Gafat Info Center-ጋፋት የመረጃ ቋት

  • Home
  • Gafat Info Center-ጋፋት የመረጃ ቋት

Gafat Info Center-ጋፋት የመረጃ ቋት ወቅታዊ፣ ትኩስና ተዓማኒ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እ

"በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ" (በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)ከሰሞኑ ጤና ሚንስቴር የሚሰጠው የኮቪድ-19 መግለጫ ላይ "በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ" የሚል አዘውትረን እየተመለከ...
12/06/2020

"በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ"

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

ከሰሞኑ ጤና ሚንስቴር የሚሰጠው የኮቪድ-19 መግለጫ ላይ "በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ" የሚል አዘውትረን እየተመለከትን ነው ፤ ይህ ጉዳይ ህብረተሰቡ ላይ ጥያቄን ፈጥሯል።

በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ ማለት:-

1. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ምርመራ ሳይደረግ የኮሮና ተጠቂ ሆኖ የህልፈቱ ምክንያት ኮሮና ቫይረስ ሲሆን፣

2. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ምርመራ ሳይደረግ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሆኖ ተጓዳኝ በሽታ ሲኖርበት፣

3. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ናሙና ሰጥቶ ዉጤቱ ሳይደርስ ህይወቱ ሲያልፍ፣

ታድያ አስከሬን መመርመር ለምን አስፈለገ ?

ለዚህ ጥያቄ መልስ ሊሆነን የሚችለው የሞቱን ምክንያት ለማወቅ እና በኮሮና ቫይረስ ከሆነ ንክኪ እና ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች ለመለየት ነው።

' ሟች ቫይረሱን ከየት አመጣው ? ' የሚል ጥያቄ ያስነሳ ይሆናል ፤ ነገር ግን ባሁኑ ሰዓት ሁሉም ሰው ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ስለሆነ በየትኛውም ቦታ እና ከማንኛውም ሰው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ሊይዘን ስለሚችል ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው።

 #በሰላም ነው ግን  !!!የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዕ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፀው የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከስራቸው በፍቃዳቸው ለቀዋል!ሙሉ መግለ...
08/06/2020

#በሰላም ነው ግን !!!

የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዕ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፀው የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከስራቸው በፍቃዳቸው ለቀዋል!

ሙሉ መግለጫው

ታቃውሞ የበረታባት አሜሪካ ወታደሮቿን በተጠንቀቅ አንዲሆኑ አዘዘችበዚህም በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ተቃውሞ መከሰቱን ተከትሎ ሁሉም ግዛቶች ወታደሮቻቸውን በተጠንቀቅ እንዲሆኑ አዘዋል፡፡ባሳለፍነ...
31/05/2020

ታቃውሞ የበረታባት አሜሪካ ወታደሮቿን በተጠንቀቅ አንዲሆኑ አዘዘች

በዚህም በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ተቃውሞ መከሰቱን ተከትሎ ሁሉም ግዛቶች ወታደሮቻቸውን በተጠንቀቅ እንዲሆኑ አዘዋል፡፡

ባሳለፍነው ሰኞ አንድ ነጭ ፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊን ጆርጅ ፍሎድን በጉልበቱ አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ በአሜሪካ በሁሉም ግዛቶች ከፍተኛ ተቃውሞ እየተደረገ ነው የሚገኝው፡፡

ሰልፈኞቹ በትላንትናው እለት ሚኒያፖሊስ ውስጥ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያን ያቃጠሉ ሲሆን በኒዮርክም የፖሊስ ተሸከርካሪዎችን አውድመዋል ሲል ነው አልጀዚራ ያስነበበው፡፡

አሜሪካ ውስጥ በ2019 ብቻ ከ1 ሺ በላይ ጥቁሮች በፖሊስ ተተኩሶባቸው ሕይታቸው ማለፉ ተገልጿል።

•አሁን በመላው አገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በመፍራት ጆርጂያ እና አትላንታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡ የመረጃ ምንጭ:- VOA »»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»>

ሱዳን ውስጥ በ2 ቀን 279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ባወጣው የሁለት ቀን ሪፖርት (ግንቦት 20 እና ግንቦት 21) ተጨማሪ 279 ሰዎች በ...
31/05/2020

ሱዳን ውስጥ በ2 ቀን 279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ባወጣው የሁለት ቀን ሪፖርት (ግንቦት 20 እና ግንቦት 21) ተጨማሪ 279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል።

እንዲሁም በሁለቱ ቀናት 29 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 457 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሱዳን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 4,800 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ262 ሰዎች ህይወት አልፏል። 1,272 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ቻይና 1ኛ ለማለት ሩብ ጉዳይ የቀረው መረጃ ፤ በቻይና የኮቪድ-19 ክትባት እያዘጋጁ የሚገኙት ሳንቲስቶች (ከሶኖቫክ ባዮቴክ) ክትባቱ 99% ውጤታማ እንደሚሆን   ተግረዋል።በአሁን ሰዓት ክት...
30/05/2020

