ሾፌሩ

ሾፌሩ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሾፌሩ, Media, .

አፋር ማኅበረሰብ አቀፍ የመንገድ አጠቃቀም ግንዛቤ ድጋፍ ሰጭ የሾፌሮች ልማት ማኅበር መቋሙን መረጃ ደርሶናል ይህ መልካም እና የሚደገፍ ተግባር ነው በርቱ እንላለን ::
03/06/2024

አፋር ማኅበረሰብ አቀፍ የመንገድ አጠቃቀም ግንዛቤ ድጋፍ ሰጭ የሾፌሮች ልማት ማኅበር መቋሙን መረጃ ደርሶናል ይህ መልካም እና የሚደገፍ ተግባር ነው በርቱ እንላለን ::

ጥንቃቄየምትመለከቱት ተሽከርካሪ በአዳይቱ እና ሚሊ መሃከል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የወደቀ ነው መንገድ ስለያዘ በጥንቃቄ እንተላለፍ
02/06/2024

ጥንቃቄ
የምትመለከቱት ተሽከርካሪ በአዳይቱ እና ሚሊ መሃከል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የወደቀ ነው መንገድ ስለያዘ በጥንቃቄ እንተላለፍ

ሞጆም እንደ ጅቡቲ የኮቴ ጀመረች?ሞጆ ከተማ የኮቲ 2000 ብር ካልከፈላችሁ ወደ እስር ቤት ትጋዛላችሁ በሚል ማስፈራራት አሽከርካሪን በማንገላታት ተግባር  ላይ መሰማራታቸውን መረጃ እየደረሰን...
10/03/2024

ሞጆም እንደ ጅቡቲ የኮቴ ጀመረች?

ሞጆ ከተማ የኮቲ 2000 ብር ካልከፈላችሁ ወደ እስር ቤት ትጋዛላችሁ በሚል ማስፈራራት አሽከርካሪን በማንገላታት ተግባር ላይ መሰማራታቸውን መረጃ እየደረሰን ነው።

ኪሱ የጎደለበት ካዝናው የተራቆተበት ሁሉ ደረሰኝ አሳትሞ የኮቲ የምን እያለ ህዝብን የሚዘርፍበት ስርአት እያየን ነው። ተሽከርካሪ ለጫነው ጭነት ቀረጥ ከፍሎ ለሚጉዋዝበት መንገድ በአመት የሮድ ፈንድ በሚከፍልበት ሂደት ማንም እየተነሳ ክፈል እያለ ማንገላታት የሃገር ክሽፈት ምልክት ነው።

ሹፌሩ እንደ ወጣ ቀረ 😢ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድረው በመኪና አሽከርካሪነት ነው ። እንደወትሮው ሁሉ ከዳር አገር ወደ መሃል አገር የሚደርስ ጓዝ በመኪናው ጭኖ በማምጣት በርካታ ዕድሜውን አሳልፏ...
10/03/2024

ሹፌሩ እንደ ወጣ ቀረ 😢

ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድረው በመኪና አሽከርካሪነት ነው ። እንደወትሮው ሁሉ ከዳር አገር ወደ መሃል አገር የሚደርስ ጓዝ በመኪናው ጭኖ በማምጣት በርካታ ዕድሜውን አሳልፏል ።

እንደምታውቁት በተለይ የአገር አቋራጭ መኪና ሾፌሮች ከሚያከናውኗቸው ነገሮች አንዱ በመንገዳቸው የሚያገኙትን ቤተ ክርስቲያ ቆም ብለው ለቤተሰባቸው እና ለመንገዳቸው ሰላም ይጸልያሉ ።

ይኸ ወንድማችንም ወለንጪቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሲደርስ ጸሎቴን ላድርስ ብሎ ከመኪናው ወረደ ። ነገር ግን ወደ መኪናው በሰላም አልተመለሰም ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ይህ ሹፌር በወንበዴዎች እጅ ወደቀ ።

በረሃ ለበረሃ ከመኪና መሪ ጋር እጁን ያስተሳሰረው ሾፌር በወንበዴዎች እና በክፉዎች ሰዎች እጅ ታሰረ ። አልራሩለትም ፣ የጭካኔአቸውን ጥግ አሳዩ ። እንደ ወጣ አስቀሩት ።

በዚህ ዘመን ትልቁን ገፈት እየቀመሱ ከሚገኙ ተጋላጭ ወገኖቻችን መካከል ሾፌሮች ዋነኞቹ ናቸው ። ደሞዛቸው እና ሥራቸው ካለመጣጣሙ በተጨማሪ የማትተካ ሕይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል ።

ፈጣሪ ነፍሱን ይማርልን !

