸውን ጦሮችን አሰልፎ ተዋግቷል፣ ነገር ግን አለኝ የሚላቸውን አጥቷል፣ መቋቋም አቅቶት ወደ ቆላ ተንቤን እየፈረጠጠ ነው ብለዋል። ፋኖ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ ጋር የሚለዬን ነገር የለም፣ በአንድ ምሽግ አድረናል፣ በአንድ ኮዳ ጠጥተናል፣ በአንድነት ለአንድ ዓላማ እየተዋጋን ነው ብለዋል።

በግዳጅ ውስጥ ምንም አይነት ሚና የሌላቸው ሰዎች ፋኖ በመምሰል የሚንቀሳቀሱ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል። ፋኖ ሲያጠፋም በሕግ እንዲጠየቅ ኾኖ መደራጀቱንም አንስተዋል።

ሌላኛው የፋኖ መሪ አርበኛ ደረጀ በላይ(አባ ናደው) ትግሉ የተሳካ እንዲሆን እያገዘ ላለው ሕዝብ ምስጋና ይድረሰው ነው ያሉት፣ ፋኖ ከቀደሙት አባቶች የሚሰመውን ታሪክ እየደገመና እያስመሰከረ ስለመሆኑ ነግረውናል። በመካከላቸው ምንም አይነት ልዩነት አለመኖሩንም ገልፀዋል። ፋኖ የአማራ ሞተር ነው ያሉት አርበኛው የፋኖ አደረጃጀት ሊገደብ አይገባም ብለዋል። የአማራ ሕዝብ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን፣ ልዩ ኃይሉን ከመቀላቀል በላፈ ፋኖን እየተቀላቀለ ሀገሩን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

ሌላው የፋኖ መሪ የሺህ አለቃ ባየ ቀናው ፋኖ ከጠላት እየማረከ እየታጠቀ በድል እየገሰገሰ ነው፣ በጀታችን እና ደጀናችን ሕዝባችን ነው ብለዋል። ጠላትን እስከመጨረሻው መምታት አደራችን ነው፣ ብዙ ድል አግኝተናል፣ የመጨረሻችን ግን አይደለም፣ ጠላት እንዳያንሰራራ አድርገን መምታት አለብን ነው ያሉት።

> እንደተባለ ከፋኖ ፊት ሲደርሱ ፈሪ ካልሆኑ መጨረሻው ሞት ነው። ጥይታቸው አይምርም፣ አፈሙዛቸው አይስትም። ጀግንነታቸው የሚታይ ነው፣ ምሽግ ሰብረው እንደ አሞራ በረው ከጠላት አናት ላይ የሚሰቀሉ ድንቆች ናቸው።

በታርቆ ክንዴ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share