ቻይና 1ኛ ለማለት ሩብ ጉዳይ የቀረው መረጃ ፤

በቻይና የኮቪድ-19 ክትባት እያዘጋጁ የሚገኙት ሳንቲስቶች (ከሶኖቫክ ባዮቴክ) ክትባቱ 99% ውጤታማ እንደሚሆን ተግረዋል።

በአሁን ሰዓት ክትባቱ በሁለተኛ ደረጃ የሙከራ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ሶስተኛው ደረጃ የሙከራ ሂደት በዩይትድ ኪንግደም እንደሚደረግ ሳይንቲስቶቹ ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን አሁን ያለው ሙከራ ሂደት ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ቢገኝም ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ሙከራው ተጠናቆ በስፋት ለሰዎች እስኪቀርብ ድረስ ወራትን ይፈጃል።

በትግራይ ክልል የ1 ሰው ህይወት አለፈ!በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 45 ሰዎች መካከል የአንዲት ሴት ህይወት ማለፉን (ከማይካድራ) የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎ...
30/05/2020

በትግራይ ክልል የ1 ሰው ህይወት አለፈ!

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 45 ሰዎች መካከል የአንዲት ሴት ህይወት ማለፉን (ከማይካድራ) የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) አረጋግጠዋል።

27/05/2020

#ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በክፍለ ከተሞች (በቅደም ተከተል)

1. ልደታ - 122 ሰዎች
2. አዲስ ከተማ - 69 ሰዎች
3. ቦሌ - 54 ሰዎች
4. ገለሌ - 38 ሰዎች
5. ኮልፌ ቀራንዮ - 38 ሰዎች
6. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 27 ሰዎች
7. የካ - 25 ሰዎች
8. አራዳ - 21 ሰዎች
9. ቂርቆስ - 16 ሰዎች
10. አቃቂ ቃሊት - 8 ሰዎች
11. አድራሻቸው ያልታወቀ - 18 ሰዎች

-------------------------
መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍለን
አሁንም ጥንቃቄ አይለየን !





ምንጭ፣ ዮሐንስ መኮንን

25/05/2020
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሦስት ወረዳዎች 23 ሚሊዮን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት ተገኘማዕድኑ መገኘቱ የተረጋገጠው የአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በተያዘው በጀት ዓመት ባ...
25/05/2020

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሦስት ወረዳዎች 23 ሚሊዮን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት ተገኘ
ማዕድኑ መገኘቱ የተረጋገጠው የአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በተያዘው በጀት ዓመት ባካሔደው የማዕድን ጥናት ነው።
የግራናይት ክምችት እንዳላቸው በጥናቱ የተረጋገጡ ወረዳዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙት ባሶ ሊበን፣ ጎዛምን እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች መሆናቸውን አብመድ ዘግቧል።
የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ይታየው ተስፋሁን፣ በባሶ ሊበን እና ጎዛምን ወረዳዎች 67 ነጥብ 02 ካሬ ኪ.ሜ የሚሸፍን የማዕድን ፍለጋ እና ክምችት ላይ ጥናት ተካሒዶ፣ በተለይ ለምንጣፍ የሚሆን 21 ሚሊዮን 151 ሺህ 195 ነጥብ 2 ቶን የግራናት ማዕድን እንዳለ መረጋገጡንም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በደብረ ኤሊያስ ወረዳ 28 ካሬ ኪ.ሜ የሚሸፍን ጥናት ተካሒዶ፣ 2 ሚሊዮን 438 ሺህ 100 ቶን የግራናይት ማዕድን መገኘቱን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል እምቅ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኑን ያስታወቀው ኤጀንሲው፣ ሀብቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አመልክቷል።
የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ1 ሺህ 775 ግለሰቦች የማዕድን ማምረት እና ምርመራ ፈቃድ እንደተሰጠም ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥም ስምንቱ በከፍተኛ የግንባታ ማዕድናት ማምረት፣ አራቱ በአነስተኛ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ማምረት፣ 58ቱ አነስተኛ የግንባታ ማዕድናት ማምረት ፈቃድ የወሰዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
አምስቱ የምርመራ፣ 1 ሺህ 691 የባሕላዊ ማዕድናት ማምረት ፈቃድ አንዲሁም ዘጠኙ የከበሩ ማዕድናት ዕደ ጥበብ (ላፒደሪ) ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህ በፊት የማዕድን ፈቃድ ወስደው ጉድለት ባሳዩ 155 የማዕድን ማምረት ፈቃዶች ላይ ማስጠንቀቂያ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱንና በአራት ፈቃዶች ላይ ዕገዳ መጣሉንም አስታውቀዋል።
እርምጃው የተወሰደው በገቡት ውል መሠረት ወደ ሥራ ያልገቡ፣ በውላቸው መሠረት ክፍያ የማይፈጽሙ፣ ተቋሙን ሳያሳውቁ ሥራ ባቆሙ ላይ እንደሆነም አብራርተዋል።
@ኢቢሲ

25/05/2020

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት 73 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ2 ሺህ 844 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 73 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ከእንቅስቃሴ ውጭ የተደረገው 'አብነት' አካባቢ!(አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኙበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች ...
25/05/2020

ከእንቅስቃሴ ውጭ የተደረገው 'አብነት' አካባቢ!
(አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኙበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች በአንዱ ፣ አብነት አካካቢ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሲባል ሙሉ በሙሉ አንድ መንደር በእንቅስቃሴ ውጭ ተደርጎ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉን ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በልደታ ክፍለከተማ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ግለሰቡ በተጎዳኝ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፎል፡፡