አንድ በተለምዶ 25 ሊትር የሚይዝ በዛ ቢባል ከ28 ሊትር በላይ የማይዝ ጀሪካ ናፍጣ ከማደያ ውጭ እስከ 3,400 ብር በደረሰ ዋጋ ይሸጣል :: ይህ ማለት በሊትር 121 ብር ከ41 ሳንቲም ማ...
23/02/2024

አንድ በተለምዶ 25 ሊትር የሚይዝ በዛ ቢባል ከ28 ሊትር በላይ የማይዝ ጀሪካ ናፍጣ ከማደያ ውጭ እስከ 3,400 ብር በደረሰ ዋጋ ይሸጣል :: ይህ ማለት በሊትር 121 ብር ከ41 ሳንቲም ማለት ነው የነዳጅ ዋጋ 80.01 በሆነበት አካባባቢ ከሊትር የ41 ብር ጭማሪ ተደርጎ ይሸጣል

ይህ ማለት በህጋዊ ከማደያ 2240 መሸጥ የነበረበት ከማደያ ውጭ 3400 ብር ሲሸጥ 1160 ብር ከአንድ ጀሪካ ላይ ጭማሪ ይደረጋል ማለት ስለዚህ ማደያዎች ለህጋዎ ቀጅወች በዋጋው ከመሸጥ በጀሪካ ለሚሸጡ አሳልፎ መስጠትን ይመርጣሉ ለዛም ነው የነዳጅ እጥረት የሚከሰተው ::

ከአንድ ጀሪካ 1160 ብር ትርፍ ካለ ከውጭ የሚሸጡት ከማደያ በሊትር 100 ብር ቢገዙት ያዋጣቸዋል ይህ ተግባር ነው ለመኪኖች ነዳጅ እጥረት አንዱ ምክንያት ::

ንግድ ቢሮ የሚባል የዘራፊ የመንታፊ ሽፋን ሰጭ ተቋም ባለበት ሃገር ከድቀት ህዝብ ከእንግልት ሊድን አይችልም::

ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ጉንዶይን ከተማ ፖሊስ እጅግ እናመሰግናለንበ28/10/2015 ደብረወርቅ መግቢያ ላይ ሾፌር እና ረዳቱን ገለው የጫነውን መኪና ራሳቸው ይዘው ሲጓዙ የጉንዶይን ከተማ ፖሊ...
06/07/2023

ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ጉንዶይን ከተማ ፖሊስ እጅግ እናመሰግናለን

በ28/10/2015 ደብረወርቅ መግቢያ ላይ ሾፌር እና ረዳቱን ገለው የጫነውን መኪና ራሳቸው ይዘው ሲጓዙ የጉንዶይን ከተማ ፖሊስ ገዳይ ወንበዴዎችን ጥሰው ለማለፍ ሲሞክሩ የፊት ጎማውን በመምታት 3 ነፍሰ በላ ዘራፊወች ከእነ መኪናው በቁጥጥር ስር አውሏል ማንም ገሎ ማምለጥ እንደማይችል የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረድ የጉንዶይ ፖሊስ አሳይቶናል እናመሰግናለን

ካሁን በፊት እዛው አካባቢ ቡና የጫነ ሾፌር መገደሉ ይታወቃል ገዳዮቹ እነዚህ ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥልቅ ምርመራ ይደረግ

እንዲህ ያሉ ነፍሰ በላወች የማበረሰቡን ስም የሚያረክሱ እንስሶች መቀጣጫ የሚሆን ፍርድን ሊሰጣቸው ይገባል::

"ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባው ሬንጀር ሁለት ነው "⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️'እሱም የመከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ብቻ ነው።'
07/04/2023

"ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባው ሬንጀር ሁለት ነው "
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
'እሱም የመከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ብቻ ነው።'

አፋልጉን ያልነው ሃይሉክስ ፒክ አፕ መኪና ከነሌባው በቁጥጥር ስር  ውለዋል::****************************************ከአዲስ አበባ ተሰርቆ ሲጓዝ የነበረ ኮድ-3 አ.አ...
31/03/2023