ቀድሞ የተወሰደው ናሙና ሟቹ ግለሰብ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማሳየቱ ከሳቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ ምርመራና ክትትል ተደርጎ 32 ስዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከባለሙያዎች ተሰምቷል።

ይህንን ተከትሎም በወረዳው (አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኙበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡ ወደ መንደሩ በሚያስገባው ቅያስ ላይ ፖሊሶች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ቆመው ከነዋሪው ሌላ ሰው እንዳያልፍ ሲከለክሉ መመልከቱን ሬድዮ ጣቢያው ግልጿል፡፡

ለነዋሪው የአስቤዛ ፤ የፅህና መጠበቂያ ሳሙና ፤ሳኒታይዘር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አቅርቦቱ ከዚህ በፊት ለወረርሽኙ ተብለው ከተለያዩ አካላት ከተሰበሰበው እየተሸፈነ ይገኛል። በተለይም የአሊባባ ድጋፍ በእጅጉ እንዳገዘ የወረዳው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የስራቸው ሁኔታ ግድ ከቤት የሚያስወጣ ለሆነባቸው ነዋሪውች ለሚሰሩበት ተቋም የትብብር ደብዳቤ እየተፃፈ ነው፡፡

በዚህ መንደር የሚኖሩት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እዛው ባሉበት ተለይተው በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የታለመ ነው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተቋቋመው አደረጃጀት ውስጥ ያሉ በጎ ፍቃደኞችም የችግሩ ሰለባ ናቸው ተብሏል።

በዚያው ክፍለከተማ አምስተኛ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳይ በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንክኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለከተማ እና ልደታ ክፍለከተማ ጤና ሚኒስቴር ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለዚህ ሲባል የተቋቋመው ግብረሃይል ከዚህ የበለጠ እንዳይሰራጭ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁሉም ህንፃዎች ላይ ምርመራ ተደርጎል፡፡ ምርመራውን ሲሸሹ የነበሩ ሰውችንም ነበሩ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ

 #ውድ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ጥንቃቄ አይለየን !!!ሱዳን ውስጥ በአንድ ቀን የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ!√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√የሱዳን ጤና ሚኒቴር ባወጣው መግለጫ የ...
25/05/2020

#ውድ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ጥንቃቄ አይለየን !!!

ሱዳን ውስጥ በአንድ ቀን የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ!
√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√
የሱዳን ጤና ሚኒቴር ባወጣው መግለጫ የአስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች ህይወት ማለፉን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 165 ደርሷል።

በተጨማሪ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት (192) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ሰለሳ አራት (34) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

(በቫይረሱ የተያዙ 3,820፣ ሞት 165፣ ያገገሙ 458)

22/05/2020

ዛሬ በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 4 ሰዎች መካከል ሁለቱ (2) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና መጥተው በተደረገው ምርመራ የተገኙ ናቸው።

አጭር መረጃ ፦

- ሁለቱም በ50ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው።

- አንደኛው ታማሚ ማክሰኞ ከሰዓት ነው ወደ ሆስፒታል የመጡት፤ ሌላኛው ታማሚ ደግሞ እሮብ ጥዋት ነው ወደ ሆስፒታል የመጡት።

- የምርመራው ውጤት ትላንት ነው የወጣው፤ ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በሆስፒታሉ የመተንፈሻ አካላት እና ተዛማጅ በሽታዎች ያለባቸውን ታማሚዎች የመርመር ስራ እየተሰራ በመሆኑ ነው እኚህ የኮቪድ-19 ታማሚዎች የተገኙት።

- በሆስፒታሉ ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን በሙሉ ኳራንታይ እንዲደረጉ ተደርጓል (የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ማንኛውም ሆስፒታል ውስጥ ያሉና ግንኙነት የነበራቸው)

- ከሆስፒታል ውጭ ደግሞ ከመጡበት አካባቢ ጀምሮ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመፈለጉ እና ኳራንትይን እንዲገቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው።

- አንደኛው ታማሚ ባህር ዳር ሄደው ነው የመጡት የከተማ አስተዳደሩ ከታማሚው ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ ሰዎችን ኳራንታይ የማድረግ ስራ እየሰራ ነው አሁንም ኳራንታይን የተደረጉ አሉ።

- ሁለተኛው ታማሚ ከጯሂት ነው የመጡት መጀመሪያ ያከሟቸው ሃኪምን ጨምሮ ኳራንታይ ተደርገዋል።

 #በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል ፤በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 82 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ ሰማንያ ሁለት (82) ሰዎች በኮቪድ-19...
22/05/2020

#በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል ፤
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 82 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ ሰማንያ ሁለት (82) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 563 ደርሰዋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ስድስት (6) ሲሆኑ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ደግሞ ስድስት (6) ናቸው።

 #ዜና እረፍት ፥የአፍሪካ ሙዚቃን ለአለም በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም አርቲስት የነበረው ጊኒያዊው ሞሪ ካንቴ ዛሬ በ70 አመቱ ህይወቱ አልፏል!የሞሪ ካንቴ "Yeke Yeke" የሚለው ስራው እ...
22/05/2020

#ዜና እረፍት ፥

የአፍሪካ ሙዚቃን ለአለም በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም አርቲስት የነበረው ጊኒያዊው ሞሪ ካንቴ ዛሬ በ70 አመቱ ህይወቱ አልፏል!

የሞሪ ካንቴ "Yeke Yeke" የሚለው ስራው እጅግ ዝነኛ ያረገው ነበር፣ እጅግ ተወዳጅም ነበር። ተጋበዙ:
https://youtu.be/BVmS0SSSdWM

Mory kante - yeke yeke (Official video)

የጤና ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያ መመሪያ፦*************የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና የሕክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ ሠራተኞች የማበ...
22/05/2020

የጤና ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያ መመሪያ፦
*************
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና የሕክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያ እንዲሰጥ ወሰነ።
ምክር ቤቱ በሰባት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያሳለፈ ሲሆን የጤና ዘርፍ ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያን ለመወሰን በተዘጋጀው መመሪያ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ሠራተቹ ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠርና በሚደረገው ጥረት በግንባር ቀደምነት በሙያቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ እጅግ የላቀ ከመሆኑም በላይ፤ የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ጤንነትና ሕይወት ለአደጋ በማጋለጥ የሚፈጸም ሙያዊ አስተዋጽዖ መሆኑን ምክር ቤቱ አምኖበታል።
በመሆኑም የጤና ሚኒስቴር ባቀረበው ረቂቅ የማበረታቻ አበል ክፍያ መመሪያ ላይ ከተወያየ በኋላ ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
አሐዱ ቴሌቪዥን
ግንቦት 14/2012

በዋይት ሃውስ ለ11 ፕሬዚዳንቶች ያገለገሉት አስተናጋጅ በኮሮናቫይረስ ሞቱ-------------------------------------------------------------------------በ...
22/05/2020

በዋይት ሃውስ ለ11 ፕሬዚዳንቶች ያገለገሉት አስተናጋጅ በኮሮናቫይረስ ሞቱ
-------------------------------------------------------------------------
በዋይት ሃውስ ውስጥ ለ11 የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች፣ ለአምስት አስርት አመታት ያህል ያገለገሉት የቀድሞው አስተናጋጅ በ91 አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ።
የቀድሞው አስተናጋጅ ዊልሰን ሩዝቬልት ጀርማን ስራቸውን የጀመሩት በፕሬዚዳንት አይዘንሃወር አስተዳደር በጎርጎሳውያኑ 1957 ነው።
በመጀመሪያ በዋይት ሃውስ ውስጥ በፅዳት አገልግሎት ተቀጥረው ይሰሩ የነበረ ሲሆን የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጃኪ ኬኔዲ ወደ አስተናጋጅነት አሳደገቻቸው።
በዋይት ሃውስ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ ያገለገሉት በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ሲሆን፤ የአስተናጋጆችም ኃላፊ ተደርገው ነበር።
"ማንኛውንም ሰው ለማገልገል ቅን ነበር፤ እንዲሁም የሚወዳትን ሃገሩን ለማገልገል የነበረው ፍላጎት ከምንም በላይ ነው፤ ለሰዎችም የነበረው ፍቅር ጥልቅ ነው። ቸር የሆነ መንፈስ ነበረው እሱንም ጥሎልን አልፏል" በማለት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሚሸል ኦባማ ተናግረዋል።
Amharic

19/05/2020

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 2,591፣ ሞት 105፣ ያገገሙ 247

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,502፣ ሞት 59 ፣ ያገገሙ 178

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,618 ፣ ሞት 7 ፣ ያገገሙ 1,033

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 963 ፣ ሞት 50 ፣ ያገገሙ 358

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 365፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 120

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 347 ፣ ሞት 6፣ ያገገሙ 4

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 39

ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ  : ከሁሉ አስቀድመን በመቐለ ከተማ በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ባለፈው ትግራዋይ ወጣት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገ...
19/05/2020

ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
: ከሁሉ አስቀድመን በመቐለ ከተማ በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ባለፈው ትግራዋይ ወጣት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰቦቹ ለወዳጆቹና ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ እንዲሁም ለሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን ::
ህዝባችን በዚህ ፈታኝ ወቅት ያጋጠመውን ድርብ ፈተናና ችግር በማለፍ ወደሚፈልገውና ወደሚገባው የሰላም፣ የብልጽግና የመረጋጋት፣ የዲሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስት ሆነ በፓርቲ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች ህዝባዊነታቸው፣ የአመራር እሴቶቻቸውና ጥበባቸው የሚፈተንበት ታሪካዊ ጊዜ ላይ እንደምንገኝም ማስተዋልና መበርታት ይገባል።