አፋልጉን ያልነው ሃይሉክስ ፒክ አፕ መኪና ከነሌባው በቁጥጥር ስር ውለዋል::
****************************************
ከአዲስ አበባ ተሰርቆ ሲጓዝ የነበረ ኮድ-3 አ.አ የሰሌዳ ቁጥር 16411 ሃይሉክስ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ እስከነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ማዋሉን በስልጤ ዞን የዓለምገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ትላንት አሳወቀን ::መረጃ የደረሰው የከተማው ፖሊስ ከፍተኛ ፍተሻ፣ ክትትልና ጥበቃ ሲያደርግ ቆይቶ፤ ከሌሊቱ በግምት 7:45 አካባቢ ተጠርጣሪው መኪናውን በከፍተኛ ፍጥነት እያሽከረከረ ወደ ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ ሲደርስ፤ እንዲቆም በፖሊስ ትዕዛዝ ቢሰጠውም እንቢ ብሎ ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር በፓትሮል እግር በእግር በመከታተል፤ ጎማውን በጥይት መትቶ በማስተንፈስ፤ ተጠርጣሪውን እስከነ መኪናው በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አደም ከድር ገልጸዋል::

ሰላም Driving in ADDIS ለመረጃ እና ለጥንቃቄ እንዲሆን ዘንድ በእኔ ላይ የደረሰውን የማጭበርበር ዘዴ ላካፍላችሁ   ቅዳሜ ቀን ነበር ከቃሊቲ ማሠጠኛ እየወጣሁ አንድ ልጅ መቶ መኪና ...
29/03/2023

ሰላም Driving in ADDIS

ለመረጃ እና ለጥንቃቄ እንዲሆን ዘንድ በእኔ ላይ የደረሰውን የማጭበርበር ዘዴ ላካፍላችሁ

ቅዳሜ ቀን ነበር ከቃሊቲ ማሠጠኛ እየወጣሁ አንድ ልጅ መቶ መኪና በርካሽ እንደሚያለማምድና በ100 ሜትር 27 ብር ነው ላለማምድሽ ብሎ በግድ አግባባኝ!
ከዛ ለ 30-40 min አለማመደኝና 147 መጣ ከዛ እሱን በ 27 ብር አባዢው ብሎ 3,969 ብር መጣ በጣም ደነገጥኩ እና እኔ ራሱ auto መንጃ ፍቃድ ለማውጣት ከፍዬ የተለማመድኩት በ 9,000 ብር ነው ስላቸው ነግረንሽ ነበር እኮ ብለዉ ተኮሰታተሩ እኔም ስለፈራሁና ግራ ስለገባነኝ ባጋጣሚ ከያስኩት ብር ይሄ ነው ብዬ ግማሽ 4000 birr አውጥቼ ሰጠኋቸው ።አይናቸውን ሳያሹ ተቀብለዉኝ ሄዱ። ከዛ ስሰማ በትክክለአኛ calculation ወደ 397 birr እንደሚመጣ አወኩ። እባካችሁ እዛ አካባቢ ስትሄዱ ተጠንቀቁ ለማለት እወዳለሁ።
ለአጭበርባሪዎቹም የሰዉ ላብና ሀቅ እርግማን ይሆንባችኋልና ተዉ እግዚአብሔር አይወድም።
# ሜሪ.

 #436 - ፍቅረኛዬ በቃላት ግድፈት አጣሁት። ምን ትመክሩኛላችሁ? ሰላም ለፍቅር ቤተስቦች። ከጓደኛዬ ጋር የተዋወቅነው በጓደኛው በኩል ነበር። እሱም እኔም በእህትነትና በወንድምነት እንጅ ወ...
15/12/2022

#436 - ፍቅረኛዬ በቃላት ግድፈት አጣሁት። ምን ትመክሩኛላችሁ?

ሰላም ለፍቅር ቤተስቦች። ከጓደኛዬ ጋር የተዋወቅነው በጓደኛው በኩል ነበር። እሱም እኔም በእህትነትና በወንድምነት እንጅ ወደ ፍቅር ይቀየራል የሚል አንድም ቀን አላሰብንም ነበር። ግን ተቀየረ። ለፍቅራችን ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ። አይሆንሽም በሚል ከአባቴ ጋር ተጣልቻለሁ። መጠጥ ይጠጣ ነበር እሱን ተወ። እውጭ ያመሽ ነበር እሱንም አስተውኩት። ብቻ ያሉበትን መጥፎ ፀባዮች አስተውኩ። አልፎ አልፎ እንጣላለን፡ ግን ወዲያው ችግሩን ተናጋግረን እንፈታለን። በዚህ ፀባዩ በጣም እወደዋለሁ። የወደድኩትም በመልኩ ወይም ገንዘቡ አይደለም፡ በፀባዩ እንጅ ።

ለሱ ያልሆንኩት የለኝም እሱ ታስሮ ምሽት ነበር ከጓደኞቹ ጋር ታፍኖ ወደ ሁመራ ወስደውት ከ2ወር በላይ አልቅሻለሁ ፀልያለሁ ተስያለሁ በዛን ወቅት ከእህቱ ጋር ነበር የምንገናኘው። ያለውን ትነግረኝ ነበር ሲመጣም እህቱ ነገረችኝ በደስታ አለቀስኩ ስራ ስሰራ በደስታ ውስጥ ስለነበርኩ ቢላ እጀን ቆርጨ ጤና ጣቢያ ገባሁ እሱም ደውሎ ያለውን ነገር አጫወተኝ።

እየመጣ እንደሆነ ብር እንደሚያስፈልገው በጓደኞቹ ወዳው በሞባይል ባንኪንግ ለራሴ 200 አስቀርቸ ያለኝን ላኩለት ከዛም በደህና መጣ የሆነ ስአት ሌሊት ላይ እንዳይደብርሽ የጓደኛዬ አባት እሰው ጋር ተጣልቶ ቤቱን መስተዋት ሰባብረውበት እዛነኝ ልጁ እየመጣነው ። እሽ አልኩት ።

መልሶ ከ20ቀን በኋላ ምሽት ደውሎ ዛሬም እጓደኛየ ቤት ነው የማድረው ስልኩን ሳይለንት ስለማደርገው አጋጣሚ ከደወልሽ እንዳይደብርሽ አለኝ እኔም እሽ እራስህን ጠብቅ ብየ ዘጋሁ።

በሌላ ቀን ስደውል አያነሳም ስደግም ታስሬ ገና ተፈታሁ ባወራሽ ብዙነው ምንም አይሰራልሽ አለኝ ። እሽ አልኩት ።

ምሽት ስደውል አይነሳም ስደግም ስልኩ ተዘግቷል ግራ ገባኝ። መልሶ ታስሮ ወይስ እስኪነጋ ቸኮልኩ ስራ ገብቸ በጓደኛነ ስልክ ስደውል አነሳው ዘጋሁን እሱ ደወለ ሚስኮል አግኝቸ አለ ዘጋችው ከ15ደቂቃ በኋላ ስደውል ሄሎ ሄሎ ብቻ አይሰማም ወይስ ማውራት አለፈለክም ብየ ቴክስት ላኩለት።

ቆይቶ ደወለ ስልኬ ተበላሽቶ የማዘርን አምጥቼ ነው ደግሞ ማታም እዛው ነው ያደርኩት አለኝ እሽ አልኩ ። ማታም ስልኩ ዝግነው ጧት ቢሮ ስገባ በሌላ ስልክ ደውሎ ስልኩ እንደተበላሸና ሲሙ ከጓደኛው ጋር እንደሆነ ነገረኝ እሽ አልኩ።

በሌላ ቀን ስደውል አነሳው ቆይቶ ሲደውል አላየሁትም ስደውል አያነሳም በሌላ ስልክ ስደውል ያነሳል ምሽትም ስደውል ተደጋጋሚ አይነሳም ቆይቶ ደወለ አላነሳሁም አሁንስ አበዛሽው ሲለኝ መደወሉነው ይቅርታ አልኩት።

እኔ ስደውል ዘግቶታል ሰሞኑን ምኑነህነው እኔማላውቀው ችግር አለንዴ የተፈጠረ? ፀባይህ ተቀያየረ እኔ ፀባይህንጅ መልክህን ወይም ገንዘብህን ብየ አይደለም የቀረብኩህ ፀባይህ ከተቀየረ ከማን ጋር እቆያለሁ ብየ ቴክስት አደረኩለት።

ይሄን በፊትም እለው ነበር አሁን ግን አስቀየመው ይሄን መናገር አይጠበቅብሽም ድህነቴንም አስቀያሚነቴንም አውቀዋለሁ። አወ አንች ቆንጆነሽ ሀብታምነሽ ላደረግሽልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ ውለታሽን ሰው መክፈል አይችልም እኔግን ለመክፈል እሞክራለሁ አልረሳም አለኝ