የትግራይ ህዝብ ከመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ጋር በአንድነት በመሆን ባካሄደው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ በከፈለው መስዋእትነት የሰላምና ዴሞክራሲ ብልጭታ የማየት ፍላጎቱ በቀረበው ቁጥር የሚሸሽበት ምናባዊ አለም ብቻ እየሆነበት መጥቷል።
በቅርቡ የአንድ ወጣት ህይወት እንዲያል ከመደረጉም በሻገር ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ የተከሰተው ለአንድ ወጣት ክቡር ህይወት ህልፈትና ለሁለት ወጣቶች የመቁሰል አደጋ በክልሉ ዉስጥ የሰላምና ዲሞክራሲ እጦት ማሳያ ነዉ፡፡ ሰላም ወዳዱና እንግዳ አክባሪ በሆነዉ የመቐለ ከተማ ነዋሪ መሪር የሀዘንና ውጥረት ድባብ ዉስጥ ይገኛል። ይህ ክቡር የሰው ህይወት የጠፋበትና ከባድ የመቁሰል አደጋ ያጋጠመበት ክስተትም ሰላምንና ፀጥታን በህግ አግባብ ለማስጠበቅ ሃላፊነት በተሰጠው የፀጥታ አካል የተፈፀመ መሆኑ እጅጉን በጣም አሳዛኝ ያደርገዋል። ይህም ድርጊት ብዙ መስዋእት ለከፈለ ህዝብ የማይገባዉ ነዉ፡፡ በመሆኑም የወጣቱ ግብረመልስም በክልሉ ሰላምና ዲሞክራሲ ጉዳይ ላይ የኔ ጉዳይ ነዉ የሚል ከፍተኛ የሰላም፣ የልማትና የለውጥ ፍላጐቶችና ቁርጠኝነት እንዲሁም ዝግጁነት መኖሩን በግልፅ አሳይቷል።
እንደሚታወቀዉ በአስቸኴይ ጊዜ አዋጅ የማስተዳደርና የማሰፈፀም አግባቦች ውስጥ የሰው ልጅን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን ማክበርና በህግ የማስከበር የመንግስት ግዴታ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ይሁን እንጂ እንደ አለመታደል ሆኖ በትግራይ ክልል በወቅቱ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ ክስተቶች አፈናና ግልፅ የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳለ ማስተዋል ተችሏል።
በተለይም እራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ ወጣቶች ላይ መተኪያ የሌለውን ክቡር ህይወታቸዉን እስከመቅጠፍ የደረሰ የሃይል እርምጃ በየትኛውም መለኪያ መወገዝ ያለበትና ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እኩይ ተግባር ነው። ድርጊቱም በፍጥነት ተጣርቶ የተወሰደው የእርምት እርምጃ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን ::
ይህንን ዓነቱን የክልሉ ወጣቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እና መሰል የአፈና ተግባራት የክልሉ ወጣት ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ አጥብቆ እንዲታገለው የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጥሪውን እያቀረበ፤ በአጠቃላይ ሀገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ የነቃ ፖለቲካዊ ተሳትፎ በማድረግ በክልሉና በሀገር ደረጃ የተደቀኑ ችግሮችን ለመቅረፍ በምታደርጉት እንቅስቃሴ ፓርቲያችን ድጋፉ እንደማይለያችሁ ለመግለፅ እንወዳለን።
"ወደ ህዝብ የተኮሰ ውድቀቱን አፋጠነ" እንደሚባለው፣ የገዢዎች የውድቀት ምልክት የሚጀምረዉ ወደ ህዝብ መተኮስ የጀመሩ እለት ነው። ስለሆንም በትግራይ ክልል በተለይ ደግሞ በመቐለ ከተማ ባጋጠመው ክስተት፣ በክልሉ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉዳይ የክልሉ ገዢ ፓርቲና መንግስት አካሄዱን ቆም ብሎ እንዲመረምር አስገዳጅ ማንቂያ ደወል ነው። የትግራይ ብልፅግና ፓርቲም ጉዳዩን በአፅንኦት እንደሚከታተለውና ለሚመለከታችሁ ሁሉ በጥብቅ ያሳስባል።
በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም የትግራይ ወጣት እና ለውጥ ፈላጊ አካላት በሙሉ ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በመሆን የለውጥ ሂደቱን እንዲያፋጥኑ ከፓርቲያችን ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን:: ፓርቲያችን የትግራይ ህዝብ እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የሚገባዉን ጥቅም እንዲረጋገጥ እና ሃገራዊ አንድነቱ እንዲጠናከር ይሰራል፡፡ በጥቂት ገዥ የህወሓት ቡድን በተለይ በዝምድና እና ጥቅም ትስስር እንዲሁም በሥልጣን ጥማት ምክንያት ትግራይን ከሌሎች የሃገሪቱ ህዝቦች ለመነጠል የሚደረግ ስራም ሆነ ሴራ በጥብቅ የምንታገለዉና የምናወግዘዉ መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን::
በመጨረሻም ለሟች የዘለዓለም እረፍት፣ ለቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ከልብ እንመኛለን።

ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ
ግንቦት 11/2012 ዓ.ም

19/05/2020
ኬንያ ከታንዛኒያና ሶማሊያ ጋር ያላትን ድንበር ዘጋችናይሮቢ —  ኬንያ ከታንዛኒያና ሶማሊያ ጋር ያላትን ድንበር በኮቪድ - 19 ምክንያት መዝጋቷን አስታወቀች። የኬንያ መንግሥት በአካባቢዉ እ...
19/05/2020

ኬንያ ከታንዛኒያና ሶማሊያ ጋር ያላትን ድንበር ዘጋች

ናይሮቢ — ኬንያ ከታንዛኒያና ሶማሊያ ጋር ያላትን ድንበር በኮቪድ - 19 ምክንያት መዝጋቷን አስታወቀች። የኬንያ መንግሥት በአካባቢዉ እየተንሰራፋ የመጣዉን የኮቪድ - 19 ወረርሺኝን ለመቆጣጠር ከሶማሊያ እንዲሁም ከታንዛኒያ ጋር ያላትን ድንበር ዝግ መሆኑን አስታወቀ። የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ድንበሮቹ ከባለፈዉ ቅዳሜ ጀምረዉ መዘጋታቸዉን ገልጸው፣ ታውጆ በሥራ ላይ ያለው ሰዓት ዕላፊም በሦስት ሳምንታት መራዘሙን ይፋ አድርገዋል።