እኔ ደግሞ ከነሁሉ ጥፋቱ ድክመቱ ተቀብየዋለሁ እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ እሱ የለውም አሁን ተደጋጋሚ ብደውልም አላነሳልኝ አለ እወደዋለሁ። ሰላም አጣሁ ሁሉም ጥያቄ ሆነብኝ ምክንያት ነው ወይስ ከ1 አመት በላይ አብረን ቆይተናል ልፋቴ ድካሜ ገደል ገባ በማይረባ አማረኛ የኔ ጥፋት ምንድነው ጥፋቴ አልገባኝም፣ የፍቅር ቤተሰቦች ምክራችሁ ያስፈልገኛል። አመሰግናለሁ።

 #ለጥንቃቄ ለአሽከርካሪዎች ቅድመ ጥንቃቄ ይድረሳቹ * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * ከአድስ አበባ ወደ ጅማ የምወስደው ዋናው መንገድ ልክ በየም ልዩ ወረ...
08/10/2022

#ለጥንቃቄ
ለአሽከርካሪዎች ቅድመ ጥንቃቄ ይድረሳቹ
* * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * *
ከአድስ አበባ ወደ ጅማ የምወስደው ዋናው መንገድ ልክ በየም ልዩ ወረዳ ሳጃ ከተማ እንዳለፉ የኮሾ ድልድይ መዳረሻ ላይ መሬቱ ሸርተት ብሎ ዋናው አስፓልት ስለሰመጠ ጥንቃቄ አድርጋቹ አሽከርክሩ፡፡

ብዙ አሽከርካሪዎች በቀን እንኳን ቦታውን አስተውሎ ሳይመለከቱ እይተዘናጉ ከመውደቅ በጥቂት እየተረፉ ነው ያየሁት፡፡

የምመለከተው አካል የሰው ህይወት ላይ እና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ማስተካከያ ወይም አማራጭ መንገድ ብበጅለት፡፡

መንገዱ ከጅማ ወደ አድስ አበባ ለሚያሽከረክሩ ቦታው አዳጋች ስለሆነ ጠቋሚ ምልክት ብደረግበት እያልኩት፤ የአከባቢው ነዋሪዎች ለምልክት ይበጅ ዘንድ ምልክት በማድረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

ዛሬ ጠዋት በመቅደላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ።በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ዛሬ ጠዋት መነሻዉን ከማሻ ከተማ በማድረግ ወደ ጎጎስ ለቅሶኛ ጭኖ የሄደ ኮድ አማ...
01/10/2022

ዛሬ ጠዋት በመቅደላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ።

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ዛሬ ጠዋት መነሻዉን ከማሻ ከተማ በማድረግ ወደ ጎጎስ ለቅሶኛ ጭኖ የሄደ ኮድ አማ -22645 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ልዩ ስሙ "መተከዥያ "የተባለ ቦታ በደረሰበትበት የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ወዲያዉኑ አልፏል።

የአደጋዉ መንስኤና የጉዳት መጠኑ እየተጣራ ያለ ቢሆንም ከመጠን በላይ ጭነት ለአደጋዉ መንስኤ እንደሆነ ከጉዳቱ የተረፉ ግለሰቦች ተናግረዋል ሲል የመቅደላ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ገልጿል።

‘ የሚሳሳሙ አለቶች ’ ይባላል። ይሄን አለት ላለማፍረስ መንገዱ እንዲጠብ ተደርጓል።ስዊትዘርላንድ ሀገር ይገኛል
30/09/2022

‘ የሚሳሳሙ አለቶች ’ ይባላል። ይሄን አለት ላለማፍረስ መንገዱ እንዲጠብ ተደርጓል።

ስዊትዘርላንድ ሀገር ይገኛል

ከባድ የመኪና አደጋ ደረሰ!! ዛሬ በአዲስ አበባ ናዝሬት የፍጥነት መንገድ ላይ አደገኛ የመኪና አደጋ ተፈጥሯል።  ስለደረሰው የጉዳት መጠን መረጃው አልደረሰንም። ፎቶውን በአካባቢው ያለ ሰው ...
29/09/2022

ከባድ የመኪና አደጋ ደረሰ!!