የጅቡቲ መስመር ላይ የሚሰሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች በጅቡቲ ፖሊሶች ግፍ እየተፈፀመብን ነው ብለዋል!ባለፉት ሶስት ቀናት በርካታ መልእክቶችን ሲያደርሱኝ የነበሩት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሹፌሮች ...
19/05/2020

የጅቡቲ መስመር ላይ የሚሰሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች በጅቡቲ ፖሊሶች ግፍ እየተፈፀመብን ነው ብለዋል!
ባለፉት ሶስት ቀናት በርካታ መልእክቶችን ሲያደርሱኝ የነበሩት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሹፌሮች እንግልት፣ ጉቦ አምጡ መባል፣ መታሰር እና መደብደብ እየበረከተ እንደመጣ ገልፀው ትናንት ደግሞ የአስለቃሽ ጭስ እንደተተኮሰባቸው ነግረውኛል።
የጅቡቲ ድንበርን አቋርጠው እንደገቡ የሀገሪቱ ፖሊሶች የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት ጉቦ እንደሚጠይቁ፣ ሹፌሮችም ምንም አማራጭ ሲያጡ ከኪሳቸው እየከፈሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
መንግስት እየደረሰብን ያለውን በደል አይቶ መፍትሄ ይስጠን ብለዋል።

Meseret

 ሱዳን ውስጥ በአንድ ቀን 325 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 325 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰ...
17/05/2020



ሱዳን ውስጥ በአንድ ቀን 325 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 325 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,289 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 97 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 222 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸዉ ተገልጿል።
t.me/gafat2012

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዛሬ ይጀምራልበኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የጀርመን ቡንደስሊጋ ያለተመልካች ዛሬ ይጀምራል። ተጨዋቾች፣ ሙያተኞችና ዳኞችን ጨምሮ በስታድየም ውስጥ 300 ያክ...
16/05/2020

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዛሬ ይጀምራል

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የጀርመን ቡንደስሊጋ ያለተመልካች ዛሬ ይጀምራል። ተጨዋቾች፣ ሙያተኞችና ዳኞችን ጨምሮ በስታድየም ውስጥ 300 ያክል ሰዎች ይኖራሉ። ተጫዋቾች ሁሉም የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸዋል። አልፎም ከሜዳ ውጭ ማሕበራዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ታዘዋል።

t.me/gafat2012
ምንጭ፥ ቢቢሲ

15/05/2020

ኤርትራ "ከኮሮናቫይረስ ነጻ" አገር ሆነች።

በኤርትራ በቫይረሱ ተይዘው ህክምና ላይ ከነበሩ ሰዎች መካከል የመጨረሻው ታማሚ ዛሬ ከቫይረሱ አገግሞ ወደ ቤቱ መሸኘቱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኤርትራ በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ ሰዎች ብዛት 39 ሲሆን ምንም ሞት ሳይመዘገብ ሁሉም ከበሽታው መዳን ችለዋል🙏

ሲያናድድ !  መከላከል አይችል።
15/05/2020

ሲያናድድ ! መከላከል አይችል።

እስራኤል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደችን ሴት ቤተ እስራኤላዊት በሚኒስተርነት ሾመች።.......................................................................
15/05/2020

እስራኤል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደችን ሴት ቤተ እስራኤላዊት በሚኒስተርነት ሾመች።..............................................................................

ቤተ እስራኤላዊቷ ኒና ታማኖ-ሻታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር የአንድነት መንግሥት እየመሰረቱ ያሉትና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ በሚረከቡት ቤኒ ጋንትዝ ነው ለሚኒስትርነት የታጨችው።
https://bbc.in/2zDTdHN

እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደችን ሴት ቤተ እስራኤላዊት በሚኒስተርነት ሾመች።

የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!በአውሮፓ ለሚዘጋጁ ክትባቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ  #ክትባት በቀጣዩ አንድ (1) ዓመት...
15/05/2020

የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!

በአውሮፓ ለሚዘጋጁ ክትባቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ #ክትባት በቀጣዩ አንድ (1) ዓመት ውስጥ እውን ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

ምንጭ፥AlAin

«ትግራይ እንዳለችው ካደረገች እርምጃ ይወሰድባታል»የብልጽግና ፓርቲየትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተ...
14/05/2020

«ትግራይ እንዳለችው ካደረገች እርምጃ ይወሰድባታል»የብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ለክልሉ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ በሀገር ደረጃ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ተብሎ የሚደመደም ከሆነ ህዝብና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሳትፍ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ የፌደራሉን መንግስት የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
እንደ ጀርመን ድምፅ ዘገባ።

14/05/2020

#በደቡብ ክልል እስከ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮቪድ - 19 ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ ሲል የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስጠንቅቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንዳሉት የከፋ የተጋላጭ ሁኔታ አመልካች እንደሚያሳየው አሁን በበሽታው ዙሪያ የሚያታየውን 'የጥንቃቄ ጉድለት' መቅረፍ ካልተቻለ በክልሉ 60 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ በቫይረሱ ሊጠቃ ይችላል።