ዛሬ በአዲስ አበባ ናዝሬት የፍጥነት መንገድ ላይ አደገኛ የመኪና አደጋ ተፈጥሯል። ስለደረሰው የጉዳት መጠን መረጃው አልደረሰንም። ፎቶውን በአካባቢው ያለ ሰው ነው ያጋራን። እባካችሁን ጥንቃቄ እያረግን እናሽከርክር።

አሳዛኝ መረጃ‼️በአደዓ በርጋ በደረሰ የመኪና አደጋ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ‼️በምስራቅ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማ...
29/09/2022

አሳዛኝ መረጃ‼️
በአደዓ በርጋ በደረሰ የመኪና አደጋ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ‼️
በምስራቅ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። ሰዎችን አሳፍሮ ሲሄድ የነበረው መኪና ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፣ 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 30 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እና በ2 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

መስከረም 17/2015 ከቀኑ 8:00 ሰአት አካባቢ መነሻውን አጣዬ ያደረገ አሸዋ ጭኖ ወደ መሐል ሜዳ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጓሳ አካባቢ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎ...
29/09/2022

መስከረም 17/2015 ከቀኑ 8:00 ሰአት አካባቢ መነሻውን አጣዬ ያደረገ አሸዋ ጭኖ ወደ መሐል ሜዳ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጓሳ አካባቢ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ1ሰው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለየማዲንጎበ90ዎቹ መጀመሪያከመጡተወዳጅድምፃዊያን መሀል አንዱ ነው::በሙዚቃ ስራውም ሶስት አልበሞችን ጨምሮ በግል እና በተናጥል የተጫወታቸው ነጠ...
27/09/2022

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ማዲንጎበ90ዎቹ መጀመሪያከመጡተወዳጅድምፃዊያን መሀል አንዱ ነው::

በሙዚቃ ስራውም ሶስት አልበሞችን ጨምሮ በግል እና በተናጥል የተጫወታቸው ነጠላ ዜማዎችን ሰርቷል::

በተለያዮ ማህበራዊ እና አገራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ የሆነው ድምፃዊ ማዲንጎ የኤች አይ ቪ ኤድስ ዘመቻ የህዳሴ ግድብ እና የትራፊክ ህብረዝማሬዎችም ላይ ተሳትፏል::

ከዚህ በተጨማሪም ማዲንጎ በቅርብ ባጋጠመ የሰሜኑ ግጭት ግንባር ላይ የሚገኘውን ሰራዊት ቦታው ድረስ በመሄድ ማበረታታቱ የሚታወስ ነዉ።

ለቤተሰቦቹ ለወዳጂ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ

.....አንድ በጣም ድሃ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር። አንድ ቀን በጣም ረጅም ፀጉር ያላት ሚስቱ ፀጉሯ በደንብ እንዲያድግ  ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው። ሰውየው በጣም አዘነ እና አልች...
23/09/2022

.....አንድ በጣም ድሃ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር።

አንድ ቀን በጣም ረጅም ፀጉር ያላት ሚስቱ ፀጉሯ በደንብ እንዲያድግ ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው።

ሰውየው በጣም አዘነ እና አልችልም አላት ። አሁን የሰበረውን የእጅ ሰዓት ማሰሪያ ለመጠገን እንኳን በቂ ገንዘብ እንዳልነበረው አስረድቷል።

ጥያቄዋን ድጋሚ አልጠየቀችም።

ሰውዬው ወደ ሥራ ሄዶ በሰዓት ሱቅ በኩል አለፈ፣ የተበላሸውን ሰዓቱን በዝቅተኛ ዋጋ ሸጦ ለሚስቱ ማበጠሪያ ገዝቶ ሄደ።

ለባለቤቱ ሊሰጣት ማበጠሪያውን በእጁ ይዞ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት መጣ።

ሚስቱ በጣም በአጭሩ ፀጉሯን ተቆርጦ ሲያይ ተገረመ።

ፀጉሯን ሸጣ አዲስ የእጅ ሰዓት ገዝታ ይዛ ነበር።

እንባ ከዓይኖቻቸው በአንድ ጊዜ ፈሰሰ፣ ለድርጊታቸው ከንቱነት ሳይሆን ለፍቅር ተካፋይነት።

ሞራል፡ መውደድ ምንም አይደለም፣ መወደድ ግን አንድ ነገር ነው፣ ግን መውደድ እና በሚወዱት ሰው መወደድ ነው፣ ያ ሁሉም ነገር ነው። ፍቅር የህግ ሁሉ ፍፃሜ ነውና እንደ ቀላል ነገር አንየው መልካም ቀን።

ትዝብት !እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ከእለት ዕለት እየተባባሱ ነው ። የተበላሹ መንገዶችን በበጎ ፈቃድ የሚጠግኑ ቅን ሰዎች እንዳሉ ሆነው ይህንን ክፍተ በመጠቀም ገንዘብ መሰብሰቢያ እያደረጉ ያ...
22/09/2022

ትዝብት !

እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ከእለት ዕለት እየተባባሱ ነው ። የተበላሹ መንገዶችን በበጎ ፈቃድ የሚጠግኑ ቅን ሰዎች እንዳሉ ሆነው ይህንን ክፍተ በመጠቀም ገንዘብ መሰብሰቢያ እያደረጉ ያሉ ወጣቶች በየቦታው እየተበራከተ ነው ።

ለምሳሌ ይህ በምስሉ የሚታዩት ወጣቶች ከሞጆ ፈጣን መንገድ እንደወጡ ወደ ሞጆ ከተማ ለመግባት የባቡር መንገድ ድልድይ ሥር በእዚህ መልኩ ሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ላይ መኪና እያስቆሙ ገንዘብ በኃይል ለመቀበል ጥረት የሚያደርጉ ወጣቶች ናቸው ። በየቀኑ ወጣቶቹ ይቀያየራሉ አንዳንዴም ሹፌር ሳይሰጣቸው ሲቀር ወደ መኪና ድንጋይም ይወረውራሉ ።

በቅርብ እርቀት የጸጥታ አካላት ቢኖሩም ድርጊታቸውን ሲኮንኑ አይታይም ።

በ2014 ዓ.ም የሲኖትራክን ሚና በሚገባ የተወጣው Suzuki Dzire… በዝግታ እና አስተውለን እንንዳ
22/09/2022

በ2014 ዓ.ም የሲኖትራክን ሚና በሚገባ የተወጣው Suzuki Dzire…

በዝግታ እና አስተውለን እንንዳ

22/09/2022
ይህ የዳሸን ባንክ ተሽከርካሪ ሾፌር ወለጋ መስመር አርጆ ወጣ ብሎ 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ በ 27/12/2014  በተከፈተ ተኩስ ህይወቱ አልፏል መንግስት የሾፌሮችን ሞት ለማስቀረት ሊሰራ ይገ...
03/09/2022

ይህ የዳሸን ባንክ ተሽከርካሪ ሾፌር ወለጋ መስመር አርጆ ወጣ ብሎ 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ በ 27/12/2014 በተከፈተ ተኩስ ህይወቱ አልፏል መንግስት የሾፌሮችን ሞት ለማስቀረት ሊሰራ ይገባል።
ነፍስ ይማር

ወልዲያን ከቆቦ የሚያገናኘው የአላውሃ ድልድይ ዛሬ ሌሊቱን በጎርፍ ተወስዶ የእግረኛ መንገዱም ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል።
26/08/2022

ወልዲያን ከቆቦ የሚያገናኘው የአላውሃ ድልድይ ዛሬ ሌሊቱን በጎርፍ ተወስዶ የእግረኛ መንገዱም ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል።

የአሽከርካሪዎች ህይወት ለአደጋ የተጋለጠበት ጊዜ!!      የአርባምንጩ ልጅ ሾፌር ጀማል  እንድሪስ (ጀማል ኤልቢስ ይባል ነበር ) ለአመታት በአይሱዙ ሹፍርና ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ቢኖርም ...
26/08/2022