(የጀርመን ድምፅ)

 በኬንያ የሟቾች ቁጥር አርባ ሁለት (42) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።በተጨማሪ 1,486 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አንድ (...
14/05/2020



በኬንያ የሟቾች ቁጥር አርባ ሁለት (42) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።

በተጨማሪ 1,486 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አንድ (21) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 758 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ሶስት (3) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 284 ደርሰዋል።

ምንጭ ፤

 የምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት IGAD ለጤና ሚኒስቴር 800 ሺ ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።የተደረገው ...
14/05/2020



የምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት IGAD ለጤና ሚኒስቴር 800 ሺ ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

የተደረገው ድጋፍ በድንበር ላይ ፤ በተፈናቃዮቸ አከባቢ እና በስደተኞች ካምፕ የሚሰራውን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ተግባርን ለማገዝ የሚዉል ነው ተብሏል።

ምንጭ ፥

 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,580 ላቦራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ ...
14/05/2020



በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,580 ላቦራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 272 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5 ወንድ እና 4 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ17 እስከ 66 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 4

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 3

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 2

ኮቪድ-19 ኢኮኖሚውን ክፉኛ እያዳከመው ነው!በአዲስ አበባ የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በወር በአማካይ እስከ 35 ሚሊዮን ዶላር እያጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ሆቴል ...
14/05/2020

ኮቪድ-19 ኢኮኖሚውን ክፉኛ እያዳከመው ነው!

በአዲስ አበባ የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በወር በአማካይ እስከ 35 ሚሊዮን ዶላር እያጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር አስታውቋል።

ኮቪድ 19 የዓለም ወረርሸኝ በመሆን የተለያዩ አገራት የጤና ቀውስ ከመሆንም ባለፈ ኢኮኖሚያቸውን ክፉኛ እያዳከመ ይገኛል።

ቫይረሱ ዓለም አቀፍ መፍትሄ እስካላገኘ ድርስ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች ላይም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ መበርታቱ የማይቀር መሆኑ ይገመታል።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለይ የቱሪዝምና የመስተንግዶ ዘርፉ፣ ግብርናው፣ አምራች ኢንዱስትሪውና የውጪ ንግዱ ክፉኛ እየተጎዳ መሆኑን ጥናቶች እያመላከቱ ነው ።

ምንጭ፤

የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲቀጥል ተወሰነ***********************************************በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የቤተክርስ...
14/05/2020

የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲቀጥል ተወሰነ
***********************************************
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወሰነች፡፡

ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እንደገለፁት በቤተክስትያኗ አጥቢያዎች የሚሰጠው አገልግሎት መቋረጡ በምዕምኑ መንፈሳዊ ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን አብራርተዋል፡፡

እናም ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ አገልግሎቱ እንዲቀጥል ሲኖዶሱ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ ፤ #ኢቢሲ

 በሱዳን በአንድ  ቀን 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!የሱዳን ጤና ሚንስቴር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ7 ሰዎች ህይ...
08/05/2020



በሱዳን በአንድ ቀን 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 10 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,111 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 59 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 102 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ከበሽታው ማገገማቸዉ ተገልጿል።

07/05/2020

#በአገራችን፥
#የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የመከላከል ጉዳይ ጥንቃቄ ይሻል፤

* አጠቃላይ የላብራቶሪ ምርመራ:_28,445
* የተያዙ:_191
* የሞቱ:_4
* ያገገሙ:_93
* በፅኑ ታማሚ:_1

በኬንያ በጎርፍ አደጋ የ200 ሰዎች ሕይወት አለፈአዲስ አበባ፣ሚያዚያ 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት የ200 ሰዎች ህይወት ማለፉ...
07/05/2020

በኬንያ በጎርፍ አደጋ የ200 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት የ200 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው 200 ሰዎች በተጨማሪ 100 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ነው የተነገረው።

ከዚያም ባለፈ በሺዎች የሚቆጠሩ ሔክታር ሰብሎች መውደማቸውን የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

07/05/2020

መንግስት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል እርምጃዎችን ለመውሰድ ይገደዳል- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል ህገ መንግስቱን የሚጥሱ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ባስተላለፉት መልእክት፥ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎልተው ከወጡ የህዝብ ፍላጎቶች አንዱ ህዝብ የሚሳተፍበትና የሚሰማበት የአስተዳደር ወይም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት ነው ብለዋል።
ይህ ፍላጎትም እያደገ ዛሬ ላይ መድረሱንና በዚህ ትውልድም ይህንን የበለጠ ለማጎልበት የሚረዳ ኩነት ቀጣዩ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ መሆኑንም አንስተዋል።

ለዚህም በርካቶች ምርጫውን በጉጉት ሲጠብቁት ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ አንዳንድ ፓርቲዎችና ልሂቃን ምርጫው መደረግ የለበትም የሚል አቋም በያዙበት ጊዜ መንግስት ግን ሀገራዊ ፋይዳውን በመረዳት ምርጫው በጊዜው መካሄድ እንዳለበት አምኖ ሲዘጋጅ ነበር ብለዋል።