የአሽከርካሪዎች ህይወት ለአደጋ የተጋለጠበት ጊዜ!!
የአርባምንጩ ልጅ ሾፌር ጀማል እንድሪስ (ጀማል ኤልቢስ ይባል ነበር ) ለአመታት በአይሱዙ ሹፍርና ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ቢኖርም ፣ በተለምዶ FSR የሚባል ከፍ ያለ የጭነት መኪና ገዝቶ ስራ መስራት ከጀመረ ገና አንድ ወር አልሞላው ።
' ቀነ ጎደሎ' በሚባለው አጋጣሚ በጭነት ተሽከርካሪው ፣ ከሞቀ ቤቱ ፣ ከተረጋጋና ሰላማዊ ከሆነው የትውልድ ቀየው አርባምንጭ ተነስቶ ፣ ወደ ሐረር ሙዝ ጭኑ ይጓዛል። ጭነቱንም በሰላም አድርሶ ' አገር ሰላም ነው ' በሚል መልሶ ወደ አፋር ሌላ ጭነት ጭኖ ጉዞ ይጀምራል።
የአገራችን ብዙ አካባቢዎች ሰላም እየደፈረሰ፣ መረጋጋት እየነጠፈ፣ ግጭትና መባላት ተመላልሶ እያገረሸ ነውና ወጥቶ በሰላም መግባት ብርቅ እየሆነ መጥቷል። ለምሽት ጉዞና ዳር አካባቢ ሰራተኞችማ ፈተናው የበዛ ሆኗል።
ይህን መሬት ላይ ያለ ሀቅ የዘነጋው ወጥቶ አዳሪው ሾፌር ጀማል ግን ፣ ልጆች ለማሳደግ ብሎ ከላይ ታች ሲል ፣ ያልጠበቀው መከራ ገጠመው ። ነብሰ ገዳዮች እጅ ላይም ወደቆ ህይወቱ ተቀጠፈች ። እንደወጣም ቀረ!!
ከአሳይታ ወደ አዲስ አበባ በ13/12/14 ምሽት 6 ሰአት ሲጎዝ ፣ በእንደፎና ገዳማይቱ መሀል በተለምዶ "ቴሌ" የተባለ አካባቢ (በቅርብ ርቀት የፌደራል ፖሊስ ካምፕ መኖሩን ልብ ይሏል። ) ተሽከርካሪውን ታጣቂዎች አስቆመው ሾፌሩን ገደሉ ፣ ረዳቱና አብሮ ሲጎዝ የነበረው የአሽከርካሪው ወንድም ለጊዜው አምልጠው ህይወታቸው ቢተርፍም ፣ የያዙት ንብረት ሁሉ ተዘረፈ።
የሟች ወገኖችን በብዙ መከራ የልጃቸውን አስከሬን አምጥተው በሶስተኛው ቀን አርባምንጭ አፈር አልብሰዋል። ስለነብሰገዳዮቹ ግን በቂ መረጃ እንኳን አላገኙም ። ተሽከርካሪውም እዚያው በፖሊስ እጅ ይገኛል ።
አንዳንዶቹ በኢሳና አፋር ድንበር በነበረ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ፣ የመንደር ሽፋታዎች ወይም ኮንትሮባንዲስቶችና የታጠቁ የመንግስት ሀይሎች ናቸው የገደሉት ይላሉ ። ሌሎች ደግሞ ወንድማቸውን የገደለውት የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሰዎች እንደሆኑም ጠርጥረዋል ። ህልፈቱ ግን የሰርቶ በላና የንፁሀን እንደመሆኑ ማንንም ያሳዝናል።
ለሁሉም ዘመድ ወገኖቹ አስከሪንም አግኝተው ለመቅበር የረዳቸውን መከላከያ ሰራዊትን ያመሠገኑ ሲሆን፣ የዞኑ ፖሊሶችም ግማሽ መንገድ የአምቡላንስ ትብብር በማድረግ እስከ ሞጆ በመሸኘታቸው ፣ ወገናዊነታቸውን አሳይተዋል። ሾፌር ጀማል ግን ሶስት ልጆቹን በትኖ ላይመለስ ሄዷል።
ነብሱን ይማረው !! ።
# BMH

አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስትያን አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈነሐሴ 20፤ 2014 ዓ.ም.(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ...
26/08/2022

አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስትያን አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

ነሐሴ 20፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስትያን አካባቢ በሚገኘው እና ወደ ቦሌ ሚካኤል ከሚወስደው ድልድይ ላይ ወደ መኖሪያ ቤቶች በወደቀ ተሽከርካሪ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተሰማ።

በድልድዩ ላይ ሲጓዝ የነበረው ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ከድልድዩ በታች ወደሚገኙት መኖሪያ ቤቶች በመውደቁ የደረሰ አደጋ ሲሆን አደጋው በግምት ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ የደረሰ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች።

በአደጋው ህይወቷ ያለፈው ሴት በሲኖ ትራኩ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበረች ሴት ሲሆን በነዋሪዎች ላይ አደጋ አላደረሰም ተብሏል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ስለአደጋው መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ለአዲስ ዘይቤ አስታውቋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሾፌሩ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share