ሆኖም በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ሳቢያ ምርጫውን ቀድሞ በተያዘለት ሰሌዳ ማካሄድ እንደማይችል በህግ ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 22 ቀን 2012 ማስታወቁንም አስታውሰዋል።
በዚህም ምክንያት ምርጫውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ የግድ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የምርጫ መተላለፍ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የዓለም ሀገራትም ምርጫን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ
ስፖርታዊ ሁነቶች መሰረዝ ማስከተሉንም በምሳሌነት እንስተው አብራርተዋል።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ከገለፀበት ጊዜ ጀምሮም መንግስት የተለያዩ አማራጮችን በህግ ባለሙያዎች ሲያስጠና መቆየቱን በመግለፅ፥ የህግ ባለሙያዎችም ምርጫው መተላለፍ የሚችልበትን የህግ አማራጮችን ማቅረባቸውንና በዚህም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል ብለዋል።

ይህንን ተከትሎም የፌደራሉ መንግስት ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በጉዳዮ ላይ ህገ መንግስታዊ ትርጓሜ እንዲሰጥበት ለህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ መምራቱንም ገልፀዋል።
የቀረቡትን አማራጮች ተከትሎ በርካቶች የተለያየ ሀሳብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ገንቢ ሀሳብ ለሚያቀርቡት ምስጋና አቅርበው፤ ሆኖም ግን አማራጮቹ ተቀባይነት የላቸውም፣ ህገ መንግስቱ የሚተረጎም አንቀጽ የለውም በሚል የሽግግር መንግስት ሀሳብ ያቀረቡ መኖራቸውንም አንስተዋል።

ህገ መንግስቱ የሚተረጎም አንቀጽ የለውም የሚለው ክርክር አውቆ ላለማወቅ ከወሰነ አካል ወይም ጥልቅ የሆነ አላዋቂነት ውስጥ ከተዘፈቀ ሰው የሚቀርብ ሀሳብ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አክለውም አሁን ያለው መንግስት ህግ የሚያወጣ፣ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችን የሚፈርም፣ በጀትና እቅድ የሚያፀድቅ ህጋዊ መንግስት መሆኑን በመጥቀስ፤ ብልፅግና ፓርቲም በመላ ሀገሪቱ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መዋቅር ያለው፣ ሀገራዊ ለውጡን በመምራት የበርካቶችን ድጋፍ ያገኘ ግዙፍ ፓርቲ ነውም ብለዋል።
ህጋዊ በሆነ አግባብ የኮቪድ-19 ስጋት እስኪቀረፍ እና ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ደግሞ ሀገር የማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ፓርቲ መሆኑንም ገልፀዋል።
ያለ ምርጫ እንዲሁ ተጠራርቶ ስልጣን የመከፋፈል ህጋዊም ሆነ ህገ መንግስታዊ አግባብ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስልጣን ይገባኛል የሚለው ፈሊጥ ዴሞክራሲያዊም ህገ መንግስታዊም አይደለም ብለዋል።

ህገ መንግስቱ ከደነገገው ውጪ በህገወጥ ምርጫ ስልጣን ለመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለፅ፤ እንዲህ አይነቱ እንቅሰቃሴ የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሀገሪቱንና ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጥስ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በአንቀፅ 50 የፌደራል መንግስት ስልጣንና ተግባር ሲዘረዝር ቁጥር አንድ አድርጎ ያስቀመጠው ህገ መንግስቱን የመጠበቅና የመከላከል ኃላፊነት ነው፤ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን ሲሉም ገልፀዋል።

በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ካልሆነ በስተቀር የጨረባ ምርጫ ለማድረግ መነሳት ሀገርንና ህዝብን ለከፋ አደጋ የሚዳርግ በመሆኑ፤ መንግስት ሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳልም ብለዋል።

ስልጣን የሚፈልጉ የፖለቲካ ሀይሎች የሀሳብ ክርክሮቻቸው ወጣቱንና እናቶችን በማይጎዳ መልኩ እንዲያደርጉት ይመከራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐቢይ፥ ፖለቲከኞች ስልጣን እንዲይዙ ወጣቶች ማለቅ፣ እናቶች ማልቀስ፣ ቤቶች መፍረስና ህዝቦች መፈናቀል የለባቸውም ብለዋል።

የከሮናቫይረስ ስጋት ተጋርጦብን፤ የሀገር ሉአላዊነትና ደህንነት ለአደጋ ተጋልጦ ባለበት ጊዜ ስልጣንን ያለ ምርጫ እና ከህግ አግባብ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁኝ ሀገር አተራምሳለው የሚል ማንኛውንም ሀይል መንግስት እንደማይታገስ በማሳሰብ ፤ ለዚህም በሁሉም ረገድ ዝግጁ ነን ሲሉም ገልፀዋል።

ምንጭ፣FBC

ህይወታችሁን ገብራችሁ፤ ደማችሁን አፍስሳችሁ  ለዛሬ ኩራትና ክብራችን ላበቃችሁን አርበኞች
06/05/2020

ህይወታችሁን ገብራችሁ፤ ደማችሁን አፍስሳችሁ ለዛሬ ኩራትና ክብራችን ላበቃችሁን አርበኞች

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gafat Info Center-ጋፋት የመረጃ ቋት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gafat Info Center-ጋፋት የመረጃ ቋት:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share